Chagni Primary Hospital

Chagni Primary Hospital Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Chagni Primary Hospital, Hospital, Chagni 04, Awi Zone, Chagne.

Chagni Primary Hospital is a public health institution providing quality, safe, and people-centered primary and emergency healthcare services in line with the Ethiopian Ministry of Health standards.
📅 Established: May 3, 2007 E.C.
👥 272 HR

23/10/2026



የቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2019 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ***********//********//**************📍 ቻግኒ |  ጥቅምት 12/201...
22/10/2026

የቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2019 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ
***********//********//**************
📍 ቻግኒ | ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም
የቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የማኔጅመንት አባላት፣ የሥራ ሂደት ኃላፊዎች፣ ፎካሎች እና የሆስፒታሉ ሠራተኞች በተገኙበት የ2019 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በስኬት ተካሂዷል።
📊 የ1ኛ ሩብ ዓመት ዋና ዋና ስኬቶች በቁጥር፦
🏥 52,700 ተመላላሽ ታካሚዎች የታከሙ ሲሆን (92.3%)
👶 812 እናቶች በሰለጠነ ባለሙያ የታገዘ የወሊድ አገልግሎት አግኝተዋል (>100%)
🩺 6,683 እናቶች የማኅፀን በር ካንሰር ምርመራ ተደርጎላቸዋል (>100%)
🛏 1,121 ታካሚዎች የተኝቶ ሕክምና አገልግሎት አግኝተዋል (>100%) | 91% የአልጋ መያዝ ምጣኔ (BOR)
🚑 100% የድንገተኛ ሕክምና ታካሚዎች ከ5 ደቂቃ በታች ፈጣን ምላሽ አግኝተዋል
💊 82.4% የመድኃኒት እና 92% የላቦራቶሪ ምርመራዎች መገኘት ተረጋግጧል
💻 95% Information Revolution (Model Level)
🔬 SLIPTA 4-Star (★★★★) የላቦራቶሪ ደረጃ ማረጋገጫ ላይ ይገኛል
📋 90% የክሊኒካል ኦዲት (Clinical Audit) እና 89% የሪፎርም (EHSIG) አፈፃፀም
💰 5,376,824.00 ብር የውስጥ ገቢ ተሰብስቧል
🧭 የቀጣይ (የ2ኛ ሩብ ዓመት) ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎቻችን፦
የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስቀጠል እና ክፍተቶችን በመሙላት በቀጣይ ትኩረት የሚሰጣቸው አበይት ግቦች፦
👶 የጨቅላ ሕፃናት የሞት ምጣኔን መቀነስ፦ የሞት ምጣኔውን ከ5% ወደ 2% ዝቅ ማድረግ።
📊 ከ5 ዓመት በታች ሕፃናት የእድገትና ክትትል (GMP) ማሻሻል፦ ቅድመ-ምርመራንና የዕድገት ክትትል ሽፋንን ማሳደግ።
💊 የቪታሚን ኤ (Vitamin A) አገልግሎት ማሳደግ፦ ሁሉንም መስፈርቱን የሚያሟሉ ሕፃናት ተዳራሽ ማድረግ።
✅ የሕክምና አገልግሎት ጥራትና የታካሚ ደህንነትን የበለጠ ማጠናከር።
✅ አሰራራዊ ክፍተቶችን መሙላትና ዲጂታል የክትትል ሥርዓትን ማሳደግ።
✨ "ስኬት ሲታወቅ ይደገማል፤ ጥረት ሲመሰገን ይጠናከራል!"
ጤና ለሁሉም!
🏥 ቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

✍️ቻግኒ የመጀመሪያ  ደረጀ ሆስፒታል_ከማዴክስ ዲያግኖስቲክስ ኢትዮጵያየእውቅና እና የምስጋና በሰርተፊኬት አገኛ  ━━━━━━⭕️━━━━━ቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን...
13/10/2026

✍️ቻግኒ የመጀመሪያ ደረጀ ሆስፒታል_ከማዴክስ ዲያግኖስቲክስ ኢትዮጵያ
የእውቅና እና የምስጋና በሰርተፊኬት አገኛ
━━━━━━⭕️━━━━━
ቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን የህክምና አገልግሎት ጥራት ለማረጋገጥ ከሚያደርጋቸው ጥረቶች መካከል የግብአት አቅርቦት ሰንሰለትን ማጠናከር ዋናው ነው።

በዚህም መሰረት ማዴክስ ዲያግኖስቲክስ ኢትዮጵያ በመድኃኒት፣ በህክምና መሳሪያዎች እና በላቦራቶሪ ሬጀንቶች አቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ላሳየው የላቀ አፈጻጸም፣ ግብአቶችን በወቅቱና በጥራት ለማሟላት ላደረገው የማይተካ ሚና እንዲሁም ህብረተሰባችንን በጥረት ለመቀየር በጋራ በመስራታችን የ የምስክር ወረቀት (Certificate of Recognition) ተበርክቶለታል።

ላሳዩት የላቀ አጋርነት እያመሰገንን፣ ወደፊትም ህብረተሰባችንን በጋራ የማገልገል እቅዳችን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እናረጋግጣለን!

08/10/2026
✍️ታላቅ የድልና የኩራት ዜና! 🏆🎉🥇 እንኳን ደስ አለን! ቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል! 👏"ስኬት ልማዳችን ነው!"የሚለውን የሥራ ባህላችንን በተግባር ያረጋገጠው ሆስፒታላችን፣ ዛሬም በዞ...
04/10/2026

✍️ታላቅ የድልና የኩራት ዜና! 🏆🎉
🥇 እንኳን ደስ አለን! ቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል! 👏
"ስኬት ልማዳችን ነው!"
የሚለውን የሥራ ባህላችንን በተግባር ያረጋገጠው ሆስፒታላችን፣ ዛሬም በዞኑ የጤና ተቋማት መካከል በግንባር ቀደምትነት በመገኘት ሌላ አዲስ የስኬት ታሪክ ጽፏል! 💪✨
🎯 ታላቅ ውጤት! በሴቶች ላይ የማህፀን ጫፍ ካንሰር የሚያስከትለውን ሕመምና ሞት ለመቀነስ እና እስከ 2030 ዓ.ም. የተቀመጠውን አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ግብ ለማሳካት በሚደረገው ጥረት፤
🏆 በ2018 በጀት ዓመት የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራና ሕክምና አገልግሎት አፈጻጸም በዞኑ ከሚገኙ ሆስፒታሎች መካከል 1ኛ ደረጃ በማግኘት፡ 📜 የልዩ አፈጻጸም ምስክር ወረቀትና የምስጋና ሽልማት ተቀብለናል! 🥇👏
💚 ይህ ድል የሁላችንም የጋራ ጥረት ውጤት ነው! ይህ በየቀኑ፣ በየሰዓቱና በየደቂቃው የማህበረሰባችንን ጤናና ሕይወት ለመጠበቅ በትጋት የሚሰሩት ውድ የሕክምና ባለሙያዎቻችን፣ የጤና ባለሙያዎቻችን፣ የአስተዳደርና የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞቻችን የጋራ ጥረት፣ ቁርጠኝነትና ትጋት ማረጋገጫ ነው! 🙏❤️
👏 ለመላው የቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቤተሰብ — እንኳን ደስ አላችሁ!
🌟 ይህ ስኬት የመጨረሻችን ሳይሆን፣ የበለጠ ለመስራት የሚያበረታን አዲስ መነሻችን ነው!
📌 ማህበረሰብን በቅድሚያ • ጥራትን በተግባር • ስኬትን በልማድ!
🏥 ቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል "ጤና ለሁሉም!" | "አንድ ቡድን • አንድ ተልዕኮ"
#ኢትዮጵያ

29/09/2026
✍️መልካም የደመራና የብርሃነ መስቀል በዓል መልዕክት ከቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ (አቶ አዳነ ገበየሁ)እንኳን ለብርሃነ መስቀሉና ለደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!መ...
26/09/2026

✍️መልካም የደመራና የብርሃነ መስቀል በዓል መልዕክት ከቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ (አቶ አዳነ ገበየሁ)

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉና ለደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

መስቀል የፍቅር፣ የጽናት፣ የመስዋዕትነት እና የብርሃን ታላቅ ማኅተም ነው። ደመራ ሲበራ ጨለማ እንደሚገፈፍ ሁሉ፣ ይህ የተቀደሰ በዓል በሀገራችን፣ በወገናችን እና በቤታችን ላይ የመደጋገፍ፣ የእርስ በርስ መተሳሰብ እና የተስፋን ብርሃን ይበልጥ የሚያበራ ይሁንልን።

የቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል መላው ማህበረሰባችን እንዲሁም ሕሙማንን በፍቅርና በትጋት የማገልገል ተልዕኳችንን በላቀ ቁርጠኝነት እየተወጣችሁ ያላችሁ ባለሙያዎች፣ በዓሉ ለሁላችንም፡

• የጤና፣ የአንድነትና የእውነተኛ ፍቅር፣ የሰላምና የልብ እረፍት የሚሆንበት እንዲሆንልን በሙሉ ልብ እንመኛለን!

በዓሉን ስናከብር ስለ ሌሎች ማሰብን፣ ድካመኞችን መደገፍንና ለጤናችን ጥንቃቄ ማድረግን አንዘንጋ።

ቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

“ጤና ለሁሉም!”

መስከረም 16/2019 ዓ.ም

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሠላም አደረሳችሁ!በዓሉ የሠላም፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብና የደስታ ኢንዲሆንላችሁ እንመኛለን! ቻግኒ የመጀመሪያ ደረጀ ሆስፒታል“የእርሶ ጤና የኛ ተልዕኮ!”
26/09/2026

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሠላም አደረሳችሁ!
በዓሉ የሠላም፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብና የደስታ ኢንዲሆንላችሁ እንመኛለን!

ቻግኒ የመጀመሪያ ደረጀ ሆስፒታል
“የእርሶ ጤና የኛ ተልዕኮ!”

✍️ የታላቅ የህክምና ስኬት እና የሙያ አጋሮቻችን አድናቆት!____________📯_________________ዛሬ በህክምና ማዕከላችን እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ የተዋጣለት ሙያዊ ብቃት የሚጠይቅ ው...
23/09/2026

✍️ የታላቅ የህክምና ስኬት እና የሙያ አጋሮቻችን አድናቆት!
____________📯_________________
ዛሬ በህክምና ማዕከላችን እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ የተዋጣለት ሙያዊ ብቃት የሚጠይቅ ውስብስብ ቀዶ ጥገና (Malignant Ovarian Tumor Excision with Total Abdominal Hysterectomy) በሙሉ ስኬት ተጠናቋል!

በዚህ አበራች ኦፕሬሽን የማህፀን እና የኦቫሪ ካንሰር ዕጢው ሙሉ በሙሉ ተወግዶ የታካሚዋን ህይወት መታደግ ተችሏል።

ይህንን ፈታኝና ትልቅ ቀዶ ጥገና በላቀ ቅንጅትና ጥረት ላከናወኑት የቀዶ ጥገና ቡድን አባላቶቻችን የላቀ ምስጋና እና ፍጹም አክብሮት እናቀርባለን፦

የሰው ልጅ ህይወት ለማዳን ሌሊትና ቀን ያለዕረፍት ለምትተጉ የጤና ባለሙያዎቻችን በሙሉ ኩራት ይሰማናል! 🙏💙

የቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትለተከበራችሁ የማህበረሰባችን አባላት፣ ውድ ታካሚዎቻችን እና የህይወት አድኚው የሆስፒታላችን ቤተሰ...
10/09/2026

የቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
ለተከበራችሁ የማህበረሰባችን አባላት፣ ውድ ታካሚዎቻችን እና የህይወት አድኚው የሆስፒታላችን ቤተሰቦች በሙሉ፤
በቅድሚያ ለተስፋው አዲስ ማለዳ—ለ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት በሰላም፣ በጤና እና በፍቅር አደረሳችሁ!
አዲስ ዓመት የዘመን መለወጫ ብቻ አይደለም፤ የህይወት፣ የጤና እና የአዲስ ተስፋ የምንመኝበት ዘመን ነው። በሆስፒታላችን ግቢ ውስጥ በእያንዳንዱ ቀን የምናየው ጥንካሬ፣ የተስፋ ብርሃን እና የህይወት ትግል እኛን በሙሉ ልባችን እንድንሰራ ያበረታታናል። ያለፈውን ዓመት ፈተናዎችና የመሠረተ-ልማት ተፎካካሪ ሁኔታዎችን በፅናት አልፈን፣ የበርካቶችን ህይወት ለመታደግና ፈገግታን ለመመለስ የቻልነው በእናንተ እምነትና በትስስራችን ነው።
በ2019 ዓ.ም. አዲሱ ዘመን፦
• የህመም ስቃይ በፈውስ የሚተካበት
• የተስፋ መቁረጥ ስሜት በብሩህ ነገ የሚተካበት
• የእናትና የሕፃናት ፈገግታ በየቤቱ የሚያበራበት
እንዲሆንልን በሙሉ ፍቅርና ርህራሄ እንመኛለን።
እኛ የቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቤተሰቦች፣ በአዲሱ ዓመትም ቢሆን ከጎናችሁ ሆነን ህይወትን ለመጠበቅ፣ ቁስልን ለመጠገን እና ጤናችሁን ለመንከባከብ በታላቅ ሰብአዊነትና ፍቅር የተጋን ነን።
አዲሱ ዓመት የጤና፣ የሰላም፣ የደስታ እና የፈውስ ዘመን ይሁንልን!
👉ጤናዎ የኛ ቀዳሚ ተግባር ነው! ጤና ለሁሉም !!

መልካም የ2019 አዲስ ዓመት!
ቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

Address

Chagni 04, Awi Zone
Chagne

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Chagni Primary Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category