Gondar Ayera General Hospital

Gondar Ayera General Hospital Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gondar Ayera General Hospital, Hospital, Gindar, Gondar.

የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል በጎንደር ከተማ የሚገኝ ሆስፒታል ሲሆን ለህብረተሰቡ ጥራት ያለው፣ ተደራሽ እና ቀልጣፋ የጤና አገልግሎት ለመስጠት ይሰራል። ሆስፒታሉ በብቁ የጤና ባለሙያዎች አማካኝነት የሕክምና፣ የላቦራቶሪ፣ የፋርማሲ፣ የእናቶችና ህጻናት ጤና እና ሌሎች የህክምና አገልግሎቶችን ይሰጣል።

30/07/2026
30/07/2026
የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ሰራተኞች የEHSIG ስልጠና መውሰድ ጀመሩየጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ሰራተኞች የEHSIG ስልጠና በጎንደር ከተማ መውሰድ ጀምረዋል።የEHSIG ተግባር ቀ...
29/07/2026

የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ሰራተኞች የEHSIG ስልጠና መውሰድ ጀመሩ

የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ሰራተኞች የEHSIG ስልጠና በጎንደር ከተማ መውሰድ ጀምረዋል።

የEHSIG ተግባር ቀደም ሲል የተጀመረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ባደረገው ማስተባበር የሆስፒታሉ ሰራተኞች ስልጠናውን እየወሰዱ ይገኛሉ።

ስልጠናው በጤናው ዘርፍ እየተተገበረ ያለውን የሪፎርም ሥራ ለማጠናከር፣ የጤና መረጃ ጥራትንና አጠቃቀምን ለማሻሻል፣ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥን ለማጠናከር እንዲሁም ለማህበረሰቡ የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል — የጤና ሪፎርሙን በብቃት በመተግበር ጥራት ያለውን አገልግሎት ለማህበረሰቡ ለማድረስ በቀጣይነት እየሰራ ይገኛል።

የአይን ሞራ ግርዶሽ (Cataract) የቀዶ ሕክምና አገልግሎት በCure Blindness Project ድጋፍ በጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል እየተሰጠ ነው።በCure Blindness Projec...
29/07/2026

የአይን ሞራ ግርዶሽ (Cataract) የቀዶ ሕክምና አገልግሎት በCure Blindness Project ድጋፍ በጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል እየተሰጠ ነው።

በCure Blindness Project ድጋፍ የአይን ሞራ ግርዶሽ (Cataract) የቀዶ ሕክምና አገልግሎት በጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል በስኬት እየተሰጠ ይገኛል።

በዚህ መርሃ ግብር ከጎንደርና ከአካባቢው እንዲሁም ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ የአገልግሎት ፈላጊዎች በሆስፒታሉ በመገኘት የአይን ሞራ ግርዶሽ የቀዶ ሕክምና እና ተያያዥ የአይን ሕክምና አገልግሎቶችን እያገኙ ይገኛሉ።

ይህ ፕሮግራም በአይን ሞራ ግርዶሽ ምክንያት የተፈጠረ የዕይታ እክልን በመቀነስ የተጠቃሚዎችን የኑሮ ጥራት ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው።

ጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል
ጤናዎ ቀዳሚ ትኩረታችን ነው!

🩸 የአይራ ጠቅላላ ሆስፒታል የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሄደየአይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ሠራተኞች ዛሬ ከጧት 2፡30 ጀምሮ በተቋሙ የተዘጋጀውን የደም ልገሳ መርሃ ግብር በከፍተኛ ተሳትፎ አካሂደ...
20/07/2026

🩸 የአይራ ጠቅላላ ሆስፒታል የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሄደ

የአይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ሠራተኞች ዛሬ ከጧት 2፡30 ጀምሮ በተቋሙ የተዘጋጀውን የደም ልገሳ መርሃ ግብር በከፍተኛ ተሳትፎ አካሂደዋል።

መርሃ ግብሩ በሕክምና ተቋማት የደም እጥረትን ለመቀነስና ደም የሚያስፈልጋቸውን ታካሚዎች ሕይወት ለማዳን የሚያግዝ ሲሆን፣ የሆስፒታሉ ሠራተኞችም በፈቃደኝነት በመሳተፍ ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን በተግባር አሳይተዋል።

የአይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ሕይወትን ለማዳን የሚደረጉ በጎ ተግባራትን በቀጣይነት በመደገፍ ለማኅበረሰቡ ጤና እና ደህንነት ያለውን አስተዋፅኦ ያጠናክራል።

"ደም መለገስ ሕይወትን ማዳን ነው!"

🌱 የአይራ ጠቅላላ ሆስፒታል የ2018 ዓ.ም. የክረምት ችግኝ ተከላ ዝግጅትየአይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ሰራተኞች ለተከታታይ ሶስት ቀናት የችግኝ ጉድጓድ ቁፋሮ ሥራን በትጋትና በትብብር እያከናወኑ...
17/07/2026

🌱 የአይራ ጠቅላላ ሆስፒታል የ2018 ዓ.ም. የክረምት ችግኝ ተከላ ዝግጅት
የአይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ሰራተኞች ለተከታታይ ሶስት ቀናት የችግኝ ጉድጓድ ቁፋሮ ሥራን በትጋትና በትብብር እያከናወኑ ይገኛሉ።
በዚህ መርሃ ግብር በንቃት እየተሳተፋችሁ ላላችሁ ሁሉም ሰራተኞቻችን ከልብ እናመሰግናለን።
"ዛሬ የምንተክለው ችግኝ የነገን አረንጓዴ ተስፋ ይገነባል!" 🌿
#

📌 የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል የነርሲንግና ሚድዋይፈሪ (Nursing and Midwifery) ዲፓርትመንት ዓመታዊ ሪፖርት ተገምግሟል!የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል የነርሲንግና ሚድዋይ...
16/07/2026

📌 የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል የነርሲንግና ሚድዋይፈሪ (Nursing and Midwifery) ዲፓርትመንት ዓመታዊ ሪፖርት ተገምግሟል!

የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል የነርሲንግና ሚድዋይፈሪ (Nursing and Midwifery) ዲፓርትመንት የ2018 ዓ.ም. ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በሆስፒታሉ አመራሮችና ባለሙያዎች ፊት ቀርቦ ተገምግሟል።

ሪፖርቱን ያቀረቡት የሆስፒታሉ ሜትረን አቶ ካሳውማር አቡየ ሲሆኑ፣ በ2018 ዓ.ም. የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በዝርዝር አቅርበዋል።

በግምገማው ወቅት የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሙኤል፣ የተገኙ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል እና ድክመቶችን በማረም በተለይም የጥራት (Quality) ሥራዎችን በትኩረት ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል።

በማጠቃለያም የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ገ/ዮሀንስ የሺነህ፣ የተጀመሩ ጥሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ የእናቶችና ሕፃናት አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራት እንዲሻሻል፣ እንዲሁም የነበሩ ተግዳሮቶች በቀጣዩ የበጀት ዓመት በቅድሚያ እንዲፈቱ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል
"ጥራት ያለው አገልግሎት ለህብረተሰባችን!" 💙

08/07/2026

🩸 የደም ልገሳ ጥሪ 🩸

📢 ለአይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ሰራተኞችና ተገልጋዮች በሙሉ

በነገው ዕለት ሐሙስ ሐምሌ 1/2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በአይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ የደም ልገሳ መርሃ ግብር ይካሄዳል።

🩸 አንድ ጊዜ ደም መለገስ እስከ ሦስት ሰዎች ሕይወት ለማዳን ሊረዳ ይችላል።

ስለዚህ ሁሉም ብቁ ሰራተኞችና ተገልጋዮች በመርሃ ግብሩ በንቃት እንዲሳተፉ የአይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ክብር ያለውን ጥሪ ያቀርባል።

❤️ "ደም ስጡ፤ ሕይወት ያድኑ!"

📍 ቦታ: አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ግቢ
🕣 ሰዓት: ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ
📅 ቀን: ሐሙስ ሐምሌ 2/2018 ዓ.ም.

አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል
"ጤና ለሁሉም፤ ሕይወት ለሁሉም!"

08/07/2026

በጤና ተቋማት የታየው የጽዱ ኢኒሼቲቭ ትግበራ በሌሎችም ተቋማት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፤


#አብክመጤናቢሮ

07/07/2026

Address

Gindar
Gondar
DD

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gondar Ayera General Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category