19/05/2026
Alzheimer Awareness Ethiopia ስለ የአእምሮ መረሳት ዓይነቶቹ ምን ያውቃሉ? 🧠
ብዙ ሰዎች "አልዛይመር" እና "ዴሜንሻ" አንድ አይነት ህመም ይመስላቸዋል። ነገር ግን ዴሜንሻ የአእምሮ መረሳት ህመሞች አጠቃላይ መጠሪያ ሲሆን፣ አልዛይመር ግን ከነዚህ ዓይነቶች መካከል ዋነኛውና በጣም የተለመደው ብቻ ነው።
📌 ዋና ዋናዎቹ የዴሜንሻ (የአእምሮ መረሳት) ዓይነቶች፦
1. አልዛይመር (Alzheimer's Disease)፦ በጣም የተለመደውና ሰፊው የዴሜንሻ ዓይነት ሲሆን፣ በአንጎል ውስጥ ፕሮቲኖች ባልተገባ መልኩ በመከማቸታቸው ህዋሳቱ እንዲሞቱ ያደርጋል።
2. ቫስኩላር ዴሜንሻ (Vascular Dementia)፦ ወደ አንጎል የሚሄደው የደም ፍሰት በሚስተጓጎልበት ወቅት (ለምሳሌ፦ በስትሮክ/Stroke ምክንያት) የሚከሰት ሁለተኛው ትልቅ የዴሜንሻ ዓይነት ነው።
3. ሌዊ ቦዲ ዴሜንሻ (Lewy Body Dementia)፦ በአንጎል ህዋሳት ውስጥ ያልተለመዱ የኬሚካል ክምችቶች በመፈጠራቸው የማሰብ፣ የማስታወስ እና የእንቅስቃሴ መዛባትን የሚያስከትል ህመም ነው።
4. ፍሮንቶ-ቴምፖራል ዴሜንሻ (Frontotemporal Dementia)፦ በዋናነት የአንጎላችንን የፊትና የጎን ክፍሎች በማጥቃት፣ በባህሪ እና በቋንቋ አጠቃቀም ላይ ከፍተኛ ለውጥ የሚያመጣ የህመም ዓይነት ነው።
💡 ድብልቅ ዴሜንሻ (Mixed Dementia)፦ አንዳንድ ሰዎች ከአንድ በላይ የዴሜንሻ ዓይነት በአንድ ጊዜ ሊኖራቸው ይችላል። ለምሳሌ አልዛይመር እና ቫስኩላር ዴሜንሻ በአንድ ላይ ሊከሰቱ ይችላሉ።
💡 በወጣቶች ላይ የሚከሰት ዴሜንሻ (Young-Onset Dementia)፦ ዴሜንሻ የአረጋውያን ብቻ ህመም አይደለም! አንድ ሰው ዕድሜው ከ65 ዓመት በታች እያለ ዴሜንሻ ሊይዘው ይችላል።
💚 The Different Types of Dementia
Dementia is not a single disease; it is an umbrella term caused by many different underlying conditions that affect the brain in different ways.
While Alzheimer's disease is the most common form, here are the other common types of dementia you should know:
✅ Alzheimer's Disease — The most prevalent form, caused by abnormal protein build-ups that damage brain cells.
✅ Vascular Dementia — Caused by reduced blood flow to the brain, often following a stroke.
✅ Lewy Body Dementia — Leads to difficulties with thinking, memory, and physical movement due to chemical deposits in brain cells.
✅ Frontotemporal Dementia — Primarily affects the front and sides of the brain, causing major changes in behavior and language.
📌 Important Concepts:
* Mixed Dementia: It is possible to develop multiple types of dementia simultaneously.
* Young-Onset Dementia: When a person develops dementia before the age of 65, this is known as young-onset dementia.
#የአእምሮመረሳት #አልዛይመር #ተንከባካቢዎች