Dr. Nurahmed

Dr. Nurahmed Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dr. Nurahmed, Doctor, Werabe, Silt'e.

10/09/2024

የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ የመተላለፊያ መንገድና ምልክቶች

በአሁኑ ወቅት የዓለም የጤና ስጋት ተብሎ በዓለም ጤና ድርጅት የተፈረጀው የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ በዝንጀሮ በጂነስ ኦርቶፖክስ ቫይረስ የሚመጣ ተላላፊ በሽታ ነው።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ተላላፊ ህመም ሲሆን÷ በሽታው ካለበት ሰው ወይም እንስሳ በንክኪ ሊይዘን ይችላል።

በበሽታው ከተያዘ ሰው የመተንፈሻ አካላት ብናኞች፣ የቆዳ ቁስል ወይም የሰውነት ፈሳሾች አማካኝነት በቅርብ ንክኪ፣ መሳሳም፣ መተቃቀፍ፣ በግብረ ሥጋ ግንኙነት እና በቆዳ ለቆዳ ንክኪ ይተላለፋል።

እንዲሁም በበሽታው የተያዘ ሰው ተጠቅሞባቸው ከተበከሉ አልባሳት፣ የቤት እቃዎችንና ሌሎች ግኡዝ ነገሮችን በመንካት ሊተላለፍ ይችላል፤ ነፍሰ ጡር እናቶች ቫይረሱን ወደ ጽንሱ ሊያስተላልፉ ይችላሉ።

የበሽታው ምልክቶች መታየት የሚጀምሩት አንድ ሰው ለቫይረሱ ከተጋለጠ ከሳምንት በኋላ ሲሆን÷ አንዳንዴ በቶሎ ወይም ሌላ ጊዜ ዘግየት ብሎ ሊጀምር ይችላሉ።

የተለመዱ የበሽታው ምልክቶች ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የእጢ እብጠት፣ የመገጣጠሚያ ህመምና ድካም ጨምሮ ቆዳ ላይ የሚወጣ ቁስል (ሽፍታ) ዋነኛ መገለጫው ነው።

ይህ የቆዳ ምልክቶች መጀመሪያ ላይ ጠፍጣፋ ቀላ ያለ ሽፍታ ሆኖ ይጀምርና ከዚያ አብጦ ፈሳሽ ይቋጥራል፤ በመቀጠልም ይፈርጥና ይቆስላል።

ይህ ቁስል በፊት ላይ፣ በአፍ ውስጥ እና እንደ እጆች፣ እግር፣ ደረት፣ የመራቢያ አካላት ወይም ፊንጢጣ ያሉ ሌሎች የአካል ክፍሎች ላይ ሊወጣ ይችላል።

ቁስሉ ሲቆይ ይደርቅና ተቀርፎ ይወድቅና በቦታው አዲስ ቆዳ ይተካል።

Via

09/09/2024

" ስለ አስም(Asthma) ምን ያክል ያውቃሉ""

✍️አስም ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የመተንፈሻ አካል ህመም ሲሆን የአየር ቧንቧን በማቁሰል ፣በማሳበጥና በማጥበብ ለመተንፈስ አስቸጋሪ ሁኔታን ይፈጥራል።
✍️አስም ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች አነዱ ሲሆን ምልክቶች በአየር ቱቦ ሂደቶች ምክንያት የሚመጣ ሲሆን ሶስት ምክንያቶች ተጠቃሽ ናቸው።.የአየር መመላለሻ ቱቦዎች መጥበብ ፤የአየር ቱቦዎች ቁስለት ፤የአየር ቱቦ ቁጣ መሆናቸው ይጠቀሳል።
✍️ በእነዚህ ምክንያቶች የተነሳ የሚከተሉት ምልክቶች ይታያሉ፦ ሳል በተለይም ጧትና ማታ ላይ የሚጨምር፤ በሚተነፍሱበት ጊዜ ከሳንባ የሚነሳ በተለይም አንገት አካባቢ የፉጨት አይነት ድምጽ ማሰማት ፤ለመተንፈስ መቸገር ፤ደረት አካባቢ ጥብቅ አድረጎ መያዝና የደረት ህመም፤ ቶሎ ቶሎ መተንፈስ፤ በትንፋሽ ማጠር ምክንያት ለመተኛት መቸገር የመሳሰሉት ናቸው።
✍️መቼ ወደ ህክምና መሄድ አለብዎት ፦ለመጀመሪያ ጊዜ ከላይ ከተጠቀሱት ምንም አይነት ምልክት ካለ :-
የአስም ህክምና እየተከታተሉ ከሆነ ፤ቶሎ ቶሎ መተንፈስ ፤የፊት እና የከንፈር መገርጣት/መጥቆር ፤ሲያወሩ፣ሲተነፈፍሱ፣ሲራመዱ አየር ማጠር ፤በሚተነፍሱበት ጊዜ የደረት ቆዳ ወደ ውስጥ መግባት ምልክቶች ሲታዩ ወደ ሀኪም መሄድ ይገባል።
✍️አስም የሚቀሰቅሱ ነገሮች ፦
•ሳይነስ፣ጉንፋንና ሌሎች የሳንባ ህመሞች
•የአበባ ፣የእንስሳት ቆዳ፣የፈንገስ፣ የአቧራ ብናኞች
•ከባድ ሽታ ያላቸው እንደ ሽቶ፣ አልኮል ፣ለማፅዳት የሚያገለግሉ ፈሳሾች
from amharahealth

Address

Werabe
Silt'e

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr. Nurahmed posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category