Ethiopian health today

Ethiopian health today Ethiopian Health Today is for awareness creation: health, education,foreign relation,Aid organizations,and professional development.

Ophthalmologist needed at University of Gondar
04/06/2026

Ophthalmologist needed at University of Gondar

Psychiatrist needed at University of Gondar Comprehensive Specialized Hospital
04/06/2026

Psychiatrist needed at University of Gondar Comprehensive Specialized Hospital

ከደም ስር መጥበብ እስከ ጋንግሪን መንስኤዎችና ቅድመ ጥንቃ ::ጋንግሪን በደም ዝውውር እክል (መታቀብ) ምክንያት የሰውነት ክፍል (በተለይ እጅ ወይም እግር) ሲሞት የሚከሰት አደገኛ የጤና ች...
02/06/2026

ከደም ስር መጥበብ እስከ ጋንግሪን መንስኤዎችና ቅድመ ጥንቃ ::

ጋንግሪን በደም ዝውውር እክል (መታቀብ) ምክንያት የሰውነት ክፍል (በተለይ እጅ ወይም እግር) ሲሞት የሚከሰት አደገኛ የጤና ችግር ነው። የደም ስር ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ሲዘጋ፣ ወደ ታችኛው የሰውነት ክፍል የሚሄደው ደም ይቋረጣል።

ደም የማይደርሰው የሰውነት ክፍል ኦክስጅን እና አልሚ ምግቦችን ስለሚያጣ ሴሎቹና ቲሹዎቹ (ጡንቻ፣ ቆዳ፣ ነርቭ)መሞት ይጀምራሉ፤ ይህም ወደ ጋንግሪንነት ያመራል። ይህ ችግር ልብ ላይ ሲከሰት የልብ ድካም፣ አንጎል ላይ ሲከሰት ስትሮክ፣ እግር ላይ ሲከሰት ደግሞ ጋንግሪን ያስከትላል።

የደም ስር መዘጋት ሲታሰብ በቀጥታ ወደ አእምሮ የሚመጣው የልብ ሕመም ወይም ስትሮክ (የአንጎል ደም ስር መዘጋት) ናቸው፡፡ ይህ የደም ስር መጥበብና መዘጋት እግር እና እጅ ላይ በሚከሰትበት ጊዜ ‹‹ጋንግሪን›› የተሰኘውንና የሰውነት አካልን እስከ ማጣት የሚያደርሰውን አስከፊ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡

ጋንግሪን በአካል ላይ ሙሉ ለሙሉ የደም ዝውውር ሲቋረጥና ኦክስጅን ሲታጣ የሚከሰት የሴሎች መሞት ሂደት ነው። በኢትዮጵያ በአብዛኛው ለእግር መቆረጥና ለጋንግሪን መከሰት ዋነኛው ምክንያት ሳይታወቅ የሚቆይ ወይም በአግባቡ የማይታከም የስኳር በሽታና የደም ስር መደደር ነው።

ይህ ጽሑፍ በድንገትና ቀስ እያሉ የሚመጡ የጋንግሪን ዓይነቶችን፣ ሰውነት አስቀድሞ የሚሰጣቸውን ማሳሰቢያ ምልክቶች እና አካልን ከአደጋ እንዴት መታደግ እንደሚቻል ያብራራል፡፡ ለዚህም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መምህርና የቀዶ ጥገና ሐኪም ፕሮፌሰር ነብዩ ስዩም የሰጡንን ማብራሪያ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

የደም ስር መዘጋት እና ጋንግሪን

ጋንግሪን በደም ዝውውር መታቀብ ወይም በደም ዝውውር እክል ምክንያት የሚመጣ ችግር ነው። ጋንግሪን በትርጉሙ ከሰውነት ክፍል እጅ፣ እግር ወይም ሌላው የሰውነት አካል ሙሉ ለሙሉ የደም ዝውውር ሲያጣ፣ በተለያዩ ምክንያቶች የደም ዝውውሩ ሲታቀብ፣ ደም ስር ሲዘጋ ወይም እንደ ኢንፌክሽን ባሉና በሌላ ጉዳት ምክንያቶች የደም ስር ሲመታ የደም ዝውውር ሲጎዳ የሚደርስ የበሽታ ዓይነት ነው።

ከጋንግሪን በፊት ብዙ ምልክቶች አሉ። ጋንግሪንን የሚያመጡት በድንገት የሚከሰቱም አሉ፣ ቀስ እያሉም የሚመጡ አሉ፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል። በድንገተኛ የሚከሰቱት በአብዛኛው በደም መርጋት ምክንያት ነው።

የደም ቧንቧ ውስጥ ደም ሲረጋ ወይም አንዳንድ ጊዜ ትልልቅ የደም ስሮች ሲዘጉ ጋንግሪን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ብዙ ጊዜ የተለመደው ምክንያት ደም መርጋት ነው። በደም ስር ውስጥ ደም መርጋት ወይም የረጋ ደም ከሌላ ቦታ መጥቶ አንድ የደም ስር ሲዘጋ የሚከሰት ነው።

ብዙ ጊዜ ደም የሚረጋው ልብ ውስጥ ነው፡፡ የረጋው ደም ከልብ ውስጥ ይሄድና በአንድ የደም ስር ውስጥ ይቀመጣል። ለምሳሌ የግራ ወይም የቀኝ እግር ውስጥ ይገባና ወደ ታች ያለውን የደም ፍሰቱን ሲዘጋው ከዛ በታች ያለው ክፍል ኦክስጅን እና ሌሎች ምግቦችን ያጣል። በዚያን ጊዜ ጋንግሪን ይከሰታል ማለት ነው።

ሂደቱ ሙሉ ለሙሉ ወይም በግማሽ መዘጋት ሊሆን ይችላል። ሙሉ ለሙሉ ሲዘጋ አጣዳፊ ሆኖ ቶሎ ጡንቻው፣ ቆዳው፣ አጥንቱ፣ ነርቩ ተጎድቶ ወደ ጋንግሪን ሊሄድ ይችላል። ነገር ግን በከፊል ሲዘጋ ጊዜ ሊሰጥ ይችላል፣ አሳሳችም ነው። ሰዎች ሌላ ነገር እየመሰላቸው በሙቀት በወጌሻ ለመታሸት ይሞክራሉ፡፡ በአብዛኛው ወደ ሕክምና የሚመጡት ችግር ውስጥ ከገቡ በኋላ ነው፡፡

ሙሉ ለሙሉ ሲሆን ግን ምልክት የሚሰጠው ቶሎ ነው። እግር መደንዘዝ ይመጣል፣ ከለር መቀየር ይታያል፣ ማንቀሳቀስ ይቸገራሉ እና ሲነካም ምንም አይሰማም። እንደዚህ ዓይነት ምልክት ሲኖራቸው ቶሎ ይመጣሉ። ግን በዚህ ደረጃ ሲደርስ ለማከም አስቸጋሪ ይሆናል፡፡

ዋናው ሕክምና የሚሆነውም የተጎዳውን አካባቢ ማስወገድ ይሆናል። ጋንግሪን የሆነ አካባቢ በጣም ትንሽ እንደጣትና መሰል አካባቢ ከሆነና ኢንፌክሽን ከሌለው ራሱ እንዲወድቅ ጊዜ ይሰጠዋል። ነገር ግን የተጎዳው ትልቅ አካል ከሆነ በሕክምና ማስወገድ ግድ ይላል፡፡ ይሄ ድንገት የሚከሰተው የደም ስር መዘጋት ሲሆን ነው።

ሌላው ቀስ እያለ በጊዜ ሂደት የሚከሰት ብዙ ጊዜ ተላላፊ ያልሆኑና አሁን የጤና ሚኒስቴርም ትኩረት የሰጣቸው በሽታዎች ናቸው፡፡ ለደም ስር መዘጋት ከፍተኛ አጋላጭ የሚሆኑት እንደ ስኳር፣ የደም ግፊት፣ ኮሌስትሮል ዓይነቶችና ሲጋራ ማጨስ ናቸው።
በእነዚህ ምክንያት የደም ስሩ መደደርና መወፈር ኮሌስትሮል እየተከማቸበት ደም ስሩ እየጠበበ ይመጣና መጨረሻ ላይ ቀስ እያለ ይዘጋል፡፡ እነዚህ ስር እየሰደዱ (chronic) በሚባሉ ቀስ እያሉ የሚመጡ ናቸው። በአብዛኛው ጋንግሪን የሚከሰተውም በክሮኒኮቹ ነው።

አብዛኞቹ እድሜያቸውም የገፋ ከሃምሳ ዓመት ከስልሳ ዓመት በላይ የሆኑ ናቸው። ወጣት ላይ ደግሞ የሚከሰተው ሲጋራ በብዛት የሚያጨሱ ሰዎች ላይ ነው። የሚያመጣው ችግርም የደም ስር መደደር ነው፡፡ የደም ስሩ ይቆጣል እየደደረ ይመጣና ሊዘጋም ይችላል።

እነዚህ ደም ግፊት፣ ኮሌስትሮል፣ ስኳር ግን የደም ስሩ መደደርና መወፈር ይመጣና ኮሌስትሮል እየተከማቸ ወደ ታች የሚወርደውን ደም ስር ይጎዳዋል። ወደታች የሚወርደው ደም በቂ ባልሆነ ጊዜ እግሩ የምግብና የኦክስጅን እጥረት ሲያጥረው መጀመሪያ ቁስለት ይጀምራል፡፡

ከቁስለትም በፊት የሚሰጣቸው ምልክቶች አሉ። የፀጉሩ መፈርፈር፣ ቆዳው ማብለጭለጭ ይጀምራል፣ ጥፍሩ መቡነን ወይም መፈርፈር ይጀምራል። እግር መቅላት፣ ወደታች ሲያንጠለጥሉት መቅላት፣ ወደ ላይ ሲያደርጉት ደግሞ መንጣት ዓይነት ምልክቶች ይሰጥና ቀስ እያለ ቁስለት ያመጣል ከቁስለት በኋላ ጋንግሪን ያመጣል፡፡

ቁስል ኢንፌክትድ ይሆናል፤ በሽታው እየተባባሰ ወይም ቁስሉ ይሰፋና ወደ ጋንግሪንነት ይቀየራል፡፡ የደም ዝውውሩ በቂ ደም ካላገኘ ወይም በሕክምና ካልተረዳ ጋንግሪን ይመጣል፡፡ ይሄ በአብዛኛው የሚከሰተው ስኳር ታማሚዎች ላይ ነው። ሌላ ሀገር ሃምሳ ዓመትና አርባ ዓመት ሲሞላ ማንኛውም ሰው ስኳር ምርመራ ያደረጋል፡፡

በኢትዮጵያ በአብዛኞቹ ታማሚዎች ሆስፒታል እንደዚህ ዓይነት ችግር ይዟቸው ሲመጡ ነው ተመርምረው ስኳራቸው ከፍተኛ እንደሆነ የሚታወቀው፡፡ ዘግይተው ሲመጡ ስኳሩንም ኢንፌክሽኑንም ለመቆጣጠር ያስቸግራል፡፡ ደም ስሩም በጣም የተጎዳ ይሆናል፡፡

በአብዛኛው ዓለም ላይ እግር የሚያስቆርጥ ጋንግሪን የሚያመጣው የስኳር በሽታ ነው። የስኳር በሽታን በትክክል መቆጣጠር ያስፈልጋል፡፡ ሐኪሞች ጋር ቀርቦ ወቅታዊ የሆነ ምርመራ ያስፈልገዋል፡፡

ከምርመራውም በኋላ ከስኳር ጋር ተያይዘው ሊመጡ የሚችሉ የእግርና የእጅ እንዲሁም ከልብና ከአንጎል ውጪ ያሉ ደም ስሮች መታወክ ምርመራ ማድረግ ይገባል፡፡ የልብና የአንጎል ደም ስር ምርመራ ማድረግም ያስፈልጋል።

የልብ ድካም የሚባለው ወይም ኤም አይ ማዮካርዲያል ኢንፋርክሽን በአብዛኛው አንጎልም ላይ ስትሮክ የሚያመጣው የደም ስር ጥበትና ደም መርጋት ነው። እነዚህ ነገሮች ልብም አንጎልም ላይ የሚከሰተው እግር ላይ ሲከሰት ጋንግሪን ያመጣል፤ ልብ ላይ ሲከሰት የልብ ድካም ያመጣል፡፡ አንጎል ላይ ሲከሰት ደግሞ ስትሮክ ያመጣል።

በሽታውን ለመከላከል ወቅቱን የጠበቀ የስኳር ሕመም ክትትልና ሕክምና ያስፈልጋል፡፡ የደም ግፊትም እንደዛው፡፡ ኮሌስትሮልም፣ ሲጋራ ማጨስ ማስወገድ፣ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ይገባል፡፡እድሜ ከ40 ዓመት በላይ ወይም ስኳር፣ ግፊት ኮሌስትሮል ያለባቸው ሰዎች በሳምንት አራት ወይም አምስት ቀን ከ40 ደቂቃ እስከ አንድ ሰአት ያህል አካላዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ይመከራል።

ገፍቶ ከሄደ ደግሞ መድኃኒቶች አሉ፤ በሽታው ከጀመረ ወይም አጋላጭ ምክንያት የሚባሉት እንደ ስኳር፣ ግፊት፣ ኮሌስትሮል በሽታዎች ካሉ የሚወሰዱ መድኃኒቶች አሉ። ደም እንዳይረጋ የሚከላከል የአስፕሪን ዘሮች አንታይ ፕላትሌትን መውሰድ ያስፈልጋል፣ ኮሌስትሮል የሚቀንሱ መድኃኒቶች ስታቲን የሚባሉት በጣም ውጤታማ እንደሆኑ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

የልብ ድካምን በመከላከል ስትሮክን በመከላከልና ጋንግሪንን በመከላከል ደረጃ በጣም ጥሩ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ይነገራል፡፡ ከሐኪሞች ጋር ክትትል ሲደረግ ስኳርና ግፊት ያለበትን ሰው ሁሉም ያው ኮሌስትሮላቸው እየታየ ወይም እድሜ እየታየ አስፕሪንና የኮሌስትሮል መድኃኒቶች እንዲጀምሩ ይደረጋል፡፡

ጥሩ ውጤት አለው፡፡ የመከላከል አቅሙም በጣም ጥሩ እንደሆነ ይነገራል፡፡ የተለያዩ ጥናቶች ይሄንን ያሳያሉ፡፡ በሽታው በተለይ ክሮኒክ በሚባለው ቀስ እያለ ጊዜ ወስዶ በኮሌስትሮል መዘጋት ሲመጣ ምልክቶቹ የቆዳ መለስለስና የማብለጭለጭ፣ ፀጉሩ ከእግር ላይ መውደቅ፣ ጥፍሮች መፈርፈር ይጀምራሉ፡፡

እንደዚህ ዓይነት ለውጦች ሲኖሩ ሕክምና ማግኘት ያስፈልጋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ምልክቶች ወይም አጋላጮቹ ማለትም ስኳር፣ ግፊት፣ ኮሌስትሮል፣ ሲጋራ ማጨስ ያሉ ነገሮች ሲኖሩ በጊዜ ስሮችን ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል።
College of Health Sciences Addis Ababa University

02/06/2026
We are a neutral and impartial organization. It is a principled choice that allows us to cross divides and bring help wh...
01/06/2026

We are a neutral and impartial organization. It is a principled choice that allows us to cross divides and bring help where it matters most.

We take action, not sides.

Learn more about our fundamental principles: http://ms.spr.ly/6181vGIYU

Ending the Ebola outbreak in eastern DRC’s Ituri Province will depend on the role of local leaders who best know their c...
01/06/2026

Ending the Ebola outbreak in eastern DRC’s Ituri Province will depend on the role of local leaders who best know their communities, the challenges and the solutions that can be taken in such a complex context.

I deeply appreciated the chance to meet with and listen to community leaders from faith, women’s, youth, business and other sectors last night in the Ituri capital, Bunia.

We discussed the critical importance of community ownership of the response to Ebola. This is essential to building the trust needed to life-saving behaviors, including urging people to report early for medical care, safe and dignified burials and fighting misinformation.

DRC has strong experience in ending Ebola outbreaks, and doing so has relied heavily on community action. I committed
World Health Organization (WHO)'s unwavering support to local leaders to end the outbreak as rapidly as possible.
✍️ Tedros Adhanom Ghebreyesus

Trust your community
30/05/2026

Trust your community

As the DRC battles a rapidly growing Ebola outbreak, investment in community health surveillance is critical,…

Every outbreak starts in a community.Long before laboratories confirm a diagnosis, before emergency teams mobilise, and ...
30/05/2026

Every outbreak starts in a community.
Long before laboratories confirm a diagnosis, before emergency teams mobilise, and before the world pays attention, communities are often the first to see the warning signs.

In his latest article published by SciDev.Net, Dr Githinji Gitahi explains why the current Ebola outbreak is a reminder that community trust, early detection, and strong community health systems remain our best defence against future health emergencies.

"The next outbreak is not a question of if, but when. The time to strengthen trusted community systems is now."

Read the full article via the link below:
https://newsroom.amref.org/op-ed/2026/05/drc-ebola-outbreak-exposes-community-health-gaps/

World Health Organization (WHO) Country Office in Uzbekistan World Health Organization (WHO)

✍️ Amref Health Africa

SciDev.Net: Bringing science & development together through news and analysis.

Africa is getting bigger but only in...(አፍሪካ/ቃ ትልቅ ሆነ)👇The MapIt need to be big in everything though, let's hope for it
30/05/2026

Africa is getting bigger but only in...
(አፍሪካ/ቃ ትልቅ ሆነ)👇
The Map
It need to be big in everything though, let's hope for it

Address

Zambiya Street
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian health today posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Ethiopian health today:

Share