Hakim

Hakim Ethiopian blend of medicine, history & humor.
(239)

Message to Mekelle University's Medicine class of 95 & 96Dear Mekele University's CHS school of medicine first Batch, cl...
14/09/2026

Message to Mekelle University's Medicine class of 95 & 96

Dear Mekele University's CHS school of medicine first Batch, class of 1995 and 96 EC, kindly DM Dr. Sofanit Haile with the following link https://www.facebook.com/share/1MZDMDnikv/

In the DM include your current contact information, Phone number, email adress & more.

We are organizing an alumni and a reconnecting event. Those of you abord you will join us virtually. Once we have all you contact we will send the invitation and the venue.

It is going to be big.
Thank you in advance.

Dr. Sofanit Haile, Obstetrician and Gynecologist

ግንዛቤን እንጨምር ፤ ፍርሃትን አንዝራ✅ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ብቻ ከ2 እና 3 ዓመታት በፊት የጡት ካንሰር በጊዜው ተመርምረው የነበሩ ሁለት ታካሚዎችን አይቻለሁ።    ✅ በወቅቱ የ...
14/09/2026

ግንዛቤን እንጨምር ፤ ፍርሃትን አንዝራ

✅ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ብቻ ከ2 እና 3 ዓመታት በፊት የጡት ካንሰር በጊዜው ተመርምረው የነበሩ ሁለት ታካሚዎችን አይቻለሁ።

✅ በወቅቱ የሁለቱም የህመም ደረጃ የመጀመሪያዎቹ ደረጃ ላይ ስለነበር ቀዶ ሕክምና እንዲያደርጉ ተመክረው ነበር። ሆኖም ሕክምናውን በመተው ወደ ጸበልና ወደ ባህላዊ ሕክምና ሄዱ።

✅ አሁን ግን በሽታቸው ወደ ደረጃ 4 ካንሰር ከተስፋፋ በኃላ መጡ። በዚህ ደረጃ ደግሞ በሽታውን ለመፈወስ የሚደረግ ቀዶ ሕክምና አማራጭ አይሆንም፤ ሕክምናውም የበለጠ አስቸጋሪ ሲሆን የመዳን ዕድሉም በአጠቃላይ ዝቅተኛ ነው።

✅ ቀደም ብሎ የተገኘ የጡት ካንሰር በተገቢውና በወቅቱ ሕክምና ሲደረግለት የመፈወስ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑን ልብ ይበሉ።

🙏 እምነት፣ ጸሎት እና ዘመናዊ ሕክምና እርስ በራሳቸው የሚቃረኑ አይደሉም። ታካሚዎች ጸበል መጠመቅ፣ መጸለይ፣ መንፈሳዊ ምክር መቀበል እና ባህላዊ ድጋፍ ማግኘት እንዲሁም በተመሳሳይ ጊዜ ተገቢውን የሕክምና እርዳታ ማግኘት ይችላሉ።

👉 እባክዎ የካንሰር ሕክምናን በማዘግየት ተአምርን ብቻ አይጠብቁ።

👉 በጊዜው የሕክምና ምክር ይጠይቁ፣ በቂ መረጃ ከትክክለኛ ምንጭ ያግኙ፣ የሕክምና አማራጮችዎን ይረዱ።

❤️ ግንዛቤን እንጨምር ፤ ፍርሃትን አንዝራ።
ዶ/ር ተስፋዬ አጋ የጡት እና ኢንዶክራይን ቀዶ ህክምና ሰብ-ስፔሻሊስት

ለማማከር/ቀጠሮ: 6646 / +251986444400

Telegram: t.me/HakimEthio

On Wednesday, September 9, 2026 (Pagume 4 Unity Day), Ethio-Tebib Hospital proudly participated in a major community hea...
14/09/2026

On Wednesday, September 9, 2026 (Pagume 4 Unity Day), Ethio-Tebib Hospital proudly participated in a major community health and charity event held at Meskel Adababay, Addis Ababa.

The event was organized by the Ministry of Health in collaboration with the Office of the Prime Minister and the Government Communication Service, bringing together public and private health facilities in a collective effort to provide accessible healthcare services to the community and promote health and national unity.

Ethio-Tebib Hospital medical team provided a range of free medical screening and consultation services, including:
🔹 Blood pressure and vital-sign assessment

🔹 Abdominal ultrasound screening

🔹 Cervical cancer screening through VILI (Visual Inspection with Lugol’s Iodine)

🔹 Gynecological health assessment and consultation

Ethio-Tebib Hospital remains committed to advancing preventive healthcare, early detection, and accessible health services for the community.

📞For more information and to schedule an appointment, call +251933745555 or call our toll-free number 9000.

📍Our address is located on the road leading to Kolfe, Masalemiya Sefereselam.

📱Telegram 📱Tiktok 📱Facebook 📱Instagram 📱Youtube

𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨-𝐓𝐄𝐁𝐈𝐁 𝐇𝐨𝐬𝐩𝐢𝐭𝐚𝐥
We strive for your health!!

የግል ህክምና በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል በግል ህክምና የሚሰጡ አገልግሎቶች ፦🔹የቀዶ ህክምና አገልግሎት በስፔሻሊሰት እና ሰብ-ስፔሻሊሰት ሃኪሞች🔹የአጥንት ቀዶ ህክምና አገልግሎት🔹የጭንቅላት እ...
14/09/2026

የግል ህክምና በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል

በግል ህክምና የሚሰጡ አገልግሎቶች ፦

🔹የቀዶ ህክምና አገልግሎት በስፔሻሊሰት እና ሰብ-ስፔሻሊሰት ሃኪሞች
🔹የአጥንት ቀዶ ህክምና አገልግሎት
🔹የጭንቅላት እና ህብረ-ሰረሰር ቀዶ ህክምና አገልግሎት
🔹የደም ስር (ቫስኩላር) ቀዶ ህክምና አገልግሎት
🔹የህፃናት ቀዶ ህክምና አገልግሎት
🔹የፕላስቲክ እና ሪኮንስትራክቲቭ ህክምና አገልግሎት
🔹የውስጥ ደዌ ህክምና አገልግሎት
🔹የልብ ህክምና (ካትላብ)አገልግሎት
🔹የማህፀን እና ፅንስ ክትትል ህክምና አገልግሎት
🔹የስነ-ልቦና እና ማማከር ህክምና አገልግሎት
🔹የጥርስ ህክምና አገልግሎት
🔹ከአንገት በላይ ህክምና አገልግሎት
🔹የቆዳ ህክምና አገልግሎት
🔹የፊዚዮቴራፒ ህክምና አገልግሎት
🔹የራጅ (X-ray) ፣ የአልትራሳውንድ ፣ የሲቲ ስካን (CT-scan) ፣ የኤም.አር.አይ (MRI) ፣ የፓቶሎጂ እና የተለያዩ የላብራቶሪ ምርመራዎች አገልግሎት
🔹ስፒች ቴራፒ

የግል ህክምና አገልግሎት የሚሰጥባቸው ቀናት ፦

🔹ከሰኞ እስከ ሐሙስ
➪ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት ድረስ

🔹ዓርብ
➪ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት ድረስ

🔹ቅዳሜ ፣ እሁድና የበዓል ቀናት
➪ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ

የግል ህክምና የምትፈልጉ ሁሉ በተጠቀሱት ቀናት እንዲሁም ሰዓታት ውስጥ አገልግሎቱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

አድራሻ ፦ አዲስ አበባ - ጉለሌ ክፍለ ከተማ - ወረዳ 1 - ከሽሮሜዳ ወደ እንጦጦ በሚወስደው መንገድ ላይ ያገኙናል።

Can We Transform the Ethiopian Health System Without Transforming the Health Worker?We are building bigger hospitals, sp...
14/09/2026

Can We Transform the Ethiopian Health System Without Transforming the Health Worker?

We are building bigger hospitals, specialized centers, and more advanced facilities. These investments matter. But a fundamental question remains: Who will turn these buildings into a better health system?

A hospital is infrastructure.
A health system is people.

Yet for many health-care workers, the daily conversation is not about patients, innovation, or better care.

It is about survival:
When will my duty payment come?
How will I pay my rent?
How will I support my family?

These may sound like personal problems. They are health-system problems. A health-care worker consumed by financial stress and exhausting working conditions has less time and mental space to think about patient safety, efficiency, innovation, and improving care.

You cannot expect people to transform a system while they are struggling to survive within it.

This is not an argument against building hospitals. We need the buildings. But we also need to build the people who make them work.

Invest in infrastructure. But invest equally in the workforce. Because a sophisticated machine cannot care for a patient. People do.

Perhaps the greatest untapped resource in Ethiopia’s health system is not another building. It is the knowledge, creativity, and commitment of the people already inside it.

Dr. Mengisteab kassahun
Assistant Professor of internal medicine
Selale University

Telegram: t.me/HakimEthio

በተደጋጋሚ የፅንስ መቋረጥ ምንድን ነው? ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የእርግዝና መቋረጥ (ውርጃ) ሲከሰት ነው ተደጋጋሚ ዉርጃ ይባላል:: እርግዝናው በሽንት፣ በደም (hCG) ወይም በአልትራሳውን...
14/09/2026

በተደጋጋሚ የፅንስ መቋረጥ ምንድን ነው?

ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የእርግዝና መቋረጥ (ውርጃ) ሲከሰት ነው ተደጋጋሚ ዉርጃ ይባላል:: እርግዝናው በሽንት፣ በደም (hCG) ወይም በአልትራሳውንድ የተረጋገጠ መሆን በቂ ነው::

ውርጃዎቹ ተከታታይ (consecutive) መሆን ግዴታ አይደለም። ከማህፀን ውጭ የሚከሰት እርግዝና (Ectopic) እና ሞላር (Molar pregnancy) በዚህ ምድብ ውስጥ አይካተቱም። መቋረጡ ከ22 ሳምንታት በፊት የሚከሰት ነው።

ዋና ዋና ምክንያቶች (Causes)

የፅንሱ ክሮሞሶም እክሎች (Genetic/Chromosomal)፡ በጣም የተለመደው ነው። ከ50–60% የሚሆኑት የመጀመሪያ ሶስት ወር መቋረጦች የፅንሱ ክሮሞሶም መዛባት ያሳያሉ። የእድሜ መጨመር ዋነኛ ተጽዕኖ አለው።

የማህፀን መዋቅር ችግሮች (Anatomic)፡ የማህፀን ግድግዳ መከፈል (Uterine septum)፣ ፖሊፕ፣ እጢዎች የማህፀን ውስጥ ሽፋን መጣበቅ (adhesions) ወይም የመሀፀንበር መላላት

የሆርሞንና የሜታቦሊክ እክሎች (Endocrine & Metabolic)፡ የታይሮይድ ወይም እንቅርት ችግር እና ቁጥጥር ያልተደረገበት የስኳር በሽታ።

የደም መርጋትና የበሽታ መከላከል ችግሮች፡ በዋናነት Antiphospholipid Syndrome (APS)።

የአኗኗር ዘይቤ፡ ማጨስ፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣ ከፍተኛ የአልኮል ወይም ካፌይን አጠቃቀም።

ያልታወቁ ምክንያቶች (Unexplained RPL)፡ ብዙ ጊዜ የተወሰነ ምክንያት አይገኝም።

የምርመራ ሂደት

የመጀመሪያው እርምጃ፡ የተቋረጠው የፅንስ ቲሹ ክሮሞሶም ምርመራ (Chromosome testing of miscarriage tissue) – በተቻለ መጠን ለሁሉም በሁለተኛዉ መቋረጥ ግዜ እንዲደረግ ይመከራል

የማህፀን ምርመራ፡ ለሁሉም ምክንያቱ ያልታወቀ ዉርጃ ላለቸዉ

ሌሎች ምርመራዎች
- የታይሮይድ ምርመራ (TSH)
- የስኳር ምርመራ (HbA1c)
- Antiphospholipid antibodies (APS መስፈርት ሲሟላ)
- የወላጆች Karyotype (ያልተመጣጠነ ክሮሞሶም ሲገኝ ወይም ቲሹ ምርመራ።

ሕክምና

መንስኤውን ማከም፡ የማህፀን ቅርጽ እክል ካለ በቀዶ ሕክምና ማስተካከል፤ ታይሮይድ ወይም ስኳር በማረጋጋት መቆጣጠር።

APS ካለ፡ ዝቅተኛ መጠን ያለው አስፕሪን + ሄፓሪን።

የአኗኗር ማሻሻያ፡ ማጨስ ማቆም፣ ክብደት መቆጣጠር፣ ፎሊክ አሲድ መውሰድ፣ ጤናማ አመጋገብ።

ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ፡ ለሁሉም ጥንዶች በጣም አስፈላጊ ነው። ተደጋጋሚ ውርጃ ከፍተኛ የስነ-ልቦና ጫና ያስከትላል።

ጠቃሚ መልዕክት

ተደጋጋሚ የፅንስ መቋረጥ ያጋጠማቸው ሴቶች ተገቢውን ምርመራና ክትትል ሲያደርጉ ከ50% እስከ 80% በሚደርስ ዕድል ጤናማና የተሳካ እርግዝና ማግኘት ይችላሉ። ብዙ ጊዜ ልዩ ሕክምና ሳያስፈልግም እንኳን ስኬታማ ይሆናሉ።

ተስፋ መቁረጥ አያስፈልግም!

Ketsela Lemma: MD, MPH, Obstetrician and Gynecologist, Maternal fetal medicine sub-specialist

Telegram: t.me/HakimEthio

"ምች" - Oral Herps /Cold Soresበብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከንፈራችን ላይ፣ አፋችን አካቢቢ እና ውስጥ በድንገት የህመም ስሜት ያላቸው ትንንሽ ውሃ የቋጠሩ ሚመስሉ አይነት እብጠ...
14/09/2026

"ምች" - Oral Herps /Cold Sores

በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከንፈራችን ላይ፣ አፋችን አካቢቢ እና ውስጥ በድንገት የህመም ስሜት ያላቸው ትንንሽ ውሃ የቋጠሩ ሚመስሉ አይነት እብጠቶች ወይም ቁስለት ሲያጋጥመን 'ምች መቶኝ ነው' የሚል የተለመደ የህመም አገላለፅ አለን።

በተለይ' የተወሰኑ ምግቦችን ከተጠቀምኩ ቡሀላ አፌን በደንብ ሳልታጠብ ወደ ፀሀይ ስወጣ... ነው ምች ያገኘኝ' እንላለን።

'ፀሀይ ላይ ምግብ አትብላ ምች ይመታሀልም' ስንባል ያደግንም ብዙዎች ነን።

'ምች ይደጋገምብኛል : ይፀናብኛል: ያስቸግረኛል... እያሉ 'የሚናገሩም ብዙ ሰዎች አሉ።

'ምች ይምታህ' .. የሚለው ቃል ደግሞ የልጅነት የእርግማን ወይም ስድብ ትዝታችን ነው

ምች ምንድነው?

በአብዛኛው ማህበረሰባችን ዘንድ' ምች ተብሎ' ተብሎ የሚታወቀው ፦በአፍ ውስጥ ከንፈር እና አካባቢው የሚከሰት እና በትንንሽ ህመም ያላቸው ውሃ የቋጠሩ ሚመስሉ እብጠቶች ወይም ቁስለት ምልክቶቹ በዋናነት የሚገለፀው ሲሆን ፥በሳይንሳዊ መጠሪያው 'Oral Herps/Cold sores' ወይም አንዳንዴ ከንፈረ ላይ ብቻ ሲወሰን 'Herps labialis' ተብሎ ከሚጠራው የቫይረስ ኢንፌክሽን ጋር የሚስተካከል ህመም ነው።

ሆኖም ግን ሌሎች ከ Herps ቫይረስ ውጪ ባሉ ምክንያቶች የሚከሰቱ የአፍ ውስጥ እና አካባቢው ቁስለቶችም አንዳዴ በምልክት መመሳሰል የተነሳ በሰዎች ዘንድ ምች ተብለው ሊገለፁ እንደሚችሉም ማስተዋል ያስፈልጋል።

እናም በዚህ ፅሁፍ ላይ' ምች' ስል ለመገልፅ እየሞከርኩ ያለሁት በ herps ቫይረስ ሚከሰተውን እና ከአብዛኛው ማህበረሰባችን የምች ምልክቶች አገላለፅ ጋር የሚጣጣመውን 'Oral Herps' መሆኑን ቀድሜ ላስገነዝብ እፈልጋለሁ።

ምች/Oral Herps

ይህ 'Herps simplex virus 1 (HSV-1) ተብሎ በሚታወቅ የቫይረስ አይነት የሚመጣ በአፍ ውስጥ ስጋዎች (ምላስ : ድድ...): ከንፈር እና አካባቢው ባለው ቆዳ ላይ የሚከሰት ኢንፌክሽን ነው።

ሁለት አይነት የ HSV አይነቶች ሲኖሩ HSV-1 አፋ እና አካባቢውን ሲያጠቃ HSV-2 ተመሳሳይ ኢንፌክሽን በመራቢያ አካላት ላይ ያስከትላል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ 3.8 ቢሊየን (64%) እድሜያቸው ከ50 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች የOral Herps (ምች) የሚያመጣው ቫይረስ ተጠቂዎች ናቸው።

ቫይረሱ እንዴት ነው የሚሰራው?

ምች (Oral herps) በከፍተኛ ሁኔታ ተላላፊ ኢንፌክሽን ሲሆን በዋነኝነትም በቀጥታ የበሽታው ምልክት (ቁስለት : እብጠት : ምራቅ..) ጋር በሚደረግ ቀጥተኛ ንክኪ ይተላለፋል።

አንዳንድ ጊዜ ምንም ምልክቱ ከማይታይባቸው (ከሌለባቸው) የቫይረሱ ተሸካሚ ሰዎችም ጋር በሚደረጉ የጠበቁ ንክኪዎች (በመሳሳም : በምራቅ...) ሊተላለፍ ይችላል።

አንድ ሰው አንዴ በዚህ ቫይሰረስ (HSV-1) ከተጠቃ (ቫይረሱ ወደ ሰውነቱ ከገባ) ቡሀላ; ቫይረሱ እድሜ ልኩን አብሮት የሚኖሮ ሲሆን ፤ አብዛኛውን ወቅት ላይ ግን ምንም አይነት ምልክቶችን (ህመሞችን) አያሳይም።

ቫይረሱ አንዴ ወደሰውነታችን ከገባ ቡሀላ አብዛኛው ጊዜውን ፊታችን አካባቢ በሚገኝ ነርቭ ህዋስ (Trigeminal ganglion) ውስጥ ተደብብቆ(ፀጥ ብሎ/አድፍጦ/Dormant/inactive) የሚቀመጥ ሲሆን ፤ ምቹ አጋጣሚዎችን ሲያገኝ ግን ከመጠን በላይ በመራባት እና በመሰራጨት ጥቃት መፈፀሙን ጀምሮ ጉዳቶቹን/ምልክቶችን በአፍ ውስጥ ከንፈር እና አካባቢው ላይ ያሳያል። የዚያኔ 'ምች መታኝ' ወይም Oral Herps ተከሰተ እንላለን።

ምልክቶቹ

1. የህመም ስሜት ያለቸው ውሀ የቋጠሩ ሚመስሉ ትንንሽዬ እብጠቶች

2. የተላጠ ቁስለት (እብጠቶቹ ፈንድተው ሊፈጠር ሚቾል ቁስለት አይነት)

3. በተጨማሪም ማቃጠል: ማሳከክ: መውጋት: የመቅላት... አይነት ስሜቶች ሊኖሩ ይችላሉ

እንዲሁም ኢንፌክሽኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ የተከሰተው ከቁስለቶቹ እና እብጠቶች በተጨማሪ የሰውነት ህመም : ትኩሳት :ራስ ምታት :የጉሮሮ ህመም እና አንገት አካባቢ ያሉ ንፍፊቶች (cervical lymphnodes) እብጠት ሊኖር ይችላል።

ምች አንድ ሰው ላይ ለምን በየጊዜው ይመላለስ? (Recurrent Oral herps)

ምች ድንገት ወይም ደግሞ በተለያዩ አጋላጭ ነገሮች ምክንያት ሊነሳ ይችላል

ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው አንዴ ሰውነታችን ከገባ ቡሀላ የማይወጣ እና አፍ አካባቢ በሚገኝ ነርቭ ህዋሳችን ውስጥ በትንሽ መጠን ራሱን ደብቆ በአብዛኛው ምንም ምልክት ሳያሳይ (ጉዳት ሳያደርስ) አጋጣሚዎችን እየጠበቀ የሚኖር ሲሆን ፤ ራሱን ለማውጣት አቅም በሚያገኝበት እና ይበልጥ መራባት የሚችልበት እድል ሲያገኝ የተለመደው የአፍ እና አካቢው ቁስለቶች እብጠቶች እና ህመሙን ያስከትላል።

ለቫይረሱ አቅም ማግኘት እና ድጋሚ ህመም የመፍጠር ብቃትን የሚሰጡት ነገሮች ምንድናቸው?

1. አጠቃላይ የሰውነታችን የበሽታ መከላከል አቅም መዳከም ሲኖር

2. የተለያዩ የሰውነት ህመሞች ወይም ትኩሳት ሲኖር

3. ቀጥታ ፊታችንን ለፀሀይ ጨረር በምንጋለጥበት ወቅት

4. ከፋተኛ ጭንቀት: ድባቴ:.. በሚኖርበት ወቅት

5. የወር አበባ እና የሆርሞን መቀያየር ሲኖር

6. አፍ አካባቢ አደጋ ወይም ቀዶ ህክምናዎች

እነዚህ ከላይ የተገለፁ አጋላጭ ምክንያቶች በሚኖሩበት ወቅት በዋነኝነት የሰውነታችን አጠቃላይ በሽታን የመከላከለ አቅም ስለሚዳከም አካባቢያዊ ምክንያቶችም ተዳብለው ቫይረሱ በቀላሉ ከተደበቀበት ወጥቶ በመራባት እና በመሰራጨት አፋችን እና አካባቢው ላይ ጉዳቶቹን (ህመመሞቹን) ያስከትላል።

እውን እንዳንድ ምግቦች ምችን ያስከትላሉ?

እስካሁን ባለው ተጨባጭ የትኛውም አይነት ምግብ በቀጥታ ምች (Oral herps) ያመጣል ተብሎ አይታሰብም።

ሆኖም ግን አንዴ ቫይረሱ ወደ ሰውነታችን ገብቶ ከተደበቀ ቡሀላ አንዳንድ የምግብ አይነቶች ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች ቫይረሱ እንዲነቃቃ እንዲራበ እና ህመም እንዲፈጥር ሊያደርጉት ይችላሉ።

አመጋገባችን ታድያ በሁለት አይነት መንገድ ቫይረሱን ጉልበት እንዲያገኝ (እንዲነቃቃ) ሊያደርገው ይችላል

1. አመጋገባችን በቂ እና ተመጣጣኝ ሳይሆን ሲቀር እና የሰውነት የመከላከል አቅማችንን መደገፍ ሲሳነው

2. አንዳንድ የምግብ አይነቶች በውስጣቸው የያዙት ኬሚካል (አርጂኒን የተባለ ፕሮቲን) የቫይረሱን የመራባት እና የመስራት አቅም ስለሚጨምር

ጥናቶች እንደሚያሳዩት 'አርጂኒን 'የተባለው በተለያዩ የምንመገባቸው መአዶች ውስጥ የሚገኝ ፕሮቲን(አሚኖ አሲድ) የተወሰኑ ቫይረስ አይነቶች እድገትን በሰውነታችን ውስጥ የሚያነቃቃ እና የሚደግፍ ሲሆን ከእነሱም አንዱ ደግሞ ምች የሚስከትለው ቫይረስ HSV1 ነው።

ሰለሆነም አንዳንድ ሰዎች የተመረጡ ምግቦችን በልተው ለፀሀይ ሲጋለጡ በተደጋጋሚ ወዲያው ምች ይመታናል የሚሉት አንዱም ምክንያት ;ምን አልባትም ምግባቸው ከፍተኛ አርጂኒን ይዘት ያለው ሆኖ :፤ ቫይረሱ ፀሀይ እና አርጂኒኑ አንድ ላይ ድንገት ተገጣጥመውለት በአንዴ ከፍተኛ ጉልበት አግኝቶ ተጠቅሞበት ሊሆን ይችላል።

ምች ይታከማልን?

አብዛኛውን ጊዜ የሰውነት በሽታ መከላከል አቅማቸው ደህና የሆኑ እና ብዙም 'ያልተጎዱ' ሰዎች ከሽታው በራሳቸው ከአንድ እስከ ሁለት ሳምንት ባለው ጊዜ ውስጥ ያገግማሉ

በተጨማሪም የተለያዩ መድሀኒቶች ምችን ለማከም ሊታዘዙ የሚችሉ ሲሆን ፤ህክምናውም በዋነኝነት በተቻለ አቅም በፍጥነት የህመሙን ስሜቶች ቁስለቶችን እና ደረጃ መቀነስ እና ማጥፋት ነው

እንዲሁም አንዳንዴ ምች በጣም በተደጋጋሚ የሚያስቸግራቸው ሰዎች ከቅድመ ጥንቃቄዎች በተጨማሪ አነስተኛ መጠን ያለው ፀረ ቫይረስ መድሃኒት በየቀኑ አንዴ መውሰዱ (Suppressed therapy ) ድግግሞሹን ለመቀነስ ሊረዳቸው ይችላል።

እንዴት መከላከል ይቻላል?

1. የምች ምልክት ከሚያሳዩ ግለሰቦች ጋር ቀጥታ የአፍ ንክኪን መቀነስ (መሳሳም: የገራ መጠጫዎች...

2. የተመጣጠነ ምግብ መመገብ እና የሰውነት ጤናን መጠበቅ

3. በቂ ፈሳሽ መውሰድ

4. በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ

5. ጭንቀት:ድባቴ... መቀነስ

6. በ'አርጅኒን' ይዘት ባላቸው ምግቦች ምክንያት የሚመጣን የቫይረስ መነቃቃት ለመቀልበስ 'ላይዚን' በተባለው ፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን (እርጎ :አይብ: አፕል: አሳ...) ማዘውተር ወይም የላይዚን ሰፕልመንት ፒልሶችን መጠቀም።

7. እለንዲሁም ለፀሀይ ጨረር በመጋለጥ ምክንያት ምች በተደጋጋሚ ለሚያጠቃቸው በተቻለ መጠን ራስን ከቀጥታ የፀሀይ ጨረር ተጋላጭነት ማራቅ እና የፀሀይ መከላከያዎችን (Sunscreens) መጠቀም ይመከራል።

በመጨረሻም ፥ 'ምች አይምታቹ'

*ማጣቀሻ መፀሀፍት መረጃዎች

1. World Health Organization (WHO)
https://www.who.int

2. National Institutes of Health (.gov)
https://pmc.ncbi.nlm.nih.gov
Treatment and prevention of herpes labialis

ዶ/ር ፉአድ መሀመድ DMD,OMFS
የአፍ : የመንጋጋ እና ፊት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት

Telegram: t.me/HakimEthio

A Memorable Experience at the 14th European Conference on Mental Health in Prague, Czech Republic I am thrilled to share...
13/09/2026

A Memorable Experience at the 14th European Conference on Mental Health in Prague, Czech Republic

I am thrilled to share my recent experience at the 14th European Conference on Mental Health (ECMH) held in the enchanting city of Prague from September 9 to 11.

This conference brought together participants from 43 different countries, creating a vibrant tapestry of cultures and perspectives.

It was my first opportunity to engage on such an international stage, and I was eager to disseminate my research on the Prevalence and Determinants of Postpartum Depression Among Mothers Attending Postnatal and Immunization Clinics in Mekelle, Tigray.

Presenting my poster was not just a chance to share my findings; it was also an invaluable experience for connecting with fellow researchers and practitioners.

Engaging in discussions about our shared challenges and successes helped me realize that while our contexts may differ, our commitment to mental health remains a common thread that unites us all. I left with new insights and collaborations that I believe will enhance my work moving forward.

Beyond the academic engagements, I was captivated by the beauty of Prague. The city is a living museum, with stunning architecture that tells stories of centuries gone by.

Watching the Astronomical Clock come alive was a moment of pure magic, and strolling along the Charles Bridge offered breathtaking views of the Vltava River and the iconic Dancing House.

I would like to take this opportunity to express my heartfelt gratitude to my sponsors who supported me from the inception to the completion of this project and generously covered my accommodation for this event.

A special thank you goes to the Spanish Agency for International Development Cooperation (AECID), The Italian Agency for Development Cooperation, The European Union, The Ministry of Health Ethiopia, and Fundación CSaI. Your support has been instrumental in making this journey possible.

I also want to extend my appreciation to Mekelle University College of Health Sciences for organizing this event and providing the necessary support to bring my research to light. Lastly, I am deeply grateful to the organizers of the 14th European Conference on Mental Health for selecting me to present my research and for organizing such a beautiful event.

This experience in Prague has not only enriched my professional journey but has also left me with lasting memories of a beautiful city and a new chapter in my career.

Dr. Akebom Kidanemariam
Assistant Professor of Gynecology and Obstetrics
Mekelle University College of Health Sciences.

Telegram: t.me/HakimEthio

ጡት ማጥባት የጡት ካንሰርን ለምን ይቀንሳል?ጡት ማጥባት የጡት ካንሰርን ስጋት ሊቀንስ የሚችለው በሦስት ዋና ዋና መንገዶች እንደሆነ ይታሰባል። እነዚህም የቀረቡ ሳይንሳዊ መላምቶች (hypot...
13/09/2026

ጡት ማጥባት የጡት ካንሰርን ለምን ይቀንሳል?

ጡት ማጥባት የጡት ካንሰርን ስጋት ሊቀንስ የሚችለው በሦስት ዋና ዋና መንገዶች እንደሆነ ይታሰባል። እነዚህም የቀረቡ ሳይንሳዊ መላምቶች (hypotheses) ናቸው፦

1. እንቁላል መውጣትን እና የኢስትሮጅን መጠንን መቀነስ
ጡት ማጥባት የወር አበባ መመለስን ሊያዘገይ ይችላል (lactational amenorrhea)።

ይህም በሕይወት ዘመን ለኢስትሮጅን እና ፕሮጀስትሮን የሚኖረውን አጠቃላይ ተጋላጭነት ይቀንሳል። እነዚህ ሆርሞኖች የጡት ሴሎችን እድገት ሊያበረታቱ ይችላሉ።

2. የጡት ሴሎች ሙሉ በሙሉ እንዲዳብሩ ማድረግ

እርግዝና እና ጡት ማጥባት የጡት ህብረ ሕዋሳት የበለጠ እንዲዳብሩና እንዲበስሉ ያደርጋሉ። ይህም ሴሎቹ ለዲኤንኤ (DNA) ጉዳት የሚኖራቸውን ተጋላጭነት ሊቀንስ ይችላል።

3. የተጎዱ ሴሎችን ማስወገድ

ጡት ማጥባት ከተቋረጠ በኋላ የሚከሰተው የጡት ህብረ ሕዋሳት መልሶ መዋቀር (involution) የተጎዱ ሴሎችን ለማስወገድ ሊረዳ ይችላል፤ እነዚህ ሴሎች ካልተወገዱ ወደ ካንሰር ሊለወጡ ይችላሉ።

በአጠቃላይ ፣ አንዲት ሴት በሕይወቷ ውስጥ ለረዘመ ጊዜ ጡት ባጠባች ቁጥር የጡት ካንሰር ስጋቷ የበለጠ ሊቀንስ ይችላል።

ዶ/ር ሀናን አለባቸው: የጡት እና የኢንዶክራይን ቀዶ ሕክምና ሰብ ስፔሻሊስት

📞 ስለማንኛውም የጡት ችግር እኔን ለማማከር፦

* ኢትዮጠቢብ ሆስፒታል: 9000 ይደውሉ
* ኬርላንድ ሆስፒታል: 8699 ይደውሉ
* ኒው ሊፍ ሜዲካል ኮምፕሌክስ: 8565 ይደውሉ

Telegram: t.me/HakimEthio

The Patient Who Changed MeAs a medical intern, every shift teaches me something that no textbook ever could. One busy da...
13/09/2026

The Patient Who Changed Me

As a medical intern, every shift teaches me something that no textbook ever could.

One busy day in the emergency department, patients kept arriving one after another. Everyone was rushing, and it was easy to overlook someone who looked "stable."

I noticed an elderly man sitting quietly, holding his chest. He wasn't shouting or demanding attention. In fact, he kept apologizing for bothering us.

Something about him made me pause. I sat beside him, took a focused history, examined him, and immediately requested an ECG.

Within minutes, the ECG revealed an acute ST-elevation myocardial infarction (STEMI).

Everything changed instantly.

The team activated emergency management, and the patient received timely treatment. Before he left the hospital, he looked at me with tears in his eyes and said,

"Thank you for listening to me. If you had ignored me like everyone else, I might not be alive today."

I stood there speechless.

That day, I realized that medicine is more than interpreting ECGs, prescribing medications, or making diagnoses. It is about paying attention, trusting your clinical instincts, and remembering that every patient deserves to be heard.

As medical interns, we may still be learning, but compassion, careful listening, and acting at the right moment can save a life.

The most important lesson I learned wasn't from the ECG—it was that behind every heartbeat is a human being who trusts us with their life.

One last thing... let me share this page from my notebook: Some lessons are taught in lecture halls. The most important ones are written in our notebooks.

— Dr. Aklilu Tesfaye, MI (AHMC)

Telegram: t.me/HakimEthio

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hakim posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share