Adare General Hospital, Hawassa

Adare General Hospital, Hawassa One of general hospital in sidaama region and serving more than 2 million people

የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል የ2018 በጀት ዓመት 4ኛ ሩብ ዓመት የህዝብ ፎረም መድረክ አካሄደ።ሆስፒታሉ የ2018በጀት ዓመት የ4ኛ ሩብ ዓመት የህዝብ ውይይት መድረክ ያካሄደ ስሆን በፎረሙ ላ...
30/07/2026

የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል የ2018 በጀት ዓመት 4ኛ ሩብ ዓመት የህዝብ ፎረም መድረክ አካሄደ።

ሆስፒታሉ የ2018በጀት ዓመት የ4ኛ ሩብ ዓመት የህዝብ ውይይት መድረክ ያካሄደ ስሆን በፎረሙ ላይ ከሁሉም ክፍለ-ከተማ የተወጣጡ የህዝብ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

በመርሀግብሩ መሰረት ተሳታፊዎች ሆስፒታሉ እየሰጠ ያለውን አገልግሎት እና በቅርቡ ተመርቆ በከፊል አገልግሎት የጀመረውን የማስፋፊያ ግንባታ ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡ ይህንን ግዙፍ ፕሮጀክት በጥራት ገንብቶ ላጠናቀቀው የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምስጋና አቅርበዋል።

ከጉብኝቱ በኋላ የሆስፒታሉ ዓመታዊ አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል፤ በአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት፤ በመድሀኒት እና ግብዓት አቅርቦት እና አስተዳደራዊ ስራዎች ያሉበትን ደረጃ በተሳታፊዎች ተገምግሞ ጠንካራ አፈጻጸሞች ተጠናክረው እንቀጥሉ እና መሻሻል ያለባቸው ነጥቦች ላይ በትኩረት እንዲሰራ ሀሳብ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

ከዝህም ባሻገር ህንጻው በሙሉ አቅሙ አገልግሎት እንድሰጥ ቀሪ ጉዳዮች እና ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎች በመንግሰት በኩል እንዲሟሉ ሁሉም የበኩሉን ጥረት ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል።

ከተሳታፊዎች ለተነሱ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ዘነበ ቱርጨ ምላሽ ሰጥተው ቀሪ ስራዎችን በጋራ በመረባረብ ለህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸው ገልጸው ተሳታፊዎችን አመስግነው መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።

ሐምሌ 22/2018 አዳሬ አ/ሆስፒታል ሀዋሳ።

🩸❤️ ደም ይለግሱ — ሕይወትን ያድኑ! ❤️🩸በአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል አስተባባሪነት ከሰኔ 22--24/2018ዓም. ድረስ በፒያሳ ሲዳማ ባህል አዳራሽ ፊት ለፊት የደም ልገሳ እየተካሄደ ይገኛ...
30/06/2026

🩸❤️ ደም ይለግሱ — ሕይወትን ያድኑ! ❤️🩸

በአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል አስተባባሪነት ከሰኔ 22--24/2018ዓም. ድረስ በፒያሳ ሲዳማ ባህል አዳራሽ ፊት ለፊት የደም ልገሳ እየተካሄደ ይገኛል።

ደምዎን በፍቅር ሲለግሱ የአደጋ ተጎጂዎችን እና ደም የሚያስፈልጋቸውን እናቶች፤ ህጻናት፤አረጋዊያን እና የነገ ተሰፋ ወጣቶችን በህይወት የመኖር ተስፋን ያለመልማሉ።



🙏 እንስጥ… በፍቅር እንለግስ፣ ህይወትን በማዳን ጀግና እንሁን!

❤️🩸

ሆስፒታሉን ለረጅም አመታት ላገለገሉ የቀድሞ ራተኞች የእውቅና እና የሽኝት መርሀ-ግብር ተካሄደ።አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል በቀድሞ አጠራሩ የአዋሳ የወባ ህክምና ክሊኒክ እና ጤና አጠባበቅ ጣቢያ...
29/05/2026

ሆስፒታሉን ለረጅም አመታት ላገለገሉ የቀድሞ ራተኞች የእውቅና እና የሽኝት መርሀ-ግብር ተካሄደ።

አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል በቀድሞ አጠራሩ የአዋሳ የወባ ህክምና ክሊኒክ እና ጤና አጠባበቅ ጣቢያ እንዲሁም የመጀመሪያ ደረጃ እና አጠቃላይ ሆስፒታል በነበረበት ወቅት ተቋሙን እጅግ በላቀ የሙያ ስነ-ምግባር፤ በታማኝነት እና በታታሪነት ላገለገሉ 16 የቀድሞ ሰራተኞች የምስጋና እና የሽኝት መርሀ-ግብር ያደረገላቸው ስሆን በእለቱ የሲዳማ ብ/ክ/መ/ጤና ቢሮ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ ሙንጣሻ ብርሀኑ ለዛሬው ስኬት መሰረት ሆነው በላቀ የሙያ ስነምግባር ያገለገሉት ተቋም ዛሬ አድጎ ለፍሬ በበቃበት ማግስት ለእናንተ እውቅና ስንሰጥ ክብር ይሰማናል ብለው ረጅም እድሜና ጤናን ተመኝተውላቸዋል፡፡

እውቅና የተሰጣቸው የቀድሞ ሰራተኞች አቶ ሹምባ ዱጋሞ፤ ሲ/ር የሺሀረግ ሞገስ፤ ሲ/ር ንገስት ዋዳ፤ ሲ/ር አስቴር ጀልዴሳ፤ ወ/ሮ ዘሪቱ መኮንን፤ ሲ/ር አስናቀች በለጠ፤ አቶ አለማየሁ ንጉሴ፤ አቶ ሽፈራው ዩንካ፤ አቶ ፀጋዬ ንጋቱ፤ ወ/ሮ ክብረወርቅ በቀለ፤ ሲ/ር እልፍነሽ ናውሼ፤ ሲ/ር አስናቀች ደቦጭ፤ ሲ/ር አልማዝ ሽፈራው፤ ሲ/ር መሰለች ቱሌ፤ ሲ/ር ኩሪ ሻረው እና አቶ ታደለ ሐጎስ ናቸው፡፡

በመጨረሻም የሀዋሳ ከተማ ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ ይርዳቸው አናቶ እና ሆስፒታሉን በቅብብሎሽ የመሩ የቀድሞ ስራ አስኪያጆች አቶ ፍቅሩ ተስፋዬ፤ አቶ ፍሬው ሀንቄ፤ አቶ ሙንጣሻ ብርሀኑ እና የወቅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ዘነበ ቱርጬ በጋራ በመሆን ካባ እና ጋቢ የማልበስ ስነ-ስርዓትን መርተው በመጨረሻም የእውቅና ምስክር ወረቀት በመስጠት እና በጋራ ማእድ በመቁረስ መር-ግብሩ ተጠናቋል፡፡
ለፕሮግራሙ መሳካት ከሀሳብ አመንጭነት ጀምሮ ትልቁን ድርሻ የተወጣውን "Adare MCC" ቡድንን እናመሠግናለን።

ግንቦት 21/2018 ዓም. አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ሀዋሳ፡፡

እንኳን ደስ አላችሁ!🎉🎉🎉🎉🎉💥💥💥💥🎉🎉🎉🎉🎉​የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል የማስፋፊያ ፕሮጀክት የሆነው ባለ 8 ወለል ህንጻ (B+G+8)፣ በዛሬው ዕለት ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም. በይፋ ተ...
27/05/2026

እንኳን ደስ አላችሁ!

🎉🎉🎉🎉🎉💥💥💥💥🎉🎉🎉🎉🎉

​የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል የማስፋፊያ ፕሮጀክት የሆነው ባለ 8 ወለል ህንጻ (B+G+8)፣ በዛሬው ዕለት ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም. በይፋ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

​የማስፋፊያ ህንጻውን የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ በክብር እንግድነት መርቀው የከፈቱት ሲሆን፤ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልሉና የከተማው አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የህብረተሰብ ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

​በዛሬው ዕለት የተመረቀው ይህ ህንጻ፣ ሆስፒታሉ ቀደም ሲል ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት ብዛትና ጥራት በብዙ እጥፍ ከፍ ከማድረግ ባለፈ፣ ለከተማዋ የጤና ቱሪዝም ዘርፍ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሎ ይጠበቃል።
​ህንጻው በሚከተለው መልኩ የተደራጀ ነው፦
​ከወለል በታች (Basement): ዘመናዊ ዲያግኖስትክ ራዲዮሎጂ ክፍሎች፣
​የመጀመሪያ ወለል (Ground Floor): የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት፣
​1ኛ ፎቅ: ስፔሻሊቲ እና ሰብ-ስፔሻሊቲ የተመላላሽ ህክምና አገልግሎት፣
​2ኛ ፎቅ: የእናቶች እና ጨቅላ ህጻናት ህክምና አገልግሎት፣
​3ኛ ፎቅ: ጠቅላላ ቀዶ ህክምና፣
​4ኛ ፎቅ: የህጻናት እና የአዋቂዎች ጽኑ ህክምና ክፍል (ICU)፣
​5ኛ እስከ 7ኛ ፎቅ: የተኝቶ ህክምና አገልግሎት፣
​8ኛ ፎቅ: የአስተዳደር እና ተያያዥ አገልግሎቶች።
​ህንጻው በሙሉ አቅሙ ሥራ ሲጀምር፣ 232 የተኝቶ ህክምና አልጋዎች፣ 5 ሜጀር እና 7 ማይነር ኦፕሬሽን ክፍሎች፣ 24 የድንገተኛ ህክምና ማቆያ አልጋዎች እንዲሁም 22 የጽኑ ህክምና አልጋዎችን ይይዛል።

​ይህ ህንጻ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ተገንብቶ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ለዚህ ታላቅ ስኬት አሻራቸውን ላኖሩ የክልል እና የከተማ አስተዳደሩ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች እንዲሁም በየደረጃው ላሉ አመራሮች ሆስፒታሉ ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል።
በተጨማሪም ተቋሙ በሙሉ አቅሙ ህብረተሰቡን እንዲያገለግል፣ ቀሪ ያልተሟሉ ግብዓቶችን ለማሟላት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከጎናችን እንዲቆሙ ጥሪ እናቀርባለን።

​አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል
ግንቦት 19 ቀን 2018 ዓ.ም.
ሀዋሳ

የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል የ3ኛ ሩብ ዓመት የህዝብ ፎረም አካሄደ።ሆስፒታሉ በዛሬው እለት የ3ኛ ሩብ ዓመት የህዝብ ውይይት መድረክ ያካሄደ ስሆን በፎረሙ ላይ ከሁሉም ክፍለ-ከተማ የተወጣጡ የ...
15/05/2026

የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል የ3ኛ ሩብ ዓመት የህዝብ ፎረም አካሄደ።

ሆስፒታሉ በዛሬው እለት የ3ኛ ሩብ ዓመት የህዝብ ውይይት መድረክ ያካሄደ ስሆን በፎረሙ ላይ ከሁሉም ክፍለ-ከተማ የተወጣጡ የህዝብ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡
በመርሀግብሩ መሰረት ተሳታፊዎች ሆስፒታሉ እየሰጠ ያለውን አገልግሎት እና በቅርቡ ተመርቆ አገልግሎት የሚጀምረዉን የማስፋፊያ ግንባታ መጠናቀቁንና አገልግሎት ለማስጀመር እየተደረገ ያለውን ቅድመ ዝግጅት ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

ከጉብኝቱ በኋላ የሆስፒታሉ የ9 ወራት አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል፤ በአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት፤ በመድሀኒት እና ግብዓት አቅርቦት እና አስተዳደራዊ ስራዎች ያሉበትን ደረጃ በተሳታፊዎች ተገምግሞ ጠንካራ አፈጻጸሞች ተጠናክረው እንቀጥሉ እና መሻሻል ያለባቸው ነጥቦች ላይ በትኩረት እንዲሰራ ሀሳብ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

ውይይቱን የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ዘነበ ቱርጨ፤ የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ጻዲቁ ጌታቸዉ እና የሀዋሳ ከ/ጤ/መምሪያ ሜድካል ሰርቪስ ዳይሬክተር አቶ ወ/ሰንበት ዳንኤል በጋራ መርተዋል፡፡

ግንቦት 7/2018 አዳሬ አ/ሆስፒታል ሀዋሳ።

ለአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል አስተባባሪዎች እና ባለሙያዎች "በTSEDU-Clean Hospital, የህሙማን ደህንነት(Patient Safety) እና Hospital Accredation ዙሪያ ስልጠና...
27/04/2026

ለአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል አስተባባሪዎች እና ባለሙያዎች "በTSEDU-Clean Hospital, የህሙማን ደህንነት(Patient Safety) እና Hospital Accredation ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ስልጠናው በአቶ ዘነበ ቱርጬ የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ዋና ስራአስኪያጅ የመግቢያ ንግግር የተከፈተ ሲሆን በንግግራቸው በEHAQ 4TH CYCLE EBC በሀገር አቀፍ ደረጃ ሆስፒታላችን ያስመዘገብነው የላቅ ውጤት በTSEDU-Clean Hospital, የህሙማን ደህንነት(Patient Safety) እና Hospital Accredation ለማስመዝገብ እና ሞዴል የሆነ ሆስፒታል ለመፍጠር ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልጸው በጤናው ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት የጤና ባለሙያዎች የአመለካከት ለውጥ መምጣት ለነገ የማይባል ጉዳይ መሆኑን አሳስበዋል ፡፡

የሲዳማ ብ/ክ/መ/ጤና ቢሮ የጥራት ቁጥጥር ስራ ሂድት አስተባባሪ አቶ ጉዱራ ፉንቴ "በHospital Acredetation" በሁሉም የአገልግሎት አርዕስቶች ላይ የተቀመጡ ስታንዳርዶች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ስተዋል።

በሆስፒታሉ የጥራት ማሻሻያ ዳይሬክተር ዶ/ር አባይ በትሩ "በህሙማን ደህንነትን Patient safety" አስመልከቶ በሥራ ክፍላቸው ቡድን የተከናወነ የSafety and Risk Assessment ጥናታዊ ጽሁፍ ዋና ዋና ግኝቶችን ለሰልጣኞች በማቅረብ ተቋማችን በአሁን ሰዓት የሚገኝበትን ሁኔታ በቀጣይ የተኙት ክፍተቶች ታርመው ምቹ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎትን ለታካሚዎቻችን ለመስጠት መደረግ የሚገባቸውን ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች አመላክተዋል፡፡

በመጨረሻም በሆስፒታሉ የጥራት ማሻሻያ IPC ተጠሪ በአቶ ታገል ተስፋዬ ስለ TSEDU-Clean Healthcare Facility Initiative ምንነትና በሀገር አቀፍ እና በጤና ተቋማት ደረጃ ሊከናወኑ የታቀዱ ዋና ዋና ተግባራትን በመግለጽ ግንዛቤ የሰጡ ሲሆን ከዚሁ ጋር አያይዘው በተለያየ ጊዜ የተሰሩ የጥናት ውጤቶች ሪፖርትን በማቅረብ ተቋሙ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ከመቼውም ጊዜ በላይ መስራት እንዳለበት አመልክተዋል፡፡

በስልጠናው ማጠቃልያ የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ በቀጣይ የሚጠበቁ ተግባራትን በመግለፅ እና ሆስፒታላችን ምቹ እና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት የሰልጣኞች ሚና እጅግ የጎላ መሆኑን በማስገንዘብ ሞዴል የሆነ ሆስፒታል ለመፍጠር ሁላችንም ርብርብ ማድረግ እንደሚጠበቅብን መልክት በማስተላለፍ ስልጠና በይፋ ተጠናቋል፡፡

ሚያዝያ 19/2018 አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል -ሀዋሳ

የጌታችን የመድሀኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ መታሰቢያ በዓልን በስራ ገበታቸው ህብረተሰቡን እያገለገሉ ያሉትን ሰራተኞች የሆስፒታላችን ማነጅመንት አበረታቷቸዋል።በዛሬው እለት በዓልን በ...
12/04/2026

የጌታችን የመድሀኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ መታሰቢያ በዓልን በስራ ገበታቸው ህብረተሰቡን እያገለገሉ ያሉትን ሰራተኞች የሆስፒታላችን ማነጅመንት አበረታቷቸዋል።

በዛሬው እለት በዓልን በስራ ተረኛ ሆነው እያገለገሉ ያሉትን ሰራተኞች የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ፤ ማኔጀመንት እና MCC አባላት ሰራተኞችን በየስራ ክፍላቸው በመገኘት እና በማበረታታት የትንሳኤን መልካም ምኞት በመግለጽ በጋራ አሳልፈዋል።

አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል -ሚያዝያ 2018

የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል የትንሳኤ በዓልን ምክኒያት በማድረግ በሆስፒታሉ ስር የተለያዩ ድጋፍ ለሚደረግላቸው ህፃናት እና ዝቅተኛ የገቢ ምንጭ ላላቸው ወገኖች የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ።በፕሮ...
09/04/2026

የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል የትንሳኤ በዓልን ምክኒያት በማድረግ በሆስፒታሉ ስር የተለያዩ ድጋፍ ለሚደረግላቸው ህፃናት እና ዝቅተኛ የገቢ ምንጭ ላላቸው ወገኖች የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ።

በፕሮግራሙ ላይ የሐዋሳ ከተማ አስ/ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ይርዳቸው አናቶ ፤የአዳሬ አ/ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ዘነበ ቱርጬ፤ የማናጅመንት አባላት፤ ሲኒዬር ሀኪሞች እና አስተባባሪዎች የዕለቱ ተገኝተዋል።

የሆስፒታሉ MCC "Adare Awuuto" በተሰኘ እንሼቲቭ ቅን ልብ ባላቸው የሆስፒታሉ ሰራተኞች ከወርሀዊ ደሞዛቸው በሚቆረጥ የተመሠረተ ቡድን የሆስፒታሉ ሰራተኛ የሆኑ እና የገቢ ምንጫቸው ዝቅተኛ የሆኑ እናቶችን እገዛ የሚያደርግ እና እናቶች ልጆቻቸው ከትምህርት ገበታቸው እንዳይርቁና ትምህርታቸውን በአግባቡ በመከታተል ውጤታማ እንዲሆኑ በማለም በሆስፒታሉ ባለሙያ ለሆኑ ፈቃደኛ ለሆኑ ለአንድ ባለሙያ 1 ህፃን በመመደብ እንዲከታተሏቸው፤ Mentor እንዲያደርጉዋቸው እና የእነሱን አርአያ በመከተል ለሀገር መልካም ዜጋ እንዲሆኑ እገዛ እያደረጉ ይገኛል።

ይህ እንሼቲቭ በስሩ 20 ልጆችን ያቀፈ ሲሆን ላለፉት 3 ዓመታት የት/ት ሠርጃ መሳሪያዎችን ጨምሮ የኪስ ገንዘብና ሌሎችንም ድጋፎች ሲያደርግ ቆይቷል።
በፕሮግራሙ ላይ በሆስፒታሉ ውስጥ በፅዳትና በተለያዩ የድጋፍ ስራ ላይ ያሉ እና የገቢ ምንጫቸው አነስተኛ ለሆኑ ሰራተኞች በዘንድሮ ለበአል መዋያ እንዲሆን ከ"Adare Awuuto" እና ከሆስፒታሉ የገንዘብ ደጋፍ ተደርጎለቸዋል።

በመጨረሻም ይህ ሆስፒታል በቀል ሪፎርም በሁሉም የመንግስት እና የግል ተቋማት ቢተገበር እንደሀገር ተወዳዳሪ እና ብቁ ዜጋን ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊኖረው እንደሚችል ተመልክቷል።

በዝህ በጎ ተግባር ለተሳተፉ ልብ ቀና የሆስፒታሉ ሰራተኛ እና ፕሮግራሙን ላሰናዱ የ"Adare MCC" አባለት ሆስፒታሉ ምስጋናውን ያቀርባል።

አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ሚያዝያ 1/2018 ሀዋሳ።

የአዳሬ አ/ሆስፒታል ሰራተኞች ሆስፒታሉ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ባገኘው እውቅና መደሰታቸውን ገለጹ።"መረጃን መሠረት ያደረገ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ- Evidence  Based Care(EBC)" ...
08/03/2026

የአዳሬ አ/ሆስፒታል ሰራተኞች ሆስፒታሉ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ባገኘው እውቅና መደሰታቸውን ገለጹ።

"መረጃን መሠረት ያደረገ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ- Evidence Based Care(EBC)" ሆስፒታላችን ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ሲተገበር የቆየ ሲሆን በዘንድሮ የEHAQ-4TH CYCLE መጨረሻ የመዝጊያ መድረክ ላይ የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ባገኘው ሽልማት እና እውቅና መደሰታቸውን የገለጹት የሆስፒታሉ ሰራተኞች በቀጣይ ለህብረተሰቡ ለሚሰጡት አገልግሎት ከፍተኛ መነሳሳትን እንደፈጠረላቸው ገለጸዋል።

እንኳን  ደስ  አላችሁ/አለን🎉🎉 ‼  በሀገር አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው የሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ አዳሬ አጠቃላይ  ሆስፒታል  የዋንጫ፣የሰርተፍኬት እና 2,000,0...
06/03/2026

እንኳን ደስ አላችሁ/አለን🎉🎉 ‼

በሀገር አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው የሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል የዋንጫ፣የሰርተፍኬት እና 2,000,000 ብር ተሸላሚ ሆኗል።

የጤና ሚንስቴር ኢንሼቲቭ የሆነውን "መረጃን መሠረት ያደረገ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ- Evidence Based Care(EBC)" ሆስፒታላችን ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ሲተገበር የቆየ ሲሆን በዘንድሮ የEHAQ-4TH CYCLE መጨረሻ ምዘና በብቃት እና በትጋት በማለፍ ተሸላሚ ሆኗል።

ለዚህ ስኬት አስተዋጽኦ ያደረጉትን የሆስፒታላችን ትጉህ ሰራተኞች፤ የክልል ጤና ቢሮ አመራሮች እና ባለሙያዎች፤የሆስፒታሉ ስራ አመራር ቦርድ፤ የሀዋሳ ከተማ ጤና መምሪያ እና የሆስፒታሉን ማኔጅሜንት ከልብ እናመሰግናለን።

እንዲሁም ከክልላችን በሀገር-አቀፍ ደረጃ ተሸላሚ ለነበራቸው ይርጋለም፤ለኩ እና ሞቲቴ ፉራ ሆስፒታሎች እንኳን ደስ አላቸው!!

አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል:ሲዳማ :ኢትዮጵያ
የካቲት 27-2018

Address

Central Piassa
Hawassa
251

Telephone

+251462211661

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Adare General Hospital, Hawassa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Adare General Hospital, Hawassa:

Shortcuts

Share

Category