13/05/2024
ፅንሱ ሆድ ውስጥ ባለበት ሰአት መታወቅ ይችላል ወይስ አይችልም?
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
▶ዳውን ሲንድሮም ማለት የ21ኛው ክሮሞዞም መብዛት ምክንያት የሚመጣ የአምሮ ዝግመትና ሌሎች ችግሮች የሚያመጣ ችግር ነው።
▶አብዘሀኛውን ጊዜ አንዲት ሴት እድሜዋ ገፍቶ ከ35 ዓመት በላይ ስታረግዝ የሚፈጠር ችግር ነው።
▶በእርግዝና ሰአት በሚደረጉ የተለያዩ ምርመራዎች ዳውን ሲንድሮምን ከ80-99% ማወቅ የምንችልበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል።
▶በቀላሉ ሊደረጉ የሚችሉ 3የምርመራ አይነቶች:-
➜ #1ኛ ማድረግ የሚቻለው ምርመራ አልትራሳውንድ ሲሆን ከ11-14 ሳምንት ባለው የእርግዝና ጊዜ የአንገት ቆዳና የአፍንጫ አጥንት የአልትራሳውንድ ምርመራ ተደርጎ የዳውን ሲንድሮም ሪስክ አለው ወይስ የለውም የሚለውን ማወቅ ይቻላል።
➜ #2ተኛ የምናደርገው ምርመራ ከደም ወስዶ የተለያዩ ሆርሞኖችና የኬሚካሎችን በመመርመር ከአልትራሳውንዱ ጋር በመቀላቀል ፅንሱ የዳውን ሲንድሮም ሪስክ አለው ወይስ የለውም የሚለውን ልናውቅ እንችላለን።
➜ #3ተኛ ማድረግ የሚቻለው ምርመራ ከ10ሳምንት ጀምሮ የናትየውን ደም በመውሰድ እናት ደም ውስጥ ያለውን የልጁ ዲኤንኤ (DNA)መመርመር ከዛም ዳውን ሲንድሮም አለው ወይስ የለውም የሚለውን ነገር ማወቅ እንችላለን።
▶በነዚህ ምርመራዎች ደግሞ ፅንሱ የዳውን ሲንድሮም ሪስክ አለው ተብሎ ከታወቀ ለማጣራት ከልጁ ሳፕል በመውሰድ በተለይ አሚዮሰተስስ በሚባል መርፌ በማድረግ ወደላይ የልጁን እንሽርጣ በመውሰድ ዲኤንኤ(DNA) መርምሮ 100% አለ የለም የሚለውን ነገር ማጣራት ይቻላል ማለት ነው።
#ማጠቃለያ
✔️ከእርግዝና በፊት በሚደረጉ ምርመራዎች ዳውን ሲንድሮም እንዳለ ማወቅ ይቻላል።
✔️ለሁሉም እርጉዝ ለሆኑ ይሄን ምርመራ ማድረግ ቢያስፈልግም በተለይ ግን አንድ ሴት እርጉዝ ሆና እድሜዋ ከ35 ዓመት በላይ ከሆነ ከ10-16 ሳምንት ባለው የእርግዝና ጊዜ ላይ የዳውን ሲንድሮም ምርመራ በማድረግ ሪስኳን እንድታውቅ ይመከራል።
⊰━━━━━━━⊱⊰━━━━━━━⊰
⊰━━━━━━━⊱⊰━━━━━━━⊱
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/dr_kiflom_tesfaye