Dr.zeset elif

Call Contact the practice

Dr.zeset elif የጤና ትምህርት እና ጤና ነክ ጉዳዮች የምንነጋገርበት ፔጅ ነ?

01/10/2026
☦⛪️⛪️⛪️⛪️☦⛪️⛪️⛪️⛪️☦በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ✍️የደ/ኃ/ቅ/ራጉኤል አ/ብ ሰ/ት/ቤት በትምህርት ዐቢይ ክፍል ተከታታይ ትምህርት ማስተባበሪያ ንኡስ ክፍ...
16/09/2026

☦⛪️⛪️⛪️⛪️☦⛪️⛪️⛪️⛪️☦

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

✍️የደ/ኃ/ቅ/ራጉኤል አ/ብ ሰ/ት/ቤት በትምህርት ዐቢይ ክፍል ተከታታይ ትምህርት ማስተባበሪያ ንኡስ ክፍል 5ኛ ዙር የቀዳማይ የኦንላይን ትምህርት ለመስጠት ተማሪ ምዝገባ ጀምሯል

https://forms.gle/Cmfxier6xPsNcPS88

በኦንላይን ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት መማር የምትፈልጉ ምእመናን ከላይ በተቀመጠው ሊንክ ገብታችሁ እንድትመዘገቡ

Tg ,

በሚለው ይግቡ

✍️የሚሰጠው ትምህርት

፩/ ትምህርተ ሃይማኖት
፪/ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
፫/ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ
፬/ ግእዝ
፭/ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

✍️ትምህርቱ የሚሰጠው :- zoom ,telegram እና ሌሎች ማኅበራዊ ሚድያ ነው።

✍️ትምህርቱ የሚጀመረው ጥቅምት 2 2019 ዓ/ም ይሆናል።

✍✍ መመዝገቢያ ; 300 ብር

ማሳሰቢያ፡
✍️Online ገብቶ መማር ግዴታ ነው

ለጓደኞቻችሁ ሼር አድርጉ

የርቀትና ተልዕኮ ንዑስ ክፍል የኦንላይን ተማሪዎች መመዝጋቢያ ቅጽ

15/09/2026

Celebrating my 5th year on Facebook. Thank you for your continuing support. I could never have made it without you. 🙏🤗🎉

You can call for any pediatric services
16/07/2026

You can call for any pediatric services

ልጆቻችሁ ስድስት ወር የሞላቸውና ከዛ በታች ሆነው የምግብ ፍላጎት ያላቸው ራሳቸውን ችለው መቀመጥ ከቻሉ ከታች የተዘረዘሩትን ምግቦች ማጀመር እንችላለን ነገር ግን የጡት ወተት ወይም የሕጻናት...
29/06/2026

ልጆቻችሁ ስድስት ወር የሞላቸውና ከዛ በታች ሆነው የምግብ ፍላጎት ያላቸው ራሳቸውን ችለው መቀመጥ ከቻሉ ከታች የተዘረዘሩትን ምግቦች ማጀመር እንችላለን ነገር ግን የጡት ወተት ወይም የሕጻናት ወተት ፎርሙላ መቋረጥ ወይም ከበፊቱ መቀነስ የለባቸውም።
እያንዳንዱን ምግብ ለሦስት ወይም አራት ተከታታይ ቀናት መሞከር ይስፈልጋል ምክንያቱም አለርጂክ የሆነባቸውን ምግብ ለመለየት ያስችለናል ። ውሀ ምግብ የጀመሩ ልጆች ስለሚያፈልጋቸው በቀን ቢያንስ ስልሳ ሚሊ አጠጡ
1.ስኳር ድንች
2.ድንች
3. ካሮት
4.አፕል
5.ዱባ
6.ሙዝ
7.አቮካዶ
8.እርጎ
9.እንቁላል ተቀቅሎ አስኳሉን ብቻ
10.ፎሶልያ
11.ብሮኮሊ
12.ገንፎ

ዶ/ር ምትኩ ኩማ
የሕጻናት ህክምና ስፔሻሊስት

07/06/2026

የስብእና በሽታ #

አድናቆት የሚፈልግ ፣ትችት የማይቀበል ፣ራሱን ብቻ ተፈላጊ አዋቂ ባለብሩእ አዕምሮ ተሰጥኦ ያለው ፣ሥልጣን ወዳድ፣ በወሬ ሁሉንም የሚጠቀልል ፣በሌሎች ልፋት ራሱን የሚያፀድቅ፣ ሌላውን አለማመስገን እውቅና አለመስጠት ፣ራሱን የበላይ አድርጎ ለማሳየት ሌላውን የሚያንቋሽሽ የሚሰድብ የሚንቅ፣ ሲተቹት ወይም አስተያየት ሲሰጡት ግልፍተኛ ፣ በራሱ እና በክብሩ በሥልጣኑ ሲመጡ የማይቀበል በጥቅሉ ባለሙሉ ስብእና እኔ ብቻ ነኝ ብሎ የሚይምን የስብእና መዛባት በሽታ ነው

23/01/2026

የጉበት ስብ ክምችት Fatty Liver (Hepatic Steatosis)

• ሰላም ዉድ ቤተሰቦች ለዛሬ ስለ ጉበት መስባት (በጉበት ላይ ስለሚከማች ስብ) ጠቃሚ መረጃ እናቀብላለን።
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

•✍ለመሆኑ የጉበት መስባት ምን ማለት ነው?

ከፍተኛ የሆነ የስብ ክምችት በጉበት ላይ ሲኖር የጉበት መስባት(Fatty Liver) ይባላል። ትንሽ መጠን ያለው የስብ ክምችት እንደ ችግር አይቆጠርም።

እንደሚታወቀው ጉበት ከሰውነታችን አካል ክፍሎች በትልቅነቱ 2ኛ ደረጃ ሲሆን በምግብና መጠጥ አማካኝነት ወደ ሰውነታችን የገቡ ነገሮችን በማጣራትና በመፈተሽ ሰውነትን ሊጎዱ የሚችሉ ነገሮችን በማስወገድና የጉዳት መጠናቸውን በመቀነስ ሰውነት ላይ ሊደርስ የሚችልን ከባድ ችግር ያስቀራል።

ባጭሩ ጉበታችን ለሰውነታችን ዋና የጉምሩክ ጣቢያና ባትሪም ነው። ሞባይልም ሆነ ኮምፒውተር ያለባትሪ ዋጋ እንደሌለው ሰውነትም ያለጉበት ባትሪ ሎው ብሎ ሕይወትን ያቆማል።

መጠኑ የጨመረ የስብ መጠን ለጉበት መጠቃትና መመረዝ ያጋልጣል። ይህም ጉበት ላይ ጠባሳ እንድፈጠር ያደርጋል። ይህ ደግሞ ጉበት ስራውን በአግባቡ እንዳያከናውን ያደርገዋል።

የጉበት ስብ እንድፈጠር መጠኑ የጨመረ የአልኮል መጠን ትልቁን ድርሻ ይይዛል።

✍በጉበት ውስጥ ስብ ሲከማች ሊታዩ የሚችሉ ምልክቶች

🍐ብዙ ጊዜ ቶሎ አያሳይም። እየቆየ ግን በቀኝ የላይኛው የሆድ ክፍል ላይ ህመምና መጥፎ ስሜት
🍐የጉበት ጠባሳ መፈጠር

የጉበት ጠባሳ ካለ የሚታዩ ምልክቶች

1. የምግብ ፍላጎት መቀነስ
2. የክብደት መቀነስና ድካም ስሜት
3. አቅም ማነስ
4. በአፍንጫ ደም መፍሰስ
5. የቆዳ ማሳከክ
6. ቆዳና አይን ቢጫ መሆን
7. የሆድ ህመም
8. የሆድ ማበጥ
9. የእግር ማበጥ
10. በወንዶች ላይ ጡት ማበጥ
11. ግራ መጋባት

የጉበት ጠባሳ በጣም ከባድ ችግር ነው።

ለሕይወትም አስጊ ስለሆነ የጤና ባለሙያ ክትትልና እንክብካቤ በእጅጉ አስፈላጊ ነው።

✍በጉበት ላይ ለምን ስብ ይጠራቀማል?

🍐ሰውነት ስብን መጠቀም አለመቻል።
🍐 ብዙ ጣፋጭ ተጠቃሚ መሆን
🍐መጠኑ ከፍ ያለ አልኮል መጠጣት

✍ችግሩን የሚያባብሱ ነገሮች

🍐 ውፍረት
🍐 ከፍተኛ ደም ግፊት
🍐 ስኳር በሽታ
🍐ብዙ ስብ በሰውነት ውስጥ መከማቸት
🍐የጉበት ቫይረስ ሲ
🍐መድኃኒቶች(methotrexate, tamoxifen, amiodorone and valproic)
🍐 ለመርዛማ ነገሮች መጋለጥ
🍐 እርግዝናና ሌሎችም ናቸው።

✍መመርመሪያ መንገዶች

🍐 የተለያዩ ጥያቄዎች በመጠየቅ
🍐የተለያዩ ምልክቶችን በማየት
🍐አካላዊ ምርመራ በማድረግ
🍐 የደም ናሙና በመውሰድ
🍐የተለያዩ የማያ መሳሪያዎች በመጠቀም
🍐ከጉበት ናሙና በመውሰድ

✍ህክምናው

🍐የሚታዘዝ መድኃኒት ባይኖርም አልኮልን ባለመጠጣት ፣ክብደትን በመቀነስና የባለሙያ ምክርንና ክትትልን በማክበር መቀነስና ከችግሩ መላቀቅ ይቻላል።

22/01/2026

የልበ-አሸንዳ ስርአት በሽታዎች
ክፍል ሶስት

የልብ ድካም ህመም (heart failure)

የልብ ድካም በአለማችን ቁጥር አንድ ገዳይ በሽታ ነው። በአለማችን ላይ በአመት ወደ ሰባት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በልብ ድካም ሳቢያ ህይወታቸውን የሚያጡ ሲሆን በሃገራችንም ቁጥሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአሳሳቢ መልኩ እየጨመረ ይገኛል።

የልብ ድካም ሲከሰት ወደ ልብ ጡንቻ የሚዘዋወረው ደም በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የሚቋረጥ ሲሆን ወደ ልብ ህዋሳት መሄድ ያለበት ኦክስጅንና ሌሎች ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች ስለማይደርሱ የልብ የመምታት ስራ ይስተጓጉላል ማለት ነው።

የልብ ድካም በዋነኝነት መንስኤው የልብ ደም ስር መጥበብ ሲሆን በተጨማሪም የኦክስጅን እጥረት፣ የልብ ደም ስር መኮማተርና የልብ ቀዶ ህክምና ሌሎች የልብ ድካም መነሻ ሊሆኑ ይችላሉ።

☑️ የልብ ደም ስር መጥበብ እንዴት ይመጣል?

የልብ ጡንቻዎች ደም በተገቢው መልኩ ወደ ሰውነታችን ለማድረስ ያልተቋረጠ ኦክስጅንና ሌሎች እንደ ግሉኮስ ያሉ ንጥረ ነገር ያስፈልጋቸዋል፤ ይህንንም ለማግኘት ቀጫጭን የሆኑ የልብ የደም ስሮች በልብ ጡንቻዎች መሃል ተዘርግተው ይገኛሉ።

አዘውትረን ቅባትና ስብ የበዛበት ምግቦችን የምንጠቀም ከሆነ እንደ ኮሌስትሮል ያሉ መጥፎ ስቦች በልብ ደም ስር ውስጥ መከማቸት ይጀምራሉ ፤ በጊዜ ሂደትም (እስከ 10 አመታት) የልብ የደም ስር መጥበብን ያስከትላል።

ከልክ ያለፈ ውፍርት፣ የደም ግፊት፣ ሲጋራ ማጨስ፣ የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ የስኳር በሽታ ለልብ ድካም ተጋላጭነትን ይጨምራሉ።

☑️ የልብ ድካም ምልክቶች

በልብ የደም ስር የተከማቸው ስብ በድንገት ተላቆ የደም ዝውውሩን ሲገታ የልብ ድካም ምልክቶች ይከሰታሉ። ምልክቶቹም ከሰው ሰው ሊለያዩ ይችላሉ፤ እንዲሁም በሴቶችና ወንዶች መካከል ሊለያይ ይችላል። የልብ ድካም ያጋጠመው ሰው የሚከተሉትን ምልክቶች ያሳያል።

🍀 የደረት ህመም፡ የህመሙ ደረጃ ከትንሽ እስከ ከባድ ሊሆን ይችላል፤
🍀 ታማሚው ደረቱ ላይ መክበድ፣ መጨምደድ፣ መግፋት ሊሰማው ይችላል፤
🍀 ህመሙ ከ3 እስከ 5 ደቂቃ የሚቆይ ወይም ሄድ መለስ የሚል ይሆናል ነገር ግን ህመሙ ከ10 ደቂቃዎች በላይ ከቆየ አስጊ ደረጃ የመድረሱ ማሳያ ነው።
🍀 የልብ ድካምን ህመም ከቃር ጋር ሊመሳሰል ይችላል። ህመሙ የአቀማመጥ ቦታን በመቀያየር አይጠፋም።
🍀 የህመሙ ስሜት ወደ ትከሻ፣ የግራ እጅ፣ አገጭና አንገት መሰራጭት ሊኖረው ይችላል።
🍀 ለመተንፈስ መቸገር፣ ትንፋሽ መቆራረጥ፣ ቶሎ ቶሎ መተንፈስ፤
🍀 በላብ መዘፈቅ፣ ማዞርና ድንግዝግዝ ማለት፤
🍀 ማቅለሽለሽና ማስመለስ፤
🍀 ድካም ድካም ማለት፤
🍀 የሰውነት መገርጣት፣ ከንፈርና ጣቶች አካባቢ መጥቆር፤
🍀 ራስን መሳት ሌሎች የልብ ድካም ምልክቶች ናቸው።

የልብ ድካም ምልክቶች በሴቶች፣ በአዛውንቶች እና በስኳር ታማሚዎች ላይ የተለየ ምልክቶች ወይም ከነ ጭራሹም ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ።

☑️ የልብ ድካም እንዴት እንከላከል?

💥 የደም ግፊት በትክክል መቆጣጥርና የታዘዘን መድሃኒት በትክክል መውሰድ፣
💥 የተመጣጠነ የአመጋገብ ስርአት መከተል (ፍራፍሬ፣ ጥራጥሬ፣ የእጽዋት ተዋጽኦ ዘይቶችን…)
💥 የኮሌስትሮል መጠን መቀነስ፤
💥 ስኳር ህመም ካለ በአግባቡ ክትትል ማድረግ፣
💥 አደንዛዥ ዕፅ ከመጠቀም፣ ሲጋራ ከማጨስ፣ አልኮል ከመጠቀም መቆጠብ
💥 ከመጠን ያለፈ ውፍረት ማስወገድ እንዲሁም አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ያስፈልጋል።

Add members

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️የልበ -አሸንዳ በሽታዎች ክፍል ሁለት❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️🍏የልብ ምት በሽታዎች(Arrhythmia)🍎✍ምንነት የልብ ምት በሽታዎች ...
11/01/2026

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
የልበ -አሸንዳ በሽታዎች
ክፍል ሁለት
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

🍏የልብ ምት በሽታዎች(Arrhythmia)🍎

✍ምንነት

የልብ ምት በሽታዎች ማለት የልባችን ከተለመደው በተለይ የምት ልኬት፣ የምት ምጣኔ እና የኤሌክትሪክ ስርአት ፍሰት መዛባት ነው። ትክክለኛው የልብ ምት ምጣኔ በአንዱ ሙሉ ምት እና በተከታታዮቹ መካከል ያለው ምጣኔ እኩል ርዝማኔ እና ቆይታ አለው የአንድ አዋቂ የልብ ምት ልኬት በደቂቃ ከስልሳ እስከ መቶ ይመታል በአማካይ ደግሞ ሰባ ሁለት ይመታል።

✍ የልብ ምት በሽታ አከፋፈል

በምት ልኬት እና ከሚነሳበት ፉካ አንጻር በየፈርጁ ይመደባሉ እነዚህም
📌 ከልኬት በታች :- ይህም የልብ ምት ልኬት መቀነስ፣ የኤሌክትሪክ ፍሰት መቋረጥ እና የኤሌክትሪክ ምንጩ መቆም ናቸው።
📌 ከልኬት በላይ :- ይህም የልብ ምት ልኬት መጨመር ከሚነሳበት ፉካ አንጻር ከሰጪ ልበ ገንዳ በላይ እና ሰጪ ልበ ገንዳ ምት በሽታ ተብለው ይከፈላሉ። ከሰጪ ልበ ገንዳ በላይ ያሉት የልብ ምት በሽታዎች ተቀባይ ልበ ገንዳ እርግብግቢት ፣ ሁናታዊ ሰጪ ልበ ገንዳ በላይ ምት መጨመር፣ ብዝሀ መነሻ ተቀባይ ልበ ገንዳ ልብ ምት መጨመር ናቸው። ከሰጪ ልበ ገንዳ የሚነሱ የልብ ምት ችግሮች ሰጪ ልበ ገንዳ ምት መጨመር፣ ሰጪ ልበ ገንዳ እርግብግቢት ናቸው።

✍ ምክንያቶቹ ምንድናቸው ?

የተለያዩ ምክንያቶች ሲኖሩት ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው ።
📌የታወቀ የልብ በሽታ ( ክፍ ከድ ልብ በሽታ፣ ልበ ጡንቻ በሽታ፣ የልብ ደም ቧንቧ በሽታ )
📌 ታይሮድ ሆርሞን መጨመር
📌 የንጥረ ነገሮች መዛባት
📌 መድኃኒቶች

✍ የሚያሰየው ምልክቶች ምንድን ነው?

📌 ሽርካታ( ልብ ምት መሰማት)
📌የትንፋሽ ማጠር
📌ራስን መሳት እና ራስን ማዞር
📌የልብ ምት መቆም ስሜት መኖር
📌ደረት ላይ ምቹ ያልሆነ ስሜት መሰማት
📌የልብ ድካም ካመጣ የልብ ድካም ምልክቶች መኖር ( ሳል፣ትንፋሽ ማጠር ፣ሲተኙ ትራስ ደርበው መተኛት ፣በትንፋሽ ማጠር ምክንያት ከእንቅልፍ መንሳት ፣ የሰውነት ማበጥ)
📌ድንገተኛ ሞት

✍ የሚሰሩ ምርመራዎች

📌 ሙሉ የደም ምርመራ
📌 የነጥረ ነገር ምርመራ
📌 የደረት እጅ
📌 የልብ አልትራሳውንድ(ECHO)
📌 የልብ የኤሌክትሪክ ፍሰት ምርመራ (ECG)
📌የታይሮይድ ሆርሞን ምርመራ
📌 የደም መርጋት ምርመራ

✍የሚሰጡ ህክምናዎች

📌 የልብ ምት ማስተካከያ መድኃኒት መስጠት
📌 አምጪውን ምክንያት ማከም
📌 የኤሌክትሪክ ሾክ መስጠት
📌 ቀዶ ህክምና የሚያስፈልገው ከሆነ ቀዶ ህክምና ማድረግ
📌 የደም ማቅጠኛ መስጠት

ዶር ምትኩ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

በቅንነት ሼር ያድርጉ ፣ ጓደኞቻችሁንም ጨምሩ
💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚

የጤና ትምህርት ለሁሉም

Address

Addis Ababa

Telephone

+251921322360

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr.zeset elif posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Dr.zeset elif:

Shortcuts

Share

Category