BELT- Public Health & Family Wellbeing

BELT- Public Health & Family Wellbeing We discuss maternal health, mental well being, parenting, and family relationships in an evidence- based and supportive way.

Knowledge, Confidence and Practical life skill.
እዉቀት ፣ መተማመን ፣እድገት !

22/06/2026

አባት ገንዘብ የሚያመጣ ሰው ብቻ አይደለም፤ የቤቱን ሰላምና ፍቅር የሚገነባ ሰው ነው።

ልጆች ከአባታቸው የሚያስታውሱት ያመጣውን ነገር ብቻ አይደለም፤ ከእነሱ ጋር ያሳለፈውን ጊዜ፣ ለእናታቸው ያሳየውን ክብር፣ እና በቤት ውስጥ የፈጠረውን ፍቅርና መተማመን ነው።

አንድ አባት ለቤተሰቡ የሚሰጠው ትልቁ ስጦታ መገኘቱ ነው።

መልካም የአባቶች ቀን!

18/06/2026

የክረምት ዕረፍት/ ትምህርት ቤት ሲዘጋ……. ያኔ እና ዛሬ
እኛ ልጆች ሳለን ለክረምት ትምህርት ሲዘጋ ማለት ከጓደኞቻችን ጋር መጫወት፣ መጽሐፍ ማንበብ፣ የቤት ስራ ማገዝ፣ ዘመድ ጋር ክፍለሀገር ወይም ሌላ ሰፈር መሄድ፣ አዳዲስ ነገሮችን መሞከር እና የሕይወት ትምህርቶችን መማር ነበር።
ዛሬ ግን ብዙ ልጆች የበጋ ዕረፍታቸውን በስክሪን ፊት ብቻ ሲያሳልፉ እናያለን።
የክረምት ዕረፍት ትምህርትን ለመርሳት ሳይሆን በትምህርት ቤት ሁልጊዜ ለማይማሩት ክህሎቶች ጊዜ የምንሰጥበት እድል ነው።

የማንበብ ልምድ
የኮምፒውተር ክህሎት
የመግባቢያ ችሎታ
ፈጠራ እና ስነ-ጥበብ
የማህበራዊ ክህሎቶች
የሕይወት ክህሎቶች
ወላጆች ሆይ፣ ይህን የክረምት ጊዜ ልጆቻችን የሚያስታውሱት ስክሪን ላይ ያሳለፉትን ሰዓት ሳይሆን የተማሩትን እና ያደጉበትን ልምድ እንዲሆን እንርዳቸው።

እርስዎ በልጅነትዎ የክረምት ዕረፍት ጊዜ ምን ይታወስዎታል?

Send a message to learn more

07/06/2026

እንኳን ወደ BELT ገጽ በደህና መጣችሁ!
ቤተልሄም አለማየሁ እባላለሁ። ኤክስፐርት የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ ስሆን በዘርፉ የበርካታ ዓመታት የሥራ ልምድ አለኝ። ባለትዳር እና የሁለት ልጆች እናትም ነኝ።
በትምህርቴና በሥራዬ አማካኝነት፣ በተለያዩ የምርምር እና የማህበረሰብ ተሳትፎ ሥራዎች ላይ በመሳተፍ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር የመገናኘት ዕድል አግኝቻለሁ። በዚህ ሂደትም ውስጥ ማህበረሰቡ በተደጋጋሚ የሚያነሳቸውን የጤና እና ማህበራዊ ጉዳዮች በቅርበት ለማወቅ ችያለሁ።
ይህ ገጽ የተጀመረው እነዚህን እና ተያያዥ ጉዳዮችን በሳይንሳዊ መረጃ፣ በሕይወት ልምድ እና በማህበረሰቡ ነባር ጥበብ በማጣመር ለመወያየት፣ ለመማር እና አብረን ለማደግ ነው።
ይህ ገጽ መረጃ የሚሰጥበት ብቻ ሳይሆን የሁላችንም የውይይት እና የመማማር መድረክ ነው።
አብረን እንወያይ፣ እንማር፣ እንበረታታ!
እውቀት ! በራስ መተማመን ! እድገት!

Hello and welcome to BELT!
I am Bethelehem Alemayehu, Expert public health professional specialist with over 10 years of experience in the health sector, especially in research.
I am also a mother of two, balancing family life, professional work, and continuous learning. Through my carrier and life journey I have had the chance to see public health related gaps. BELT is created to fill those gaps to create peoples understanding and decision- making. This platform isn’t just about sharing information.it is a space to discussion, learn, and grow together based on experience, science, and community knowledge. Professionals from different fields will be invited and this page will be the page you all prefer for discussion and knowledge sharing.
Let’s stay connected and grow together through BELT!

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when BELT- Public Health & Family Wellbeing posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share