28/07/2026
16ኛው የዓለም የቫይራል ሄፓታይተስ ቀን “የቫይራል ሄፓታይተስ ምርመራና ህክምና አገልግሎት ተደራሽነት ተግዳሮቶችን እናስወግድ" በሚል መሪ ቃል በጋዜጣዊ መግለጫ እና በግንዛቤ ማስጨበጫ ተከብሯል።
_______
ቫይራል ሄፓታይተስ ቢ እና ሲ መከላከልና መታከም ስለሚችሉ ማንም ሰው በእነዚህ በሽታዎች መሞት እንደሌለበት በመድረኩ ተገልጿል።
በጤና ሚኒስቴር የኤች አይ ቪ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ያደታ እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ የቫይራል ሄፓታይተስ ስርጭት እየጨመረ መሆኑን በተደረገ ጥናት መረጋገጡ የበሽታው ጫና እንደሚያመለክት ገልጸዋል።
ጤና ሚኒስቴር በሽታውን ለመቆጣጠር
የግንዛቤ ማስጨበጫ፣ የክትባት አቅርቦት፣ የምርመራና የህክምና ተቋማት የማስፋፋት፣ የመድሀኒትና ግብአት አቅርቦትን እንዲሁም የበለሞያ አቅምን በማጠናከር ረገድ ተከታታይ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አቶ ፍቃዱ ተናግረዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ዶ/ር ሰብለ አባተ፣ ኢትዮጵያ በ2030 ቫይራል ሄፓታይተስን ከህዝብ ጤና ስጋትነት ለማስወገድ እያደረገች ያለውን ጥረት በማድነቅ፣ ህመሙን የመከላከል፣ የምርመራና ህክምና ከጤና ሚኒስቴርና አጋሮች ጋር በመሆን ለመስራት የአለም ጤና ድርጅት እገዛውን እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።
የቅዱስ ጴጥሮስ እፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ዶክተር አብርሃም እሸቱ በበኩላቸው፣ ሆስፒታሉ በቫይራል ሄፓታይተስና በኤች አይ ቪ ምርመራና ህክምና ትልቅ ማዕከል ያለው መሆኑን ገልጸው፣ የዘንድሮው የዓለም የቫይራል ሄፓታይተስ ቀን በሆስፒታሉ እንዲከበር መመቻቸቱ አበረታች መሆኑን ጠቅሰው አመስግነዋል።
የኢትዮጵያ የጋስትሮኤንተሮሎጂ ማህበር ፕሬዝዳንት ዶክተር ጂኪሳ ዴቤሳ ማህበሩ የመመሪያዎችን ዝግጅትት፣ ጥናትና ምርምር ማካሄድ፣ የባለሙያዎችን አቅም ግንባታ ስልጠናና የህብረተሰብ ግንዛቤን በማሳደግ ቫይራል ሄፓታይተስን ለመቆጣጠር እገዛውን እያበረከተ መሆኑን ገልጸዋል።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V