Migibaru Kebede Memorial Anbesame Primary Hospital

Migibaru Kebede Memorial Anbesame Primary Hospital Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Migibaru Kebede Memorial Anbesame Primary Hospital, Hospital, Anbesame, Gondar.

23/07/2026
23/07/2026

ደም መቼ እንደሚያስፈልገን አናውቀውም!
****************
የደም ልገሳ በበጎ ፍቃደኝነት ብቻ የሚደረግ የጤና ሂደት ነው። በአንድ ጊዜ የሚደረግ የደም ልገሳ የሦስት ሰዎችን ህይወት ያድናል። በመላው ዓለም ላይ በርካታ ዜጎች መዳን እየቻሉ በደም እጦት ምክንያት ህይወታቸውን ያጣሉ።

በኢትዮጵያም የኅብረተሰቡ ደም የመለገስ ባህል በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝና የአቅርቦት መጠኑ ዝቅተኛ መሆኑ ካለፉት ተሞክሮዎች ትምህርት መውሰድ ይቻላል፡፡ ሆኖም ግን በተደጋጋሚ በተሰጠው ግንዛቤ በክልል ደረጃ ሲታይ የህብረተሰቡ ደም የመለገስ ባህል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መጥቷል።

ነገር ግን ከሚፈለገው አንጻር ሲታይ ገና ብዙ የሚቀር በመሆኑ ጥቂት የማይባሉ ወገኖች አሁንም በደም እጦት ለሞት እየተዳረጉ ይገኛሉ፡፡

በወሊድ እና በድህረ ወሊድ ከፍተኛ ደም የሚፈሳቸው እናቶች፣ ህጻናትና የካንሰር ህመምተኞች የችግሩ ግንባር ቀደም ተጎጂዎች ናችው፡፡ የደም እጥረት እንዳያጋጥም በሁሉም ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የደም ማሰባሰብ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

በክረምት በጎ ፈቃድ የደም ልገሳ መርሐ ግብር በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች እየተካሄደ ሲሆን ማህበረሰቡ በተለይም ወጣቱ ይህን በጎ ዓላማ ያለውን ተግባር ከፊት ሆኖ ማስተባበር ይጠበቅበታል፡፡ ደም መቼ እንደሚያስፈልገን አናውቀውም፡፡ በመሆኑም ዜጎች በሁሉም ዞኖች በተዘጋጁ ጣቢያዎች በመገኘት በበጎ ፈቃደኝነት ደም እንዲለግሱ ጥሪ ማስተላለፍ ይገባል።

ደም መለገስ ምንም አይነት የጎንዮሽ የጤና ጉዳት የለውም ብቻ ሳይሆን የህሊና እርካታ ይሰጣል፡፡ ከምንም በላይ በወሊድም ሆነ በሌላ ምክንያት ደም የሚፈልጉ ሰዎችን ህይወት ለማዳን እድሉን ማግኘት ደግሞ እጅጉን ያስደስታል፡፡

ደም መለገስ ሰዎችን ከህመማቸው ከመፈወስና ከሞት ከማዳን ባሻገር ለደም ለጋሾችም ጤና ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ይህንኑ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል።


#አብክመጤናቢሮ

የምግባሩ ከበደ መታሰቢያ አንበሳሜ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከደራ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት እና ከአንበሳሜ ጤና ጣቢያ ጋር በመተባበር ከ 09/11/2017 ዓ.ም ጀምሮ እየሰጠን ያለነው የክረምት ...
23/07/2026

የምግባሩ ከበደ መታሰቢያ አንበሳሜ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከደራ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት እና ከአንበሳሜ ጤና ጣቢያ ጋር በመተባበር ከ 09/11/2017 ዓ.ም ጀምሮ እየሰጠን ያለነው የክረምት የበጎ ፈቃድ የጤና ምርመራና ህክምና አገልግሎት አሁንም ያለማቋረጥ የበጎ ፈቃድ የጤና አገልግሎት ስራችን በጊዜያዊ ማዕከል ደረጃ የቀጠለ ሲሆን እስካሁን ከታዩት ተገልጋዮች ውስጥ
1. HTN screening =345 የደም ግፊታቸው የጨመረ=29
2. Dm screening 229 በደም ውስጥ የስኳር መጠናቸው የጨመረ =3
3. PITC done =96
Positive =0
4. Tt case detected =11
5. Cataract case detected=13
6. Glacoma case detected =4
7. Tb Suspected=13 link to Gene X-pert =13
8. Cervical ca =2
9. Breast ca = 1
እነዚህንና ሌሎች ተጨማሪ ተግባራትን እያከናወንን በማቀናጀት ስራችን አጠናክረን የምንቀጥል ሲሆን ለዚህ የተቀደሰ ተግባር መሳካት የአንበሳውን ድርሻ እየተወጡ ላሉት የአንበሳሜ ጤና ጣቢያ ባለሙያዎች፣ የደራ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት ኦፊሰሮች እና የሆስፒታላችን ተመዳቢ ሀኪሞች በበጎ ፈቃድ ተጠቃሚው ማህበረሰብ ስም ምስጋናችንን እናቀርባለን።
ሀምሌ 16-2018
አንበሳሜ

ሆስፒታላችን ምግባሩ ከበደ መታሰቢያ አንበሳሜ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሆስፒታሉ የቦርድ አመራሮች፣ የ ሲኒየር ማናጅመንት አባላት፣ ኬዝ ማናጀሮች፣ የ PMT(Performance Monitor...
09/07/2026

ሆስፒታላችን ምግባሩ ከበደ መታሰቢያ አንበሳሜ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሆስፒታሉ የቦርድ አመራሮች፣ የ ሲኒየር ማናጅመንት አባላት፣ ኬዝ ማናጀሮች፣ የ PMT(Performance Monitoring team ) አባላት፣ የክፍል አስተባባሪዎችና የሆስፒታሉ የድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች በተገኙበት የ 2018 በጀት አመት አመታዊ የስራ አፈፃፀም መድረክ አካሄደ።

መድረኩን ያስጀመሩት እና የመሩት የደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና የሆስፒታሉ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አለባቸው ዳምጤ በመክፈቻ ንግግራቸው ጤና እጅግ ውስብስብ የሆነ፣ ህይወታችን በሙሉነት የምትመሰረትበት፣ ሰው ከመሆናችን ጋር የማይለያይ ክስተት መሆኑን ጠቅሰው ይህንን ውድ የሆነውን የሰው ልጅ ጤና መጠበቅ ደግሞ የዚህ ባለሙያ ሀላፊነትም እድልም ጭምር በመሆኑ ሁልጊዜ ጥንቁቅ መሆን ይገባል ብለዋለ።
አቶ አለባቸው በንግግራቸው አክለውም አስቸጋሪው እና የተወሳሰበው ጊዜ ሳይበግራችሁ ሰብአዊነትን ተላብሳችሁ ህይወት ማዳንን እቅድ አድርጋችሁ በርካታ የወረዳውን ማህበረሰብ የጤና ፍላጎት በማየት ስላገለገላችሁት ምስጋና ይገባችኋል ብለዋል።
የሆስፒታሉ የቦርድ ሰብሳቢው ሀሳባቸውን ሲቀጥሉ ሆስፒታሉ በጥንካሬ የፈፀማቸውን በማስቀጠል በድክመት የተነሱት አፈፃፀሞች በተለይም የታካሚዎች የአገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታ ምንጮች እንደ ግብአት አለመሟላት፣ ሪፈራል ቅብብሎሽ ፣ የመሰረተ ልማት ችግሮች እና ሌሎችም በቅደም ተከተል እንደ አሳሳቢነታቸው ተለይተው እንዲፈቱ በቅርበት እንደሚሰሩ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
በመድረኩ የታደሙት የሆስፒታሉ ሰራተኞች ሀሳባቸውን ሲያስረዱ ሆስፒታላችን በጥሩ አፈፃፀም ወደ ፊት እንዲወጣ የቻልነውን ሁሉ እናደርጋለን ነገር ግን ደግሞ ቦርዱ በቅርበት ማገዝ ያለበትን ጉዳዮች ለይቶ ማገዝ እንዳለበት በማንሳት እኛ ስራችን ጋር ነን ከየትኛውም የበላይ አካላት ጋር እየተገናኘን አይደለም እናንተ ከበላይ አካላት ጋር በምታገኙት ድግግሞሽ ሁሉ ጥያቄያችን አስረዱልንና የምናነሳቸው መሬት ላይ ያሉ ጥያቄዎቻችን እንዲፈቱ እንደ ቦርድ ይዛችሁ ስሩልን ብለዋል።

ሌላኛው የሆስፒታሉ የቦርድ አመራርና የደራ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ፀጋዬ አስፋው ሆስፒታሉ ባለፈው ከነበረበት ክፍተት ወጥቶ በዚህ ልክ በራሱ አቅም ተግባራት መስመር እንዲይዙ በማድረግ የተሄደበትን ሂደት አድንቀው ከአመት አመት የሆስፒታሉ ችግር ሆነው እየቀጠሉ ያሉ የተጠቀሱ አንዳንድ ተግዳሮቶች በሆስፒታሉ አቅም መፈታት ያለባቸው በመሆኑ ውጤታማ ጥናት በማድረግ ወደ ተግባር በመግባት የሚቀረፉበትን ሁኔታ ለማየት እንደ ቦርድ ዝግጁ ነን በቀጣይ መስተካከል ያለባቸውን ከአሁኑ የመለየት ስራ ይሰራ የሚል አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ሌላኛው የቦርዱ አመራር ፀሀፊ እና የደራ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጋሻው ከበደ በበኩላቸው የታመመችና ስቃይ ላይ ያለች ነብስ ከፈጣሪ በታች በጤና ባለሙያ እጅ ሆና ወደ መደበኛ ህይወት ትመለሳለች ካሉ በኋላ በአሁኑ ወቅት ብዙ ፈተናወች እንዳሉ ይታወቃል በዚህ ጊዜ እንደ ጤናው ዘርፍ ሰራተኛ ከህዝብ ጎን መቆማችን በየትኛውም ሁኔታ ብርቱና የማይናወጥ አቋም ያለው የጤና ባለሙያ መፈጠሩ እንደሚያስደስተው በመግለፅ ከጥቅማጥቅም አንፃር የሚነሱ ጥያቄወችን ለማስፈጸም ደረጃ በደረጃ የቻልነውን ሁሉ እናደርጋለን ካሉ በኋላ የሆስፒታሉ Regulatory Inspection የሚሰራው በ 4 ''P'' መለኪያዎች ሲሆን እነርሱም:-
1. Premises
2. Profession
3. Product and
4. Practice ናቸው ስለዚህ እነዚህ ላይ ከሰራን ሆስፒታሉ በቀጣይ ደረጃውን በማሻሻል ወደ ጠቅላላ ሆስፒታል እንዲያድግ ቴክኖሎጅን በመጠቀም ጭምር መስራት ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ አምባቸው ደጀን እንደተናገሩት ሆስፒታላችን እንደ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሲመዘን ከጅምሩ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆኑት መሰረተ-ልማቶች ሳይሟሉ በዚህ ሁኔታ መገኘቱ ቁርጠኛ አመራር፣ ቁርጠኛና ተቆርቋሪ ሰራተኛ እንዳለ ለማየት ችለናል ለዚህም የሆስፒታላችን ጥሩ አገልጋይ የሆኑ ሰራተኞች ክብር ይገባቸዋል ብለዋል።

ስራ አስኪያጁ ሀሳባቸውን ሲቀጥሉ ሆስፒታሉ የራሱ የሆነ የሚተዳደርበት የጤና ሚኒስቴር እና የአብክመ ጤና ቢሮ አሰራር አለ እሱን በመከተል ወደ ተግባር ገብተናል ሙሉ ትኩረታችን የሆስፒታል ደረጃዎች አተገባበር መመሪያ ላይ ነው ከዚህ ጀርባ ሆነው ሊጎትቱን የሚሞክሩ የውጭ አካላት፣ የሆስፒታላችን ሰራተኞች ጭምር አሉ እነሱን በጎ ተፅዕኖ በማድረግ ወደ ለውጥ እንዲገቡ የተጠያቂነት መስመርን እንዘረጋለን ብለዋል።
አንድ ተቋም ከፍተኛ አፈጻጸም እንዲኖረው በውስጡ ከፍተኛ ተነሳሽነት ያላቸው ብዙ ሰራተኞች ያስፈልጉታል ያሉት ስራ አስኪያጁ ነገር ግን አሁን ላይ ይህ እየሆነ አይደለም በቀጣይ ሁላችንም ከላይ እስከታች የበኩላችን በመወጣት ችግር ፈች መሆን አለብን ብለዋል።
በማስቀጠልም የተነሱትን ሁሉ ችግሮች ማለትም :- የሆስፒታል መሰረተ ልማት ግንባታ ችግሮች ለምሳሌ የውሀ የውስጥ ለውስጥ ዝርጋታ ችግር፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር፣ የመድሀኒት አለመኖር ምጣኔ ከፍተኛ መሆን ችግር፣ የቡድን አስተሳሰብ ችግር ፣ የፋይናንስ አስተቃቀድ አሰባሰብና አጠቃቀም ችግር፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመውሰድ ደረጃ በደረጃ በመለየት የቅድሚያ ቅድሚያ በመስጠት የጤና ቴክኖሎጅዎችን በማስተሳሰር እንሰራለን ቦርዱም በቅርብ ሆኖ ሊያግዘን ይገባል ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ሆስፒታሉ ላይ ችግር የሆኑት
1. ከፍተኛ የሰው ሀይል እጥረት ነርስ ፣ላብራቶሪ ፣ ፋርማሲ ፣ ጠቅላላ ሀኪም እና አንዳንድ የድጋፍ ሰጭ መደቦች ክፍት መሆንና ለስራ መቸገር
2. የመሰረተ ልማት ችግር የክፍሎች ለስራ አለመመቸትና መጣበብ፣ የውሀ፣ የኢንተርኔት፣ የ ቢሮ ፈርኒቸሮች እጥረት
3. የህክምና መሳሪያዎች እጥረት ለምሳሌ የ CBC ማሽን 1 ብቻ በመሆኗ መቆራረጡ፣ Chemistry
( ጭራሽ ስራ ላይ አለመሆን)
1. የባለሙያዎች የ 6 ወር ትርፍ ሰዓት ክፍያ አለመከፈል
2. የ EPSS መድሀኒት የማቅረብ ምጣኔ ዝቅተኛ መሆን
3. የተሽከርካሪ እጥረት ችግሮች እንዳሉና ለስራ እንቅፋት መሆናቸውን በአፅንኦት አስረድተዋል።
ከዚህ በመቀጠል የዚህ በጀት አመት እንዲህ ሆኖ ቢያልፍም በተለያዩ ጊዜያት በተለይም የአብክመ ጤና ቢሮ ፣ የፈለገህይወት ስፔ/ሆስፒታል፣ የደራ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት ላደረጉልን ያልተገደበ እገዛ ምስጋና ይገባል በማለት በቀጣይ ሆስፒታሉ እንዲሻሻል በተለይም በጤና ቢሮው በልዩነት መታየት እንዳለበት መልእክት አስተላልፈዋል።
የምግባሩ ከበደ መታሰቢያ አንበሳሜ የመጀ/ደ/ሆስፒታል
ሀምሌ 02/ 2018 አንበሳሜ

ሆስፒታላችን ያወጣቸው ከዚህ በታች የተለጠፉ 2 የስራ መደቦች ላይ መመዝገብ እና መወዳደር ትችላላችሁ!
05/07/2026

ሆስፒታላችን ያወጣቸው ከዚህ በታች የተለጠፉ 2 የስራ መደቦች ላይ መመዝገብ እና መወዳደር ትችላላችሁ!

መልካም ዜና ለ ደራና አካበቢው ማህበረሰብ በሙሉ፤የምግባሩ ከበደ መታሰቢያ አንበሳሜ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከአብክመ ጤና ቢሮ የተበረከተለትን የዲጂታል ኤክስሬይ ማሽን እንሆ ዛሬ ከአዲስአ...
19/06/2026

መልካም ዜና ለ ደራና አካበቢው ማህበረሰብ በሙሉ፤
የምግባሩ ከበደ መታሰቢያ አንበሳሜ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከአብክመ ጤና ቢሮ የተበረከተለትን የዲጂታል ኤክስሬይ ማሽን እንሆ ዛሬ ከአዲስአበባ በመጡ የባዮሜዳካል ባለሙያዎች ተገጥሞ ለሚመለከታቸው የሆስፒታሉ ባለሙያወች መሰረታዊ እውቅና በመፍጠር በይፋ ስራ አስጀምሯል። በዚህም ከዚህ በኋላ በየቀኑ ይህንን አገልግሎት ለማግኘት ወደ ባህርዳር ሪፈር የሚባሉ የሆስፒታሉ ታካሚዎች እዚሁ ሆስፒታላችን ላይ አገልግሎቱን በማግኘት ይደርስባቸው የነበረው ከፍተኛ እንግልት ታሪክ ይሆናል።
ለዚህ ተግባር መሳካት ሙሉ በሙሉ ሀላፊነት ወስዶ ለሆስፒታላችንና አካባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት ድጋፍ ያደረገው የአብክመ ጤና ቢሮ ከአጋር ድርጅቶች ጋር፣ የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅርቦት አገልግሎት በሆስፒታሉ ተጠቃሚ ማህበረሰብ ስም ምስጋናችን ይድረሳችሁ። ወደፊትም ሆስፒታላችን ላይ ያሉ የመሰረተ ልማት ችግሮች ላይ እንደዚህ ያለ ትብብር በመውሰድ እንደምትፈቱልን እንተማመናለን!

በድጋሜ እናመሰግናለን!
''ፍትሀዊና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለሁሉም''
ሰኔ 12/2018 ዓ.ም

19/06/2026

በኦፕራሲዮን እስከ ስንት ጊዜ መውለድ ይቻላል???

በኦፕራሲዮን መውለድ ወይም cesarean delivery ከምንጊዜውም በላይ ምቹ እና safe እየሆነ በመምጣቱ በኦፕራሲዮን የሚወልዱ እናቶች ቁጥር እየጨመረ መቷል።

እስከ ስንት ጊዜ በኦፕራሲዮን መውለድ ይቻላል? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስም የተቀመጠ ቁርጥ ያለ መልስ የለም። ''not limit number''

የአለም ጤና ድርጅት /world health organization WHO or American collage of obstetrician and gynecologists ACOG ወይም ሌላ ማንኛውም professional organization ያሰቀመጠው ቁጥር የለም።

19/06/2026

እርግዝና እና የክንታሮት በሽታ

ክንታሮት በእርግዝና ጊዜ በጣም ከተለመዱ በሽታወች አንዱ ሲሆና ከሰባተኛው ወር ጀመሮ እስከ 40% በሚሆኑ እናቶች ላይ ሊከሰት ይችላል።

ምልቶች
በፊንጢጣ አካባቢ የማቃጠል ስሜት; የማሳከክ ስሜት
በፊንጢጣ ደም መድማት
ፊንጢጣ አካባቢ እብጠት አና ህመም ሲሆኑ በአብዘኛው እንትየዋንም ይሁን ጽንሰን እማይጎዳ በሽታ ነው

ህክምናው

በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት ኪንታሮት ከወሊድ በኋላ ባሉት ጥቂት ሳምንታት የሚጠፋ ቢሆንም እሰኪጠፋ ድረስ

1-ለብ ያለ ውሀ በሰፈ አድርገን ከ20-30 ደቂቃ መዘፍዘፍ

2-እትክልት እና ፍራፍሬ እንዲሁም ያልተፈተጉ ጥራጥሬወችን መመገብ
3-በቂ ውሃ መጠጣት
4-አንደ ፓይሎኬን / pyloocaine አይነት የሚቀቡ ክሬሞችን መጠቀም።

መከላከያ መንገዶች

1_ለረጅም ጊዜ ሽንት ቤት አለመቀመጥ
2_በቂ ፈሳሽ መጠጣት
3_ለረጅም ጊዜ አለመቀመጥ ስንቀመጥም ክብ እና መሀላቸው ክፍት የሆኑ ትራሶች ላይ መቀመጥ/የዶናት ቅርጽ ያላቸውን ትራሶች
4 አትክልት ፍራፍሬ እና ያልተፈተጉ ጥራጥሬወችን ማዘውተር

Address

Anbesame
Gondar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Migibaru Kebede Memorial Anbesame Primary Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category