07/04/2026
ልጆችን በቤት ውስጥ ስራ ማሰራት
=======================
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ልጆች የቤት ውስጥ ስራ ወላጆቻቸውን የሚያግዙ ከሆነ፣ በመጪ ዘመናቸው ፡-
1- ከወላጆቻቸው ጋር የተሻለ ተግባቦት ይኖራቸዋል፡፡
2- ኃላፊነት የሚሰማቸው ግለሰቦች ይወጣቸዋል፡፡
3- ቤት ውስጥ አስፈላጊ የቤተሰቡ አባል እንደሆኑ እንዲሰማቸውና ለራሳቸው የሚኖራቸው ክብር እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
4- ሥራ አጥ የመሆን እድላቸው ዝቅተኛ ነው፡፡ ሥራቸውን ጠብቀው የመቆየት እድላቸውም ከፍ ያለ ነው፡፡
4- ለሱስ የሚኖራቸው ተጋላጭነትም ዝቅተኛ ነው፡፡
ስለዚህ ልጆችን ቤት ውስጥ ስራ እንዲያግዙን ማድረግ እንደሕጻናት ጉልበት ብዝበዛ ሊቆጠር አይገባም፡፡ ምን ምን ይስሩ?
አልጋ ማንጠፍቤት ማስተካከል፣ ቤት ማጽዳትምግብ ማዘጋጀት፣ ምግብ ለቤተሰቡ ማቅረብ፣ የተበላባቸውነ ዕቃ እንዲመልሱ ማድረግ ፣ እንዲያጥቡ ማድረግ (ሁለቱም ጾታዎች እኩል ማሳተፍዎን አይዘንጉ) የጓሮ አትክልት መንከባከብ፣ የቤት እነስሳት መንከባከብ መላላክ እና የመሳሰሉትን መስራት ይችላሉ።
"እናንተ ልጆቻችሁን ታሰራላችሁ ወይ?" ለሚለው ጥያቄ፡ "እየሞከርን ነው! " 😊
https://www.facebook.com/1368127853/posts/10242088210286283/?app=fbl
Via
Mezgeb Gedefe Molla