Nifas silk lafto woreda 12 Health center

Nifas silk lafto woreda 12 Health center We thrive to see healthy and prosperous community

22/07/2026
ለህፃናት የተለየ ትኩረት! በንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ 12 ጤና ጣቢያ የተሟላ የህፃናት ጤና ማዕከልየንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ 12 ጤና ጣቢያ፣ ለህፃናት ጤና የላቀ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛ...
18/07/2026

ለህፃናት የተለየ ትኩረት! በንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ 12 ጤና ጣቢያ የተሟላ የህፃናት ጤና ማዕከል
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ 12 ጤና ጣቢያ፣ ለህፃናት ጤና የላቀ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል። አሁን ላይ የህፃናትን ጤና አጠባበቅ ይበልጥ ለማዘመን እና ወላጆች ከረጅም ወረፋ እና እንግልት ነፃ እንዲሆኑ የሚያስችል "የህፃናት ጤና ማዕከል" በጤና ጣቢያችን ውስጥ በልዩ ሁኔታ ተቋቁሟል።
በአዲሱ አደረጃጀታችን ምን ያገኛሉ?
✅ ለህፃናት የተለየ ማዕከል፡ ከትላልቅ ታካሚዎች በተለየ መንገድ፣ ለህፃናት ምቹ በሆነ ሁኔታ የተዘጋጀ የህክምና አገልግሎት።
✅ ዲጂታል የአገልግሎት ካርድ (Service Card): የህፃናትን የህክምና ታሪክ በአንድ ቦታ የሚይዝ ዘመናዊ የካርድ ስርዓት ዘርግተናል። ይህም የክትባት እና የህክምና ክትትል ታሪክን ያለምንም መረጃ መጥፋት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመያዝ ያስችለናል።
✅ ያለ ወረፋ እና ፈጣን አገልግሎት፡ የዜጎች ቻርተርን መሰረት ባደረገ መልኩ፣ ህፃናት ሳይጉላሉ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ቅድሚያ የሚሰጥ አሰራር ተዘርግቷል።
✅ የተቀናጀ የክፍያ ስርዓት፡ የአገልግሎት ክፍያን ጨምሮ የሂደት አያያዙን በማዘመን፣ ወላጆች በትንሽ ጊዜ ውስጥ የተሟላ አገልግሎት እንዲያገኙ እናደርጋለን።
ወላጆች ሆይ!
የልጅዎ ጤናማ እድገት የእኛ ትልቁ የቡድን ስራ ነው። አዲሱ የህፃናት ጤና ማዕከላችን ለህፃናት ፍቅር እና ክብር የሚሰጥ፣ በዘመናዊ አሰራር የታገዘ ነው። ለክትባት፣ ለምርመራ ወይም ለጤና ምክር በየጊዜው ወደ ጤና ጣቢያችን በመምጣት የልጅዎን የጤና ካርድ ያስከፍቱ።
ጤናማ ህፃናት፣ ጤናማ ትውልድ!
📍 አድራሻችን፡ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 12፣ አዲስ አበባ
📞 ለበለጠ መረጃ፡ 0114700603
#የህፃናትጤና #ንፋስስልክላፍቶ #ወ

"ወርቃማ ሰኞ ለወርቃማ ውጤት " የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ጤና ጣቢያ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ጤና ጣቢያ የወር...
17/07/2026

"ወርቃማ ሰኞ ለወርቃማ ውጤት "
የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ጤና ጣቢያ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ጤና ጣቢያ የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር የ PHCU ዲፓርትመንት የ eCHIS (Electronic Community Health Information System) የማዘመን ሰራን በማስጆመር ፕሮግራም ተካሂዷል::

የ ብሎክ ተጠሪዎች, ዲፓርትመንት ሃላፊ,ቡድን መሪዎች እና የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በተገኙበት eCHIS [Electronic Community Health Information System] ዙሪያ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ተሰርቷ ።

በዕለቱ በክፍለ ከተማ PHCU ዲፓርትመንት ቡድን መሪ, በጤና ጣቢያ ስራ አስኪያጅ, በምክትል ሜዲካል ዳይሬክተር, ስለቀጣይ ስራ አቅጣጫ ተሰቷል ::

በቀጣይ የሚጆመረውን የማዘመን ስራ በተመለከተ እያንዳንዱ የሚሰበሰቡ መረጃዎች ጥራት እና ፍጥነት ላይ ትኩረት አድርገን ለመስራት ተግባብተናል!

በመጨረሻም ለ ም /ሜ/ዳ, ለዲፓርትመንት ሃላፊ, ለቡድን መሪ እና ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች እስካሁን ለንበራቸው የላቀ አፈፃፀም ምስጋና በቀጣይ ለሚጀመረው ሰራ ማበረታቻ የሚሆን ማበረታቻ ሽልማት ተደርጎላችዋል 🙏🙏🙏

በመክፈቻ ፕሮግራም ላይ ከጤና ጽህፈት ቤት የተገኙልንን የ phcu ዲፓርትመንት ሃላፊ አቶ ገብረ ማርያምን በወረዳ 12 ጤና ጣቢያ ስም እናመሰግናለን 🙏🙏🙏

ዛሬ በቀጠና አንድ ቆስጣ ሰፈር የሕፃናት ዕድገት ክትትል (Growth Monitoring and Promotion) እየተካሄደ ሲሆን፣ ዓላማውም የሕፃናትን የዕድገት ሁኔታ በመከታተል የምግብ እጥረ...
17/07/2026

ዛሬ በቀጠና አንድ ቆስጣ ሰፈር የሕፃናት ዕድገት ክትትል (Growth Monitoring and Promotion) እየተካሄደ ሲሆን፣ ዓላማውም የሕፃናትን የዕድገት ሁኔታ በመከታተል የምግብ እጥረትን ቀድሞ ለመለየትና ለወላጆች በተገቢው የሕፃናት አመጋገብ፣ የጡት ወተት አጠቃቀም እና የጤና እንክብካቤ ዙሪያ ግንዛቤ ለመስጠት ነው። ይህ አገልግሎት ጤናማና በተሟላ ሁኔታ የሚያድጉ ሕፃናትን ለማፍራት ከፍተኛ ሚና ያለው ነው።

በቀን 17/10/18FHT 5 ወርሀዊ ድጋፋዊ ክትትል ታስክ ፎርስ ያደረግን ሲሆን በተጨማሪም Eerly chilledhood development program parental coach workers በ...
17/07/2026

በቀን 17/10/18
FHT 5 ወርሀዊ ድጋፋዊ ክትትል ታስክ ፎርስ ያደረግን ሲሆን በተጨማሪም Eerly chilledhood development program parental coach workers በቼክሊስት ድጋፋዊ ክትትል አድርገናል።

17/07/2026

ሰላም
የ2018 ዓ.ም የ2ኛ ግማሽ ዓመት የሞዴል ቤተሰብ , ት/ቤት , ወጣት ማዕከል እና ብሎክ ምዘና የእቅዳችንን 100% ማሳካት ተችሏል 👍👍👍👍

👉24 ቱም ት/ቤቶች ሞዴል ሆነዋል👌

👉ወጣት ማዕከላችን ሞዴል ሆኖል👌

👉ካሉን 55 ብሎኮች 34 ቱ ሞዴል ሆነዋል
34÷55×100 = 62% (እቅዳችን ከ60 % በላይ ሞዴል ማድረግ ነበር 62% ላይ ነን በቀጣይ በደንብ መስራት ይጠበቅብናል )👌
👉👉👉 የሞዴል ቤተሰብ ስልጠና ከእቅዳቹ በላይ በወሊድ ፍቃድ ላይ የነበሩ (ያሉ) 3 ባለሞያዎቻችንን እቅድ ጨምራቹ በማሰልጠናቹ ከ100% በላይ አሳክተናል💪💪

ይህ ውጤት100% የእናንተ የድካም ውጤት ነው🙏🙏🙏
ሁላቹንም በዲፓርትመንታችን ስም እናመሰግናለን🙏🙏🙏
በቀጣይ በጀት ዓመት በዚህ የስራ መነሳሳት ,መደጋገፍና አንድነት በጋራ የሚጠበቅባቹን እንደምታሳኩ ባለሙሉ ተስፉ ነን 👍👍👍👍👏👏👏👏🙏🙏🙏🙏🙏👍

ዛሬ በወረዳ 12 የመጀመሪያ አህድ ጤና ክብካቤ ተቋም ከጥር  እስከ ሰኔ 2018   የተሰጠውን የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም የሞዴል ቤተሰብና የመኖረያ አካባቢ ፖኬጆች ስልጠናና ተግባር በተሟላ...
17/07/2026

ዛሬ በወረዳ 12 የመጀመሪያ አህድ ጤና ክብካቤ ተቋም ከጥር እስከ ሰኔ 2018 የተሰጠውን የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም የሞዴል ቤተሰብና የመኖረያ አካባቢ ፖኬጆች ስልጠናና ተግባር በተሟላ ሆኔታ ያጠናቀቁ ሞዴል ቤተሰቦችን አስመርቀናል🎓🎓🎓

Address

NL_12_4887 Street.40
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nifas silk lafto woreda 12 Health center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share