Dr. Ashebir Medium Clinic-AMC, Wolaita Sodo

Dr. Ashebir Medium Clinic-AMC, Wolaita Sodo We stand for your health! Your Home!

15/11/2025

ማርበርግ ቫይረስ

1) በሽታው ምንድን ነው?

#የቫይረሱ አይነት: ማርበርግ ቫይረስ የፋይሎቫይረስ (Filoviridae) ቤተሰብ አባል ሲሆን ይህም ኢቦላ ቫይረስ የሚገኝበት ቤተሰብ ነው። ለዚህም ነው ሁለቱም በሽታዎች ተመሳሳይ የሕመም ምልክቶች እና የሞት መጠን ያላቸው።

#ክብደት: በሽታው ከባድ እና ከፍተኛ የሞት መጠን ያለው ሲሆን፣ በቅርብ ጊዜ በተከሰቱ ወረርሽኞች በበሽታው ከተያዙት ውስጥ እስከ 88% የሚደርስ ሰዎች ሞተዋል (እንደ ወረርሽኙ ሁኔታ ሊለያይ ይችላል)።
#ታሪክ: በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ በ1967 ዓ.ም በጀርመን ማርበርግ እና በፍራንክፈርት እንዲሁም በሰርቢያ ቤልግሬድ ከተሞች ተከስቷል። ቫይረሱ የመጣው ከዩጋንዳ በመጡ የላብራቶሪ ምርምር ዝንጀሮዎች አማካኝነት ነው ይባላል።

2) ስርጭት (በሽታው እንዴት ይተላለፋል?)
+++ ዋናው #ምንጭ: የማርበርግ ቫይረስ ተሸካሚዎች ፍራፍሬ ላይ የሚያዘወትሩ የሌሊት ወፎች (Rousettus bats) ናቸው። ሰዎች በቫይረሱ ሊያዙ የሚችሉት በእነዚህ የሌሊት ወፎች ባሉበት ዋሻዎች ወይም ማዕድናት ውስጥ በመገኘት ነው።

+++ ከሰው ወደ ሰው የሚኖረው #ስርጭት: ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በበሽታው የተያዘ ሰው ወይም እንስሳት በሚወጡ ፈሳሾች (ደም፣ ምራቅ፣ ማስታወክ፣ ሰገራ፣ ሽንት፣ የዘር ፈሳሽ እና ሌሎች) ጋር በቀጥታ በመገናኘት ነው።
3) #ምልክቶች
የበሽታው ምልክቶች በአብዛኛው ከ2 እስከ 21 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ ይታያሉ።

የሚከተሉትን እንመልከት
#የመጀመሪያ ደረጃ ላይ : ከፍተኛ ትኩሳት፣ ከባድ ራስ ምታት፣ ከባድ የጡንቻና የመገጣጠሚያ ህመም፣ ድካም ስሜት።
#ሁለተኛ ደረጃ (ከጥቂት ቀናት በኋላ): ከባድ ተቅማጥ፣ የሆድ ቁርጠት፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ የደረት እና የጉሮሮ ህመም።
#የከፋ ደረጃ (ከ5-7 ቀናት በኋላ) ከባድ የደም መፍሰስ (ከአፍንጫ፣ ከድድ፣ ከዓይን እና የቆዳ ስር)፣ የጉበት እና የኩላሊት ድካም፣ የንቃተ ህሊና መሳት፣ የብዝሃ-አካል ስራ መቆም (Multi-organ failure) እና ሞት። ከዚህ በተጨማሪ የዓይን መቅላት፣ የቆዳ ሽፍታ (በተለይ በደረት፣ ጀርባና ሆድ አካባቢ)።

4)የሚሰጠው ህክምና እና መከላከያ መንገዶች
#ፈውስ: ለጊዜው ቫይረሱን የሚያጠፋ የተረጋገጠ መድኃኒት ወይም ክትባት የለም።
#ህክምና: የሚሰጠው ህክምና ምልክቶችን ለማስታገስ (Supportive Care) ነው።
#ፈሳሽ መተካት (IV fluids): በከፍተኛ ተቅማጥ እና ማስታወክ የጠፋውን ፈሳሽ መሙላት ነው።
#የደም መፍሰስ ቁጥጥር: የደም ግፊትን ማረጋጋት እና የደም መርጋት መከላከል/ማከም።
#የተጎዱትን የአካል ክፍሎች (ኩላሊት፣ ጉበት) ድጋፍ መስጠት።

በጣም #አስፈላጊው ነጥብ
-) የግል መከላከያ ቁሳቁስ (PPE): የጤና ባለሙያዎች የታመሙ ሰዎችን ሲያክሙ ጓንት፣ ጋውን፣ ጭንብል እና የዓይን መከላከያ የግድ መጠቀም አለባቸው።
_) ንጽህና: እጅን በአግባቡ በሳሙና መታጠብ፣ በተለይ የታመመ ሰው የነካን ወይም የጎበኘን ከሆነ።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ
1) የዓለም ጤና ድርጅት (World Health Organization - WHO): Marburg Virus Disease (MVD)

2) የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከላት (Centers for Disease Control and Prevention - CDC : Marburg Hemorrhagic Fever (Marburg HF)

30/03/2022

ከወሊድ በዃላ ደም መፍሰስ(POSTPARTUM HEMORRHAGE) ።

ከወሊድ በዃላ የደም መፍሰስ(postpartum hemorhage) ምንድን ነው?

✓ከወሊድ በዃላ ደም መፍሰስ (Postpartum hemorrhage )የምንለው በመደበኛ (vaginal birth ) የምትወልድ እናት >=500ml ወይም በቀዶ ጥገና ለወለደች እናት ደግሞ >=1000ml ወይም የ Hematocrit መጠን ከመነሻ(baseline) >10 % ሲወርድ ወይም የፈሰሰው ደም እጅግ ወሳኝ የሆኑት የአንድን ሰው ጤንነት የሚገለፁልን መሰረታዊ መለኪያዎች(vital signs) መሆን ከሚገባው በላይ ወይም በታች እንዲሆን ካደረገው ነው።

ምክንያቶቹ ምን ምን ናቸው?
✓ከወሊድ በዃላ የሚፈጠር ደም መፍሰስ ዋነኛው ምክንያት ልጅ ከተወለደ በዃላ የማህፀን ወደ ቦታ አለመመለስ(Uterine atony)፣በማህፀን አካባቢ አደጋ(trauma)፣በምጥ ጊዜ በማህፀን በር እና በብልት አካባቢ መሰንጠቅ(cervical and vaginal laceration)፣የደም መርጋት ችግር(Coagulopathy)፣ኢንፌክሽን(infection)፣የእንግዴ ልጅ ከማህፀን ሳይወጣ ሲቀር(retained placenta) ዋነኛዎቹ ሲሆኑ ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች ተጋላጭነትን የሚጨምሩት ምክንያቶች ለምሳሌ በእርግዝና ጊዜ የደም ግፊት፣የደም ማነስ ችግር፣የህፃኑ ክብደት መሆን ከሚገባው በላይ መሆን፣ከአንድ በላይ ፅንስ መፀነስ ይጠቀሳሉ።

እናቶች ምን አይነት ምልክት ሊያሳዩ ይችላሉ?
✓እነዚህ እናቶች በፈሰሰው ደም መጠን ምልክት ሲያሳዩ ከነዚህም መካከል ከመጠን በላይ በብልት የደም መፈሰስ፣የድካም እና የማዞር ስሜት፣ብርድ ብርድ ማለት፣የታችኛው የሆድ አካል ላይ የህመም ስሜት፣የልብ ምት መጨመር፣የሰውነት መገርጣት፣የደም ግፊት መቀነስ፣እራስን መሳት፣የሽንት መጠን መቀነስ

እነዚህን እናቶቻችን እንዴት እናክማቸው?
✓ዋናው እና ትኩረት መስጠት ያለብን መከላከል ላይ ሲሆን ይህንንም ዋንኛው አንድ እናት ጤና ተቋም ሄዳ ነው መውለድ ያለባት ከዛም ልትወልድ ሶስተኛ ደረጃ ምጥ ላይ እያለች ያለው የህክምና ስርአት (Active management of third stage of labor) በብቁ የጤና ባለሙያ መሆን አለበት።
✓እጅግ በጣም ወሳኙ ነገር እያንዳንዱ ሆስፒታል የ PPH protocol ሊኖረው ይገባል።ከዚህ በተጨማሪ ሁሉን ያማከለ ባለሙያ(multidisciplinary team) ሁልጊዜም ዝግጁ ሆነው መቀመጥ አለበት።
✓ከዚያም ይህ ችግር በሚያጋጥምበት ጊዜ እረዳታ በአፋጣኝ መጠየቅ(Shout for help) እንለዋለን።
ወዲያውን የመጀመሪያ እርዳታ ማግኘት ስላለባት ወዲያውኑ እናትዬዋን በጀርባ አሰተኝተን ኦክስጅን ካስፈለጋት መስጠት፣በዚህ ሰአት ሁለት የደም ስር መሰመር ማድረግ(secure bilateral iv line) እና በ protocol መሰረት በቂ የደም ዝውውር እስኪኖራት ድረስ ፈሳሽ እየሰጠን በዚህ መሀል ወዲያውኑ ደም መፍሰሱ መቆም ስላለበት መንስኤውን ለማወቅ መሞከር እና ሚፈሰውን ደም ማቆም ይጠቅብናል።
✓ምክንያቱ ከታወቀ ደም መፍሰሱን በprotocol መሰረት ማከም ለምሳሌ ማህፀን ማሳጅ(uterine massage) ማድረግ፣መድሀኒቶች ለምሳሌ Oxytocine,Tranxemic Acid እንደ አስፈላጊነቱ መስጠት ፣ማህፀን ላይ መጠንኛ ግፊት በማድረግ መጫን(Bimanual compression)፣ሆድ ላይ ያለውን ትልቁን የደም ቧንቧ መጫን(Aortic compression)፣ማህፀንን በቀዶ ጥገና ማውጣት(Hysterectomy)፣የቀረ ወይም ያልወጣ የእንግዴ ልጅ (retained placenta) ካለ ማውጣት፣ኢንፌክሽን ካለ ፀረ ባክቴሪያ መስጠት ዋና የህክምና አካል ናቸው።

እኛ ሀገር ላይ በብዛት የጤና ተቋም በሌለበት ቦታ በተለይ በገጠሪቷ ኢትዮፕያ ላይ ልጅ የሚወለደው በቤት ውስጥ ስለሆነ የህክምና ተቋም ላይ የሚመጡት አማራጭ ሲጠፋ እናብዙ ደም ከፈሰሰ በዃላ ነው።ይህም እነደ ባህል ያልቀረ ነገር ግን የብዙ እናቶቻችን ሂወት አሁንም ድረስ እየቀጠፈ ስለሆነ ባለንበት ቦታ ሁሉም እናቶች የጤና ተቋም መጥተው እንዲወልዱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መሰራት አለበት ብዬ አምናለሁ።
©ሰላም ለናንተ ይሁን!!

Address

Wolaita Sodo, Back Of Stadium(near To Bus Station)
Sodo

Telephone

+251994141248

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr. Ashebir Medium Clinic-AMC, Wolaita Sodo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Dr. Ashebir Medium Clinic-AMC, Wolaita Sodo:

Shortcuts

Share