Hawassa millennium primary health care unit

Hawassa millennium primary health care unit Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hawassa millennium primary health care unit, Medical and health, Beyond theTesfaye Gizaw business center, Awassa.

Hawassa Millennium Primary Health Care Unit is a leading health center in Hawassa City, providing quality services to over 86,000 people both within and outside its catchment area..

  ‎‎የሚሊኒየም ጤና አ/ጣቢያ ላቦራቶሪ በዓለም አቀፉ የደረጃ ዕድገት የጥራት ማሻሻያ ( ) መስፈርት ተመዝኖ የኮከብ 2 (Star 2) ደረጃን በማስመዝገብ ከሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢ...
30/07/2026



‎የሚሊኒየም ጤና አ/ጣቢያ ላቦራቶሪ በዓለም አቀፉ የደረጃ ዕድገት የጥራት ማሻሻያ ( ) መስፈርት ተመዝኖ የኮከብ 2 (Star 2) ደረጃን በማስመዝገብ ከሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (SPHI) የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶለታል::

‎ይህ ስኬት ወደ አለም አቀፍ የISO ደረጃ ለመድረስ ትልቅ እርምጃ ሲሆን ለዚህ ስኬት ሌት ተቀን የደከማችሁ የላቦራቶሪ ባለሙያዎቻችን እና መላው የጤና አ/ጣቢያው ሰራተኞች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!

‎ #ሚሊኒየም ጤና አ/ጣቢያ
‎ #ሐዋሳ

‎ #ጥራትን ማረጋገጥ ቀዳሚ ተግባራችን ነው!

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባት በሚሊኒየም ጤና ጣቢያ የመስክ ጉብኝት አደረጉ። #ሐምሌ 21/2018 ዓ/ምበጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎችንና የተመዘገቡ ውጤቶችን በተጨባጭ ለመገምገ...
28/07/2026

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባት በሚሊኒየም ጤና ጣቢያ የመስክ ጉብኝት አደረጉ።

#ሐምሌ 21/2018 ዓ/ም

በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎችንና የተመዘገቡ ውጤቶችን በተጨባጭ ለመገምገም ይረዳቸው ዘንድ፣ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ፋንታዬ ከበደ የሚመሩት የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎችና አመራሮች በሚሊኒየም ጤና ጣቢያ በመገኘት የመስክ ጉብኝት አድርገዋል።

በጉብኝታቸውም ተቋሙ የገበራቸውን በርካታ ከወረቀት ነፃ የአገልግሎት (paper-free digitalization services) እና የተመዘገቡ ውጤቶችን እንዲሁም አዲሱ የG+3 ማስፋፊያ ሕንፃ እየሰጠ ያለውን አገልግሎት በአካል በመገኘት ተመልክተዋል።

#ሚሊኒየም _ጤና አ/ጣቢያ
#ሀዋሳ

በሚሊኒየም ጤና አጠባበቅ የተዘጋጀው የክረምት ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር  ተካሄደ።የ"ፅዱ ጤና ተቋም" መርሃ-ግብር አካል በሆነው በዚህ መድረክ ላይ የጤና ባለሙያዎቻችን በመሳተፍ አረንጓዴ አሻ...
16/07/2026

በሚሊኒየም ጤና አጠባበቅ የተዘጋጀው የክረምት ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተካሄደ።

የ"ፅዱ ጤና ተቋም" መርሃ-ግብር አካል በሆነው በዚህ መድረክ ላይ የጤና ባለሙያዎቻችን በመሳተፍ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።

በሚሊኒየም ጤና አጠባበቅ የ4ኛ ሩብ ዓመት የቦርድ ስብሰባ ተካሄደ። #ሐምሌ 01/2018 ዓ.ምበዛሬው ዕለት የሚሊኒየም ጤና አ/ጣቢያ የ2018 ዓ.ም የ4ኛ ሩብ ዓመት መደበኛ የቦርድ አባላት ...
08/07/2026

በሚሊኒየም ጤና አጠባበቅ የ4ኛ ሩብ ዓመት የቦርድ ስብሰባ ተካሄደ።

#ሐምሌ 01/2018 ዓ.ም

በዛሬው ዕለት የሚሊኒየም ጤና አ/ጣቢያ የ2018 ዓ.ም የ4ኛ ሩብ ዓመት መደበኛ የቦርድ አባላት ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን በመድረኩም የሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት እና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ የተለያዩ አጀንዳዎች ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

/አ/ጣቢያ
#ሀዋሳ

የሚሊኒየም ጤና ጣቢያ EPAQ 2nd Cycle BRIDGE ክላስተር የ2018 ዓ.ም የአራተኛ ሩብ ዓመት ክላስተር meeting እና የዓመቱ ማጠቃለያ መድረክ አካሄዱ። #ሰኔ 25/2018 ዓ.ም ...
02/07/2026

የሚሊኒየም ጤና ጣቢያ EPAQ 2nd Cycle BRIDGE ክላስተር የ2018 ዓ.ም የአራተኛ ሩብ ዓመት ክላስተር meeting እና የዓመቱ ማጠቃለያ መድረክ አካሄዱ።

#ሰኔ 25/2018 ዓ.ም

ዛሬ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው ክላስተር የማጠቃለያ መድረክ ላይ ሁሉም የክላስተሩ ጤና ጣቢያዎች እና የሀዋሳ ከተማ ጤና መምሪያ የEPAQ 2nd Cycle BRIDGE መሪዎች የተገኙ ሲሆን፣ በመድረኩ ላይ የ2018 ዓ.ም የአራተኛ ሩብ ዓመት እና የዓመቱ ማጠቃለያ ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

/አ/ጣቢያ
#ሀዋሳ

ሚሊንየም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ  የ4ኛ ሩብ ዓመት ደም ልገሳ መርሃግብር አካሄደ:: #ሰኔ - 09/2018 ዓ/ምበዛሬው ዕለት የጤና ጣቢያው  ባለሙያዎች ደም የለገሱ ሲሆን፥ በደም እጥረት ምክን...
16/06/2026

ሚሊንየም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የ4ኛ ሩብ ዓመት ደም ልገሳ መርሃግብር አካሄደ::

#ሰኔ - 09/2018 ዓ/ም

በዛሬው ዕለት የጤና ጣቢያው ባለሙያዎች ደም የለገሱ ሲሆን፥ በደም እጥረት ምክንያት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የህይወት መጥፋት አደጋዎችን ለመታደግ የበኩላቸውን አስተዋፅዖ አበርክተዋል።

#ደም በመለገስ በደም እጥረት የሚሞቱ ወገኖቻችንን ህይወት እንታደግ!

አ/ጣቢያ

"የሚሊኒየም ጤና ጣቢያ MCC ከበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ጋር በመተባበር ያስገነባውን የአቅመ ደካማ አረጋውያን መኖሪያ ቤት አስረከበ።"
12/06/2026

"የሚሊኒየም ጤና ጣቢያ MCC ከበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ጋር በመተባበር ያስገነባውን የአቅመ ደካማ አረጋውያን መኖሪያ ቤት አስረከበ።"

 #የአገልግሎታችንን ጥራት ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሻሻል የእርስዎ አስተያየት በእጅጉ ያግዘናል!ተቋማችን በሚሰጠው የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ አስተያየት ለመስጠት ይህንን👇 ሊንክ በመጫን ወይም...
11/06/2026

#የአገልግሎታችንን ጥራት ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማሻሻል የእርስዎ አስተያየት በእጅጉ ያግዘናል!

ተቋማችን በሚሰጠው የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ አስተያየት ለመስጠት ይህንን👇 ሊንክ በመጫን ወይም ከዚህ በታች ያለውን QR Code Scan በማድረግ አስተያየትዎን ያስቀምጡ።

#ለጤናዎ የምንሰጠውን አገልግሎት ተመራጭ ተቋም አድርገው ስለመረጡን እናመሰግናለን!

06/06/2026

የቤተሰብ ተኮር ጤና አገልግሎት

 !!የሚሊኒየም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የG+3 ማስፋፊያ ህንፃ ግንባታ ተጠናቆ በዛሬው ዕለት በይፋ ተመረቀ!የአካባቢውን ማህበረሰብ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራት ይበልጥ የሚያሳድገው ይህ ...
27/05/2026

!!

የሚሊኒየም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የG+3 ማስፋፊያ ህንፃ ግንባታ ተጠናቆ በዛሬው ዕለት በይፋ ተመረቀ!

የአካባቢውን ማህበረሰብ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራት ይበልጥ የሚያሳድገው ይህ ዘመናዊ የG+3 ማስፋፊያ ህንፃ፤ በሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ አማካኝነት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

#በምረቃው ፕሮግራም ላይ፦
የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ፣ የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍፁም አሰፋ፣ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ፣ የሀዋሳ ከተማ የብልፅግና ፓርት ኃላፊ አቶ ማራዶና ዘለቀ፣ የሀዋሳ ከተማ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ይርዳቾ አናቶ፣ የምስራቅ ክ/ከተማ ኃላፊ አቶ ጴጥሮስ በጤላ እንዲሁም የክልሉና የከተማው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የአካባቢው ማህበረሰብ በክብር ተገኝተዋል።

ይህ የጤና መሠረተ-ልማት ግንባታ መጠናቀቅ ማህበረሰባችንን በተሻለ፣ በጥራትና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው። ለዚህ ስኬት መገኘት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ሁሉ ምስጋናችን የላቀ ነው።

#ሚሊኒየም ጤና አ/ጣቢያ
#ሀዋሳ፣
#ሲዳማ _ኢትዮጵያ

Address

Beyond TheTesfaye Gizaw Business Center
Awassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hawassa millennium primary health care unit posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share