Fikir PsychΨ

Fikir PsychΨ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Fikir PsychΨ, Health & Wellness Website, Addis Ababa.

"ቁጥር ሲለወጥ ዘመን ተለወጠ ይባላል፤ ልብ ሲለወጥ ግን ሰው ተለወጠ ይባላል።" አቡነ ቴዎፍሎስእንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ!በየዓመቱ መስከረም ሲጠባ የቀን መቁጠሪያችንን እንቀይራለን፤ የ...
11/09/2026

"ቁጥር ሲለወጥ ዘመን ተለወጠ ይባላል፤ ልብ ሲለወጥ ግን ሰው ተለወጠ ይባላል።" አቡነ ቴዎፍሎስ
እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ!
በየዓመቱ መስከረም ሲጠባ የቀን መቁጠሪያችንን እንቀይራለን፤ የዓመቱን ቁጥርም በቁጥር እንጨምራለን።

እውነተኛው "አዲስ ዓመት" የሚጀምረው ግን የቀን መቁጠሪያው ገጽ ሲገለጥ ሳይሆን የውስጥ አስተሳሰባችን፣ ስሜታችን እና የልቦናችን እይታ ሲታደስ ነው።

ዘመን በጊዜ ሂደት በራሱ ይለወጣል፤ የልቦና ለውጥ ግን በራስ-ግንዛቤ (Self-awareness)፣ በውሳኔ እና በስነልቦናዊ ዝግጁነት የሚመጣ እውነተኛ የውስጥ ትራንስፎርሜሽን ነው።

ይህ አዲስ ዓመት የቀን መቁጠሪያችን ብቻ ሳይሆን አስተሳሰባችን፣ የስሜት ጤንነታችን፣ የተግባር አቅጣጫችን እና ስነልቦናዊ ጥንካሬአችን የሚታደስበት ይሁንልን!
🌼 መልካም የልቦና እና የዘመን መለወጫ በዓል! 🌼ፍቅር ሆሊስቲክ ኬር
https://t.me/fikirpsychchannel

10/09/2026

2018 ለእናንተ ምን ትልቅ ትምህርት አስተማራችሁ? ሀሳባችሁን አጋሩን!

አዲስ ዓመት ሲመጣ አዲስ ዕቅድ ማወጣታችን የተለመደ ቢሆንም፣ የትናንት ችግራችንን ሳንረዳ የምናቅደው ብዙም አይዘልቅም።
ያለፉ ውድቀቶችና የቆዩ አስተሳሰቦች ሳናውቀው የወደፊት ስኬታችን ላይ ተፅዕኖ የማሳደር አቅም አላቸው።
2019ን በእውነት የተለየ ለማድረግ ከትናንት ስህተቶች መማርና አነስተኛ ነገር ግን ቀጣይነት ያላቸውን ልማዶች መገንባት ያስፈልጋል።

ስለዚህ በ2019 ዕቅዶቻችን እንዲሳካ ቅድሚያ የስነልቦና ችግሮቻችን ላይ እንስራ።እንዳግዛቹ የምትፈልጉ በውስጥ መስመር አውሩኝ🙏

https://t.me/fikirpsychchannel
https://www.tiktok.com/t/ZP831GeVt/

27/07/2026

ሰላም ውድ ቤተሰቦቼ በአዲስ ነገር ተመልሻለሁ የምታውቁኝ በ ፍቅር ሳይክ ነበር።አሁን ደሞ Fikir Holistic Care(ፍቅር ሁለንተናዊ እንክብካቤ) በሚል መጥቻለሁ።የትምህርት ዝግጅቴ የጤና መኮንን፣የስነልቦና እና ስነመለኮት ደግሞ በማጥናት ላይ እገኛለሁ።ታዲያ እነዚህን የሙያ ዘርፎች በአንድ ላይ አካታች የሆነ የጤና ስርዓት ቢኖረን አስባችሁታል?

የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለን አንድ ሰው ጤነኛ የምንለው አካላዊ፣ማህበራዊ፣ስነልቦናዊ እንዲሁም መንፈሳዊ ጤናው ሁለንተናዊ በሆነ መንገድ ጤናማ ሲሆን ነው ይለናል።በስነመለኮትም ሰው ስጋ፣ነፍስ እና መንፈስ አለው እንደሚለን ታዲያ አንዱ ሲታወክ ሌላው ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል። ይህንን መሰረት በማድረግ እንደ አንድ የጤና ባለሙያ በዘርፉ ላይ መልካም አሻራ ለማሳረፍ በመስራት ላይ እገኛለሁ።
ስራዬን ስለምትደግፉ እና አብራችሁኝ ስላላችሁ አመሰግናለሁ🙏
አዲሱን የቴሌግራም ቻናልhttps://t.me/fikirpsychchannel እና የቲክቶክ አካውንቴን tiktok.com/.holistic.care እንድትወዳጁ በፍቅር ይጠይቃችኋለሁ።

ይህ መልዕክት ማንን እንደሚጠቅም አናውቅም እና ለወዳጆቻችሁ በማጋራት ቤተሰብ እንድትሆኑ እጠይቃለሁ።በቢሮ ማግኘት ለምትፈልጉ 📍 ሲምሲ ቅዱስ ሚካኤል አጠገብ ኢኮኖሚክስ አሶሴሽን 4ተኛ ፎቅ ታገኙኛለችሁ።አመሰግናለሁEthiopian Economics Associationion




🧠 “You don’t break a habit by force…You change it by understanding and replacing it.”Fikir psych "Where you talk to heal...
20/04/2026

🧠 “You don’t break a habit by force…
You change it by understanding and replacing it.”
Fikir psych "Where you talk to heal"
https://t.me/fikirpsych 🗣🧠👩‍⚕️

ሰላም ሴቶች ዛሬ ቀናችን ነው😁 እንኳን አደረሳችሁ። 🎉አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ሴትነት ለእናንተ ምንድን ነው?Lets talk to heal.☺️https://t.me/fikirpsych 🗣🧠👩‍⚕️
08/03/2026

ሰላም ሴቶች ዛሬ ቀናችን ነው😁
እንኳን አደረሳችሁ። 🎉
አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ሴትነት ለእናንተ ምንድን ነው?
Lets talk to heal.☺️
https://t.me/fikirpsych 🗣🧠👩‍⚕️

የእናንተ የፍቅር ግንኙነት ምን ይመስላል?አታችመንት ስታይል (Attachment Style) በሥነ ልቦና ውስጥ በልጅነት ጊዜ በልጅና በእንክብካቤ ሰጭ  (እናት/አባት ወይም አሳዳጊ መካከል የሚ...
14/02/2026

የእናንተ የፍቅር ግንኙነት ምን ይመስላል?

አታችመንት ስታይል (Attachment Style) በሥነ ልቦና ውስጥ በልጅነት ጊዜ በልጅና በእንክብካቤ ሰጭ (እናት/አባት ወይም አሳዳጊ መካከል የሚፈጠር ስሜታዊ ትስስርና ግንኙነት ዘይቤ ሲሆን፣ ይህም በአዋቂነት ጊዜ በፍቅር ግንኙነቶችና በሌሎች ግንኙነቶች ላይ ትልቅ ተጽእኖ ያሳድራል።

ዋና ዋናዎቹ አታችመንት ስታይል የምንላቸው እነዚህ ናቸው።

1. ደህንነቱ የተጠበቀ (Secure Attachment)
- ልጁ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ የተወደደና ድጋፍ የሚያገኝ ይሰማዋል።
- ቅርበትንም ነጻነትንም በቀላሉ ይቀበላል።
- በአዋቂነት፡ እምነት ያለው ግንኙነት፣ ጤናማ ግንኙነት፣ ስሜታዊ መረጋጋት፣ በቀላሉ ይተማመናል።

2. ጭንቀት ያለበት (Anxious / Preoccupied Attachment)
- የመተው ፍርሃት በጣም ከፍተኛ ነው።
- ቀጣይነት ያለው ማረጋገጫና ቅርበት ይፈልጋል።
- በአዋቂነት፡ ቅናት፣ ስሜታዊ ጥገኛነት፣ ስለ ግንኙነት ያለማቋረጥ ዋጋት፣ ብዙ ጭንቀት።

3. ቸልተኛ (Avoidant / Dismissive Attachment)
- እንክብካቤ ሰው ስሜታዊ ርቀት ወይም መካድ ነበረው።
- ስሜቶችን ይደብቃል፣ ብቻውን መተማመን ይማራል።
- በአዋቂነት፡ ቅርበትን ይርቃል፣ ነጻ ይመስላል ግን ቅርበት ሲፈልግ ይቸገራል፣ ስሜታዊ ርቀት ይኖረዋል።

4. የተዛባ (Disorganized /
Fearful -Avoidant Attachment)
- እንክብካቤ ሰው አስፈሪ ወይም የሚያስፈራ ነበር (ብዙውን ጊዜ ከአሰቃቂ ታሪክ ጋር የተያያዘ)።
- ልጁ ቅርበት ይፈልጋል ነገር ግን ይፈራልም፣ የተደባለቀ ባህሪ ያሳያል።
- በአዋቂነት፡ ስሜታዊ አለመረጋጋት፣ እምነት መገንባት አለመቻል፣ ከአሰቃቂ ተጽእኖዎች ጋር የተያያዙ ቅጦች።

ከዚህ በመነሳት የእርሶ የፍቅር ግንኙነት ጤናማ ነው ብለው ያስባሉ?ካልሆነ ከታች ያለውን መጠይቅ ሰርተው ምን ላይ እንዳሉ ራሶትን እና ግንኙነቶን ይመርምሩ።

ለሚመለከታችሁ ብቻ Happy Valentine's Day.❤️🪄

Fikir psych"Where you talk to heal"🦋
https://t.me/fikirpsych 🗣🧠👩‍⚕️

ሰላም የፍቅር ስነልቦና አባላት በውስጥ መስመር ከተጠየቅናቸው ጥያቄዎች በደንበኛችን ፍቃድ መሰረት ለእናንተ ያስተምራል ያልነውን ለውይይት እንሆ ብለናል።ያንብቡት"ሰዎች የገጠማቸውን ችግሮች እ...
12/02/2026

ሰላም የፍቅር ስነልቦና አባላት በውስጥ መስመር ከተጠየቅናቸው ጥያቄዎች በደንበኛችን ፍቃድ መሰረት ለእናንተ ያስተምራል ያልነውን ለውይይት እንሆ ብለናል።ያንብቡት

"ሰዎች የገጠማቸውን ችግሮች እየነገሩን ማልቀስ ቢፈልጉ ወይም ቢያለቅሱ መከልከል ወይም ማልቀሳቸውን ማስቆም ይኖርብናል ወይ? ሰዎችስ ሲያለቅሱ ምንድን ነው ማድረግ ያለብን እና የሌለብን?"

እስኪ በዚህ ጉዳይ ላይ ሀሳብ አስተያየታችሁን ስጡን እና እንወያይ።መልካም ጊዜ!
ሌሎችም በግል ማማከር የምትፈልጉ በውስጥ ፃፉልኝ🙏

Fikir psych"Where you talk to heal"🦋
https://t.me/fikirpsych 🗣🧠👩‍⚕️

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ።🙏https://t.me/fikirpsych
18/01/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ።🙏
https://t.me/fikirpsych

18/01/2026

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fikir PsychΨ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share