20/08/2026
ልጅዎ ምግብ ለመብላት እምቢ ብሏል? ማስገደድ ሳይሆን የምግብ ፍላጎቱን የሚመልሱ እነዚህን ብልህ ስልቶች ይጠቀሙ!
ብዙ ወላጆች ህፃናት ምግብ እምቢ ባሉ ቁጥር በቁጣ፣ በዛቻ ወይም በጉልበት ለማስበላት ሲጥሩ ይታያሉ። ነገር ግን ህፃናትን አስገድዶ ማብላት የምግብ ፍላጎታቸውን የበለጠ ከማጣቱ ባሻገር ከምግብ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ተቃራኒ(Negative) ያደርገዋል።ምግብን እንዲሸሹና እንዲጠሉም ያደርጋል።
ህፃናት ምግብ ለመብላት እምቢ የሚሉበት ምክንያት የጤና ችግር (ለምሳሌ፡ የጥርስ መብቀል፣ የሆድ ህመም)፣ የስነ-ልቦና ጫና ወይም ደግሞ የምግብ አቀራረብ አሰልቺነት ሊሆን ይችላል።ስለዚህም እነዚህን በጥናት የተረጋገጡ 5 ብልህ እና ፍሬያማ ስልቶች ይተግበሩ፡
• የምግብ ሰዓት ቋሚ ማድረግ: ህፃናት በፈለጉበት ሰዓት ጁስ፣ ብስኩት ወይም ጣፋጭ ነገር እንዲበሉ ከተፈቀዱ በዋናው የምግብ ሰዓት የመብላት ፍላጎታቸውን(Appetite) ይቀንሳል። በመሆኑም መክሰስ እና ዋና ምግብ የሚበሉበትን ሰዓት በስርዓት ይወሰኑ።በዛም መሰረት ምግብ ቢሰጡ ተመራጭ ነው።
• አነስተኛ መጠን ማቅረብ: በሳህኑ ላይ የተከመረ ምግብ ህፃናትን ያስፈራቸዋል። በጥቂቱ አቅርበው ሲጨርሱ ተጨማሪ እንዲጠይቁ ማበረታታት የተሻለ ውጤት አለው።
• የጋራ የምግብ ጊዜ መፍጠር: ህፃናት አዋቂዎችን የመኮረጅ ባህሪ አላቸው። በቤተሰብ ደረጃ በአንድ ላይ ተቀምጦ መመገብ የምግብ ፍላጎታቸውን ያነሳሳል።
• ምግብ በማዘጋጀት ሂደት ውስጥ ማሳተፍ: ልጅዎ እንደ እድሜው መጠን አትክልት እንዲያጥብ፣ ሳህን እንዲያቀርብ ወይም ምግብ እንዲፈጭ ያድርጉት። እራሳቸው ያዘጋጁትን ምግብ የመቅመስ ፍላጎታቸው ከፍተኛ ነው።
• ምግቡን ማራኪ እና አዝናኝ ማድረግ (Fun Presentation): ህፃናት በሚያዩት ነገር ይሳባሉ። ምግቡን በከለር ማሸብረቅ ፣ በፓስታ ወይም በፍራፍሬዎች ቅርፅ (ለምሳሌ የሰው፣ የኮከብ ወይም የቤት ቅርፅ) ሰርቶ ማቅረብ ፍላጎታቸውን ያነቃቃል።
ማሳሰቢያ: ልጅዎ ከምግብ እምቢተኝነት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሰውነት ክብደት መቀነስ፣ ፈጣን ድካም ወይም የህመም ምልክቶች ካሳየ ወደ ሆስፒታላችን በመምጣት የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስቶቻችንን እንዲያማክሩ እንመክራለን።
📍አድራሻ፦ ከ ጋሞ አደባባይ ወደ አውሮፕላን ማረፊያ መሄጃ 100 ሜትር ወረድ ብለው ወይም ከዋናው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወረድ እንዳሉ ኦቦሌ ሕንፃ ላይ ያገኙናል::ለበለጠ መረጃ 👉 ☎️046-881-08-28
አስተማማኝ ህክምና በአጠገብዎ!