Dire Dawa Qalad health center

Dire Dawa Qalad health center health care

በዛሬው እለት ሐምሌ 23/2018 የቀልአድ ጤና ጣቢያ ባለሞያዎች  የደም ልገሳ መርሃ-ግብር አካሄደዋል ።​በድሬደዋ አስተዳደር በክረምት ወራት የሚከናወኑ የተለያዩ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራ...
30/07/2026

በዛሬው እለት ሐምሌ 23/2018 የቀልአድ ጤና ጣቢያ ባለሞያዎች የደም ልገሳ መርሃ-ግብር አካሄደዋል ።
​በድሬደዋ አስተዳደር በክረምት ወራት የሚከናወኑ የተለያዩ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል።

28/07/2026
በቀልኣድ ጤ/ጣቢያ የዘንድሮ 2018 የክረምት በጎ ፍቃድ  ስራ ላይ ላይ ከተሰጡት አገልግሎቶች  # የአከባቢ  እና የግል ንፅህና አጠባበቅ  # የወባ በሽታ እና ደንጉ ትኩሳት ልየታ እና ህክ...
28/07/2026

በቀልኣድ ጤ/ጣቢያ የዘንድሮ 2018 የክረምት በጎ ፍቃድ ስራ ላይ ላይ ከተሰጡት አገልግሎቶች # የአከባቢ እና የግል ንፅህና አጠባበቅ
# የወባ በሽታ እና ደንጉ ትኩሳት ልየታ እና ህክምና
# ተላላፊ በሽታ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መከላከልና ግንዛቤ መስጠት
# የእናቶችና ህፃናት ጤና እና እንክብካቤ ላይ በስሩ
# የአፍላ ወጣቶች የጤና ትምህርት በባሉት ቀበሌዎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

መላው የቀልአድ ወረዳ ሰራተኞች ሰላም እንዴት ናችሁ🙏ለ5ኛው ሃገር አቀፍ የጤና መረጃ እና የዲጂታል ጤና ሳምንት የቀልአድ ጤና ጣቢያ እንደ ሀገር አቀፍ የዲጂታል ጤና መረጃ አፈፃጸም ከፍተኛ ...
12/05/2026

መላው የቀልአድ ወረዳ ሰራተኞች ሰላም እንዴት ናችሁ🙏
ለ5ኛው ሃገር አቀፍ የጤና መረጃ እና የዲጂታል ጤና ሳምንት የቀልአድ ጤና ጣቢያ እንደ ሀገር አቀፍ የዲጂታል ጤና መረጃ አፈፃጸም ከፍተኛ ውጤት ማስመዘገቡ ልዩ እውቅና በኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር አበረክተዋል።

ሁላችሁም እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ ዛሬ እኛ የቀልአድ ጤና ጣቢያ አመራርና ባለሞያ እንደ ድሬዳዋ አስተዳደር ይህንን ውጤት ማምጣታችን ኩራት እሰመናል በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ

የቀልአድ ጤና ጣቢያ ኃላፊ ወ/ሮ ደገን ኢሴ 👍👍👍👍👍👍👍

የድሬዳዋ አስተዳደር ቀልዓድ ጤና ጣቢያ ኃላፊ ሲ/ር ደገን ኢሴ  1447ኛው የኢድ አልፈጥር በአል አስመልክቶ ያስተላለፉት መልዕክት ውድ የቀልዓድ ጤና ጣቢያ ሠራተኞች፣ አጠቃላይ የወረዳው የሥ...
19/03/2026

የድሬዳዋ አስተዳደር ቀልዓድ ጤና ጣቢያ ኃላፊ ሲ/ር ደገን ኢሴ 1447ኛው የኢድ አልፈጥር በአል አስመልክቶ ያስተላለፉት መልዕክት

ውድ የቀልዓድ ጤና ጣቢያ ሠራተኞች፣ አጠቃላይ የወረዳው የሥራ ኃላፊዎች እና የወረዳው ማህበረሰብ እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አል-ፊጥር ረመዳን በዓል፥ በሰላም እና በጤና አደረሰን/አደረሳችሁ።

ያሳለፍነው የረመዳን ጾም ወር ፥ ዋነኛ ሥርዓቶች ከሆኑት የፀሎት እና የስግደት መንፈሳዊ ተግባራት በተጨማሪ ፥ በብዙ የበረከት ሥራዎች የታጀበ ወር ነበር።

የነገዋ የኢድ ዕለት፥ በረመዳን የጾም ወር የፈፀምናቸውን የአንድነት፥ የእዝነት፥ የመረዳዳት እና ሌሎች በርካታ መልካም እሴቶች አጠንክረን፥ በቀጣይ የዕለት ተዕለት ኑሯችን ውስጥ ለማስቀጠል ለራሳችን ቃል የምንገባበት ልዩ ቀን ናት።

'ረመዳን ሙባረክ' ተባብለን የጀመርነውን የጾም፥ ፀሎት እና ስግደት ወር በሰላም እንድንጨረስ ለረዳን ፈጣሪ ምስጋና እያቀረብኩ፥ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቼ ይህ በዓል የፍቅር፥ የመረዳዳት እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
ኢድ ሙባረክ

ቀ/ጤ/ጣቢያ  #  # ከHuman capital  Opration በተገኘ ድጋፍ የተሰጠ ስልጠና (Jaldessa worada) ።  # ከሁለቱ ወረዳ የተውጣጡ VHL እና የሃይማኖት አባቶችን በስርዓ...
04/02/2026

ቀ/ጤ/ጣቢያ #
# ከHuman capital Opration በተገኘ ድጋፍ የተሰጠ ስልጠና (Jaldessa worada) ። # ከሁለቱ ወረዳ የተውጣጡ VHL እና የሃይማኖት አባቶችን በስርዓተ -ምግብ እንዲሁም በእናቶች እና ህፃናት ጤና አጠባበቅ ላይ የአቅም ግንባታ ክህሎት ስልጠና ተሰጥቷል ። በስልጠናው ላይ የተገኙት የቀ/ወረዳ አስተዳደር ም/ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት # አቶ ፈርሀን ኡስማን ''ስልጠኞች ዛሬ እዚህ ያገኙትን ስልጠና ወደ ቀበሌያቸው ሲመለሱ በእስራቻው ላሉት አባወራዎች ግንዛቤ እንዲያስጨብጡ አሳስበዋል ። በተመሳሳይ የቀ/ጤ/ጣቢያ ሀላፊ የሆኑት ሲ/ር ደገን ኢሴ ስልጠናው በስርኣተ ምግብ ችግር ምክንያት የሚከሰቱትን ችግሮች ላይ ቀድመን ለመከላከል ያለመ እንደ መሆኑ ሰልጣኞች ከቤተሰቦቻቸው ጀምሮ በስራቸው ለሚገኙ አባወራዎች ግንዛቤውን በመስጠት የበኩላቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል ። በመጨረሻም እንደ አስተዳደራችን የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ወቅት ስለሆነ አሰልጣኞች ወደ ቄያቸው ሲመለሱ መልእክቱን እንዲያስተላልፉ ጥሪ አቅርቧል ። ቀልአድ ጤ/ጣቢያ ጥር 27/2018

1/04/2018 at Qalad HC polio orientation has been cascaded for all HEW and campaign participants
10/12/2025

1/04/2018 at Qalad HC polio orientation has been cascaded for all HEW and campaign participants

30/03/2018 Dual hand washing and HIV/AIDS day celebration at Qelad Primary and Secondary school
10/12/2025

30/03/2018 Dual hand washing and HIV/AIDS day celebration at Qelad Primary and Secondary school

በአስተዳደሩ የማልበርግ ቫይረስ በሽታን ለመከላከል የሚተላለፉ የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክቶችን ህብረተሰቡ ተግባራዊ እንዲያደርግ የድሬደዋ ሀይማኖት ተቋማት ገባኤ ጥሪ አቅርበዋል።የአስተዳደሩ ጤና ...
01/12/2025

በአስተዳደሩ የማልበርግ ቫይረስ በሽታን ለመከላከል የሚተላለፉ የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክቶችን ህብረተሰቡ ተግባራዊ እንዲያደርግ የድሬደዋ ሀይማኖት ተቋማት ገባኤ ጥሪ አቅርበዋል።

የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ የማልበርግ በሽታ ምንነትና የመከላከያ መንገዶች ዙሪያ ለድሬደዋ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሥራ አስፈፃሚ የቦርድ አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ እና በአስተዳደር ደረጃ የተሠሩ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች በዝርዝር ቀርበዋል።

በቅርቡ በሀገራችን የደቡብ ክልል የተከሰተው የማርበርግ ቫይረስ ዙሪያ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ለድሬደዋ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሥራ አስፈፃሚ የቦርድ አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥቷል።

በመድረኩ የሀይማኖት አባቶችም መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በአስተዳደሩ የማልበርግ በሽታን ለመከላከል እየተሠሩ የሚገኙ የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክቶችን የአስተዳደሩ ነዋሪዎች ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤው የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ በቅድመ ጥንቃቄ የሚተላለፉ መልዕክቶችን ሁሉም በየቤተ እምነቱ መልዕክት በማስተላለፍ ምእመኑ ጤናውን እንዲጠብቅ የአባትነት ሚናቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።

በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፋት የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዩሱፍ ሰኢድ እንዳሉት በአስተዳደሩ የማልበርግ በሽታን ለመከላከል የቅድመ ጥንቃቄ ሥራዎች በስፋት እየተሠሩ መሆናቸውን ጠቁመው ህብረተሰቡ ማንኛውም የህመም ስሜት ሲሰማው በአቅራቢያው ወደሚገኝ ጤና ተቋም መሄድ እንደሚገባ ገልፀዋል።

በአስተዳደሩ ጤና ቢሮ የሚተላለፉ የመከላከያ የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክቶችን የአስተዳደሩ ነዋሪዎች ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ አቶ ዩሱፍ አፅንኦት ሰጥተዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን
22/03/2018

Dire Dawa Religious institutions have called for the community to prevent the Marburg virus and take care of the adminis...
01/12/2025

Dire Dawa Religious institutions have called for the community to prevent the Marburg virus and take care of the administration.

Dire Dawa Administration Health Bureau has given a wide information on the identity of the board of Dire Dawa and the prevention measures taken in the administration.

Dire Dawa Administration Health Office has held an awareness meeting regarding the recent invasion of Marburg virus in the southern part of our country.

Religious leaders have also called on the program, residents of the administration are taking to implement the precautionary measures the administration is taking to prevent Marburg disease.

The council of religious institutions said that in all churches that will be held in the community to keep their health, by sending message to the religious leaders, taking precaution to protect the health of the community.

The deputy of health office of Dire Dawa administration Mr. Yusuf Said said that in the administration there are prevention measures taken to prevent Marburg disease and if the community is feeling sick they should go to the nearest health institution. The residents of the administration should follow the preventive measures that the Bureau of Health has taken. I'm so excited about this! A message to pass on.

Address

Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Dawa Qalad health center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share