Alsan Bilisummaa

Alsan Bilisummaa Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Alsan Bilisummaa, AIDS Resource Center, Addis Ababa.

23/11/2025
03/10/2025
02/10/2025
02/10/2025

በኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል አከባበር ወቅት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
***
አዲስ አበባ፤ መስከረም 22 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ በርካታ ህዝብ የሚታደምበት እና አባገዳዎች፣ ሀደ ስንቄዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚገኙበት የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል መስከረም 24 ቀን 2018 ዓ/ም በአዲስ አበባ ይከበራል፡፡

በዓሉ በሠላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት ትኩረት ሰጥተው ወደ ተግባር በመግባት እየሰሩ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጾ በተለይ በዓሉ ወደሚከበርበት ስፍራ የሚመጡ ታዳሚዎች ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ መኖሩን ተገንዝበው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡

ከዚህ ቀደም የተከበሩ ኃይማኖታዊና ብሔራዊ በዓላት በሠላም እንዲከበሩ ህብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር ወሳኝ ስራ ማከናወኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውሶ የዘንድሮው የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል በሠላም እንዲከበር የበዓሉ ታዳሚዎች እና የከተማው ነዋሪ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርጉ በፀጥታ አካላት ስም ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

በመሆኑም የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ፦
፨ ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ሜክሲኮ፣
፨ ከወሎ ሠፈር መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ፣
፨ ከቄራ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ ቡልጋሪያ፣
፨ ከመርካቶ በአቡነ ተ/ኃይማኖት ወደ ጥቁር አንበሳ የሚወስደው መንገድ አቡነ ተ/ኃይማኖት ቤ/ክ፣
፨ ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ፣
፨ ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ፣
፨ ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ፣
፨ ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር)፣
፨ ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት፣
፨ ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ፣
፨ ከራስ ሆቴል ወደ ስታድየም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል፣
፨ ከሐራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት፣
፨ ከአዲሱ ገበያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባንኮዲሮማ፣
፨ ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ፣
፨ ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ካዛንቺስ ሼል አጠገብ እንዲሁም
፨ ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወስደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ
ከመስከረም 23 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አስታውቋል፡፡

በአዲስ አበባ ዙሪያ ከሚገኙ የሸገር ከተማ አካባቢዎች በርካታ ህዝብ በዓሉን ለማክበር ከዋዜማው ጀምሮ ወደ ከተማችን የሚገባ በመሆኑ መላው ህብረተሰብ ተገቢውን አክብሮት በመስጠት የእንግዳ ተቀባይነት እሴታችንን አጉልቶ ሊያሳይ እንደሚገባ ፖሊስ አስታውሶ በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ገልጿል፡፡

በመጨረሻም ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-26-43-59 ፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በ987፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ መስመሮች ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

01/10/2025
18/07/2025

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Alsan Bilisummaa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share