Dr.Jibril

Dr.Jibril #ጤና ለሁሉም for All

28/04/2026

ወዳጅ መስሎ ስርቆት!
******
አጭበርባሪዎች የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመርን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የተለያዩ ማጭበርበሪያ ዘዴዎችን ተጠቅመው የመረጃና ገንዘብ ምዝበራ በማካሄድ ላይ ናቸው፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ አጭበርባሪዎች የዋትስአፕ እና ቴሌግራም አካውንቶችን በመጥለፍ ጓደኛ መስለው ስርቆት ይፈፅማሉ፡፡

እነዚህ አጭበርባሪዎች ዋትስአፕ/ቴሌግራሙ በተጠለፈበት ሰው ስም የሆነ አይነት ችግር ውስጥ መሆናቸውን እና በአስቸኳይ ገንዘብ እንደሚፈልጉ ወይም ሌሎች አሳሳች መልእክቶችን በመንገር ገንዘብ እንዲላክላቸው ያደርጋሉ፡፡

በመሆኑም እርሶ በማንኛውም በሚያውቁትም ሆነ በማያውቁት ግለሰብ ስም በተከፈተ የቴሌግራም ወይም ሌላ ማንኛውም የማህበራዊ ትስስር ገፅ የገንዘብ ጥያቄ ሲደርስዎ ጠያቂው በትክክል የርስዎ ወዳጅ መሆናቸውን ስልክ በመደወልም ሆነ በሌላ ዘዴ ከአንደበታቸው ሳያረጋግጡ ገንዘብ እንዳይልኩ እንመክራለን፡፡

እንዴት ከአጭበርባሪዎች ራሳችንን እንጠብቅ?

• ከማህበራዊ ሚዲያ ጓደኛ የሚመጣን የእርዳታ ጥሪ በጥንቃቄ ይፈትሹ።
• ከማያውቁት ግለሰብ የሚደርስዎትን የማኅበራዊ ሚዲያ እንወዳጅ ጥያቄ አይቀበሉ፡፡
• የቅናሽ ማስታወቂያዎችን በጥርጣሬ ይመልከቱ፤
• በኦንላይን ብቻ ለተዋወቁት ግለሰብ ገንዘብ አይላኩ፡፡
• በማኅበራዊ ሚዲያ የግል መረጃዎን አይስጡ።
• የማስታወቂያ አስነጋሪዎችን ህጋዊነት ሳያረጋግጡ ምንም አይነት እርምጃ አይውሰዱ፡፡
• ከማያውቁት አካል በሚደርስዎት አጭር የፅሁፍ መልእክት፣ ኢሜይል ወይም የማኅበራዊ ሚዲያ መልእክት የሚያገኙትን ማስፈንጠሪያ (link) አይክፈቱ፡፡
• ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆችን ይከተሉ፡፡

28/04/2026
27/04/2026

🌍 Dedicated to EV Charging Solutions | Since 2012,⚡ AC Charging Stations | DC Charging Stations | Portable Charging Boxes
🔧 OEM/ODM Customization Support | National High-Tech Enterprise,✅ Smart Charging Technology
✅ 14 Years of R&D and

27/04/2026

ACFAI (Africa Center for Artificial Intelligence) is a non-profit research center committed to leveraging AI to empower communities, promote sustainable development, and alleviate poverty across Africa.

27/04/2026
27/04/2026

የማሊ የመከላከያ ሚኒስትር ተገደሉ!

| የማሊ የመከላከያ ሚኒስትር ሳዲዮ ካማራ በታጠቁ ሀይሎች የተቀናጀ ጥቃት ተገደሉ።

ጄኔራል ሳዲዮ ካማራ በመላ አገሪቱ ባሉ ወታደራዊ ቦታዎች ላይ በተፈፀሙ የተቀናጁ ጥቃቶች መገደላቸውን የመንግስት ቃል አቀባይ አረጋግጠዋል።

ሚኒስትሩ ህይወታቸው ያለፈው የታጠቁ ሀይሎች በቤታቸው ላይ በከፈቱት ጥቃት መሆኑን ቃል አቀባዩ ኢሳ ኦስማን ኩሊባሊ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

በካቲ የጦር ሰፈር የሚገኘው የካማራ መኖሪያ ቤት በእለተ ቅዳሜ በአልቃይዳ እና በቱዋሬግ አማፂያን የጋራ ትብብር በተመሳሳይ ሰዓት ያልጠበቀው ጥቃት እንደተከፈተበት መረጃዎች ጠቁመዋል።

ጄኔራል ሳዲዮ ካማራ በ 2020 እና በ 2021 በተከታታይ በተካሄዱት የማሊ መፈንቅለ መንግስት ውስጥ አልፎ ስልጣን የያዘው የሀገሪቱ ወታደራዊ መንግስት ቁልፍ ሰው ነበሩ።

እንደ አልጀዚራ ዘገባ ሚኒስትሩ በወታደራዊ መንግስት ውስጥ ከፍተኛ ተደማጭነት ያላቸው ሲሆን የወደፊቱ የማሊ መሪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ግምቶች ይሰነዘሩ ነበር።

ካማራ ከሀገሪቱ ጊዜያዊ መሪ አሲሚ ጎይታ ከሚኖሩባት ባማኮ 15 ኪሎ ሜትሮችን ርቀው ጠንካራ ምሽግ ባላት ካቲ ይኖሩ የነበረ ሲሆን ጥቃቱ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ስለመሆኑም ተረጋግጧል።

በሌላ በኩል የካማራ ሁለተኛ ሚስት እና ሁለት የልጅ ልጆቹም በቤቱ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ተገድለዋል ሲል የኤኤፍፒ የዜና ወኪል ዘግቧል።

የአፍሪካ ህብረት፣ የእስልምና ትብብር ድርጅት ዋና ፀሐፊ፣ የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ እና የአውሮፓ ህብረት ጥቃቶቹን አውግዘዋል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

Address

Addis Ababa

Telephone

+251913675596

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr.Jibril posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Dr.Jibril:

Share

Category