Gazer Primary Hospital

Gazer Primary Hospital የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን በጋዘር ከተማ አስተዳደር ሥር የሚትገኝ የመንግስት ጤና ተቋም ነው።ከ300 ሽ በላይ ለሆኑት ህዝብ አገልግሎት ይሰጣል።በ2010 ዓም አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

በድጋሚ የወጣ የሥራ ማስታወቂያ! አንስቴዥያ ባለሙያ በድግሪ
14/09/2026

በድጋሚ የወጣ የሥራ ማስታወቂያ!
አንስቴዥያ ባለሙያ በድግሪ

‎እንኳን አደረሳችሁ‎‎ለጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውድ የጤና ባለሙያዎችና የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ሁሉ፣‎‎እንኳን ከ2018 ዓ.ም ተጋድሎና ፈተና ከበዛበት ዓመት ወደ አዲሱ የ2019 ዓ.ም...
10/09/2026

‎እንኳን አደረሳችሁ

‎ለጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውድ የጤና ባለሙያዎችና የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ሁሉ፣

‎እንኳን ከ2018 ዓ.ም ተጋድሎና ፈተና ከበዛበት ዓመት ወደ አዲሱ የ2019 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ!አደረሰን!

‎ያለፈውን የ2018 ዓ.ም የትግል ዘመን ስንዘክረው፣ በጤናው ዘርፍ ላይ የገጠሙንን እንደ የወባ ወረርሽኝ፣ የማርበርግ ቫይረስ (Marburg virus) ወረርሽኝ እና ሌሎችም ከባድ ፈተናዎችን በጋራ በመቆም ያስታውሰናል። እነዚህን አስቸጋሪ ጊዜያት በድል ተሻግረን ዛሬ አዲስ ዓመት ላይ መድረስ የቻልነው (በእናንተ) የባለሙያዎች ጥብቅ ብርታት፣ የማይናወጥ ትጋት እና የሰዓት ግድ የለሽነት ነው።

‎ከጥበቃ ሰራተኞቻችን አንስቶ እስከ ስፔሻሊስት ዶክተሮቻችን ድረስ—በየተሰለፋችሁበት የሥራ መስክ ህዝባችንን ለማዳን ያሳያችሁት ሞያዊ ጽናትና መስዋዕትነት ከፍ ያለ ግምት የሚሰጠው ነው። የድርጅታችን የዕለት ተዕለት ውበትና የህዝባችን ተስፋ የሆናችሁ ሁላችሁም ምስጋና ይገባችኋል።

‎አዲሱ 2019 ዓ.ም የሰላም፣ የጤና፣ የደስታ እና የሥኬት ዓመት እንዲሆንላችሁ እየተመኘሁ፤ በፈተናዎች ውስጥ አብረን እንዳለፍነው ሁሉ፣ በጋራ በመቆም ሆስፒታላችንን ወደ የተሻለ ከፍታ እንደምናሸጋግረው ጽኑ እምነት አለኝ።

‎መልካም አዲስ ዓመት ለእናንተና ለቤተሰቦቻችሁ ይሁን!

‎ ከአክብሮት ጋር🙏

‎ ያዕቆብ ጥላሁን

‎የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ

‎በጋዘር ከተማ አስተዳደር በጋዘር ቀበሌ ዘማች ካምፕ እና ሐሙስ ገበያ  መንደር በህፃናት ምግብ እጥረት ዙሪያ የተካሄደው የ12 ቀን ሰርቶ ማሳያ መርሃ-ግብር በስኬት ተጠናቀቀ‎‎ ጳጉሜ 3/2...
08/09/2026

‎በጋዘር ከተማ አስተዳደር በጋዘር ቀበሌ ዘማች ካምፕ እና ሐሙስ ገበያ መንደር በህፃናት ምግብ እጥረት ዙሪያ የተካሄደው የ12 ቀን ሰርቶ ማሳያ መርሃ-ግብር በስኬት ተጠናቀቀ

‎ ጳጉሜ 3/2018_ ጋዘር

‎ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን በሚገኘው በጋዘር ከተማ አስተዳደር ሥር በጋዘር ቀበሌ ለምግብ እጥረት የተጋለጡና ሊጋለጡ የሚችሉ ህፃናትን ለመደገፍና ታድገው እንዲያገግሙ ለማድረግ ሲካሄድ የቆየው የ12 ቀናት የተመጣጠነ ምግብ አሰራር Positive Deviance Hearth (PD hearth)መርሃ-ግብር ዛሬ ጳጉሜ 3 2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ተጠናቋል።

‎በዚህ አጠቃላይ የምግብ እጥረት መከላከልና የህፃናት ጤና ማሻሻያ መርሃ-ግብር ላይ ለአካባቢው ህብረተሰብና እናቶች በአካባቢ በሚገኙ የእህልና ጥራጥሬ ዓይነቶች ላይ የተመሰረተ አልሚ ምግብ አዘገጃጀት በተግባር የተደገፈ ትምህርት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ ፕሮግራሙን ሙሉ ለሙሉ ተከታትለው ያጠናቀቁ እናቶችና ህፃናት የዕውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

‎ ✍️የቅንጅታዊ አሰራሩ ዋና ዋና ተሳታፊ አካላት
‎የቀበሌ ጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፦ በየልማት ቡድኑ ድረስ በመውረድ ሰርቶ ማሳያውን በመምራትና እናቶችን በማስተማር በዋናነት ሰፊውን ሥራ አከናውነዋል።
‎የከተማ አስተዳደሩ ጤና ዩኒቶች፦ አጠቃላይ የሱፐርቪዥን፣ የክትትልና የቁሳቁስ ማስተባበር ሥራዎችን በበላይነት መርተዋል።
‎በመርሃ-ግብሩ ማጠቃለያ ላይ እንደተገለጸው፣ ይህ በየልማት ቡድኑ የተከናወነው የተቀናጀ ሥራ በቀጣይም በሁሉም ቀበሌያት ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ የህፃናትን የምግብ እጥረት ዘላቂ በሆነ መንገድ ለመቅረፍ የማህበረሰብ ተሳትፎው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

‎የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ‎‎    ነሐሴ 29/2018_ጋዘር ‎‎የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል PRT...
04/09/2026

‎የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ

‎ ነሐሴ 29/2018_ጋዘር

‎የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል PRT እና የማኔጅመንት አባላት ዛሬ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም የሐምሌ እና የነሐሴ ወራት የሆስፒታሉን እንዲሁም የዙሪያ ቀበሌያትን የጤና አገልግሎት አፈጻጸም በስፋት ገመገሙ።

‎በግምገማ መድረኩ ላይ የጋዘር ከተማ አስተዳደር የጤና ዩኒት መሪ ሲስተር እታክቱ ዱቅላ፣ የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ያዕቆብ ጥላሁን፣ የ4ቱ ቀበሌያት የጤና ኤክስቴንሽን ካቢኔዎች እና የሆስፒታሉ ማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል።

‎በስብሰባው ትኩረት የተደረገባቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

‎* የሕክምና አገልግሎት ስኬት፦ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ብቻ 238 እናቶች በሆስፒታላችን ደህንነቱ የተጠበቀ የወሊድ አገልግሎት ማግኘት ችለዋል።
‎* የወረርሽኝ መከላከልና ቅንጅት፦ በአሁኑ ወቅት ስጋት እየሆኑ የመጡትን የኤች.አይ.ቪ (HIV)፣ የቲቢ እና የወባ በሽታዎችን ለመቀነስ ከጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል። ህብረተሰቡ ጋር በቅርበት የሚገኙት የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ተጠቅመው ታካሚዎችን ወደ ሆስፒታል የማያያዝ (Link የማድረግ) ስራን ማጠናከር ላይ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
‎* የአገልግሎት ክፍሎች ግምገማ፦ የሁሉም የሥራ ሂደት ክፍሎች የሁለት ወራት አፈጻጸም ዝርዝር ግምገማ ተካሂዷል።
‎* የእናቶች ማቆያ ድጋፍ፦ በ2019 በጀት ዓመት በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሚገኙ ነፍሰጡር እናቶች የሚሆን የቀለብ አሰባሰብ ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጎ፤ ለሚመለከታቸው ቀበሌያት ጥሪ የሚያስተላልፍ ደብዳቤ ተልኳል።

‎ሆስፒታላችን ከአካባቢው የጤና መዋቅር ጋር በመቀናጀት ለአካባቢው ማህበረሰብ ጥራት ያለውና ቀልጣፋ የጤና አገልግሎት ለመስጠት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል!

‎ጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

‎ጤናዎ ህይወታችን ነው!

‎ !‎   እንኳን ደስ ያላችሁ!!‎       ነሀሴ 28/2018_ጋዘር‎‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን በሚገኘው የጋዘር ከተማ አስተዳደር ከጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጋር በመተባበር...
03/09/2026

‎ !

እንኳን ደስ ያላችሁ!!

‎ ነሀሴ 28/2018_ጋዘር

‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን በሚገኘው የጋዘር ከተማ አስተዳደር ከጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ሲካሄድ የቆየው የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የደም ልገሳ መርሃ-ግብር ዛሬ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም በታላቅ ስኬት ተጠናቋል!

‎ለአንድ ወር ያህል በጋዘር ከተማ ሐሙስ ገበያ አዳራሽ በነፃ ሲሰጥ የቆየው የጤና አገልግሎት የሚከተሉትን ዋና ዋና ተግባራት ያካተተ ነበር፡

‎ነፃ የጤና ምርመራዎች፦ የኤች.አይ.ቪ (HIV)፣ የደም ግፊት፣ የስኳር በሽታ፣ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር እና የዓይን ምርመራ፤
‎የህክምና ድጋፍ፦ ከፍለው መታከም ለማይችሉ ወገኖች የገንዘብ ማሰባሰብ፤
‎የጤና ትምህርት፦ ስለ ወባ ወረርሽኝና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች በድምጽ ማጉያ (Speaker) በመጠቀም ለገበያተኛው ማህበረሰብ የተሰጠ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስሰጥ ነበር።ይህ አጠቃላይ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እስከ ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ም ድረስ ተጠናክሮ የሚቀጥል ስሆን ከበጎ ተግባር ውስጥ አንዱ የሆነው የደም ማሰባሰብ መረሐ ግብር ዛሬ በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ከጧቱ 3:00 እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት ድረስ በድል ተሰርቷል።

‎98 ፈቃደኞች ለልገሳ የቀረቡ ሲሆን፤ በጤና ምርመራ ምክንያት 65 አልፎ 33ደግሞ አልፎ ሳይለግሱ ቀርተዋል፤ በአጠቃላይ [65] ዩኒት ደም በአንድ ጀምበር መሰብሰብ ተችሏል።

‎በዚህም መሰረት ሆስፒታሉ በ2019 ዓ.ም በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ለመሰብሰብ ያቀደውን 100 ዩኒት ደም ግብ 65 ዩኒት በማስመዝገብ 65% ማሳካት ተችሏል! ሆስፒታሉ በዓመቱ ውስጥ 400 ዩኒት ደም ለመሰብሰብ አቅዶ በየሶስት ወሩ ይህንን መርሃ-ግብር የሚያካሂድ ሲሆን፣ ይህም በሆስፒታሉ ውስጥ በደም እጥረት ምክንያት የሚጠፉትን እናቶች እና ህፃናትን ህይወት ለመታደግ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።
‎ ይሄ የሆስፒታሉ በየሩብ ዓመቱ የሚደረግ የደም ልገሳ ፕሮግራም ቀጣይ ከ3 ወር በኋላ ማለትም ህዳር 20/2019 በድጋሚ በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ይደረጋል።

‎የምስጋና መልእክት

‎የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ያዕቆብ ጥላሁን ለመርሃ-ግብሩ ስኬት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት በሙሉ የከበረ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡

‎* የጋዘር ከተማ አስተዳደር ዋና ከንቲባ ኢንጅነር በለጠ ማጎ እና የከተማ አስተዳደር አስተባባሪ ኮሚቴዎች፤
‎* የከተማ አስተዳደር ዩኒት መሪዎች እና የሴክተር ኃላፊዎች፤
‎* የጋዘር ከተማ ንቁ ወጣቶች፤
‎* የሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያዎች፣ ዶክተሮች እና አጠቃላይ የሆስፒታሉ ሰራተኞች፤
‎* የሆስፒታሉ "Hope" የእግር ኳስ ስፖርት ክለብ ተጫዋቾች።

‎"ደም በመለገስ ህይወትን እንታደግ!"

‎መልካም ዜና እና የጥሪ መልእክት ከጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል!‎‎ጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን በጋዘር ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች...
02/09/2026

‎መልካም ዜና እና የጥሪ መልእክት ከጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል!

‎ጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን በጋዘር ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ላለፉት ጥቂት ሳምንታት ሲያካሂድ የቆየውን የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት የበጎ አድራጎት አገልግሎት በታላቅ ስኬት ሲያካሂድ ቆይቷል።

‎በዚህ አገልግሎት ሆስፒታላችን 7 የጤና ባለሙያዎችን መድቦ በጋዘር ሐሙስ ገበያ አዳራሽ በመገኘት፦

‎*ለ300+ የማህበረሰብ አባላት ነፃ የስኳር፣ የደም ግፊት እና የኤች.አይ.ቪ (HIV) ምርመራ፣
‎*ለ30+ እናቶች የማህፀን ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና ቅድመ-ልየታ፣
‎* ስለ ወባ ወረርሽኝ መከላከል ሰፊ የማህበረሰብ ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት፣
‎* ድጋፍ ለሚሹ እና በገንዘብ ምክንያት መታከም ላልቻሉ ወገኖች ከ1,300 ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ የማሰባሰብ ሥራ ተከናውኗል።

‎🩸 ልዩ የደም ልገሳ ጥሪ! 🩸

‎የዚህ በጎ ተግባር አካል የሆነው የደም ማሰባሰብ ፕሮግራም ነገ ሐሙስ (ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም) ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በሆስፒታላችን ቅጥር ግቢ ይካሄዳል።

‎በዕለቱ የጋዘር ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በቦታው ተገኝተው ደም በመለገስ አርአያነታቸውን የሚያሳይበት በመሆኑ፣ እርሶም የመልካምነቱ አካል በመሆን የወገኖቻችንን ሕይወት እንዲታደጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

‎ለአንድ ሰው ሕይወት መታደግ ከሚደረጉ ስጦታዎች ሁሉ የላቀው የደም ስጦታ ነው።

‎📅 ቀን፦ ነገ ሐሙስ (ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም)
‎⏰ ሰዓት፦ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ
‎📍 ቦታ፦ በጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ

‎"አንድ ፕላዝማ ደም መለገስ የበርካቶችን ሕይወት ይታደጋል!"

‎በጋዘር ከተማ አስተዳደር በጋዘር ቀበሌ በሱብ ቁጥር ሁለት መንደር በህፃናት ምግብ እጥረት ዙሪያ የተካሄደው የ12 ቀን ሰርቶ ማሳያ መርሃ-ግብር በስኬት ተጠናቀቀ‎‎        ነሐሴ 26/2...
01/09/2026

‎በጋዘር ከተማ አስተዳደር በጋዘር ቀበሌ በሱብ ቁጥር ሁለት መንደር በህፃናት ምግብ እጥረት ዙሪያ የተካሄደው የ12 ቀን ሰርቶ ማሳያ መርሃ-ግብር በስኬት ተጠናቀቀ

‎ ነሐሴ 26/2018_ ጋዘር

‎ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን በሚገኘው በጋዘር ከተማ አስተዳደር ሥር በጋዘር ቀበሌ ለምግብ እጥረት የተጋለጡና ሊጋለጡ የሚችሉ ህፃናትን ለመደገፍና ታድገው እንዲያገግሙ ለማድረግ ሲካሄድ የቆየው የ12 ቀናት የተመጣጠነ ምግብ አሰራር Positive Deviance Hearth (PD hearth)መርሃ-ግብር ዛሬ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ተጠናቋል።

‎በዚህ አጠቃላይ የምግብ እጥረት መከላከልና የህፃናት ጤና ማሻሻያ መርሃ-ግብር ላይ ለአካባቢው ህብረተሰብና እናቶች በአካባቢ በሚገኙ የእህልና ጥራጥሬ ዓይነቶች ላይ የተመሰረተ አልሚ ምግብ አዘገጃጀት በተግባር የተደገፈ ትምህርት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን፣ ፕሮግራሙን ሙሉ ለሙሉ ተከታትለው ያጠናቀቁ እናቶችና ህፃናት የዕውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

‎ ✍️የቅንጅታዊ አሰራሩ ዋና ዋና ተሳታፊ አካላት
‎የቀበሌ ጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፦ በየልማት ቡድኑ ድረስ በመውረድ ሰርቶ ማሳያውን በመምራትና እናቶችን በማስተማር በዋናነት ሰፊውን ሥራ አከናውነዋል።
‎የከተማ አስተዳደሩ ጤና ዩኒቶች፦ አጠቃላይ የሱፐርቪዥን፣ የክትትልና የቁሳቁስ ማስተባበር ሥራዎችን በበላይነት መርተዋል።
‎የተከበሩ አቶ ለማ የጋዘር ቀበሌ አስተዳደር ህብረተሰቡን በማንቀሳቀስና ለፕሮግራሙ ስኬት አስፈላጊውን አስተዳደራዊ ድጋፍ በመስጠት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

‎በመርሃ-ግብሩ ማጠቃለያ ላይ እንደተገለጸው፣ ይህ በየልማት ቡድኑ የተከናወነው የተቀናጀ ሥራ በቀጣይም በሁሉም ቀበሌያት ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ የህፃናትን የምግብ እጥረት ዘላቂ በሆነ መንገድ ለመቅረፍ የማህበረሰብ ተሳትፎው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

የሥራ ማስታወቂያ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን በጋዘር ከተማ አስተዳደር በጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
31/08/2026

የሥራ ማስታወቂያ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን በጋዘር ከተማ አስተዳደር በጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

‎በጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል እና የደም ልገሳ መርሃ-ግብርን ለማስተባበር ያለመ የምክክር መድረክ ተካሄደ‎‎  ነሐሴ 22/2018_ጋዘር ‎‎ጋዘር መጀመሪያ ...
28/08/2026

‎በጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል እና የደም ልገሳ መርሃ-ግብርን ለማስተባበር ያለመ የምክክር መድረክ ተካሄደ

‎ ነሐሴ 22/2018_ጋዘር

‎ጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት ጥራቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እና የህብረተሰቡን የእለት ተእለት የጤና ፍላጎት በብቃት ለመመለስ የሚያስችሉ ተግባራትን በትኩረት እየከናወነ ይገኛል።
‎በዚሁ መሰረት ዛሬ ከሆስፒታሉ የላብራቶሪ ባለሙያዎች እና ከሆስፒታሉ የሥራ አመራር አባላት ጋር ተከታታይ እና ውጤታማ የሆኑ የምክክር መድረኮች ተካሂዷል። በዋናነት የላብራቶሪ አገልግሎት ጥራት እና የሥራ አካባቢ ውይይት ከባለሙያዎች ጋር ተደርጓል።ይሄውም
‎የአገልግሎት ጥራት እና ፍጥነትን ከማሳለጥ ጋር ተያይዞ ለታካሚዎች የሚሰጡ የላብራቶሪ ምርመራዎች ትክክለኝነት፣ ጥራት እና ቀልጣፋነት ይበልጥ በሚሻሻሉበት ሁኔታ ላይ በስፋት ተመካክረናል።አለመግባባቶችንም ከመፍታት አኳያ፦ በዕለታዊ የሥራ እንቅስቃሴ ወቅት የሚያጋጥሙ ክፍተቶችን እና በባለሙያዎች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት፣ ምቹ እና ፍቅር የሰፈነበት የሥራ መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የጋራ ላይ ተደርሷል።
✍️ እንድሁም ባለፉት ወራት ተቋርጦ የነበረውን ብዙ ማህበረሰባችን ያጉላላ ለከፍተኛ ወጪ ስያዳርግ የቆየውን የ CBC አገልግሎት በቂ Reagent ቀርቦ አገልግሎቱ ክፍት እንደሆኔ እና በዚህ አገልግሎት የሥራ ሂደቱ ጥራት ከፍ እንደምያደርገው ገልፀዋል።በስተመጨረሻም የ2019 1ኛ ሩብ ዓመት የደም አሰባሰብ መረሐ ግብርን ለመምራት ኮሚቴዎች ተዋቅረዋል።

‎የዝግጅት ሁኔታው፦ መጪው ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም (የፊታችን ሀሙስ) ከጧቱ 3:00 ጀምሮ የሚካሄደውን ታላቅ የደም ማሰባሰብ መርሃ-ግብር በስኬት ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ ቅድመ-ዝግጅቶች ተገምግመዋል።
‎የአመራሩ ድርሻ፦ መርሃ-ግብሩ ውጤታማ እንዲሆን የቅስቀሳ፣ የሎጅስቲክስ እና የቅንጅት ሥራዎች በከፍተኛ ኃላፊነት እንዲመሩ አቅጣጫ ተቀምጧል።

‎ለህብረተሰቡ የቀረበ ጥሪ

‎ደም መለገስ ህይወትን ማተርፍ ነው! ሐሙስ ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም በሚካሄደው በዚህ በጎ አድራጎታዊ መርሃ-ግብር ላይ ሙሉ የሆስፒታላችን ማህበረሰብ እና የአካባቢው ነዋሪዎች በመገኘት ደም በመለገስ የበርካታ ወገኖችን ህይወት እንድትታደጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

‎ጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

‎ለጤናዎ ትጉህ አጋር!

Address

Jinka Gazer
Jinka

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gazer Primary Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share