18/08/2026
የ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠናዊ ስብሰባን ለአገር ገፅታ ግንባታ ከማዋል አንጻር የሚድያ ሚና ከፍተኛ ነዉ
__________
ከነሐሴ 16/2018 ጀምሮ አገራችን የምታስተናግደው የ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠናዊ ስብሰባ (RC76) በማስመልከት ለሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ ተካህዷል።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ስለጉባዔው ግንዛቤ ለመፍጠር እና ለቅድመ ዝግጅቶች የሚደረገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ቋንቋዮች የሚሰሩ ሚዲያዎች አጋጣሚውን እንደ ኮንፈረንስ ቱሪዝም እና መልካም ስም መፍጠሪያ ያሉ ጥቅሞችን ግንዛቤ ውስጥ ባስገባ ሁኔታ መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የጤና ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነት እና ጤና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ በበኩላቸዉ ባስተላለፉት መልዕክት በተለያዩ ግዜያት እንደ ወረርሽኝ ያሉ የጤና ስጋቶችን በተቀናጀ ሁኔታ በመረባረብ ውጤቶችን እንዳስመዘገብነው ሁሉ ለአንድ ሳምንት አካባቢ በሚቆየው ይህ ትልቅ ጉባኤ በጤና ጉዳዮች ዙሪያ ከሚደረሱባቸው መግባባቶች እና ውሳኔዎች በተጨማሪ የአገር ገፅታ የሚገነባበት አጋጣሚ በመሆኑ ሁሉም የሚዲያ አውታሮች እና የሚመለከታቸው አካላት በአገራዊ ስሜት ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በአገራችን የአህጉር እና አለም አቀፍ ጉባኤዎችን በስኬት የማስተናገድ አቅም እና ልምድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተጠቁሟል።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V