23/08/2026
የአርባ ምንጭ ደም እና ሕ/ህ/ባንክ አገልግሎት ከኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አርባ ምንጭ ከቅርንጫፍ ጋር በመተባበር የደም ልገሳ መርሃ-ግብር አከናወነ።
አርባ ምንጭ ነሀሴ 17/2018 (የአርባ ምንጭ)
መርሃ-ግብሩ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግቢ "እያንዳንዱ ለጋሽ ህይወት አዳኝ ነው" በሚል መሪ ቃልም የተከናወነ ሲሆን በሂደቱም ለተቋሙ ሠራተኞች ስለ ደም ልገሳ ሠፋ ያለ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ከተሠጠ በኋላ የደም ልገሳ መርሃ-ግብሩ የቀጠለ ሲሆን በዚህም የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ሹፌሬ ሙሳን ጨምሮ ሌሎች የተቋሙ ሠራተኞች ተሳትፈዋል።
የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ -ህዋስ ባንክ አገልግሎት ተቋሙ መረሃ-ግብሩን በማመቻቸት ላደረገው መልካም ትብብር እንዲሁም በደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ለተሳተፉ ሁሉ እጅግ ከፍ ያለ ምስጋናዉን ያቀርባል።