በስልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት siltie zone mitto woreda health office

  • Home
  • Ethiopia
  • Mito
  • በስልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት siltie zone mitto woreda health office

በስልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት siltie zone mitto woreda health office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from በስልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት siltie zone mitto woreda health office, Medical and health, ሚቶ ወረዳ, Mito.

በሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሲካሄድ የቆየው የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል ተጠናቀቀ።ሰኔ 21/2018 ዓ.ም. (የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት)የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት  የ2018 ዓ.ም. የጤናው ሴክተር የ...
28/06/2026

በሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ሲካሄድ የቆየው የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል ተጠናቀቀ።

ሰኔ 21/2018 ዓ.ም. (የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት)

የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም. የጤናው ሴክተር የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድን ለማሳካት ይረዳ ዘንድ፣ በወረዳ ባሉ ጤና ተቋማት በመሰማራት የድጋፍና ክትትል ተግባራትን ለማከናወን መሠማራቱ የሚታወስ ነው።

የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ባለሙያዎች ቡድን ከሰኔ 19/2018 ጀምሮ በሚቶ ወረዳ ከቤት ለቤት ጉብኝት ጀምሮ በየደረጃው በሚገኙ የጤና ተቋማት ላይ ያካሄደውን የድጋፍና ክትትል ዛሬ አጠናቋል።

በድጋፍና ክትትሉ ወቅት በየደረጃው ለሚገኙ ለሁሉም መዋቅሮችና ባለድርሻ አካላት ግብረ መልስ መሰጠቱን ተገልጿል ፡፡

የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል ቡድኑ ለጤና ጣቢያ ማኔጅመንት አባላት በጥንካሬ እና መሻሻል በሚገባቸው ጉዳዮች ዙርያ የተለዩ ጉዳዮች ላይ የማጠቃለያ ግብረመልስ የሰጠ ሲሆን በቀጣይ የታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት የሚያስችል የድርጊት መርሃ ግብር በማውጣት፣ በወረዳው ሲካሄድ የቆየው የ2018 በጀት አመት አጠቀላይ የጤናው ሴክተር ተግባራት የድጋፍና ክትትል ተግባር ተጠናቋል።

የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የጤናው ሴክተር የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል በስሩ ለሚገኙ ጤና ተቋማት ለማካሔድ የባለሙያ ስምሪት ሰጠ።‎ሚቶ 18/2018 ዓ.ም (የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት)‎‎በወረዳው ...
25/06/2026

የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የጤናው ሴክተር የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል በስሩ ለሚገኙ ጤና ተቋማት ለማካሔድ የባለሙያ ስምሪት ሰጠ።

ሚቶ 18/2018 ዓ.ም (የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት)

‎በወረዳው በሚገኙ ጤና ተቋማት በ2018 በጀት አመት አጠቀላይ በተሰሩ ስራዎች ላይ የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል ለማድረግ ለጽ/ቤት ባለሙያዎች ኦሬንቴሽን በመሰጠት ስምሪት ተሰጥቷል።

‎የድጋፋዊ ክትትሉ አስፈላጊነት፣ ጠቀሜታ፣ አካሄድ እና አጠቃላይ ሂደት በዝርዝር የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ በአቶ ዋበላ ኡስማን በኩል ገለጻ ተደርጓል።

‎ከሰኔ 19/2018 ዓ.ም ጀምሮ በቼክ ሊስት የተደገፈ ድጋፋዊ ክትትል የቤተሰብ አባላት፣ የልማት ህብረት፣ ጤና ኬላ እና በጤና ጣቢያ ደርጃ የሚካሄድ መሆኑ ተገልጿል።

‎ለድጋፋዊ ክትትሉ ስኬት የሁሉም አካላት ትብብር አስፈላጊ በመሆኑ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ ተላልፏል

 በኢቲዮጲያ ​የTEAM and TEAM International ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ግርማ አርጋው ባጋጠማቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን ስንሰማ ታላቅ ...
25/06/2026



በኢቲዮጲያ ​የTEAM and TEAM International ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ግርማ አርጋው ባጋጠማቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን ስንሰማ ታላቅ ሀዘን ተሰምቶናል።

​አቶ ግርማ አርጋው በስልጤ ዞን በሚቶ ወረዳ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እና በጤናው ዘርፍ ሀይጅንና ሰንቴሽን ላይ በነበራቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እና በጎ ተግባር የማይረሳ ትልቅ አሻራ ጥለው አልፈዋል።

​የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በአቶ ግርማ አርጋው ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለስራ ባልደረቦቻቸው በሙሉ መጽናናትን ይመኛል።

በአመታዊ ቆጠራ ምክንያት ከሰኔ 25/2018 ዓ.ም በኃላ የመድኃኒት ሽያጭ አገልግሎት እንደማይሰጥ  በኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የደቡብ ኢትዮጵያ ክላስተርና የሐዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/...
24/06/2026

በአመታዊ ቆጠራ ምክንያት ከሰኔ 25/2018 ዓ.ም በኃላ የመድኃኒት ሽያጭ አገልግሎት እንደማይሰጥ በኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የደቡብ ኢትዮጵያ ክላስተርና የሐዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

በአመታዊ የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያ መሳሪያዎች ቆጠራ ምክንያት ከሰኔ 25/2018 ዓ.ም በኃላ ለተወሰኑ ቀናት የመድኃኒት ሽያጭ አገልግሎት እንደማይሰጥ በኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የደቡብ ኢትዮጵያ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ዘመን ለገሠ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በ 2023 በአፍሪካ ቀልጣፋና ፈጣን የመድኃኒት አቅርቦት ስንሰለት ያለዉ ተቋም ለመሆን የያዘዉን ራዕይ እዉን ለማድረግ በቴክኖሎጂ የታገዙ በርካታ የሪፎርም ፕሮግራሞችን ተግባራዊ በማድረግ ተጨባጭ ተቋማዊ ለዉጥ እያመጣ መሆኑን አቶ ዘመን ገልፀዋል፡፡
አገልግሎት መ/ቤቱ በዘረጋው የአሰራር ስርዓት መሠረትም የተቋሙ የመድኃኒትና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ማከማቻ መጋዘኖች ውስጥ በየሩብ አመቱ በሚደረግ ቆጠራ ውጤት መሠረት ጠንካራ የተጠያቂነት ስርዓት በመዘርጋቱ የመድኃኒት ብክነትን ከመከላከል አንፃር ለሌሎች የመንግስት ተቋማት ተሞክሮ የሆኑ ተቋማዊ ለውጦት መመዝገባቸውን አቶ ዘመን ገልፀዋል።

ከዚህ በፊት እስከ 2 ወር ይፈጅ የነበረዉ አመታዊ የመድኃኒት ቆጠራ ግዜን በማሳጠር ወደ 5 ቀናት ዝቅ ማድረግ መቻሉ የተቋሙ ሪፎርም ዉጤታማነት ማሳያ መሆኑን የገለፀት አቶ ዘመን የዘንድሮዉንም ቆጠራ በአጭር ገዜ በማጠናቀቅ አገልግሎቱን ክፍት ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አሳዉቀዋል፡፡

በጤና ተቋማት በነፃ ለሚሰጡት የክትባትና ሌሎች የጤና ፕሮግራሞች የሚያስፈልጉ መድኃኒቶች አቅርቦት መቆራረጥ እንዳይከሰት ለጤና ተቋማት መድኃኒቶቹን የማድረስ ስራ እየተጠናቀቀ እንደሚገኝ የገለፀት ስራ አስኪያጁ ጤና ተቋማት በግዥ የሚቀርቡ /RDF/ መድኃኒቶችን የግዥ ጥያቄ አገልግሎት ለሚያገኙበት የአገልግሎቱ ቅርንጫፎች (ሐዋሳ እና አርባምንጭ፣ ነገሌ ቦረና) በማቅረብ ግዥ መፈፀም እንደሚገባቸዉና ከሰኔ 25/2018 ዓ.ም በኃላ የሚቀርብ ጥያቄ እንደማይስተናገድ ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡
ከሰኔ 25/2018 ዓ.ም ጀምሮ የመድኃኒትና የህክምና መሳሪያዎች ቆጠራ ሂደት እስከሚጠናቀቅ ድረስ መደበኛ የመድኃኒት ሽያጭ አገልግሎት የማይሰጥ ቢሆንም ድንገተኛ የመድኃኒት ፍላጎቶች የሚስተናገዱበት Emergency Pharmaceuticals Supply System መዘርጋቱን አቶ ዘመን ገልፀዋል።

መረጃው ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ

የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ለማረጋገጥ የግል ጤና ተቋማት ሚና መጠናከር ይገባዋል- አቶ ዋበላ ኡስማንሰኔ 1/2018 (የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት)በወረዳው የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደ...
08/06/2026

የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ለማረጋገጥ የግል ጤና ተቋማት ሚና መጠናከር ይገባዋል- አቶ ዋበላ ኡስማን

ሰኔ 1/2018 (የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት)

በወረዳው የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የግል ጤና ተቋማት ሚና መጠናከር እንዳለበት የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ ዋበላ ኡስማን ገልፀዋል፡፡

በወረዳው ከሚገኙ የግል የጤና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡

የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ ዋበላ ኡስማን በዚሁ ወቅት እንዳሉት መንግስት የጤና አገልግሎትን በጥራትና በፍትሃዊነት ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

ከዚህ አንጻር የግል የጤና ተቋማት የተጀመረውን ጥረት ከግብ ለማድረስ አቅም እየሆኑ መምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡

የግል ዘርፉ በጤና አገልግሎት የሚሰማራበት ምቹ ምህዳር መፈጠሩን በመግለፅ፤ የግል ጤና ተቋማትም ሚናቸውን በቅጡ ሊወጡ እንደሚገባም በንግግራቸው ላይ አስምረውበታል፡፡

በወረዳው የሚገኙ የግል ጤና ተቋም የታካሚዎችን ፍላጎት በማስቀደም ጥራቱን የጠበቀ ፍትሃዊ አገልግሎት ሊሰጡ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

በተለይ የግሉ ዘርፍ የአሰራር ማዕቀፍን ተከትሎ መስራት ተቀዳሚ ተግባሩ ነው ያሉት አቶ ዋበላ ከመረጃ አያያዝ፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት መጓደል፣እውቅና የሌለው መድሃኒት አቅርቦት እና ሌሎች ተያያዥ ክፍተቶችን ማረም እንዳለባቸውም አዝገንዝበዋል፡፡

በምክክር መድረኩ ላይ የጽ/ቤቱ ም/ኃላፊ አቶ ዋበላ አብዶ እንደገለጹት መንግስት የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሃዊ ተደራሽነት ለማረጋገጥ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ የግሉ ዘርፍ የራሱ ወሳኝ ድርሻ እየተወጣ ነው።

አክለውም በዘርፉ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት በዋነኝነት ብቁ ባለሙያ፣የህክምና ቴክኖሎጂና የተደራጀ የአሰራር መዋቅር ተከትሎ መስራት ያስፈልጋል የሉት ም/ኃላፊው በተጨማሪ የቲቢ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት የግል ጤና ተቋማት ሚና የጎላ በመሆኑ መመሪያው በሚፈቅደው ልክ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የወረዳው ጤናና ጤና ነክ አገልግሎት ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ከድር ሁሴን እንደሉት በወረዳው በሚገኙ በግል ጤና ተቋማት ባደረገው ክትትልና ቁጥጥር መሠረት በግሉ የጤና ዘርፍ የሚጠየቁ ክፍያዎች መጠን የተጋነነ መሆኑ በመንሳት ተመጣጠኝ የሆነ የክፍያ ስርዓት በመዘርጋት አገልግሎት አሰጣጥን; ስታንደርድ ማሻሻል እና ሌሎች መሰል ችግሮችን የሚመለከቱ ጉዳዮችንም መስተካከል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎችም በግል የጤና ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን እንዴት መቅረፍ እንደሚቻል፣ የወረዳው በክትትል ሪፖርቱ የለያቸው ምክረ ሀሳቦች ስለሚተገበሩባቸው መንገዶች እና በቀጣይም ከእያንዳንዱ ባለድርሻ አካላት ምን እንደሚጠበቅ ያላቸውን አስተያየት ሰጥተዋል።

በመጨረሻም ሁሉም የግል ጤና ተቋማት ባለቤቶችና ተወካዮች የሚቶ ጤና ጣቢያ ጉብኝት በመድረግ ለሚቶ ጤና ጣቢያ ፋርማሲ ስታንደርድ ለማሻሻልና ለኦዲት ምቹ ለማድረግ/APTS ማስጀመሪያ አገልግሎ የሚውል ግብዓት ለሟሟላት 250,000 ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል።

04/06/2026
የአሚን አጠቃላይ ሆስፒታል መስራችና ባለቤት ዶ/ር መሐመድ ሽኩር ከ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ደረጃቸውን የጠበቁ ወንበሮችን በስልጤ ዞን ለሚገኙ ለ 7 ጤና ጣቢያዎች ድጋፍ ...
20/05/2026

የአሚን አጠቃላይ ሆስፒታል መስራችና ባለቤት ዶ/ር መሐመድ ሽኩር ከ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ደረጃቸውን የጠበቁ ወንበሮችን በስልጤ ዞን ለሚገኙ ለ 7 ጤና ጣቢያዎች ድጋፍ አደረጉ።

ግንቦት 12/2018ዓ.ም //የሚቶ ኮሚኒኬሽን//

የአሚን አጠቃላይ ሆስፒታል መስራችና ባለቤት እንዲሁም የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ዶ/ር መሐመድ ሽኩር ከ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ደረጃቸውን የጠበቁ ወንበሮችን በስልጤ ዞን ለሚገኙ 7 ነባርና አዳዲስ ጤና ጣቢያዎች በድጋፍ መልክ አበርክተዋል።

ለጤና ጣቢያዎቹ የተደረገውን ድጋፍ የአሚን ጄኔራል ሆስፒታል ባለቤት ዶ/ር መሐመድ ሽኩር ተወካይና የሀርላ ኢንተርናሽናል ሆቴልና ሪዞርት ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ራህመቶ ዋበላ (ዶ/ር) በወራቤ ከተማ በግንባታ ሂደት ላይ በሚገኘው የሀርላ ኢንተርናሽናል ሆቴልና ሪዞርት ሳይት ላይ ተገኝተው ለስልጤ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ ለአቶ ሸምሱ ሀይረዲንና ድጋፉ ለተደረገላቸው መዋቅሮች የጤና ጽ/ቤት ሀላፊዎች አስረክበዋል።

ለጤና ጣቢያዎቹ የተደረገው ድጋፍ የተቋማቱን አገልግሎት አሰጣጥ በማሳለጥና ደረጃቸውን በማሻሻል ውጤታማ ግልጋሎት እንዲሰጡ የሚያስችል መሆኑ ሲገለጽ ለድጋፉ ከ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉ ተመላክቷል።

የአሚን ጠቅላላ ሆስፒታል መስራችና ባለቤት ዶ/ር መሐመድ ሽኩር በዞን፣ በክልልና በሀገር ደረጃ የጤናውን ዘርፍ በመደገፍ ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ በተጋጋሚ እውቅና የተሰጣቸው ብርቱና ሀገር ወዳድ ግለሰብ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን በተለያየ መልኩ የሚያደርጉትን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም በርክክቡ ወቅት በተወካያቸው በኩል ተገልጿል።

በርክክብ መርሃ ግብሩ ላይ የሁሉም ወረዳዎች ጤና ጽ/ቤት ሀላፊዎች እና የሀርላ ኢንተርናሽናል ሆቴልና ሪዞርት ማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል ስል ስልጤ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቦታል።

የሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት የ5 ቀናት የHead Count and Accelerated mini Catch up ዘመቻ አፈፃፀም ገመገመ።     ግንባት 3/2018 ዓ.ም (የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት)የሚ...
11/05/2026

የሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት የ5 ቀናት የHead Count and Accelerated mini Catch up ዘመቻ አፈፃፀም ገመገመ።

ግንባት 3/2018 ዓ.ም (የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት)

የሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት የ5 ቀናት የHead count and Accelerated mini Catch up ዘመቻ አፈፃፀም የተገመገመ ሲሆን በዘመቻው የነበሩ ሂደቶች እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በዝርዝር መገምገም ተችሏል።

በመድረኩም ከወረደው ለድጋፍና ክትትል የተመደቡ ሱፐርቫይዘሮች የየራሳቸዉን አፈጻጸም ሪፖርት ያጋጠሙ ችግሮች እና የተፈቱበት አግባብ በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም የወረደው ማጠቃላያ ሪፖርት በኮማንድ ፖስት ቀርቦ ሰፊ ዉይይት እና ግምገማ ተደርጓል

በዘመቻውም ቤቶችን ተደራሽ ማድረግና House marking ፣ በተለያዩ ምክኒያት ከዚህ ቀደም ክትባት ያልጀመሩ እና ጀምረው የቋረጡ ህፃናት ልያታና የተለዩ ህፃናት እዚያው እንዲሰጥ የማደረግ ሰራ እና ተገቢ የሆነ መረጃ በመሰብሰብ የቀጣይ የ2019 በጀት ዓመት ማይክሮ ፕላን ማዘጋጀት እንዲሁም ሱፐርቫይዘሮች RCS/ODk በተገቢው መስራት እንዳለበት አቅጣጫዎች በማስቀመጥ ተጠናቋል።

‎ማስታወቂያ!‎👶🤰👶‎ነጻ የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ህክምና በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል! ‎‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ከወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ...
30/04/2026

‎ማስታወቂያ!
‎👶🤰👶
‎ነጻ የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ህክምና በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል!

‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ከወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፤ ከስማይል ትሬን እና ፕሮጀክት ሀረር ጋር በመተባበር በተፈጥሮ የላንቃና የከንፈር መሰንጠቅ ችግር ላለባቸው ልጆች በተከታታይ በዘጠኝ ዙሮች የተፈጥሮ የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ነፃ የቀዶ - ህክምና ዘመቻዎችን በማድረግ ከ274 በላይ ለሚሆኑ ህጻናት አገልግሎቱን በመስጠት ጤናቸዉንና ፈገግታቸዉን መመለስ ተችሏል፡፡

‎በአሁን ወቅት ህክምናው ዘወትር ሰኞ ነፃ ቀዶ ጥገና እንዲሁም ዘወትር ማክሰኞ የተመላላሽ ክትትል በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እየተደረገ ቢሆንም በ5ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የተለዩ ልጆችን እና በተለያዪ ምክንያት ከዚህ በፊት የህክምና እድል ያላገኙ ለ10ኛ ዙር ነጻ የቀዶ ህክምና ዘመቻ ተዘጋጅቷል፡፡

‎ስለሆነም ችግሩ ላለባቸው ልጆች ነፃ የቀዶ-ጥገና ህክምና ከ25-26/08/2018 ዓ.ም ለመስጠት አስፈላጊዉ ቅድመ-ዝግጅት የተጠናቀቀ ስለሆነ በ5ኛው ዙር የፖሊዮ ዘመቻ ወቅት በየመዋቅሩ ችግሩ ያለባቸዉን ልጆች ከዘመቻዉ ቀደም ብለዉ ቅዳሜ ማታ ማለትም በ24/08/2018 ዓ.ም ገብተዉ በማደር የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

በሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት በሁሉም ክላስተር በትምህርት ቤቶች የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ለልጃገረዶች መስጠት ተጀመረ፡፡        ሚያዚያ 9/2018ዓ.ም (የሚቶወረዳ ጤና ፅ/ቤት...
17/04/2026

በሚቶ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት በሁሉም ክላስተር በትምህርት ቤቶች የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ለልጃገረዶች መስጠት ተጀመረ፡፡

ሚያዚያ 9/2018ዓ.ም (የሚቶወረዳ ጤና ፅ/ቤት)

በወረዳው በሚገኘው ትምህርት ቤቶች የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ላይ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እና ዘጠኝ ዓመት ለሞላቸው ልጃገረዶች የHPV መከላከያ ክትባት መስጠት ተጀምሯል።

Address

ሚቶ ወረዳ
Mito

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በስልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት siltie zone mitto woreda health office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share