የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ Aari Zone Health Department

  • Home
  • Ethiopia
  • Jinka
  • የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ Aari Zone Health Department

የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ Aari Zone Health Department የዜጎች ጤና ለሀገር ብልጽግና በሚል መሪህ የጤና ሥርዓቱን አጠናክሮ ማስቀጠል

የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ የ2019 9ኛ ሣምንት ኮማንድ ፖስት እና የPHEOC/IMS መገምገሙን አስታወቀ ።ጂንካ_መስከረም 9/2019(ኣዞጤመ)    በመድረኩ ላይ PHEOC/IMS እና በመደበኛ ...
18/09/2026

የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ የ2019 9ኛ ሣምንት ኮማንድ ፖስት እና የPHEOC/IMS መገምገሙን አስታወቀ ።
ጂንካ_መስከረም 9/2019(ኣዞጤመ)

በመድረኩ ላይ PHEOC/IMS እና በመደበኛ የትኩረት ሪፖርት አፈጻጸም ቀርቦ በበይነመረብ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በዝህ በwk 37/2026 የወባ ሥርጭት በ24% መቀንስ መቻሉ ተመላክቷል።

በአጠቃላይ 2589 ምርመራ ተደርጎ 1290 ወባ የተገኘባቸው ሲሆን ይህም በወባ የመያዝ ምጣኔ በዞን ደረጃ 50% መሆኑ ተመላክቷል።

ከፍተኛ የወባ ጫና ያለባቸው ከዞኑ ድርሻ
1, ጂንካ ከተማ 620(48%)
2, ደቡብ ኣሪ 193(14%)
3, ባካዳውላ 152(12%)
ሲሆን ቀሪ መዋቅሮች 26% ድርሻ አላቸው።

አሁንም የወባ መከላከል እና ለመቆጣጠር የሚሰሩ ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠል ይገባል።

በእናቶችና ሕጻናት ጤና ተግባራት፣ የበሽታ መከላከል እንድሁም በኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል የተሰሩ ተግባራት አፈጻጸሞች ቀርበዉ ተገምግሟል።

የግምገማ መድረክ ላይ የሚታዩ ውስንነቶችን በቀጣይ ማሻሻል እንደሚገባ ፣ ከ5 ዓመት በታች ምግብ ዕጥረት ልየታ (GMP) እና የወባ መከላከል ሥራዎችን ትኩረት እንድሰጥባቸው እንድሁም በወቅቱ ተግባራትን በመገምገም እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ለውጥ እንድኖር ያልተቆራረጠ ግምገማ በማድረግ ለውጥ ለማምጣት በትኩረት እንድሰራ የጤና መምሪያ ኃላፊ ተወካይ አቶ ታገል ደጉ በማሳሰብ መድረኩ ተጠቃሏል።

በሣምንቱ የተከናወኑ ለሎች ዝርዝር የአፈጻጸም ሪፖርቶች ቀርበው አስተያየት የተሰጠባቸው ሲሆን የወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ማናጅመንት አካላት በበይነመረብ ተሳትፈውበታል።

// የዜጎች ጤና ለሀገር ብልጽግና//

የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ ገጾችን Follow በማድረግ እንድከታተሉን እንጋብዛለን ።

ተለግራም https://t.me/AariZoneHealthDepartment

tiktok.com/

https://www.facebook.com/profile.php?id=61565064929502

በማርበርግ ቫይረስ ወላጆቻቸውን ላጡ ህጻናት የተጀመረው የቤት ግንባታ ተጠናቆ በቀጣይ ሳምንት ርክክብ ይደረጋልጂንካ_ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ም(ኣዞጤመ)በቅን ልቦች አስተባባሪነት በጂንካ ከተማ በ...
10/09/2026

በማርበርግ ቫይረስ ወላጆቻቸውን ላጡ ህጻናት የተጀመረው የቤት ግንባታ ተጠናቆ በቀጣይ ሳምንት ርክክብ ይደረጋል

ጂንካ_ጳጉሜ 5/2018 ዓ.ም(ኣዞጤመ)

በቅን ልቦች አስተባባሪነት በጂንካ ከተማ በማርበርግ ቫይረስ በሽታ ወላጆቻቸውን ላጡ ህጻናት መቋቋሚያ የሚሆን የቤት ግንባታ ሂደት ተጠናቆ በቀጣይ ሳምንት ርክክብ እንደሚደረግ ተገለጸ።

በጂንካ ከተማ በሶስት ቦታዎች ላይ ለህጻናቱ መኖሪያና መቋቋሚያ የሚሆኑ ቤቶች እንዲገነቡ የተጀመረው የግንባታ ሥራ በጥሩ ሁኔታ ተከናውኖ ወደ መጨረሻ ደረጃ መድረሱን የጂንካ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ደግፌ ጌታቸው፣ ምክትል ከንቲባ አቶ ውባለም ገዛህኝ ፣ የጂንካ ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፈለቀ ወርቁ እና የጂንካ ከተማ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ኩማ በቦታዎቹ ተገኝተው ተመልክተዋል።

የግንባታው የመጨረሻ ሥራዎች በመጠናቀቃቸው ቤቶቹ ለህጻናቱ ምቹ የመኖሪያ ስፍራ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ዝግጅቶችም እየተጠናቀቁ መሆኑ ተጠቁሟል።

ይህ ተግባር በማርበርግ ቫይረስ ምክንያት ወላጆቻቸውንና የቤተሰብ ድጋፋቸውን ላጡ ህጻናት የመኖሪያ ችግርን በማቃለል ከእነርሱ ጎን ለመቆም በቅን ልቦች የተጀመረ የማህበረሰብ የበጎ ተግባር ተሳትፎ ነው።

የቅን ልቦች አስተባባሪ አካላት እንደገለጹት፣ የቤት ግንባታው በተሳታፊዎች የጋራ ጥረትና ድጋፍ ተጠናቆ ለህጻናቱ ርክክብ ሊደረግ መቃረቡና በተለይም በተግባሩ የተሳተፉ ወገኖች የድርሻቸውን በመወጣታቸው ለዚህ ስኬት መድረስ ተችሏል ስሉም ተናግረዋል ስል በጂንካ ከተማ መንግሥት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት/Jinka Town Government Communication Office ዘግቧል።

የዜጎች ጤና ለሀገር ብልጽግና
የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ለአቅሜ ደካሞች ማዕድ አጋሩ።“ጳጉሜ 04 የህብር ቀንን” በማስመልከት ማዕድ በማጋራትና በልዩ ልዩ ኩኔት ታስቦ ውሏል።ጂንካ_...
09/09/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ለአቅሜ ደካሞች ማዕድ አጋሩ።

“ጳጉሜ 04 የህብር ቀንን” በማስመልከት ማዕድ በማጋራትና በልዩ ልዩ ኩኔት ታስቦ ውሏል።

ጂንካ_ጳጉሜ 04/2018(ኣዞጤመ)

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ክቡር እንዳሻው ሽብሩ እና አሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አብርሃም አታ ለአቅሜ ደካማ እናቶች እና በሆስፒታል ለሚገኙ ህሙማን ማዕድ አጋሩ።

ቢሮ ኃላፊው፣ የኣሪ ዞን አስተዳዳሪ እና ሌሎች አመራሮች በጋራ በመሆን በጂንካ ጠቅላላ ሆስፒታል በህክምና ላይ ያሉ ህሙማንን በመጎብኘት ማዕድ አጋርተዋል።

ለአቅሜ ደካማ እናቶች የምግብ ዱቄት እና ምግብ ዘይት የተሰጠ ሲሆን፤ በሆስፒታል በህክምና ያሉ ዜጎችን በመጎብኜት ማዕድ የደረሰ ተሰጥቷቸዋል።

ቢሮ ኃላፊው ክቡር እንዳሻው እንደተናገሩት ያለንን በማጋራትና በዓሉን በደስታ ለማሳለፍ ከአቅሜ ደካማ ወገኖች ጋር መሆን የህብራዊነት ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አብርሃም አታ በበኩላቸው እንኳን አደረሳችሁ በማለት በዓሉን በደስታ ማሳለፍ እንዲችሉ ማዕድ አጋርተዋል።

በተጨማሪም በሆስፒታሉ የተገነባውን የኦክስጅን ማምረቻ ማሽነሪዎችን ጎብኝተዋል።

ጤና ቢሮ ኃላፊው ክቡር እንዳሻው ሽብሩ ፤ በክረምት በጎ ማጠቃለያ መርሃ ግብር ወቅት አስተዋፅዎ ላበረከቱ አካላት የዕውቅና ሴርቲፊኬት አበርክተዋል።

ዕውቅና የተሰጣቸው ጂንካ ደም ባንክ፣ ቀይመስቀል ጂንካ ቅርንጫፍ፣ ለዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ፣ ጂንካ ጠቅላላ ሆስፒታል እና ለጂንካ ክላስተር ክልል ተቋማት ዕውቅና ተሰጥቷል።

በመድረኩ ከፍተኛ አስተዋፅዎ ላበረከቱ ግለሰቦችና ጤና ባለሙያዎች ዕውቅና ተበርክቷል።

በመጨረሻም ጤና ቢሮ ኃላፊ ክቡር እንዳሻው ሽብሩ በህብር ስናብር ችግሮችን እንሻገራለን ፤ መቻላችንን በጋራ ወረርሽኞችን ተቆጣጥረን አልፈናልና በመደጋገፍ ለበለጠ መተባበር ይገባናል ብለዋል።

በኩኔቱ የጤና ቢሮ ምክትል አመራሮችና ኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ፣ ኣሪ ዞን ፓሪቲ ኃላፊ አቶ አፈዶ ወርቁ፣ የኣሪ ዞን ዋና አፌጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ስመኝ ተስፋዬ ፣ የጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ በድሉ ባጊማሶ፣ የጂንካ ከተማ ከንቲባ አቶ ደግፈ ጌታቸው እንድሁም የክልል፣ የዞን እና የጂንካ ከተማ አመራሮች እና ተጋባዥ እንግዶች ተግኝተዋል።

በመጨረሻም ቢሮ ኃላፊው በዓሉ በሠላም ለማሳለፍ የደስታ እና የብልጽግና እንዲሆን ተመኝተዋል።

የዜጎች ጤና ለሀገር ብልጽግና
የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ

ጳጉሜ 04/2018 ዓ/ም " የኅብር ቀን""ኢትዮጵያ የብዝሃነት ጌጥ" በሚል መሪ ቃል በኣሪ ዞን ጂንካ ከተማ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ተከበረ።ጳጉሜ 04/2018 ጤና ቢሮ ኮሚኒኬሽን____የደቡ...
09/09/2026

ጳጉሜ 04/2018 ዓ/ም " የኅብር ቀን"

"ኢትዮጵያ የብዝሃነት ጌጥ" በሚል መሪ ቃል በኣሪ ዞን ጂንካ ከተማ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ተከበረ።

ጳጉሜ 04/2018 ጤና ቢሮ ኮሚኒኬሽን
____

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ፣ የኣሪ ዞን እና የጂንካ ከተማ የመንግስት አመራርሮችና የከተማዋ ነዋሪዎች በጂንካ ከተማ አደባባይ ቀኑን በመግለጽ ህዝባዊ የአካል እንቅስቃሴ ስፖርት እና የጎዳና ላይ ሩጫ በማካሄድ የኅብር ቀን ተከብሯል ።

በመርሐ ግብር የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ክቡር እንዳሻው ሽብሩ “ድር ብያብር አንበሳ ያስር!” እንደሚባል ሁሉ በአንድነት ቆመን ትልቅ ታሪክ መሥራት እንችላለን ብለዋል።

በቅርብ ጊዜ በጂንካ ከተማና አካባቢው የማርበርግ በሽታ ተከስቶ በአንድነት ዓለም በሚመሰክር መልኩ በአንድነት መቆጣጠር ችለናል በዚህም መላው ሕዝብ ልመሰገን ይገባል ብለዋል።

የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ሕብረብሔራዊ ቀለም ባለቤት በመሆኑ የኅብር ቀን መከበሩ ተጨማሪ ውቤታችንና አንድነታችንን ለማረጋገጥ አቅም ይፈጥርልናል ብለዋል።

የቀደሙ አባቶች በአንድነት ትልቅ ገድል ፈጽመዋል ዛሬ እኛ ደግሞ ያለ ልዩነት በድህነት ላይ ዘምተን ብልጽግናችንን እናረጋግጣለን ሲሉም ዋና አስተዳዳሪው ገልፀዋል።

በመርሐ ግብሩ የደም ልገሳን ጨምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች የኅብር ቀን ተከብሯል።

በጎዳና ላይ በነበረው ሩጫ አሸናፊ ለሆኑ አካላት ሜዳልያ እና እውቅና ተሰጥቷቸዋል ስል የክልሉ ጤና ቢሮ ኮሚኒኬሽን ዘግቧል።

የዜጎችጤና ለሀገር ብልጽግና
የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ

የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ የኤች አይ ቪ ኤድስ ፣ የጉበት በሽታ እና የቅጥኝ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት የ2018 ዓ.ም አፈጻጸም እና የ2019 በጄት ዓመት ግቦች ላይ ምክክር አ...
08/09/2026

የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ የኤች አይ ቪ ኤድስ ፣ የጉበት በሽታ እና የቅጥኝ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት የ2018 ዓ.ም አፈጻጸም እና የ2019 በጄት ዓመት ግቦች ላይ ምክክር አካህደዋል።
ጂንካ_ጳጉሜ 3/2018 ዓ.ም (ኣዞጤመ)

በኤች አይ ቪ ኤዲስ ፣የጉበት በሽታ እና የቅጥኝ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና በ2019 ዓ.ም ዕቅድ በተመለከት ምክክር ተደርጓል፡፡

በዞኑ የሚገኙ ወረዳዎች በ2018 ዓ.ም በኤች አይ ቪ ኤዲስ ፣የጉበት በሽታ እና የቅጥኝ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡

ለበሽታዉ ተጋላጭነትን የሚያባብሱ ሁኔታዎች መጨመራቸዉ ፣ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መበራከት የበሽታዉን ስርጭት ከፍ እንዳደረገውም በሪፖርት ተመላክቷል፡፡

የበሽታዉ ወረርሽኝ እንዳይስፋፋ ስለ ኮንዶም አጠቃቀም እየተሰራ ያለዉ የግንዛቤ መፍጠርና የማሰራጨት ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠቁሟል፡፡

በቫይረሱ መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የሚሰሩ ክበባት ስራቸዉን አጠናክረዉ መቀጠል እንደሚገባቸውና በበሽታዉ ተጠቂዎች ላይ የሚደረገዉ ማግለል እንዲቆም በሪፖርቱ አፅንዖት ተሰጥቷል፡፡

በተጨማሪም ቫይራል ሄፓታይትስ ከሰዉ ወደ ሰዉ በንኪኪና በሰዉነት ፈሳሽ የሚተላለፍ በመሆኑ በጊዜ ካልታከሙት አደገኛ ገዳይ በሽታ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ሄፓታይትስ ቢ /የጉበት በሽታ/ ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን የመከላከሉን ስራ በትኩረት መስራት እንደሚገባም ተመላክቷል ።

በዕቅዱ መነሻ መሠረት ትኩረት በመስጠት እንድሰራ እና ይበልጥ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የተጠናከሬ ሥራ እንድሰራ እና የመረጃ ጥራት እና የወርሃዊ አፈጻጸም ግምገማ በማድረግ ለውጦችን ማስቀጠል ይገባል ስሉ በኤች አይ ቪ ኤዲስ ፣የጉበት በሽታ እና የቅጥኝ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አቶ ፍርዱ ለማ አሳስበው መድረኩን አጠቃለዋል።

ከአፈጻጸም ሪፖርቱ በተጨማሪ PHFFA በኩል የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰንድ ቀርቦ በተሳታፊዎች አስተያየት ጥያቀዎች ተነስተው ምላሽና ማብራርያ ተሰጥቶባቸዋል።

የዜጎች ጤና ለሀገር ብልጽግና
የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ ገጾችን Follow በማድረግ እንድከታተሉን እንጋብዛለን ።

ተለግራም https://t.me/AariZoneHealthDepartment

tiktok.com/

https://www.facebook.com/profile.php?id=61565064929502

 !የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ በ2018 ሥራ ዘመን በክልሉ ካሉ የመንግስት ተቋማት በሥራ አፈፃፀሙ ተመዝኖ በጣም ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቡ በክልሉ መንግስት እውቅና ተሰጠው።የውጤቱ ባለ...
07/09/2026

!

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ በ2018 ሥራ ዘመን በክልሉ ካሉ የመንግስት ተቋማት በሥራ አፈፃፀሙ ተመዝኖ በጣም ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቡ በክልሉ መንግስት እውቅና ተሰጠው።

የውጤቱ ባለቤት የሆነው የጤና ሴክተር ቤተሰቦች፣ አጋር ድርጅቶች እና መላው የቢሮ ሠራተኞች ላበረከቱን የጋራ ጥረት እውቅና ተችረዋል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ክቡር እንዳሻው ሽብሩ ቢሮው የማይበገር የጤና ሥርዓትን በመዘርጋት እና የዜጎችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ፤ ድንገተኛ የወረርሽኝ ክስተት በመቆጣጠር እንዲሁም በመሠረታዊ ጤና አገልግሎት በክልሉ ካሉ ቢሮዎች በጣም ከፍተኛ አፈፃፀም በማስመዝገብ ዕውቅና መሰጠቱን በመግለጽ ለመላው የጤና ሴክተር ቤተሰቦች እና ቢሮ ሠራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ጳጉሜ 02/2018
የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ

የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ የ2019 9ኛ ሣምንት ኮማንድ ፖስት እና የPHEOC/IMS መገምገሙን አስታወቀ ።ጂንካ_ነሐሴ 30/2018(ኣዞጤመ)    በመድረኩ ላይ በሣምንቱ በPHEOC/IMS እና ...
05/09/2026

የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ የ2019 9ኛ ሣምንት ኮማንድ ፖስት እና የPHEOC/IMS መገምገሙን አስታወቀ ።
ጂንካ_ነሐሴ 30/2018(ኣዞጤመ)

በመድረኩ ላይ በሣምንቱ በPHEOC/IMS እና በመደበኛ የተከናወኑ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በዝህ በwk 35/2026 የወባ ሥርጭት በ29% መቀንስ መቻሉ ተመላክቷል።

በአጠቃላይ 3151 ምርመራ ተደርጎ 1515 ወባ የተገኘባቸው ሲሆን ይህም በወባ የመያዝ ምጣኔ በዞን ደረጃ 48% መሆኑ ተመላክቷል።

ከፍተኛ የወባ ጫና ያለባቸው ከዞኑ ድርሻ
1, ጂንካ ከተማ 732(48%)
2, ደቡብ ኣሪ 275(18%)
ሲሆን ቀሪ መዋቅሮች 34% ድርሻ አላቸው።

አሁንም የወባ መከላከል እና ለመቆጣጠር የሚሰሩ ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠል ይገባል።

በእናቶችና ሕጻናት ጤና ተግባራት፣ የበሽታ መከላከል እንድሁም በኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል የተሰሩ ተግባራት አፈጻጸሞች ቀርበዉ ተገምግሟል።

የግምገማ መድረክ ላይ በረጅም ጊዜ የቤተሰብ ዕቅድ አግልግሎት(ሉፕ) የሚታዩ ውስንነቶችን በቀጣይ ማሻሻል እንደሚገባ ፣ ከ5 ዓመት በታች ምግብ ዕጥረት ልየታ እና የወባ መከላከል ሥራዎችን ትኩረት እንድሰጥባቸው እንድሁም በወቅቱ ተግባራትን በመገምገም እስከታችኛው መዋቅር ግብረመልስ በመስጠት ሁሉም ዳይሬክቶሬቶች በአግባቡ ለጤና መዋቅሮች ድጋፍ በማድረግ ለውጥ ለማምጣት በትኩረት እንድሰራ የጤና መምሪያ ኃላፊ ተወካይ አቶ ታገል ደጉ በማሳሰብ መድረኩ ተጠቃሏል።

በሣምንቱ የተከናወኑ ዝርዝር የአፈጻጸም ሪፖርቶች ቀርበው አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል።

// የዜጎች ጤና ለሀገር ብልጽግና//

የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ ገጾችን Follow በማድረግ እንድከታተሉን እንጋብዛለን ።

ተለግራም https://t.me/AariZoneHealthDepartment

tiktok.com/

https://www.facebook.com/profile.php?id=61565064929502

በኣሪ ዞን ባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በጌዛ ፣ ሸጵ ጋይላና ጎይድ  ቀበሌዎች የወባ በሽታ ወረርሽኝን መከላከልያ የቤት ለቤት ከሚካል ርጭት እየተካሄደ ይገኛል     ጂንካ_ነሐሴ 26/...
01/09/2026

በኣሪ ዞን ባካ ዳዉላ ኣሪ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በጌዛ ፣ ሸጵ ጋይላና ጎይድ ቀበሌዎች የወባ በሽታ ወረርሽኝን መከላከልያ የቤት ለቤት ከሚካል ርጭት እየተካሄደ ይገኛል

ጂንካ_ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም (ኣዞጤመ)

በወረዳዉ የወባ በሽታ ጫናን ለመቀነስና ወረርሽኙን ለመከላከል የተጀመረዉ የቤት ለቤት ርጭት ሥራ ተጠናክሮ በመቀጠል በትናንትናዉ ዕለትም በጎይድ ቀበሌ የመከላከልያ የቤት ለቤት ኬሚካል ርጭቱን ሥራ ማካሄድ ጀምሯል።

ጽ/ቤቱ የኬሚካል ርጭቱን በወረዳዉ በሁሉም ቀበሌያት ለማዳረስ እየሠራ ሲሆን ማህበረሰቡ በኬሚካል ርጭት ወቅት አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በመስራት ለርጭቱ ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንዳለባቸው እንጠይቃለን።

የወባ ወረርሽኝ በኬሚካል ርጭት ብቻ የሚጠፋ ባለመሆኑ በሁሉም ቦታ የአካባቢ ቁጥጥር ስራዎች ተጠናክረው መሰራት አለባቸው።

ማህበረሰቡ በርጨቱ ወቅት በቤት ውስጥ የሚገኙ የምግብ ነክ እና የመመገቢያ እቃዎችን ከቤት ውጭ ማስወጣት እና ህፃናት ቤት ውስጥ ተኝተው እንዳይቀሩ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

እያንዳንዱ ቤት ከተረጨ በሗላ ለ2:00 ስዓት ያክል በሮችንና መስኮቶችን በመዝጋት ማቆየትና ከ2:00 ስዓት በሗላ ለ30 ደቂቃ በሩን ከፍቶ ወለሉን ጠርጎ በማጽዳት ቤቱ ከተረጨ ከ6-8 ወራት ያክል ግድግዳውን ምንም አይነት ቀለምም ሆነ ጭቃ መለቅለቅ እንደሌለበት እናሳስባለን።

የወባ በሽታን በጋራ እንከላከል!!
የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ

የሥራ ማስታወቂያ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኣሪ ዞን በጋዘር ከተማ አስተዳደር የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
31/08/2026

የሥራ ማስታወቂያ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኣሪ ዞን በጋዘር ከተማ አስተዳደር የጋዘር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ የ2019 8ኛ ሣምንት ትኩረት ሪፖርት እና የIMS መገምገሙን እንድሁም በተከለሰው የ90ቀን ተግባር ላይ ኦሬንተሽን መስጠቱን አስታውቋል።ጂንካ_ነሐሴ 22/2018(ኣዞጤ...
28/08/2026

የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ የ2019 8ኛ ሣምንት ትኩረት ሪፖርት እና የIMS መገምገሙን እንድሁም በተከለሰው የ90ቀን ተግባር ላይ ኦሬንተሽን መስጠቱን አስታውቋል።
ጂንካ_ነሐሴ 22/2018(ኣዞጤመ)

በመድረኩ ላይ በሣምንቱ በIMS እና በመደበኛ የተከናወኑ ሪፖርት አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በዝህ በwk 34/2026 የወባ ሥርጭት በ26 % መቀንስ መቻሉ ተመላክቷል።

በአጠቃላይ 4070 ምርመራ ተደርጎ 1971 ወባ የተገኘባቸው ሲሆን ይህም በወባ የመያዝ ምጣኔ በዞን ደረጃ 48% መሆኑ ተመላክቷል።

በሳምንቱ በወባ የመያዝ ምጣኔ በገሊላ ከተማ እና ባካዳውላ ወረዳ 67% ሲሆን በወረዳዎች ላይ ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል።

ከፍተኛ የወባ ጫና ያለባቸው ከዞኑ ድርሻ
1, ጂንካ ከተማ 885(45%)
2, ደቡብ ኣሪ 376(19%)
3, ባካ ዳውላ 321(16%)
አሁንም የወባ መከላከል ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠል ይገባል።

በእናቶችና ሕጻናት ጤና ተግባራት፣ የበሽታ መከላከል እንድሁም በኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል የተሰሩ ተግባራት በጥንካሬ እና በቀጣይ መስተካከል ባለባቸው አፈጻጸሞች ትኩረት ተሰጥቶባቸው ተገምግሟል።

በበይነ መረብ በተከናወነው የግምገማ መድረክ ላይ በረጅም ጊዜ የቤተሰብ ዕቅድ አግልግሎት የሚታዩ ውስንነቶችን በቀጣይ ማሻሻል እንደሚገባ ፣ ከ5 ዓመት በታች ምግብ ዕጥረት ልየታ፣ የማህጸን በር ካንሰር ልየታ እና የወባ መከላከል ሥራዎችን ትኩረት እንድሰጥባቸው በመምሪያ ኃላፊ በኩል አጽንኦት ተሰጥቶባቸዋል።

የሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ ም/ኃላፊዎች ፣ የእናቶችና ሕጻናት ፣በሽታ መከላከል ዳ/ሬት ቡድን መሪዎች እና የጤና መምሪያ ማንጅመንት የተሳተፉ ሲሆን በየሳምንቱ ግምገማ እንደሚቀጥል ገልጸው ወረዳዎች የተገመገመ በተከለሰው ሪፖርት ፎርማት እንድልኩ አሳስበው መድረኩን የመምሪያ ኃላፊ አቶ በድሉ ባጊማስ አጠቃለዋል።

በሣምንቱ የተከናወኑ የአፈጻጸም ሪፖርቶች ቀርበው አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል።

// የዜጎች ጤና ለሀገር ብልጽግና//

የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ ገጾችን Follow በማድረግ እንድከታተሉን እንጋብዛለን ።

ተለግራም https://t.me/AariZoneHealthDepartment

tiktok.com/

https://www.facebook.com/profile.php?id=61565064929502

Address

South
Jinka

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኣሪ ዞን ጤና መምሪያ Aari Zone Health Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share