Digital Hakim

Digital Hakim Physicians activist
(3)

የሀዘን መግለጫየልደታ ክፍል ከተማ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት የECD Coordinator የነበረው አቶ ቢኒያም ልዑል በድንገተኛና ያልተጠበቀ ህልፈተ ሕይወት የተሰማኝን ከፍተኛ ሐዘን እየገለፅሁ። በወ...
10/09/2026

የሀዘን መግለጫ

የልደታ ክፍል ከተማ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት የECD Coordinator የነበረው አቶ ቢኒያም ልዑል በድንገተኛና ያልተጠበቀ ህልፈተ ሕይወት የተሰማኝን ከፍተኛ ሐዘን እየገለፅሁ። በወንድማችን ድነገተኛ ህልፈት መሪር ሀዘን ለደረሰባቸው ለቤተሰቦች፣ ለጓደኞች እና በሕይወት ዘመናቸው በበጎ ለቀረቧቸው ሁሉ ልባዊ መፅናናትን እመኛለሁ።
የአስከሬን ሽኝት ወደ ወልቂጤ የሚካሄደው ዛሬ ማለትም 5-13-2018 ዓ/ም ከቀኑ 3፡30 ጀምሮ

አድራሻ፡ ልደታ ኮንዶሚኒየም ብሎክ 31 አብነት ክሊኒክ አጠገብ ነው

ነፍሱን ከደጋጐቹ ጋር በዓፀደ ገነት ያኑርልን።😭😭😭

የአማራ ህክምና ማህበር ለተለያዩ ተቋማት/ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ለክልሉ ጤና ቢሮ፣ለሲቭል ሰርቪስና የሰው ሀብት ኮሚሽን፤ለክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ፤ለኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም(ባህ...
09/09/2026

የአማራ ህክምና ማህበር ለተለያዩ ተቋማት/ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ለክልሉ ጤና ቢሮ፣ለሲቭል ሰርቪስና የሰው ሀብት ኮሚሽን፤ለክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ፤ለኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም(ባህርዳር ቅርንጫፍ)፣ለክልሉ ፍትሕ ቢሮ፣ለአማራ ሚዲያ ኮርፐሬሽን/ስለ ጤና ባለሙያዎች የ2018 ዓ.ም ያልተከፈለ ዱቲና ስለ አዲሱ የሰው ሀይል ስምሪት ይፋው ደብዳቤ ፅፈዋል።
የማህበሩ ደብዳቤ በ PDF : https://t.me/DigitalHakim1 ታገኙታላቹሁ

09/09/2026

በአብክመ ጤና ቢሮ ትኩረት የተነፈገው እና እየቀጠለ ያለው የደብረ ማርቆስ ስፔሽላይዝድ ሆስፒታል የስነ አዕምሮ ሕክምና አግልገሎት ችግር
""""""""""""""""""""""""'''''''''''''''''''''''''''''''''''
በደብረ-ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል ከሚሠጡ አግልግሎቶች አንዱ የአዕምሮ ሕክምና ነው።
ደ/ማርቆስ ሆስፒታሉ ሪፈራል ሆስፒታል እንደመሆኑ መጠን ከተለያዩ ዞኖች እና የወረዳዎች እንዲሁም ከተለያዩ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች ለሚመጡ ታካሚዎች የተሟላ አግልግሎት እየሠጠ ይገኛል።
የደብረ-ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል የስነ አዕምሮ ሕክምና አግልግሎት በአማራ ክልል ካሉ ሆስፒታሎች ትልቁ እና የመጀመሪያው ሆስፒታል ለማለት በሚያስችል ደረጃ የራሱ የሆነ የሴት እና የወንድ መኝታ ክፍል በአጠቃላይ 12 አልጋዎች አሉት።
የሙያ ሥብጥርን ስንመለከት 1 ሳይካትሪስት፣ 1 ማስተርስ እና 7 የBsc ሳይካትሪ ባለሙያዎችን ይዞ እየሠራ ይገኛል። ነገር ግን ክፍሉ ከታችኛው አመራር እስከ የክልል ጤና ቢሮ ድረስ ትኩረት ባለመሠጠቱ ጭፍን እና ምክንያታዊነት በሌለው የትርፍ ሠዓት (Duty) ሥምሪት 2 ሰው ብቻ አራቱንም ክፍል ማለትም Emergency፣ የወንድ ምኝታ ክፍል የሴት ምኝታ ክፍል እና ከተለያዩ ክፍሎች ማለትም ከሜዲካል፣ ከሳርጂካል፣ ከዴሊቨሪ እና ኢመርጀንሲ በአነስተኛ የሰው ሀይል ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ እየተስተናገደ በመሆኑ ለታካሚውም ሆነ ለባለሙያው አስቸኳይ መፍትሔ የሚያስፈልገው ጉዳይ ሁኖ ይገኛል።

ያለ አዕምሮ ጤና ጤና የለም !!!

09/09/2026

ቀን፡ 03/13/2018

ለአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ ባህር ዳር

ጉዳዩ፡- በቅርቡ የወጣውን የጤና ባለሙያዎች የትርፍ ሰዓት ስምሪት መመሪያ አስመልክቶ የቀረበ አቤቱታ፣

ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው፣ ቢሯችሁ በቅርቡ ተግባራዊ ያደረገው አዲሱ የትርፍ ሰዓት የስምሪት መመሪያ፤ መሬት ላይ ያለውን የሕብረተሰቡን የጤና ተደራሽነት እና የባለሙያውን ተጨባጭ ሁኔታ ያላገናዘበ በመሆኑ ይህንን የቅሬታ ደብዳቤ ለማቅረብ ተገደናል።

እንደሚታወቀው በገጠር ጤና ጣቢያዎች ውስጥ የሚሰሩ የነርስ ባለሙያዎች የውጭ ታካሚ ክፍልን (OPD) ጨምሮ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነውን የጤና ጣቢያውን የሥራ ጫና የሚሸፍኑት የሕክምናው የጀርባ አጥንት ናቸው። ባለሙያው አሁን ያለውን አስቸጋሪ የገጠር የኑሮ ሁኔታ እና የጸጥታ ችግር በጽናት ተቋቁሞ ሌሊት ከቀን ሕዝቡን እያገለገለ ባለበት በዚህ ፈታኝ ወቅት፣ የወጣው አዲሱ መመሪያ "ለአንድ ጤና ጣቢያ 1 ነርስ ብቻ በትርፍ ሰዓት ይመደብ" ማለቱ የባለሙያውን ሞራል በእጅጉ የሚነካ እና የስራ መነሳሳትን ገደል የሚከት ነው።

ይህ አሰራር ጤናን በበላይነት እመራለሁ ከሚል ተቋም የማይጠበቅ ሲሆን፣ ውሳኔው የሕብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ጥራት ወደኋላ የሚጎትት ነው። የዚህ መመሪያ አተገባበር ዋና ዓላማ የሕዝብን ጤና ከማሻሻል ይልቅ፣ በጀትን በመቀነስ ላይ ብቻ ያተኮረ መሆኑን በግልጽ ያሳያል። የጤና አገልግሎት በበጀት እጥረት ምክንያት ሊጓደል የማይገባው የዜጎች ህይወት አድን ተግባር ነው።

ስለሆነም፣ የሚመለከታችሁ የጤናው ዘርፍ አመራሮች ይህን ተጨባጭ የሥራ ላይ ችግር በመረዳት፤ መመሪያው የሕዝብን ጤና ደህንነት፣ የሕክምናውን ተደራሽነት እና የባለሙያውን ከፍተኛ የሥራ ጫና ታሳቢ ባደረገ መልኩ በአፋጣኝ ዳግም ታይቶ ተገቢው መፍትሔ እንዲሰጠን በአክብሮት እንጠይቃለን።

ከሰላምታ ጋር!

08/09/2026

የነፋስ መውጫ የመ/ደ/ሆስፒታል በ2018 ባለው አፈፃፀም እና የታካሚ ብዛት በክልሉ እውቅና የተሰጠው ሲሆን ነገር ግን በተሰጠው የባለሙያ የዱቲ ስምሪት ከሚድዋይፍ ውጭ ሁሉም ተቀንሶብናል።ይህ ደግሞ የባለሙያውን የስራ ሞራል እየጎዳ ስለሆነ ድምፅ ሁኑን

08/09/2026

" ሳይቃጠል በቅጠል"
ሚሊዮኖች እንዲሞቱ የወሰነውን ከላይ ያለ የጤና አመራር ችግሩ ሳይፈጠር ከወዲሁ ይጠየቅልን

መቼም እንዳለመታደል ሆኖ ሀገራችን ኢትዮጵያ የተማረ የማይከበርባት፣ ለሕዝብ ማሰብ የሌለበት፣ እንዲሁ ስለ ብልጽግና ብቻ የሚወራበት ፣በአንጻሩ ጥቂቶች ባልተገባ ጥቅም የሚከብሩባት፣ሞት የተለመደባት ሀገር ከሆነች ውሎ አድሯል።
የጤናውን ሥርዓት እንኳን ብንመለከት በኢትዮጵያ ያሉ ሐኪሞች ቁጥር አናሳ ቢሆንም በ WHO ስታንዳርድ እንኳ ለጤና ባለሙያ የሚገባውን የማይከፈለው የጤና ባለሙያ ለዘመናት ሲያገለግል ኖሯል። ለምሳሌ የአዋላጅ ነርስ የሪስክ 470 ብር ነው ይኸ ታዲያ ምንድን ነው? ይኸ ብቻ አይደለም ሰንት ነገር አለ። ይኽ እንደዚህ በሚሆንበት ጊዜ የጤና ባለሙያው መብቱን ለመጠየቅ የተለያዩ ሰልፎች (Strike)
ሲያደርግ ብዙ እንግልት የደረሰባቸው እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የታገሉትን አንዘነጋም። በዚህ ጊዜ የተባለው ለጤና ባለሙያው ጥቅማ ጥቅም ዱቲ ጨምሮ ወደ ሰባት የሚደርሱ ጥቅማጥቅሞች እንደሚከበሩለት ተነግሮ ነበር።
ነገር ግን ጉዳዩ የተገላቢጦሽ ሆነና ስድስት ሰባት ወር የሠራነው ከዚያም በላይ እንቅልፍ አልባ ሌሊቶች አሳልፈን የለፋንበት ዱቲያችንን ይሰጠናል ብለን ስንጠብቅ ቁርጣችሁን እወቁት ብለውን እርፍ።
ሲቀጥል "ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም " እንዲሉ አበው የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የዱቲ መመሪያ ብሎ ያወረደው መመሪያ ሚሊዮን ማሕበረሰብን ሐኪም ቤት ሄደው ለችግራቸው መፍትሔ ሳይሆን የባሰ ችግር፣ ድኅነት ሳይሆን ሞት እንዲያጋጥመው እኩይ መመሪያ አውርዷል።

ነገር ግን ይህ መመሪያ ሲወርድ እኛ የጤና ባለሙያዎች ደግሞ ለሚፈጠረው ችግር ውርድ ከራሳችን ብለናል። ለምን ሲባል ዛሬ እየቀለድን ሲታመም ዝም ያልነው የጤና ሥርዓት አልቅሰንም ሊድን አይችልም።
ስለዚህ ጉዳዩን
ሳይቃጠል በቅጠል
ትኩረት ለጤና
ፍትሕ ለጤና ባለሙያ

08/09/2026

የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ከአሁን በፊት ተሠመርቶ የነበረ ሁሉም አይነት ነርስ 20 ነበር ነገር ግን በአዲሡ ድልድል የተፈቀደው ነርስ 13 ብቻ ነው።ሙያተኛ ለመሥራት አስቸጋሪ ነው።የጉድ ሀገር ሰርቢሥ area እየጨመረ ባለበት ሰአት የሙያተኛ ስምሪት መቀነሱ ተገቢ አይደለም።የጉድ ሀገር የሚድያ ሽፋን ይሰራልን

የሆስፒታል CEOዎች ጭምር የተቃወሙት ያለው የአማራ ክልል አዲሱ የዱዩቲ ስምሪት
08/09/2026

የሆስፒታል CEOዎች ጭምር የተቃወሙት ያለው የአማራ ክልል አዲሱ የዱዩቲ ስምሪት

08/09/2026

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኮሬ ዞን የጤና ባለሙያዎች አደረጃጀትና አመዳደብ ላይ ያለው ችግር የጤና አገልግሎት ጥራትን በቀጥታ የሚፈታተን፣ የህብረተሰቡን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ከባድ የአስተዳደር ጥፋት ነው። በጤና ጣቢያዎች በአንድ የአገልግሎት ክፍል ውስጥ የሚመደቡ ባለሙያዎች ቁጥር ከመጠን በላይ በመብዛቱ የአዳሪ ተረኛ ማደሪያ እጥረት እና መጨናነቅ እንዲፈጠር ሲያደርግ፣ በቢሮ ደረጃ ደግሞ አንድ ባለሙያ ሶስት እና ከዚያ በላይ መደብ ይዞ እንዲሰራ መደረጉ የተዛባ ስርዓት ነው። ይህ አሰራር የጤና አገልግሎትን ሚዛን የሚያሳጣ፣ ሙስናን እና ኢፍትሃዊነትን የሚያራምድ ወንጀላዊ ድርጊት ነው።

በጤና ጣቢያዎች ውስጥ የባለሙያዎች ብዛት ከመስፈርት ውጪ ሆኖ የአዳሪ ተረኛ መብዛት፣ በተለይም በሌሊት እና በአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት ላይ ከፍተኛ ግጭትና ብጥብጥ ይፈጥራል። የማደሪያ ቦታ እጥረት፣ የንፅህና መጓደል፣ የእንቅልፍ እጦት እና የስራ ጫና መጨመር የባለሙያዎችን ትኩረት ይቀንሳል። ይህም የህክምና ስህተት፣ የክትባት መዘግየት፣ የወሊድ ክትትል መስተጓጎል እና የአደጋ ጊዜ ምላሽ መዘግየት ያስከትላል። በተለይም እናቶች እና ህጻናት ላይ የሚደርሰው ጉዳት ሊተካ የማይችል የህይወት መጥፋት ሊሆን ይችላል።

በቢሮ ደረጃ ደግሞ አንድ ባለሙያ በላይ መደብ ይዞ መስራቱ የአገልግሎት ጥራትን ያፈርሳል። አንድ ባለሙያ በተለያዩ ቦታዎች ሲሰራ፣ ትኩረቱ ይከፋፈላል፣ ተጠሪነት ይደበዝዛል፣ የስራ ግዴታዎች ይረሳሉ፣ ሪፖርቶችም ውሸት ይሆናሉ። ይህ የጤና መረጃ ስርዓትን ያበላሻል፣ የበሽታ ክትትልን ያዛባል፣ የበጀት አጠቃቀምን ያጭበረብራል። ህብረተሰቡ ትክክለኛ አገልግሎት ሳያገኝ በድብቅ ስራ ላይ ለተሰማሩ ባለሙያዎች ጊዜው ያልፋል።

በኢትዮጵያ የጤና ስርዓት አደረጃጀት ላይ የተደነገጉ መመሪያዎች ። በተለይም በክልል ጤና ቢሮ የተላለፉ የስራ መደብ እና የሰው ሃይል አመዳደብ መመሪያዎች የባለሙያዎችን ብዛት እንደ ጤና ተቋም ደረጃ በግልጽ ይደነግጋሉ። ሆኖም በኮሬ ዞን እየተፈጸመ ያለው ድርጊት ይህንን መመሪያ በግልጽ የሚጥስ ነው።

የበለጠ አሳሳቢው ይህ የሚደረገው ለህብረተሰቡ ጤና ሲባል ሳይሆን፣ ነው። ይህ ማለት የጤና ባለሙያዎች በተግባር ሳይሆን በወረቀት ላይ ተመድበው የስልጠና አበል እና የፕሮጀክት በጀት የሚያገኙበት ነው። ይህ ደግሞ የመንግስትን ሃብት በመዝረፍ ረሃብን፣ ድህነትን እና የጤና ቀውስን የሚያባብስ ወንጀል ነው።

በተጨማሪም የፍትሃዊነትን መርህ የሚጥስ ነው። ይህም ብቁ ያልሆኑ ግለሰቦች በተደበቁ መደቦች ውስጥ ገብተው የህዝብ ገንዘብ ሲመገቡ፣ ብቁ የሆኑ ወጣቶች ግን እድል ሳያገኙ ይቀራሉ። ይህ የዘር ማነቆን፣ የጎሳ አድልዎን እና የፖለቲካ ቅጥርን የሚያበረታታ ስርዓት ነው።

ይህንን የተዛባ ስርዓት የፈጠሩት እና የሚያስፈጽሙት የቢሮ ኃላፊዎች በወንጀል ተጠያቂ መሆን አለባቸው። በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ መሰረት የህዝብ ሃብት መመዝበር፣ ሙስና መስራት፣ የመመሪያ ጥሰት በማድረግ የህዝብ ጤናን አደጋ ላይ መጣል እና የስራ መደብን በግል ጥቅም ማዛባት ከባድ ወንጀሎች ናቸው።

በተለይም የጤና አገልግሎት ላይ የሚደረግ ማንኛውም ሙስና የሰው ህይወት ላይ ቀጥተኛ ጉዳት ስለሚያደርስ፣ የኃላፊዎቹ ተጠያቂነት ቀላል አስተዳደራዊ እርምጃ ብቻ ሊሆን አይገባም። የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር የሰው ሃይል አስተዳደር መመሪያ፣ የክልል ጤና ቢሮ የስራ መደብ መመሪያ፣ የሲቪል ሰርቪስ ህግ እና የጤና ባለሙያዎች የስነምግባር ደንብ ሁሉም ይህንን ድርጊት በግልጽ ይከለክላሉ። እነዚህን መመሪያዎች ጥሰው የህዝብ ጤናን አደጋ ላይ የጣሉ ኃላፊዎች በፍርድ ቤት ቀርበው እንዲከሰሱ፣ ንብረታቸው እንዲታጣ እና የእስር ቅጣት እንዲወሰንባቸው ጠንካራ የህግ እርምጃ መወሰድ አለበት።

የኮሬ ዞን አስተዳደር እና የዞኑ ሲቪል ሰርቪስ ጉዳዩን ወዲያውኑ በማጣራት የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ አለባቸው፦

1. – በጤና ጣቢያዎች ከመስፈርት በላይ ያሉ ባለሙያዎችን ወደ እጥረት ወዳለባቸው ተቋማት ማዛወር።
2. – ሁሉም መደቦች በግልጽ እንዲታወጁ እና በውድድር እንዲሞሉ ማድረግ።
3. – የመመሪያ ጥሰት እና ሙስና የፈጸሙ ኃላፊዎችን በህግ ተጠያቂ ማድረግ።
4. – አንድ ባለሙያ አንድ መደብ ብቻ እንዲይዝ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ።
5. – ማህበረሰቡ የጤና አገልግሎት ጥራት ላይ ያለውን ችግር እንዲያውቅ እና ቅሬታ እንዲያቀርብ ማድረግ።

በዞን ጤና መምሪያ፣ በከተማ አስተዳደር፣ በጎርካ ወረዳ እንዲሁም በሳርማሌ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤቶች የሚስተዋሉ ተመሳሳይ ችግሮች በግልጽ ሲታዩ ቆይተዋል። ስለዚህ በቢሮ ደረጃ በጤና ዘርፍ በማስተርስ ተመርቀው ያለ መደብ ተንሳፋፊ የሆኑ እና በጤና ጣቢያዎች በድግሪ ተመርቀው ያለ አግባብ ከቁጥር በላይ የተሰገሰጉ ሠራተኞች እንደ አስፈላጊነቱ መደብ ተሰጥቷቸው ህዝብን ሊያገለግሉ ይገባል።

በቀጣይ ዘገባችን በሁሉም የጤና መዋቅሮች በቢሮ ደረጃ ማን ምን እና ስንት መደብ ላይ እየሰራ እንደሆነ ከነ ስም ዝርዝራቸው እናቀርባለን።

08/09/2026

በአስቸኳይ መልስ ይስጥ!

የአፋር ክልል የአዋሽ አርባ ጤና ጣቢያ የአሚበራ ወረዳ
1.ህገወጥ አሰራሮችን በማስቆም ጤና ባለሞያው ራሱን ለብዙ አደጋ አጋልጦ እንቅልፍ አጥቶ የለፋበትን ክፍያ በአግባቡ በ 2018 መመሪያ መሰረት ይክፈሉ።

2.ከጤና ባለሞያ ከወር ደሞዛቸው ለብልፀግና እየተባለ እየተቆረጠባቸው ይገኛል የሚመለከታቸው አካል መፍትሄ እንዲሠጣቸው ስንል እንጠይቃለን‼️

Address

Kazanchis
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Digital Hakim posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category