21/03/2026
ክፍል 1
#ዳውን #ሲንድረም ( ) ምንድን ነው?
ዳውን ሲንድረም ማለት የዘረመል አፈጣጠር ችግር ሲሆን ዘላቂ የሆነ የጤና እክል ነው።
# በሰውነታችን ዉስጥ ያሉ እያንዳንዱ ህዋሶች 23 ዘረመል ከእናት🧬 ተጨማሪ 23 ዘረመል ከአባት 🧬ወስደው ይሰራሉ :: ስለዚህ ባጠቃላይ አንድ ሰዉ 46 ዘረመሎች በ እያንዳንዱ ህዋስ ዉስጥ አለሉት ማለት ነው!
# ከ 46ቱ ዘረመሎች በ 21ኛው ዘረመል ቦታ ላይ ሁለት ዘረመል መሆን የነበረበት ቦታ ላይ ሶስት ዘረመል ሆኖ ሲገኝ ዳውን ሲንድሮም(Down syndrome) ያለው ልጅ ሊፈጠር ይቺላል::
# በሕክምናው አለም ለምን አንዳንድ ህፃናት በዚህ ችግር እንደሚጎዱ በርግጠኝነት ባይታወቅም የእናቶች እድሜ መጨመር የዚህ የጤና እክል ያለባቸው ልጆች የመውለድ እድልን እንደሚጨምር ይታወቃል።
#ዳወን #ሲንድረም ምርመራዎች?
1. ከወሊድ በፊት / በእርግዝና ጊዜ:- የተለያዩ ምርመራዎችን በማድረግ በዕርግዝና ወቅት ፅንሱ ዳወን ሲንድረም እንዳለበት ወይም እንደሌለበት ማረጋገጥ ይቻላል።
2. ከወሊድ በኃላ :- በሚታዩ የአካል ምልክቶች ማወቅ እና በደም ምርመራ ማረጋገጥ ይቻላል።
#ዳወን #ሲንድረም ምልክቶቹ ምንድናችው
ዳወን ሲንድረም ያለበት/ባት ህፃን እንደተወለደ የሚከተሉትን አካላዊ ምልክቶች ይታዩባቸዋል
ትንሽ ራስ ቅል ( small head)
➣ጠፍጣፋ የፊት ገፅታ
➣የአንገት ማጠር
➣አንገት ኣካባቢ ድርብርብ ቆዳ
➣ወደ ላይ የተንሸዋረሩ አይኖች
➣ዝቅ ያለ ጆሮ
➣ደካም/ልል ሰውነት ጡንቻ
➣አጭር እና ሰፊ የእጅ መዳፎች
➣አንድ ወጥ የመዳፍ መስመር
ዶ/ር ቱሚም ጌታቸው (ጠቅላላ ሀኪምና ሁለንተናዊ የህጻናት እድገት ባለሞያ
ክፍል 2👇