Eka Kotebe Hospital - ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል

Eka Kotebe Hospital - ኤካ ኮተቤ  ሆስፒታል We are committed to becoming the premiere Neuroscience Institute in Africa, excelling in Mental Health, Neurology, and Neurosurgery.

This is the official page of Eka Kotebe General Hospital, Addis Ababa, Ethiopia. We are committed to becoming the first Neuroscience Institute in East Africa, with a focus on Mental Health, Neurology, and Neurosurgery.

30/08/2026

የአዕምሮ ጤና ላይ አተኩሮ የሚሰራው የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር ያደረግነውን ቆይታ ይመልከቱ፡፡ሕይወቴ ...

30/08/2026

Hospitaalli Eekkaa Kotobee Tajaajila Si'ataafi Qulqulluu Kennaa Jir...

🎓 ውጤትህ አንድ ቁጥር ነው፤ ዕድልህ ግን   በጣም ሰፊ!ነሐሴ 23 ቀን 2018:- አዲስ አበባ ውድ ወጣት፣ የ12ኛ ክፍል ውጤትህ ከጠበቅኸው በታች ሆኗል?ተስፋ አትቁረጥ! ይህ የመጨረሻህ አ...
29/08/2026

🎓 ውጤትህ አንድ ቁጥር ነው፤ ዕድልህ ግን በጣም ሰፊ!

ነሐሴ 23 ቀን 2018:- አዲስ አበባ

ውድ ወጣት፣ የ12ኛ ክፍል ውጤትህ ከጠበቅኸው በታች ሆኗል?
ተስፋ አትቁረጥ! ይህ የመጨረሻህ አይደለም።

ከፍተኛ ውጤት ማምጣት ትልቅ ዕድል ነው፤ ነገር ግን ዝቅተኛ ውጤት ማምጣት የሕይወት ዕድሎች በሙሉ ተዘግተዋል ማለት አይደለም። ዛሬ የምትኖርባት ኢትዮጵያ በፍጥነት እየተቀየረች ያለች አገር ነች። የሥራ ዓለምም እየተቀየረ ነው። ቴክኖሎጂ፣ ዲጂታል ሥራ፣ ሙያዊ ክህሎት፣ ሥራ ፈጠራ፣ ንግድ እና የፈጠራ ዘርፎች አዳዲስ እየተፈጠሩያሉ እድሎች ናቸው።

ስለዚህ ውጤትህ ዝቅተኛ ከሆነ ከራስህ ጋር የምትጠይቀው ጥያቄ፦
❌ “አልቻልኩም፤ አሁን ምን እሆናለሁ?” አይሁን።
✅ “ከዚህ በኋላ ምን መማር እችላለሁ? የትኛውን ክህሎት ማዳበር እችላለሁ? የትኛው ዘርፍ ለእኔ ይስማማል?” የሚል ይሁን።

🌱 የምትጀምረው ከዛሬ ነው
1. ከውጤቱ ይልቅ ችሎታህን ፈልግ።
ምን የተለየ ተሰጥኦ አለህ ? ቴክኖሎጂ? እጅ ሥራ? ሽያጭ? ንግድ? ፈጠራ? ሰዎችን ማገልገል? የችሎታህን አቅጣጫ ለይ።
2. አንድ ተፈላጊ ክህሎት ለይተህ ተማር።

ዛሬ የሚያስፈልገው የፈተና ውጤት ብቻ ሳይሆን ማድረግ መቻል ነው። ዲጂታል ክህሎት፣ ቋንቋ፣ የቴክኒክ ሙያ፣ የንግድ ክህሎት ወይም ሌላ ተፈላጊ የሙያ መስክ መማር ትችላለህ።
3. የሚቀጥለውን ዓመት እንደ የግንባታ ዓመት ተጠቀምበት።
አንድ ዓመት በአግባቡ ተጠቅመህ አዲስ ክህሎት ማዳበር፣ ልምድ ማግኘት እና የራስህን አቅም ማሳደግ ትችላለህ።
4. ራስህን ከሌሎች ጋር አታነጻጽር።
ዛሬ የተሳካለት ጓደኛህ በአንድ መንገድ ነው፤ አንተ ግን የዛረረውን ውጤትህን መነሻ አድርገህ ሌሎች አማራጭ መንገደሸችን ልትገነባ ትችላለህ። የሌላ ሰው መነሻ ከአንተ ጋር አይመሳሰልም።
5. ውድቀትን እንደ መረጃ ተመልከት።
ይህ ውጤት “እኔ አልችልም” የሚል መልዕክት ሳይሆን፣ “ሌላ መንገድ መፈለግ እና የተሻለ እቅድ ማውጣት አለብኝ” የሚል መረጃ ይሁንህ።
🇪🇹 ዛሬ ኢትዮጵያ የምትፈልገው ወጣት ነው
የሀገር ለውጥ የሚመጣው ደግሞ ዲግሪ ባላቸው ወጣቶች ብቻ አይደለም። ይልቁንም በሚሠሩ፣ በሚፈጥሩ፣ በሚያድሱ፣ በሚያመርቱ እና ችግር ፈቺ ሀሳቦችን በሚያመጡ ወጣቶች ነው።

ስለዚህ ዛሬ ያገኘኸውን ውጤት ተቀበል፤ ከስህተትህ ተማር፤ እቅድህን አስተካክል፤ አዲስ ራዕይ ሰንቅ። ውጤትህ ዝቅተኛ ሊሆን ይችላል፤ ህልምህ ግን ዝቅተኛ መሆን የለበትም! ያላየሀቸው በርካታ ወርቃማ ዕድሎች አሉ፤ አይኖችህን ከፍተህ ወደ ሩቅ ተመልከት!

ዛሬ የተዘጋ የሚመስለው በር ሌላ በር እንድትፈልግ የሚገፋፋህ ሊሆን ይችላል።
አትቁም። አትሸነፍ። አትተው።
የወደፊትህ ገና አልተጻፈም— የምትፅፈው አንተ ነህ! ደግሞም ትችላለህ! 🇪🇹❤️

#ወጣቶች #12ኛክፍል #ውጤት #ተስፋ #ክህሎት #የወጣቶችእድል #ኢትዮጵያ

" የአገልግሎት ጥራት አርማችን!"

“ንቁ ወጣት ለሀገር ግንባታ” ነሀሴ 21 ቀን 2018 :- አዲስ አበባ፣ የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል  ከጤና ሚኒስቴር እና ከየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር 300 ለሚሆኑ ወጣቶች “ንቁ...
27/08/2026

“ንቁ ወጣት ለሀገር ግንባታ”

ነሀሴ 21 ቀን 2018 :- አዲስ አበባ፣

የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ከጤና ሚኒስቴር እና ከየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር 300 ለሚሆኑ ወጣቶች “ንቁ ወጣት ለሀገር ግንባታ” በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት በሆስፒታሉ አዳራሽ ስልጠና ሰጥቷል።

ስልጠናው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን ከወጣቶች አቅም ግንባታና ከሀገር ግንባታ ጋር በማጣመር የተካሄደ ሲሆን፣ ወጣቶች በማህበራዊ ኃላፊነት፣ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ በፈጠራ እና በማህበረሰብ ልማት ላይ ያላቸውን ሚና እንዲገነዘቡ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን የሆስፒታሉ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር መገርሳ ዓለሙ በመክፈቻ ንግግራቸው አንስተዋል።

ወጣቶች የሀገር ኃይልና የለውጥ አራማጆች በመሆናቸው፣ ጉልበታቸውን፣ እውቀታቸውንና ችሎታቸውን ለሀገራዊ ልማት በማዋል የሀገር ግንባታ አበርክቷቸውን ማሳደግ እንደሚጠበቅባቸው በስልጠናው ተጠቁሟል።

ወጣቶች ከዕድሜያቸው ጋር ተያይዞ የሚመጡ ባህርያትን በጥበብ በመቆጣጠር ራዕይ ሰንቀው መራመድ እንደሚገባቸውም ተገልጿል።

የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ከሐምሌ 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን እያከናወነ ሲሆን በቀጣይም የተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ፣ የማዕድ ማጋራትና ሌሎች ድጋፎችንም በማጠናከር ህብረተሰቡን የማገልገል ተግባሩን በትጋት የሚቀጥል ይሆናል።

"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"

"የአገልግሎት ጥራት አርማችን!"

25/08/2026
25/08/2026
25/08/2026
"WALK the TALK"RC 76ነሀሴ 17 ቀን 2018:- አዲስ አበባ የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል አመራሮች በ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠናዊ ኮሚቴ /Regional Committe RC...
23/08/2026

"WALK the TALK"RC 76

ነሀሴ 17 ቀን 2018:- አዲስ አበባ

የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል አመራሮች በ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠናዊ ኮሚቴ /Regional Committe RC/ ስብሰባ አካል በሆነው "Walk the Talk" መርኃ ግብር ላይ ተሳተፉ።

የዓለም ጤና ድርጅት RC 76 ከነሀሴ 17-22 በተለያዩ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን በዛሬው ዕለት የተካሄደው የእግር ጉዞም የዚሁ ስብሰባ አንዱ አካል እንደሆነ ተገልጿል።

የዓለም ጤና ድርጅት RC 76ኛ ጉባኤ በአፍሪካ የጤና አጀንዳዎች እና ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር መሆኑን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

በእግር ጉዞው ላይ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንትና ስራ አስፈፃሚ አባላት እና የዓለም ጤና ድርጅት አመራሮች ተሳትፈዋል።

"የአገልግሎት ጥራት አርማችን!"

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Eka Kotebe Hospital - ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share