Dore Bafano Primary Hospital

Dore Bafano Primary Hospital Providing quality and efficient service to our community

የሀዘን መግለጫ"ትሁት ሰራተኛ እህታችንን አጣን"በዶሬ ባፋኖ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል  ባልደረባችን ናፍቆት ጌታቸው ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው  ከዚህ ዓለም በሞት መለ...
20/03/2026

የሀዘን መግለጫ
"ትሁት ሰራተኛ እህታችንን አጣን"

በዶሬ ባፋኖ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባልደረባችን ናፍቆት ጌታቸው ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ስንሰማ በጥልቅ ሀዘን ነው።😭😭😭😭😭😭

ናፍቆት በስራ ቦታዋ በነበራት ትጋት፣ ቅንነትና ለታካሚዎች በነበራት ርህራሄ በሁላችንም ዘንድ የምትወደድ ነበረች። የእሷ ማለፍ ለሆስፒታላችንና ለሁላችንም ደግሞ ከባድ ሀዘን ነው።

ለቤተሰቦቿ፣ ለወዳጅ ዘመዶቿና ለጠቅላላው የሆስፒታላችን ሰራተኞች ፈጣሪ መፅናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን።

ፈጣሪ ነፍሷን በገነት ያኑርልን

መልካም ዜና 🎉🎉 እንኳን ደስ አለን: አላችሁ!!ዶሬ ባፋኖ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በክልሉ Regulatory Authority ቡድን  በተደረገው በEFMHACA COMPULSORY STANDARD...
10/02/2026

መልካም ዜና 🎉🎉

እንኳን ደስ አለን: አላችሁ!!

ዶሬ ባፋኖ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በክልሉ Regulatory Authority ቡድን በተደረገው በEFMHACA COMPULSORY STANDARDS ዳሰሳ 75.2% ውጤት በማምጣት GREEN ደረጃ ለማስመዝገብ ተችሏል። በመመዝገቡ ሆስፒታሉ እንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ያስተላልፋል።
ምስጋና:-
• በነገር ሁሉ ለረዳን ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን
• ለሲዳማ ብ/ክ/መ/ጤና ቢሮ
• ለሆስፒታሉ ቦርድ አመራሮች
• ለሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር
• እንዲሁም ከሁሉም በላይ ደከመን ሰለቸን ሳትሉ በከፍተኛ ሞራል በመስራት ለህዝቡ የገባችሁትን ቃል በመፈጸም ይህን ውጤት ላስመዘገባችሁት ውድ ለሆስፒታላችን ሠራተኞች ምስጋናችን የላቀ ነው::
ከዚህ በኃላም ቢሆን ሆስፒታላችንን ወደላቀ ከፍታ ለማድረስ ዓላማችን የጸና ነው።

ዶሬ ባፋኖ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል!
ዶሬ/ሲዳማ/ኢትዮጵያ
የካቲት 03/2018

እንኳን አደረሳችሁ መልካም የገና በዓል ይሁንላችሁ ዶሬ ባፋኖ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል  ስራ አስኪያጅ አቶ ታምራት ዳንኤል የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት በዓልን   ምክንያት በማድረግ  ቤታቸው...
07/01/2026

እንኳን አደረሳችሁ
መልካም የገና በዓል ይሁንላችሁ
ዶሬ ባፋኖ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ታምራት ዳንኤል የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ቤታቸውን ትተው በዓሉን በስራ ላይ እያሳለፉ ላሉ ሰራተኞች ስጦታና እንኳን አደረሳችሁ የሚል መልዕክታቸውን አስተላልፏል ።

Doore bafano umi dirm hosipitaale loosu harisaanchi kalaa tamirati danielihu yesuusi illama korkaata asse ayaana minenisanna maatensa agurte loosu baayichcho sayisaano ogeeyera hawale keeruni iilishine yaani baraarisha ee towaanyo asinno!!!

Doore Bafano umi Dirim Hospitaale 2018 M.D Loosaasinete Foremena Lossu Keenoበዶሬ ባፋኖ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሠራተኞች ፎረም ተካሄደ::ጥቅም...
31/10/2025

Doore Bafano umi Dirim Hospitaale 2018 M.D Loosaasinete Foremena Lossu Keeno

በዶሬ ባፋኖ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሠራተኞች ፎረም ተካሄደ::
ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም

በዶሬ ባፋኖ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በዕለቱ የሠራተኞች ፎረም ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ታምራት ዳንኤል ሠራተኞችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ፕሮግራሙን ያስጀመሩ ሲሆን
በመቀጠልም የሆስፒታሉ የ2018 ዓ.ም የ3ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በሆስፒታሉ ልማት ዕቅድ ዘርፍ በሆኑት በአቶ አማኑኤል በኩል የቀረበ ሲሆን ሪፖርቱን ተከትሎም ዝቅተኛ አፈጻጸም በታየባቸው ዘርፎች መሻሻል ስላለባቸው ጉዳዮች ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል።

በመጨረሻም በቀጣይ ትኩረት የሚደረግባቸው ጉዳዮች የተለዩ ሲሆን እነዚህም በሆስፒታሉ የተቋረጡ እና አዳዲስ የህክምና አገልግሎቶች ማስጀመር እንዲሁም ሌሎች የጤናው ሴክተር ኢንሼቲቭ ላይ ጠንክሮ መስራት ሲሆን ሁሉም ሠራተኛ በአዲስ ሞራል እና ተነሳሽነት በመስራት ሆስፒታሉ ለማህበረሰቡ ተደራሽ የሆነ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጥ እና ተወዳዳሪና ተመራጭ ሆስፒታል እንድሆን በቁርጠኝነት እና በቁጭት ለመስራት የበኩሉን እንደሚወጣ በመስማማት የዕለቱ ስብሰባ ተጠናቋል።

ለላቀ ውጤትና ጥራት ተግተን እንሰራለን!
ዶሬ ባፋኖ መ/ደ/ሆስፒታል
ዶሬ/ሲዳማ/ኢትዮጵያ
ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም

ዛሬ በቀን 03/13/17 የዶሬ ባፋኖ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህዝብ መድኃኒት ቤትን በይፋ አስመርቀናልበምረቃው ፕሮግራም ላይ በመገኘት ያስመረቁት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ክብርት ዶ/ር ሰላ...
08/09/2025

ዛሬ በቀን 03/13/17 የዶሬ ባፋኖ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የህዝብ መድኃኒት ቤትን በይፋ አስመርቀናል
በምረቃው ፕሮግራም ላይ በመገኘት ያስመረቁት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ክብርት ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ እና የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆስፒታሉ የቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ብሩክ ሰለሞን በተገኙበት የህዝቡ ጥያቄ ሆኖ የቆየው የህዝብ መድኃኒት ቤት መርቀው ከፍተዋል

Address

Sidama
Sidama

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dore Bafano Primary Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category