Ethiopian Prosthetic and Orthotic Service - EPOS

Ethiopian Prosthetic and Orthotic Service - EPOS Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Prosthetic and Orthotic Service - EPOS, Orthotics & Prosthetics Service, Mikililand Center, Addis Ababa.

"ደም ይለግሱ ህይወት ያድኑ"  በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተካሄደ።*************************************አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2018 የኢትዮጵያ የአካ...
24/08/2026

"ደም ይለግሱ ህይወት ያድኑ" በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተካሄደ።
*************************************
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2018

የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞች የጤናዉን ዘርፍ የክረምት በጎ ፈቃድ ጥሪ በመቀበል “ደም ይለግሱ፤ ህይወት ያድኑ!” በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ መርሃ ግብር አከናወኑ።

በመርሃ ግብሩ ፈቃደኛ ከሆኑ የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞች አስፈላጊው የጤና ምርመራ ከተደረገ በኋላ 30 ዩኒት ደም የተሰበሰበ ሲሆን አንድ (1) ዩኒት ደም የ3 (ሶስት) ሰዎችን ህይወት መታደግ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ የደም ልገሳ መርሃ ግብር ደም ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች በተለይም በወሊድና በተለያዩ ምክንያት የጤና እክል ላይ ለሚገኙ ሰዎች ህይወትን ለማዳን የሚያግዝ የሰብዓዊነትና የኃላፊነት ተግባር ሲሆን በብዙ ሰዎች ህይወት ላይ የሚፈጥረዉ አስተዋጽኦ ከፊተኛ ነዉ።

የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት በክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች የማገገሚያ ህክምና አገልግሎትን ብቻ ሳይሆን ፣ሰብዓዊነትን፣በጎ ፍቃድ ስራዎችን እና የማህበረሰብ ኃላፊነትን በተግባር በመወጣት ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

👉 እርስዎም ደምዎን ይለግሱ፤ ህይወት ያድኑ! 🩸🩸 🩸
--------------------------
Website:epos.gov.et
Facebook : Ethiopian Prosthetic and Orthotic Service (EPOS)

Youtube :
https://youtube.com/?si=bmpFx6IkCOZqHzqz

TikTok: www.tiktok.com/ 2014

Telegram:https://t.me/ethiopianprostheticorthoticservi

የ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተሳታፊዎች የተሳተፉበት"Walk the Talk"  በሚል መሪ መልዕክት  የእግር ጉዞ ተካሄደ************************...
23/08/2026

የ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተሳታፊዎች የተሳተፉበት"Walk the Talk" በሚል መሪ መልዕክት የእግር ጉዞ ተካሄደ
*************************************
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2018

የእግር ጉዞው "Walk the Talk" በሚል መሪ ሐሳብ የተካሄደ ሲሆን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከልና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ለማስፋፋት ዓላማ ያደረገ ነው።

በመርሃ ግብሩ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፣የአፍሪካ ሀገራት የጤና ሚኒስትሮች፣የጤና ሚኒስቴር ሚኒስቴር ድኤታዎች ፣የዓለም ጤና ድርጅት አመራሮች፣ የጤና ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት ፣የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት አመራሮች ፣ የማናጅመንት አባላት ፣ የተቋሙ ሠራተኞች እና ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች የተሳተፉበት ሲሆን፤ መረሃ ግብሩ በአፍሪካ የጤና አጀንዳዎችና ሌሎች ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ በአዲስ አበባ የሚካሄደዉን 76ኛ የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ በማስመልከት "Walk the Talk" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የእግር ጉዞ ነዉ።
--------------------------
Website:epos.gov.et
Facebook : Ethiopian Prosthetic and Orthotic Service (EPOS)

Youtube :
https://youtube.com/?si=bmpFx6IkCOZqHzqz

TikTok: www.tiktok.com/ 2014

Telegram:https://t.me/ethiopianprostheticorthoticservi

የሐዘን መግለጫ የአቤት ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ዶ/ር ፀጋዬ ገብረ አናንያ በገጠማቸው ድንገተኛ ህልፈተ-ህይወት መላው የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት አመራ...
19/08/2026

የሐዘን መግለጫ

የአቤት ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ዶ/ር ፀጋዬ ገብረ አናንያ በገጠማቸው ድንገተኛ ህልፈተ-ህይወት መላው የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት አመራር እና ሰራተኞች የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እንገልፃለን።

ለቤተሰቦቻቸው ፣ ለጓደኞቻቸው ፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸዉ መፅናናትን እንመኛለን።

የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት

▬▬▬▬▬▬▬▬▬

የማገገሚያ ህክምና አገልግሎትን ለማጠናከር ያለመ የሰዉ ኃይል ልማት ማዕቀፍ ሰነድ በባለድርሻ አካላት ተገመገመ።                   ***********************        ...
11/08/2026

የማገገሚያ ህክምና አገልግሎትን ለማጠናከር ያለመ የሰዉ ኃይል ልማት ማዕቀፍ ሰነድ በባለድርሻ አካላት ተገመገመ።
***********************
ነሐሴ 5፣2018/አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የማገገሚያና የአሴስቲቭ ቴክኖሎጂ አገልግሎትን ለማጠናከር የተዘጋጀውን የሰው ኃይል ልማት ማዕቀፍ ሰነድ በተለያዩ ባለድርሻ አካላት ሰፊ ውይይት ተደርጎበት ተገመገመ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ሰለሞን ሰይድ፣ በዓለም ደረጃ በማገገሚያ ህክምናና በተለይም በአሴስቲቭ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ፈጣን የቴክኖሎጂና የአገልግሎት እድገት እየታየ መሆኑን ገልጸዉ፤ በሀገራችን ኢትይጵያ የማገገሚያ ህክምና አገልግሎትን ለህብረተሰቡ በተሻለ ሁኔታ ተደራሽ ለማድረግ በከፍተኛ አመራር ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ቢሆንም፣ ከሀገሪቱ ፍላጎትና ከህብረተሰቡ የማገገሚያ አገልግሎት ፍላጎት አንጻር ገና ብዙ መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል።

ይህንን ክፍተት ለመቅረፍ የባለድርሻ አካላት ትብብርና ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ያስገነዘቡት ዶ/ር ሰለሞን፣ብቁ የማገገሚያ ባለሙያዎችን ማፍራት፣ የሥልጠና አቅምን ማሳደግ፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በአገልግሎቱ ውስጥ ማካተት እና የባለሙያዎችን ቀጣይ ሙያዊ ልማት ማጠናከር ቀዳሚ ትኩረቶች መሆን እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

በመድረኩ ጥራት ያለዉ የማገገሚያ ህክምና አገልግሎት ለህብረተቡ ተደራሽ ለማድረግ ፤ የማገገሚያ ሳይንስ፣ የአሴስቲቭ ቴክኖሎጂ፣ የማገገሚያ ኢንጂነሪንግ እና አጠቃላይ የማገገሚያ ህክምና ዘርፉን በሚመለከት የላቀ የሥልጠና አቅም እንዲገነባ ምክረ ሀሳቦች ቀርበዋል።

የቀረቡት ሀሳቦች የሰነዱን ይዘት የበለጠ ለማጠናከር፣ የሰው ኃይል ልማት አቅጣጫዎችን በግልጽ ለመለየትና ሰነዱን ከሀገሪቱ ተጨባጭ ፍላጎት ጋር ለማጣጣም ጠቃሚ ግብዓት እንደሚሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት አመራሮች በበኩላቸው በመድረኩ የተነሱት ሀሳቦች በሰነዱ የመጨረሻ ይዘት ውስጥ በአግባቡ እንዲካተቱ በማድረግ፣ የማገገሚያ ህክምናና የአሴስቲቭ ቴክኖሎጂ ዘርፍን ለማጠናከር የሚያስችል ጠንካራ የሰው ኃይል ልማት ሥርዓት ለመገንባት ተቋሙ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም በቀረበው ሰነድ ላይ ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦችን በማቅረባቸው ደስተኛ መሆናቸውንና በቀጣይም ከኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ጋር በመተባበር የማገገሚያ ህክምናና የአሴስቲቭ ቴክኖሎጂ ዘርፍን ለማሳደግ የበኩላቸውን ሚና ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
________

Website:epos.gov.et
Facebook : Ethiopian Prosthetic and Orthotic Service (EPOS)

Youtube :
https://youtube.com/?si=bmpFx6IkCOZqHzqz

TikTok: www.tiktok.com/ 2014

Telegram:https://t.me/ethiopianprostheticorthoticservi

የጤና ሚኒስቴርና የሸገር ከተማ ከፊተኛ  አመራሮች ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የማገገሚያ ህክምና ማዕከል ፕሮጀክት ጎበኙ።የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የሸገር ...
05/08/2026

የጤና ሚኒስቴርና የሸገር ከተማ ከፊተኛ አመራሮች ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የማገገሚያ ህክምና ማዕከል ፕሮጀክት ጎበኙ።

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የሸገር ከተማ ከንቲባ እና የአገልግሎቱ የቦርድ አባል ዶ/ር ተሾመ አዱኛ ፣የጤና ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች እንዲሁም የሸገር ከተማና የገፈርሳ ጉጄ ክ/ከ አመራሮች በተገኙበት ተጎብኝተዋል።

በጉብኚቱም በኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት እየተገነባ ያለዉ ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የማገገሚያ ህክምና ፕሮጀክት ግንባታ ያለበት ደረጃ እና በተቋሙ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን ተመልክተዋል።

_______________

Website:epos.gov.et
Facebook : Ethiopian Prosthetic and Orthotic Service (EPOS)

Youtube :
https://youtube.com/?si=bmpFx6IkCOZqHzqz

TikTok: www.tiktok.com/ 2014

Telegram:https://t.me/ethiopianprostheticorthoticservi

https://youtu.be/iVdqCtkBFCM?si=zWToGsbuE9o9e-oM

የጤና ሚኒስቴርና የሸገር ከተማ ከፊተኛ አመራሮች ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የማገገሚያ ህክምና ማዕከል ፕሮጀክ...

በኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት "ደም ይለግሱ ህይወት ያድኑ"  በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ መርሃ-ግብር ዛሬ ተጀመረ።የክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎች ውስጥ አንዱ የሆነው የደም ልገሳ መርሃ...
04/08/2026

በኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት "ደም ይለግሱ ህይወት ያድኑ" በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ መርሃ-ግብር ዛሬ ተጀመረ።

የክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎች ውስጥ አንዱ የሆነው የደም ልገሳ መርሃ- ግብር በዛሬው ዕለት በተቋማችን የተጀመረ ሲሆን መርሃ-ግብሩ ከሐምሌ 28 እስከ ሐምሌ 30/2018 ዓ/ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል። በዚህ መርሃ-ግብርም በርካታ አመራርና ሰራተኞች የደም ልገሳ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

"ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የችግኝ ተከላ አረንጓደ አሻራ መርሃ ግብር:            ----  -----   -----  ----   -----    ----   ------  ...
04/08/2026

"ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የችግኝ ተከላ አረንጓደ አሻራ መርሃ ግብር:
---- ----- ----- ---- ----- ---- ------

_______________

Website:epos.gov.et
Facebook : Ethiopian Prosthetic and Orthotic Service (EPOS)

Youtube :
https://youtube.com/?si=bmpFx6IkCOZqHzqz

TikTok: www.tiktok.com/ 2014

Telegram:https://t.me/ethiopianprostheticorthoticservi

የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ አረንጓደ አሻራ መር...

04/08/2026

የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀዉን የችግኝ ተከላ አረንጓደ አሻራ መርሃ ግብርን ምክንያት በማድረግ በገፈርሳ ጉጄና በቡራዩ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ ለ 200 ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ለትውልድ ግንባታ ያለውን አስተዋጽኦ በተግባር አረጋግጧል።

በኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት አዘጋጅነት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በስኬት ተከናወነ።*************************************በኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ...
03/08/2026

በኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት አዘጋጅነት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በስኬት ተከናወነ።
*************************************
በኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት አዘጋጅነት የጤና ሚኒስቴር፣ የተጠሪ ተቋማት፣ የመከላከያ ሠራዊት ተወካዮች፣ የሸገር ከተማ አስተዳደር እና የገፈርሳ ጉጄ ክፍለ ከተማ የአንድ ጀምበር ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በተሳካ ሁኔታ አከናውኗል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የ800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ዘመቻ ተስፋን፣ ሕይወትን እና ዘላቂ ልማትን የምንተክልበት ታላቅ ሀገራዊ እንቅስቃሴ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ ክረምት ብቻ የጤናው ዘርፍ ከ250,000 በላይ ችግኞች እንደሚተክል ጠቅሰው፣ ሁሉም የጤና ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች በዚህ ሀገራዊ ጥረት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ በበኩላቸው፣ አረንጓዴ አሻራና የህዝብ ጤና የማይነጣጠሉ ጉዳዮች መሆናቸውን ገልጸው፣ ዛፍ መትከል ለንጹህ አየር፣ ለምግብ ዋስትና፣ ለውሃ ምንጮች ጥበቃ እና ለማህበረሰብ ጤና ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አስረድተዋል። በተለይም የአዲስ አበባ ዋና የውሃ ምንጭ ከሆነው የገፈርሳ አካባቢ ጥበቃ ላይ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል። ለመርሃ ግብሩ ስኬትም ለኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ምስጋና አቅርበዋል።

በመርሃ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ታሪኩ ታደሰ፣ በዕለቱ በሀገር አቀፍ የ800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ዘመቻ ማዕቀፍ ውስጥ ከ 30,000 በላይ ችግኞች መተከላቸውን ገልጸው፣ ተቋሙ ከማገገሚያ አገልግሎት ባሻገር በተለያዩ የበጎ ፈቃድና ማህበራዊ ተግባራት በንቃት እየተሳተፈ መሆኑን አስታውቀዋል። አረንጓዴ ልማት የአካባቢ ጥበቃን በማጠናከር የዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንዳለውም ጠቅሰዋል።

በኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የሸገር ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ተሾመ አዱኛ በበኩላቸው፣ በሸገር ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የኤኮ ቱሪዝምና የአረንጓዴ ልማት ሥራዎችን በማብራራት፣ ለመርሃ ግብሩ ዝግጅትና አስተባባሪነት ለኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ምስጋናቸውን ገልጸዋል።

አገልግሎቱ ከአካባቢ ጥበቃ ባሻገር ማህበራዊ ኃላፊነቱንም በመወጣት፣ የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ለገፈርሳ ጉጄና ለቡራዩ ክፍለ ከተሞች 200 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ለትውልድ ግንባታ ያለውን አስተዋጽኦ አረጋግጧል።

በመርሃ ግብሩ ማጠናቀቂያ፣ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የመከላከያ ሠራዊት ተወካዮችና ሌሎች እንግዶች በኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት እየተገነባ ያለዉን ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የማገገሚያ ማዕከልን በመጎብኘት የተቋሙን የአገልግሎት አቅምና እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን ተመልክተዋል።

🌿 አረንጓዴ አሻራን በመትከል አካባቢን እንጠብቅ፤ በመተባበር ጤናማና ዘላቂ የወደፊት ትውልድ እንገንባ!

_______________

Website:epos.gov.et
Facebook : Ethiopian Prosthetic and Orthotic Service (EPOS)

Youtube :
https://youtube.com/?si=bmpFx6IkCOZqHzqz

TikTok: www.tiktok.com/ 2014

Telegram:https://t.me/ethiopianprostheticorthoticservi

Address

Mikililand Center
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Prosthetic and Orthotic Service - EPOS posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share