Gondar Ayira General Hospital ጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል

  • Home
  • Ethiopia
  • Gondar
  • Gondar Ayira General Hospital ጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል

Gondar Ayira General Hospital ጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል አላማችን ህሙማን መርዳት ነዉ!!!

የጎንደር  አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል እና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በሁሉም አይነት  ህክምና ዙሪያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ*የጎንደር  አይራ ጠቅላላ ሆስፒታ...
20/02/2026

የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል እና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በሁሉም አይነት ህክምና ዙሪያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ
*
የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል እና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በጠቅላላ ቀዶ ጥገና ፣በአጥንት ስብራት ህክምና ፣በማህፀንና ፅንስ ፣ በህፃናት እና በሌሎች የህክምና ዘርፎች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የጋራ ስምምነት ዛሬ የካቲት 13/2018 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንንት ጽ/ቤት ተፈራርመዋል።

በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ገ/ዮሀንስ የሺነህ ፣ የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሙኤል አጥቃቸዉ፣ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ጤና ምሪያ ሀላፊና የሆስፒታላችን የቦርድ አመራር አቶ ሰዒድ የሻዉ እና የሆስፒታል የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን፣የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ጌታው ብርሀን፣ የሆስፒታሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው በስምምነት ሰነዱ ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

ስምምነቱ በተለይ የቀዶ ጥገና (Back Log) ቁጥሩ ከፍተኛ ሲሆን ቀጠሮ ተሰጥቷቸው ለረጅም ጊዜ በወረፋ ላይ የሚገኙ ታካሚዎችን ምልልስ በመቀነስ፣ ፈጣን የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻል ሲሆን፣ በተለይ ለበርካታ ወራት የቀዶ ጥገና ህክምናዎችን የሚጠብቁ ታካሚዎችን ቁጥር ሆስፒታላችንን በመጠቀም በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ ታካሚወች ወረፋ ከመጠበቅ ይልቅ ቶሎ ህክምና እንዲያገኙ ያለመ ስለመሆኑ በመርሀ- ግብሩ ተገልጿል። በተጨማሪም ታካሚዎች በህመማቸው ላይ ተጨማሪ እንግልትና የኢኮኖሚ ጫና ሳይደርስባቸው ጥራት ያለው ህክምና እንዲያገኙ ለማድረግ የሚያሰችል መሆኑ በስምምነቱ ተጠቅሷል።

ሁለቱ ሆስፒታሎች ከዚህ ቀደምም በሰው ኃይል እና በህክምና ቁሳቁስ ግብዓቶች ላይ የመዋዋስና የመረዳዳት ስራዎችን ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን፣ የዛሬው ስምምነት ይህንን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግርና ህጋዊ ማዕቀፍ የያዘ እንደሆነ ከቀረበው ገለፃ ለመረዳት ተችሏል።

የታካሚዎችን እርካታ ይበልጥ ለማሳደግ ከሁለቱ ሆስፒታሎች ስምምነት ጎን ለጎን ጤና ጣቢያዎችን የመደገፍ፣የማብቃትና የማጠናከር ስራዎች እንደሚሰሩ ተጠቁሟል። ይህም ህብረተሰቡ በአቅራቢያው በሚገኙ የጤና ተቋማት ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ተብሏል።

የሆስፒታሉ ህዝብ ግንኙነት
የካቲት 13/2018 ዓ. ም

18/01/2026

የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ገ/ዮሐንስ የሽነህ ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ጎንደር ፤ ጥር 10/2018 ዓ/ም የጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ገ/ዮሐንስ የከተራ እና የጥምቀት በዓላትን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አቶ ገ/ዮሐንስ በመልዕክታቸው ውድ የተቋማችን የክርስትና እምነት ተከታዮች፤ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል ።

የጥምቀት በዓል በታላቅ ድምቀትና መንፈሳዊ ስነስርዓት ከሚከበሩ ታላላቅ በዓላት አንዱ ነው። ይህ በዓል የትህትና፣ የፍቅርና የወንድማማችነት ተምሳሌት ነው።

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መሄዱ ታላቅ ትህትናን የሚያስተምር ሲሆን፤ እኛም በሥራችንና በማህበራዊ ህይወታችን በአገልግሎታችን ለአብሮነት ዝቅ ብለን ማገልገል እንዳለብን ትልቅ ትምህርት የምንወስድበት ነው ሲሉ ተናገረዋል።

የተከበራችሁ የሆስፒታላችን ባልደረቦች ፤የጥምቀት በዓል ከሃይማኖታዊ ፋይዳው ባሻገር፣ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት ጠብቀን ያቆየነውና በዓለም አቀፉ የዩኔስኮ ቅርስነት የተመዘገበ ታላቅ ብሔራዊ ሀብታችን ነው ብለዋል።

ይህ በዓል በተለይም በከተማችን በሚከበርበት ወቅት የህዝባችንን አንድነት፣ እንግዳ ተቀባይነትና ውብ ባህላችንን ለዓለም የምናሳይበት አጋጣሚ ነው።

የጥምቀት በዓል የሰላም፣ የፍቅርና የምሕረት በዓል ነው። ይህ በዓል በየዓመቱ በሚከበርበት ወቅት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ወደ አደባባይ የሚወጣበትና በጋራ የሚቆምበት በመሆኑ፣ የሕዝባችንን ጤንነት መጠበቅ ቀዳሚ ተግባራችን ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

በዓሉ በሰላም ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ በተቋማችን ለሚመጡ ታካሚወቻችን የተለመደዉን የህክምና አገልግሎት ከመስጠት ጎን ለጎን ድንገተኛ የጤና አክል ቢገጥም ሁሉም ባለሙያ የተለመደዉን እርብርብ እና ቲም አስፕሪት በመጠቀም አገልግሎት እንድንሰጥ እና ከዚህም ጎን ለጎን ተቋሙን ለመጎብኘት የሚመጡ እንግዶቻችን ካሉ ሁሉም የተቋሙ ባልደረባ የተሰሩ ስራወችን የማስተዋወቅ ሀላፊነቱን እንዲወጣ አደራ ብለዋል፡፡

በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የብልጽግና እና የአንድነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

#መልካም በዓል!
"የሆስፒታሉ ህዝብ ግንኙነት"

ቀን 16/04/2018ዓ/ም በዛሬዉ እለት በሆስፒታላችን በክልል ደረጃ ሁሉንም አቀፍ ድጋፍ  በተደረገዉ መሠረት በፕላን ኦፊሰር  Action plan ወጥቶሰፋ ያለ  ዉይይት ተደርጎባቸዋል።ክፍቶ...
25/12/2025

ቀን 16/04/2018ዓ/ም
በዛሬዉ እለት በሆስፒታላችን በክልል ደረጃ ሁሉንም አቀፍ ድጋፍ በተደረገዉ መሠረት በፕላን ኦፊሰር Action plan ወጥቶሰፋ ያለ ዉይይት ተደርጎባቸዋል።

ክፍቶችም ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል

በክፈተት የታዩ ( መስተካከል ያለባቸዉ)

1.ሆስፒታሉ ላይ የፀዳት ችግር መኖሩና 2.ለአገልግሎት እንቅፋት መሆኑ( ከበሩ ጀምሮ እስከ ወስጥ ድረስ የተጋነነ የጸዳት ችግር መኖሩ) ይህ ደግሞ ለታሚዎች ሌላ የጤና እክል ሊፈጥር እሚችል ስጋት መሆኑ
3.በሪፎርም ትግበራ ላይ ሁሉም ሰዉ እኩል ግንዛቤ ያለመኖሩ
4.የሆስፒታሉ እቅድ አስከታች ለሰራተኛዉ ያለመዉረዱና የስራ ክፍል አስተባባሪዎች አቅዱ በትክክል ለሰራተኛዉ ከማድረስ በኩል ዝቅተኛ አፈጻጸም መኖሩ(የግለሰብ እቅድ ለሁለም ሰራተኛ ያለማዉረድ ችግር)
5.ዲጅታላይዚሽን( ወረቀት አልባ) አገልግሎት ያለመጀመሩ
6.የታካሚ አልጋዎች አንሶላና ብርድልብስ አልባ መሆናቸዉ ይህ ደግሞ ለታከሚዎች ለተጨማሪ የበሽታ አይነት ለመጋለጥ ስጋት መሆኑ
7.የላዉንደሪና የምግብ ማብሰያ ማስኖች እርክክብ ያለመደረጉና ይህ ድግሞ አገልግሎቱን ሙሉ በመሉ ለመስጠት እንቅፋት መሆኑ
8.አዳዲስ የሆስፒታሉ እኒሸቲቦች(ሪፎርሞች)በእቅድ ያለመካተታቸዉ ዝቅተኛ አፈጻጸም ያላቸዉ መሆኑ
9.ዝቅተኛ የሆነ የላብላቶሪ ምርመራ አይነት መኖራቸዉ
10.ከፈተኛ የሆነ የባለሙያ እጥረት መከሰቱ ይህ ደግሞ የሆሰፒታሉን ስታዳርድ ለመፈጸም ትገዳሮት መሆኑ( የፈርማሲ ባለሙያ፤ጠቅላላ ሃኪም፤ነርስና ላብላቶሪ ባለሙያ)
11.የስራ ከፍል አስተባበሪዎች ለስራተኛዉ የግል እቅድ ያለመስጠታቸዉና ስራን እንደክፍል እየገመገሙ የድረጊት መራሃ ግብር ያለመዘጋጀታቸዉ
12.ካርድ ክፍል በር ያለመዘጋጀቱ ማለትም ክፍት መሆኑ ለካርዶች መጥፋት ስጋት መሆኑና ለህገመክ ካርዶች መጥፋት ስጋት መፈጠሩ
13.EHSIG, pt. seafty SBFR GGI ክሊኒካል ኦዲት ዝቅተኛ አፈጻጸም መኖራቸዉና ስራዉን የድርጊት መራሃግብር እያወጡ ያለመገምገም ችግር.
14.ወራሃዊ ሪፖረት ከተገመገመ በኃላ በተሰጠዉ ግብር መልስ መሰረት የስራ ክፍሎች የማስፈጸሚያ የድጊት መራሃ ግብር ያለማዉጣት ችግር
15.የተጠናከር DTC ያለመኖርና ጌዜዉን የጠበቀ ስብስባ ያለማድረግ ችግር
የመዳሀኒት ፤የስሪቨስ ክፍያ ኦዴቶችን ያለመስራት ችግር ተጠያቂነት አለማስፈን
ተቆራረጦ ያለመስራት ችግር
16.ሶሻል ኢንሹራንስ ስራተኛን ሙሉ በሙሉ ያለማስገባት ምዘገባዉን በተቀመጠዉ ግዜ ዉስጥ ያለመጨረስ
17.ሰራተኛዉን የማበረታታ ስራዓት ያለመዘርጋትና የስራ ክፈሎችን በስራቸዉ በየወሩ ያለማወዳደር ችግር
18. የሶሻል ስርቨስ አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ ስራ ያለመስጀመር
19.የህክምና እቃ እጥረት ለምሳሌ የኦርቶ ማተሪያል ጉድለት ይህ ደግሞ ያለዉን የሰዉ ሃይል ለመጠቀም ችግር መሆኑ
20.የዶፕለር አልትረሳዉንድ ያለመኖር ይህ ደግሞ የኢሚጅግ አገልግሎቱን ሙሉ እንዳይሆን ምክኒያት መሆኑ
21.የፈርኒቸር እጥረት( የታካሚ ወንበር፤ሽልፍ፤ድረቅ ወንበር)
ስለዚህ እያንዳንዱ የሆስፒታሉ ማህበረሰብ ፈፃሚ እንዲሆን የተቋሙ ስራ አስኪያጅ መልክታቸዉን አስተላልፈዋልበማስቀጠል ክፍተቶቻችን ላይ በመስራት ለዉጥ ለማምጣት ሁሉም ሰራተኛ እንዲተጋ አደራ በማለት የደገፉንን አካላት በተቋሙ ስም ምስጋና በማቅረብ ዉይይቱ ተቋጭቷል።

''የሆስፒታሉ ህዝብ ግንኙነት

Address

Gondar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gondar Ayira General Hospital ጎንደር አይራ ጠቅላላ ሆስፒታል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category