Abdu nasir

Abdu nasir No health with out mental health !

03/04/2024

የንግግር የስነ ልቦና ህክምና እንዴት ነው የሚሰጠው?
=================================
የንግግር የስነ ልቦና ህክምና ስንሰጥ ለታካሚ "ምን ማድረግ
እንዳለብህ አውቃለሁ፤ ልንገርህ።" የምንል የሚመስላቸው
ሰዎች አሉ። የምንለው ግን በተቃራኒው ታካሚን "ምን ማድረግ
እንዳለብህ ታውቃለህ፤ ንገረኝ።" ነው። በመቶዎች የሚቆጠሩ
የተለያዩ የስነ ልቦና ህክምና አይነቶች ቢኖሩም አሰራራቸው
በሶስት ደረጃዎች ሊጠቃለል ይችላል።
1) ታካሚው ጭንቀት የሚፈጥሩበት የህይወቱ ክፍሎችን
መመርመር የሚችልበት ሁኔታ ማመቻቸት፦ የጭንቀቱ ምንጭ
አስተዳደጉ ወይም አሁን ያለበት ሁኔታ፤ ከሰዎች ጋር ያለው
ግንኙነት ወይም የሚያስብበት መንገድ ሊሆን ይችላል። እዚህ
ደረጃ ላይ የሀኪሙ ሚና መደገፍ፣ ማበረታታት እና በጣም
አልፎአልፎ መጠቆም ነው። ብዙ ሰዎች ስለ ጭንቀት ለጓደኛ
ወይም ለቤተሰብ ሲያወሩ ንግግራቸውን ሳያስጨርሱ ጓደኛቸው
አቋርጦ መፍትሄ ይጠቁማቸዋል። የንግግር ህክምና ላይ ግን
መጀመሪያ ላይ ጊዜ ሰጥተን እናዳምጣለን።
2) ግንኙነቶችን እንዲረዳ ማገዝ፦ አስተዳደጉና አሁን ባለበት
ሁኔታ እንዲሁም በሀሳብ ስሜትና ፀባይ መካከል ያለውን
ግንኙነት እንዲገነዘብ ማገዝ። እዚህ ደረጃ ላይ የሀኪሙ ሚና
ነገሮችን በታካሚው አይን ለማየት መሞከርና ታካሚ ሀሳቡንና
ስሜቱን እንዲገልፅ ማገዝ ነው። ስለ ሰዎች ማንነት የምንረዳው
በአብዛኛው የሚያወሩትን ሰምተን ነው። ስለራሳችን ለመረዳትም
ስለራሳችን የምናወራውን መስማት አለብን። የስነ ልቦና ህክምና
ላይ ስለአጋጠመን ነገሮች፣ ስለ አስተዳደጋችን፣ ስለፍቅር
ግንኙነታችን በጥሞና ለሚያዳምጥ ሰው ስለምናወራ ስለራሳችን
ማንነት የተሻለ እንረዳለን።
3) አማራጭ መንገድ፦ ታካሚው የጭንቀትና ሌሎች አሉታዊ
ስሜት ትክክለኛ ምክኒያት ከተረዳ "የሁኔታዎች ውጤት ነኝ!"
ከማለት ወጥቶ "የውሳኔዬ ውጤት ነኝ!" ማለት ሲችል ጭንቀት
የሚቀንሱ አማራጭ መንገዶች ማሰብ ይጀምራል። የተወሰኑትን
በተግባር ለውጦ ይሞክራል። ከዛ ውጤት ካገኘበት ይበልጥ
እያሻሻለው ይሄዳል።
አንዳንድ የአእምሮ ህመሞች በንግግር የስነ ልቦና ህክምና ብቻ
መታከም ይችላሉ። ለአንዳንዶቹ ደግሞ ከመድሀኒት ጎንለጎን
ይሰጣል።
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

03/04/2024

Intern (የህክምና ትምህርት የመጨረሻ አመት ተማሪ)ነኝ።
ግቢ የገባሁት 2004ዓም ነው። እስከአሁን እንዴት
አልጨረስክም ልትሉኝ ትችላላችሁ። እኔ ግን እስከአሁን
ያልጨረስኩት በጤና መታወክ ነው። ከPc-1 ወደ Pc-2 አልፌ
ትንሽ እንደተማርኩ Bipolar disorder diagnosed ተደረኩ።
Exam ላይ ስለነበርኩ ለጤናዬ ትኩረት አልሰጠውም። ነገር
ግን ከጤናዬ ሳልሆን ፈተናውንም በትክክል ሳልፈተን ቀረሁ።
ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ እኔና Forced withdrawal
ተግባብተን መኖር የጀመርነው። Intern እስክሆን ብዙ
challenge የሚያደርጉ ጊዜዎችን አሳልፌያለሁ። Sodium
valproate ለ 8 አመት ወስጃለሁ፤ ግን በመሀል ብዙ ጊዜ
አቋርጫለሁ። "ምክንያቱም ብዙ መድሀኒቶች Public
pharmacy ሳይኖሩ ያሉት Private pharmacy ላይ ነው"
private ደግሞ ዋጋቸው በጣም ውድ ነው።
የሚመለከተው ባለ ድርሻ አካል ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጠን
እጠይቃለሁ።
"ያለ አእምሮ ጤና ጤና የለም "
Dr.Israel W/yohannes(Intern)

አስቸጋሪ ጊዜያት እና ቀልዶች (ኮሮና የመጣ ጊዜ የተቀለዱ)=====================================በአስቸጋሪ ጊዜያት ቀልዶች እንደ ስነ ልቦናዊ የህመም ማስታገሻያገለግላሉ።...
13/04/2022

አስቸጋሪ ጊዜያት እና ቀልዶች (ኮሮና የመጣ ጊዜ የተቀለዱ)
=====================================
በአስቸጋሪ ጊዜያት ቀልዶች እንደ ስነ ልቦናዊ የህመም ማስታገሻ
ያገለግላሉ። በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት አይሁዳውያን
ብዙ ቀልዶች እየፈጠሩ አስጨናቂውን ጊዜ ቀለል እንዲል
ለማድረግ ይሞክሩ ነበር። አንዷን እነሆ፦
አንድ አይሁድ 'አዋቂ' ጋር ይሄድና ጀርመኖች መቼ እንደሚሸነፉ
ይጠይቃል። 'አዋቂውም' በአንድ የአይሁድ አመት በአል እንደሆነ
ይነግረዋል። አይሁዱም "የትኛው አመት በአል?" ብሎ ሌላ
ጥያቄ ያሰከትላል። አዋቂውም "መቼም ቀን ጀርመኖች ይሸነፉ፤
ያን ቀን ለአይሁዶች አመት በአል ነው።" ብሎ መለሰለት።
ሲግመን ፍሮይድ Jokes and their Relations to the
Unconscious በሚለው መፅሀፉ ላይ አስቸጋሪ ነገሮች ላይ
ስንቀልድ ከአቅማችን በላይ የሆኑ ነገሮችን በትንሹም ቢሆን
የመቆጣጠር ስሜት እንዲሰማን ያደርጉናል ብሏል። "...it is
striking back or taking control. It is a poor
substitute but it may be all that is available...
ለማንኛውም ጥቂት የኮሮና ቀልዶች፦
1)ሰዎች በፊት ጉንፋን ሲይዛቸው "አሞኛል፤ ከቤት መውጣት
አልፈልግም። ጥቅል...ል ብዬ ተኝቼ ነው የምውለው።"
ኮሮና የያዛቸው ሰዎች "አሞኛል ግን ቤት መዋል ስለሚደብር
ሀይገር ተሳፍሬ፣ ስታዲየም ገብቼ ኳስ አይቼ፣ ዕድር ደረስ ብዬ፣
እግረ መንገዴን ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተሳትፌ ብመጣ ደስ
ይለኛል።
2) አሜሪካ ኮሮና ሲመጣ ብዙ ሶፍት ገዝተው ሶፍት ከገበያ ላይ
እንዲጠፋ ያደረጉት ሰዎች መኪና በከፍተኛ ፍጥነት ይነዱ የነበሩ
ሰዎች እንደሆኑ በጥናት ተረጋግጧል።
3) ጭንቀት በተሰማኝ ቁጥር ጭንቀቱን ለመቀነስ ጥቂት
ኪሎሜትሮች ሮጣለሁ። አሁን አርበጉና ደርሻለሁ። ወደ ቤቴ
እንዳልመለስ 'ትራንስፖርት' የለም።
4) ቤት ለመቀመጥ ተቸግረዋል? እንግዲያውስ ቅንድብዎን
ይላጩ።
5) አሁን ሁሉም ሰው እጁን እየታጠበ ስለሆነ መንገድ ላይ
የሚሸጠው ቆሎ ጣእሙ ጠፍቷል።
ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

Address

St,Amanuel Mental Specialized Hospital
Addis Ababa

Telephone

+251919352858

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abdu nasir posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Abdu nasir:

Share