Ethio Medical & Heart Health

Ethio Medical & Heart Health Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethio Medical & Heart Health, Medical and health, Addis Ababa.

በዶ/ር ጋሻው ሶለላ (የውስጥ ደዌ ስፔሻሊትና የልብ ህክምና ፌለው)
የጤና መረጃ ማጋራት | ማማከር | ምርመራ| ህክምና

Echocardiography | Resting ECG | Stress ECG | Holter Monitoring | Ambulatory BP Monitoring

📞 0928084444

Telegram: https://t.me/EthioMedHeart or

እጅግ አስደናቂ የህክምና ስኬት! ❤️የ18 ዓመታትን የስቃይ ጉዞ ወደ ተስፋና ደስታ ለቀየረው ለዶ/ር ዳግማዊ ገረመውና ለየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የፕላስቲክና ሪኮንስትራክቲቭ ሰርጀ...
23/08/2026

እጅግ አስደናቂ የህክምና ስኬት! ❤️

የ18 ዓመታትን የስቃይ ጉዞ ወደ ተስፋና ደስታ ለቀየረው ለዶ/ር ዳግማዊ ገረመውና ለየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የፕላስቲክና ሪኮንስትራክቲቭ ሰርጀሪ ቡድን እንኳን ደስ አላችሁ! 👏❤️

❤️ 🏃‍♂️ 10 የቤት ውስጥ   ዓይነቶች (Aerobic Exercises)• ኤሮቢክ ስፖርት ልብን፣ ሳንባንና የደም ዝውውርን በተደጋጋሚ እንቅስቃሴ የሚያሠራ የአካል ልምምድ ነው። በቤት ውስጥ...
22/08/2026

❤️ 🏃‍♂️ 10 የቤት ውስጥ ዓይነቶች (Aerobic Exercises)

• ኤሮቢክ ስፖርት ልብን፣ ሳንባንና የደም ዝውውርን በተደጋጋሚ እንቅስቃሴ የሚያሠራ የአካል ልምምድ ነው። በቤት ውስጥም ያለ ውድ መሣሪያ ሊከናወን ይችላል።

❤️ ዋና ዋና ጥቅሞች

• የልብና የሳንባ ብቃትን ለማሻሻል
• የደም ግፊትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር
• የልብና የደም ሥር ጤናን ለመጠበቅ
• የኢንሱሊን ተግባርንና የደም ስኳርን ለማሻሻል
• ጤናማ የሰውነት ክብደትን ለመጠበቅ
• ጭንቀትንና የዕለት ተዕለት ድካምን ለመቀነስ
• ጥሩ የእንቅልፍ ጊዜ ለማሳለፍ
• አጠቃላይ የአካል ብቃትን ለማሻሻል
• ከጡንቻ ማጠንከሪያ ልምምድ ጋር በመደመር የልብና የሜታቦሊክ ጤናን ለመጠበቅ

📅 የልምምድ ድግግሞሽ

• በሳምንት ቢያንስ 150 ደቂቃ መጠነኛ ጥንካሬ ያለው ኤሮቢክ ልምምድ ወይም 75 ደቂቃ ከፍተኛ ጥንካሬ ያለው ልምምድ ለማድረግ ይሞክሩ።
• ልምምዱን በሳምንቱ ቀናት ላይ ማከፋፈል ይችላሉ።
• ጀማሪዎች በትንሽ ጊዜ በመጀመር ቀስ በቀስ ጊዜውንና ጥንካሬውን ማሳደግ ይችላሉ።
• 10–15 ደቂቃ ብቻ ቢሆንም መጀመር ይቻላል።

🏃‍♂️ 10 የቤት ውስጥ የኤሮቢክ ስፖርት ዓይነቶች

1️⃣ በቦታው መራመድ (Marching in Place)

• ቀጥ ብለው ይቁሙ → አንድ እግር በተራ ወደ ላይ ያንሱ → እጆችዎንም ከእግሮችዎ ጋር ያንቀሳቅሱ → በቀስታ ይጀምሩና ፍጥነቱን ቀስ በቀስ ይጨምሩ።

2️⃣ ስቴፕ-አፕ (Step-ups)

• ጠንካራና የማይንሸራተት ዝቅተኛ መድረክ ይጠቀሙ → አንድ እግር በመድረኩ ላይ ያድርጉ → ሌላውን ያሳድጉ → በቁጥጥር ወደ ታች ይመለሱ።

⚠️ የመውደቅ አደጋ ካለ አይጠቀሙበት።

3️⃣ ዳንሲንግ (Dancing)

• የሚወዱትን ሙዚቃ ይክፈቱ → እጆችንና እግሮችን በተደጋጋሚ ያንቀሳቅሱ → የልብ ምትዎ በመጠኑ እንዲጨምር ያድርጉ።

4️⃣ ጃምፒንግ ጃክስ (Jumping Jacks)

• ቀጥ ብለው ይቁሙ → እግሮችን ወደ ጎን እየዘለሉ እጆችን ወደ ላይ ያንሱ → ወደ መጀመሪያው ቦታ ይመለሱ።

👉 መዝለል ከከበደ አንድ እግርን በተራ ወደ ጎን በማውጣት ዝቅተኛ-ተፅዕኖ (Low-impact) ልምምድ ያድርጉ።

5️⃣ ከፍተኛ ጉልበት መራመድ (High-Knee March)

• አንድ ጉልበት ወደ ወገብ አቅጣጫ ያንሱ → ወደ ታች ያውርዱ → ሌላውን በተራ ያንሱ → እጆችንም ከእግሮች ጋር ያንቀሳቅሱ።

6️⃣ ደረጃ መውጣት (Stair Climbing)

• በቀስታ ይጀምሩ → በተረጋጋ ሁኔታ ይውጡ → በጥንቃቄ ይመለሱ → በአቅምዎ መጠን ይድገሙ።

⚠️ የመውደቅ አደጋ ካለ አይጠቀሙበት።

7️⃣ ቦታ ላይ መሮጥ (Jogging in Place)

• በቀስታ መሮጥ ይጀምሩ → እጆችን በተፈጥሮ ያንቀሳቅሱ → አቅምዎ እስከሚፈቅድ ድረስ ጥንካሬውን ቀስ በቀስ ይጨምሩ።

8️⃣ ወደ ጎን መራመድ (Side-to-Side Steps)

• ቀኝ እግርን ወደ ጎን ያድርጉ → ግራውን ይከተል → ከዚያ ወደ ሌላው ጎን ይድገሙ → እጆችዎንም ያንቀሳቅሱ።

9️⃣ የኋላ ተረከዝ ማንሳት (Butt Kicks)

• በቦታው ይቁሙ → አንድ ተረከዝ ወደ ዳሌዎ አቅጣጫ ያንሱ → ወደ ታች ያውርዱ → ሌላውን በተራ ያንሱ።

🔟 ሻዶው ቦክሲንግ (Shadow Boxing)

• ቀጥ ብለው ይቁሙ → እጆችዎን ከፊት በቁጥጥር ይዘርጉ → በተራ ወደ ፊት ይምቱ → እግሮችንም በቀስታ ያንቀሳቅሱ።

💡 የልምምድ ጥንካሬን እንዴት እንለይ?

🟢 መጠነኛ ጥንካሬ (Moderate intensity)፦ በልምምድ ጊዜ መናገር ይችላሉ፣ ግን መዘመር ይከብዳል።

🔴 ከፍተኛ ጥንካሬ (Vigorous intensity)፦ ጥቂት ቃላት ብቻ መናገር ይችላሉ፤ መደበኛ ውይይት ይከብዳል።

👉 ጠቃሚ ምክር

• ከልምምድ በፊት 5–10 ደቂቃ ቀላል ማማሞቂያ (Warm-up) ያድርጉ።
• ከልምምድ በኋላ ፍጥነቱን ቀስ በቀስ በመቀነስ ሰውነትዎን ያሳርፉ።
• በተለይ በሙቀት ወቅት በቂ ውሃ ይጠጡ።
• ከጡንቻ ማጠንከሪያ ልምምድ ጋር ያጣምሩ።
• ጀማሪዎች በቀላል ልምምድ ይጀምሩና ጊዜውንና ጥንካሬውን ቀስ በቀስ ያሳድጉ።

⚠️ በልምምድ ወቅት የደረት ህመም፣ ከባድ የመተንፈስ ችግር፣ ማዞር፣ መሳት ወይም ሌላ ከባድ ምልክት ከተከሰተ ልምምዱን ያቁሙና የሕክምና ምክር ይፈልጉ።

❤️ በየቀኑ ትንሽ እንቅስቃሴ ከምንም እንቅስቃሴ ይሻላል። በመደበኛነት የሚደረግ ኤሮቢክ ልምምድ ለልብ፣ ለሳንባ፣ ለሜታቦሊክ ጤናና ለአጠቃላይ የአካል ብቃት ትልቅ ጥቅም አለው።

በዶ/ር ጋሻው ሶለላ (የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት፣ የማህበረሰብ ጤና ባለሙያና የልብ ህክምና ፌለው)

📱 Telegram:
📘 Facebook: Ethio Medical & Heart Health
📞 0928084444
💬 Telegram Consultation:

#የኤሮቢክስፖርት #የልብጤና #የአካልብቃት #የሜታቦሊክጤና

💪 🏋️‍♂️ 7 የቤት ውስጥ   የስፖርት ዓይነቶች (Resistance Exercises)• የጡንቻ ማጠንከሪያ ስፖርት ጡንቻዎችን ከተቃውሞ ጋር በማሰራት ጥንካሬያቸውንና ብቃታቸውን ለማሻሻል የሚ...
21/08/2026

💪 🏋️‍♂️ 7 የቤት ውስጥ የስፖርት ዓይነቶች (Resistance Exercises)

• የጡንቻ ማጠንከሪያ ስፖርት ጡንቻዎችን ከተቃውሞ ጋር በማሰራት ጥንካሬያቸውንና ብቃታቸውን ለማሻሻል የሚደረግ ልምምድ ነው። በቤት ውስጥም ያለ ውድ መሣሪያ ሊከናወን ይችላል።

💪 ዋና ዋና ጥቅሞች

• የጡንቻ ጥንካሬንና መጠንን ለመገንባትና ለመጠበቅ
• የአጥንት ጤናን ለመደገፍ
• የኢንሱሊን ተግባርን ለማሻሻልና የደም ስኳርን ለመቆጣጠር
• ጤናማ የሰውነት ክብደትንና የሰውነት አቀማመጥን ለመጠበቅ
• ሚዛንን፣ እንቅስቃሴንና የዕለት ተዕለት አካላዊ ብቃትን ለማሻሻል
• በእድሜ መጨመር የሚከሰተውን የጡንቻ መቀነስ ለመቀነስ
• ከኤሮቢክ ስፖርት ጋር በመደመር የልብና የሜታቦሊክ ጤናን ለመጠበቅ

📅 የልምምድ ድግግሞሽ

• በሳምንት ከ2 እስከ 3 ጊዜ ማድረግ ይቻላል።
• ተመሳሳይ የጡንቻ ቡድኖችን በሚያሠሩ ልምምዶች መካከል ቢያንስ 1 ቀን የእረፍት ጊዜ ይስጡ።
• ጀማሪዎች ከ1 እስከ 2 ዙር በመጀመር ቀስ በቀስ ወደ ከ2 እስከ 3 ዙር ማሳደግ ይችላሉ።
• በእያንዳንዱ ዙር ከ8 እስከ 15 ድግግሞሽ ማድረግ ይቻላል።
• አቅምዎ ሲሻሻል የድግግሞሽ፣ የክብደት ወይም የልምምዱን አስቸጋሪነት ቀስ በቀስ ይጨምሩ።

🏋️ 7 የቤት ውስጥ የጡንቻ ማጠንከሪያ የስፖርት ዓይነቶች

1️⃣ ስኳት (Squats) — የታፋና የዳሌ ጡንቻዎች

• እግሮችን በትከሻ ስፋት ያቁሙ → ወንበር ላይ ለመቀመጥ እንደሚያደርጉት በቀስታ ይውረዱ → ደረትዎን ቀና ያድርጉ → በእግርዎ በመግፋት ይነሱ።

2️⃣ ስፕሊት ስኳት/ላንጅ (Split Squats/Lunges) — የታፋና የዳሌ ጡንቻዎች

• አንድ እግር ወደ ኋላ ያድርጉ → በቁጥጥር ወደ ታች ይውረዱ → የፊት ጉልበት ከእግሩ አቅጣጫ ጋር እንዲሰለፍ ያድርጉ → ወደ ላይ ይመለሱ።

3️⃣ የዳሌ ማንሳት (Glute Bridge) — የዳሌና የታፋ ጀርባ ጡንቻዎች

• በጀርባዎ ይተኙ → ጉልበቶችዎን ይጠፉ → የዳሌ ጡንቻን በማጥበቅ ዳሌዎን ያንሱ → ለጥቂት ሰከንዶች ይቆዩ → በቀስታ ያውርዱ።

4️⃣ የጀርባ መሳብ (Rows) — የጀርባ ጡንቻዎች

• ቦርሳ ወይም የመቋቋም ባንድ ይጠቀሙ → ጀርባዎን ቀጥ አድርገው ወደ ፊት ትንሽ ያጎንብሱ → ክርኖችን ወደ ኋላ ይሳቡ → የጀርባ ጡንቻዎችን ያጥብቁ።

5️⃣ ፑሽ-አፕ (Push-ups) — ደረት፣ ትከሻና ክንድ

• እጆችን በትከሻ ስፋት ያስቀምጡ → ሰውነትን ቀጥ ያድርጉ → ደረትን ወደ መሬት ያውርዱ → ወደ ላይ ይግፉ። ከባድ ከሆነ በጉልበት ወይም በከፍተኛ መደገፊያ ላይ በመደገፍ ማድረግ ይቻላል።

6️⃣ የላይኛው ግፊት (Overhead Press) — የትከሻ ጡንቻዎች

• ቀላል ዳምቤል ወይም ተስማሚ ክብደት ይያዙ → ከትከሻ ደረጃ ወደ ላይ ይግፉ → ሆድዎን አጥብቀው ይያዙ → በቁጥጥር ወደ ታች ያውርዱ።

7️⃣ የእግር ባት ማንሳት (Calf Raises) — የእግር ባት ጡንቻዎች

• ቀጥ ብለው ይቁሙ → ተረከዝዎን ያንሱ → የእግር ባት ጡንቻዎን ያጥብቁ → ለጥቂት ሰከንዶች ይቆዩ → በቀስታ ወደ ታች ያውርዱ።

👉 ጠቃሚ ምክር

• ትክክለኛ አቀማመጥና ቁጥጥር ያለው እንቅስቃሴ ይጠቀሙ። ከቻሉ ይህንን ልምምድ ከመደበኛ መራመድ፣ ከኤሮቢክ ልምምድ፣ በቂ ፕሮቲን፣ በቂ እንቅልፍና ሚዛናዊ ምግብ ጋር ያጣምሩ።

⚠️ በልምምድ ወቅት የደረት ህመም፣ ከባድ የመተንፈስ ችግር፣ ማዞር ወይም ሌላ ከባድ ምልክት ከተከሰተ ልምምዱን ያቁሙና የሕክምና ምክር ይፈልጉ።

በትንሽ ጊዜ የሚደረግ መደበኛ ልምምድ ለጡንቻ፣ ለአጥንት፣ ለልብና ለሜታቦሊክ ጤና ትልቅ ጥቅም አለው።

በዶ/ር ጋሻው ሶለላ
የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት፣ የማህበረሰብ ጤና ባለሙያና የልብ ህክምና ፌለው

📱 Telegram:
📘 Facebook: Ethio Medical & Heart Health
📞 0928084444
💬 Telegram Consultation:

#የጡንቻማጠንከሪያ #የጡንቻጥንካሬ #የሜታቦሊክጤና #የልብጤና

❤️   (Valvular Heart Disease)ለታካሚዎችና ለቤተሰቦቻቸው የመረጃ መመሪያይህ መመሪያ በአውሮፓ የልብ ማህበር የልብ ቫልቭ በሽታ መመሪያዎች ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ የቫልቭ በሽታ...
19/08/2026

❤️ (Valvular Heart Disease)

ለታካሚዎችና ለቤተሰቦቻቸው የመረጃ መመሪያ

ይህ መመሪያ በአውሮፓ የልብ ማህበር የልብ ቫልቭ በሽታ መመሪያዎች ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ የቫልቭ በሽታን ምርመራ፣ ክትትልና ሕክምና ለመረዳት ያግዛል።

የልብ ቫልቭ በሽታ ምንድነው?

ልብ አራት ቫልቮች አሉት፦

- አኦርቲክ (Aortic)
- ሚትራል (Mitral)
- ትራይከስፒድ (Tricuspid)
- ፑልሞናሪ (Pulmonary)

ቫልቭ በትክክል መክፈት ወይም መዝጋት ካልቻለ የልብ ቫልቭ በሽታ ይባላል። ይህም የደም ፍሰትን ሊያስተጓጉል ይችላል።

ምልክቶችና ምክንያቶች

የምልክቶቹ መጠን በተጎዳው ቫልቭና በበሽታው ክብደት ይወሰናል። አንዳንድ ሰዎች ከባድ የቫልቭ በሽታ ቢኖራቸውም ምልክት ላይኖራቸው ይችላል።

የተለመዱ ምልክቶች

- ድካም ወይም የመንቀሳቀስ አቅም መቀነስ
- የትንፋሽ ማጠር
- ማዞር ወይም ራስ መሳት
- የእግር/የቁርጭምጭሚት እብጠት
- ፈጣን ወይም የተዛባ የልብ ምት

የተለመዱ ምክንያቶች

- የሩማቲክ ትኩሳት/የሩማቲክ የልብ በሽታ (Rheumatic heart disease)
- ከእድሜ ጋር የሚመጣ የቫልቭ ለውጥ (Degenerative valvular heart disease)
- ከተወለዱ ጀምሮ ያለ የቫልቭ ችግር (Congenital valve disease)
- የልብ ውስጣዊ ኢንፌክሽን (Infective endocarditis)
- የልብ ጡንቻ በሽታ (Cardiomyopathy)
- የቀደመ የደረት አካባቢ የጨረር ህክምና (Prior radiotherapy)
- አንዳንድ የካንሰር ኪሞቴራፒ መድሃኒቶች (Chemotherapy)

• ሃኪም በማዳመጫ መሳሪያ የሚሰማው ያልተለመደ የልብ ውስጥ ድምፅ (heart murmur) አልፎ አልፎ የቫልቭ በሽታ የመጀመሪያ ምልክት ሊሆን ይችላል።

የምርመራ ዓይነቶች

- የልብ በሽታ ምልክቶችን መፈለግ
- ልብ ውስጥ ያልተለመደ ድምፅ መፈለግ እና ሌሎች ልብ ነክ ምርመራዎች
- የሳንባ ምርመራ
- እንደ አስፈላጊነቱ BNP/NT-proBNP እና troponin የተባሉ የልብ በሽታ ጠቋሚ ምርመራዎች

❤️ የልብ ምስል ምርመራዎች

1) የልብ አልትራሳውንድ (Echocardiography)፦ ለአብዛኛው የቫልቭ በሽታ የመጀመሪያ ምርመራ ነው።

• የሚያሳየው፦

- የቫልቭ አወቃቀርና አሠራር
- የቫልቭ ችግር ክብደት
- የልብ ክፍሎች መጠን
- የልብ የመጭመቅ አቅም
- የሳንባ የደም ግፊት
- በክትትል የሚታይ የበሽታ ለውጥ

2) የልብ ሲቲ ስካን (Cardiac CT)፦ በዋነኛነት የቫልቭ አወቃቀርና የካልሲየም ክምችት ለማየት፣ የትልቁ ደም ወሳጅ ደም ስርን (አኦርታ) ለመገምገም እና አንዳንድ በካቴተር የሚሰጡ ሕክምናዎችን ለማቀድ ይረዳል።

3) የልብ ኤም አር አይ MRI (CMR)፦ የልብን አወቃቀር፣ የመጭመቅ አቅም፣ የልብ ጡንቻና የክፍሎች መጠን በዝርዝር ለመገምገም ይረዳል።

4) የልብ ካቴተር፦ በተመረጡ ታካሚዎች በልብ ውስጥ ያለውን ግፊት ለመለካት፣ የልብ ውስጥ የደም ፍሰት ሁኔታ ለመገምገም፣ የልብ ቧንቧዎችን ለመመርመር እና ሌሎች ምርመራዎች በቂ ካልሆኑ የበሽታውን ክብደት ለማረጋገጥ ይረዳል።

💊 የሕክምና አማራጮች

• ሕክምናው በቫልቭ በሽታ ዓይነትና ክብደት፣ ምልክቶች፣ የልብ አሠራር፣ የልብ ክፍሎች ላይ ያለው ተፅዕኖ፣ እድሜና አጠቃላይ ጤና፣ የሕክምና አደጋ እና በታካሚው ምርጫ ይወሰናል።
• ቀላል ወይም የተረጋጋ በሽታ ያላቸው ታካሚዎች በመደበኛ ክትትል ብቻ ሊታዩ ይችላሉ።
• ሌሎች ግን የቫልቭ ጥገና ወይም መተካት ሊያስፈልጋቸው ይችላል።

የቫልቭ ቀዶ ጥገና

- ዘላቂ ውጤት ሊሰጥ ይችላል
- የልብና የሳንባ ስራን የሚተካ ሰው ሰራሽ ማሽን ሊያስፈልገው ይችላል።
- ከአንዳንድ በካቴተር ከሚሰጡ የህክምናዎች የበለጠ የሆስፒታል ቆይታና ማገገሚያ ሊኖረው ይችላል።

በካቴተር የሚሰጥ ሕክምና

• ቀጭን ካቴተር በደም ሥር (ብዙ ጊዜ በብሽሽት አካባቢ) በመጠቀም የቫልቭ ሕክምና ሊደረግ ይችላል። በዚህ የህክምና ዓይነት የልብና ሳንባ ተፈጥሯዊ ስራ ሳይቋረጥ የሚሰራ ሲሆን ፈጥኖ ለማገገም የተሻለ አማራጭ ነው።
• ከፍተኛ የቀዶ ጥገና አደጋ ላለባቸው ታካሚዎች ጥሩ አማራጭ ነው።
• ነገር ግን የቫልቭ አወቃቀር፣ እድሜ፣ ሌሎች በሽታዎችና የሂደቱ አደጋ ተገቢነቱን ይወስናሉ።

🔧 የቫልቭ ጥገና (Valve repair)

• የቫልቭ ጥገና የታካሚውን የራሱን ቫልቭ በመጠበቅ ችግሩን ለማስተካከል ይረዳል።
• ሊያካትት የሚችለው፦
- የቫልቭ አወቃቀርን መጠገን
- ያልተለመደ የቫልቭ ክፍልን ማስተካከል/ማስወገድ
- የቫልቭ ደጋፊ ክፍሎችን መጠገን
- የተመረጡ በካቴተር የሚሰጡ ህክምናዎች
• ተገቢና ዘላቂ ጥገና ሊደረግ በሚችልበት ሁኔታ ጥገና ለአንዳንድ የቫልቭ በሽታዎች ተመራጭ ሊሆን ይችላል።

🔄 የቫልቭ ቅየራ

• የተጎዳ ቫልቭ በብረት ነክ (Mechanical) ወይም ስጋ መሰል (Biological) ቫልቭ ሊቀየር ይችላል።

• Mechanical valve
- ጥቅሙ፦ ለረጅም ጊዜ ይቆያል።
- አስፈላጊ ነጥብ፦ የቫልቭ የደም መርጋትን ለመከላከል ዕድሜ ልክ የሚዋጥ የደም ማቅጠኛ መድሃኒት (Vitamin K antagonist anticoagulation or warfarin) ያስፈልጋል።

• Biological valve

ጥቅሙ፦
- በቫልቩ ምክንያት ብቻ የዕድሜ ልክ የደም ማቅጠኛ (anticoagulation) ብዙ ጊዜ አያስፈልግም።
- አስፈላጊ ነጥብ፦ ከጊዜ በኋላ የቫልቩ ጥንካሬ ሊቀንስ ይችላል፤ ወደፊት እንደገና ሕክምና ሊያስፈልግ ይችላል።

💊 መድሃኒትና የአኗኗር ለውጥ

• መድሃኒቶች የቫልቭን መዋቅራዊ ችግር በአብዛኛው ማስተካከል አይችሉም፣ ነገር ግን፦

- ምልክቶችን ለመቀነስ
- የልብ ድካምን ለማከም
- የደም ግፊትን ለመቆጣጠር
- የልብ ምት መዛባትን ለመቆጣጠር
- አስፈላጊ ሲሆን የደም መርጋትን ለመከላከል
- የልብ ሕመም መዘዞችን ለመከላከል ሊጠቅሙ ይችላሉ።

• ጤናማ የአኗኗር ዘይቤዎች

- ጤናማ ክብደት መጠበቅ
- ሲጋራ ማጨስን ማቆም
- በሐኪም ምክር መሰረት አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ
- ጤናማ አመጋገብ መከተል
- የደም ግፊት፣ ስኳርና ኮሌስትሮል መጠንን መቆጣጠር
- የታዘዙ መድሃኒቶችን በትክክል መውሰድ
- የሕክምና ክትትልን አለማቋረጥ

❤️   (Rheumatic Heart Disease)❓ የሪዩማቲክ ልብ በሽታ ምንድነው?• የሪዩማቲክ ልብ በሽታ ከሪዩማቲክ ትኩሳት በኋላ የልብ ቫልቮች በመጎዳታቸው የሚከሰት የልብ በሽታ ነው።• ...
16/08/2026

❤️ (Rheumatic Heart Disease)

❓ የሪዩማቲክ ልብ በሽታ ምንድነው?

• የሪዩማቲክ ልብ በሽታ ከሪዩማቲክ ትኩሳት በኋላ የልብ ቫልቮች በመጎዳታቸው የሚከሰት የልብ በሽታ ነው።

• ብዙ ጊዜ ሂደቱ የሚጀምረው በባክቴሪያ (Group A Streptococcus) በሚመጣ የጉሮሮ ወይም የቶንሲል ኢንፌክሽን (Bacterial Tonsillopharyngitis) ሲሆን፣ አንዳንድ ሰዎች ላይ ይህ ኢንፌክሽን ሪዩማቲክ ትኩሳትን ሊያስከትል ይችላል። ይህም በሂደት የልብ ቫልቮችን በቋሚነት ሊጎዳ ይችላል።

🫀 የሚከተለውን ሂደት ልብ ይበሉ!

በባክቴሪያ የሚመጣ የጉሮሮ ወይም የቶንሲል ኢንፌክሽን → ሪዩማቲክ ትኩሳት → የልብ ቫልቭ ጉዳት → የሪዩማቲክ ልብ በሽታ

⚠️ ምልክቶቹ ምንድናቸው?

አንዳንድ ታካሚዎች በመጀመሪያ ምንም ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ። በኋላ ግን የሚከተሉት ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ፦

- የትንፋሽ ማጠር
- በቀላሉ መድከም
- የእግር/የእግር ጫማ እብጠት
- የልብ ምት መፍጠን ወይም መዛባት
- የደረት ምቾት ማጣት

በሪዩማቲክ ትኩሳት ወቅት ትኩሳት፣ ከአንድ መገጣጠሚያ ወደ ሌላ የሚዘዋወር የመገጣጠሚያ ሕመም/እብጠት እና ሌሎች ምልክቶች ሊኖሩ ይችላሉ።

🩺 እንዴት ይታወቃል?

• Echocardiography (የልብ አልትራሳውንድ) የልብ ቫልቭ ጉዳትን ለማወቅ ዋና የምርመራ ዘዴ ነው። እንደሁኔታው ሌሎች ምርመራዎችም ሊያስፈልጉ ይችላሉ።

🛡️ የሪዩማቲክ ልብ በሽታን እንዴት መከላከል ይቻላል?

1. 🗣️ የጉሮሮ ወይም የቶንሲል ኢንፌክሽን ምልክቶችን ችላ አለማለት

• በተለይ በልጆችና በወጣቶች የጉሮሮ ሕመም ከትኩሳት ጋር ከተከሰተ ቶሎ የጤና ባለሙያ ማማከር ያስፈልጋል።

• በባክቴሪያ (ስትሬፕቶኮከስ) የሚመጣን ኢንፌክሽን በተገቢው ጊዜ መለየትና ተገቢውን ሕክምና ማግኘት ሪዩማቲክ ትኩሳትን ለመከላከል ይረዳል።

2. 💉 የፔኒሲሊን መከላከያ ሕክምናን አለማቋረጥ

• ሪዩማቲክ ትኩሳት ካጋጠመ የጤና ባለሙያ Benzathine Penicillin G የሚባል የሚወጋ መድሃኒት ሊያዝዝ ይችላል። ይህ ሕክምና ሪዩማቲክ ትኩሳት እንዳይደገምና ተጨማሪ የልብ ቫልቭ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል ይረዳል። ስለሆነም ጤናማ ስሜት ቢሰማም መድኃኒቱን ሳያቋርጡ መውሰድ በጥብቅ ይመከራል።

3. 🩺 የሐኪም ክትትልን መቀጠል

• በመደበኛነት የሐኪም/የልብ ሐኪም ክትትል ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው። የልብ አልትራሳውንድ (Echocardiography) እና ሌሎች ምርመራዎች እንደሁኔታው ሊያስፈልጉ ይችላሉ።

4. 💊 መድኃኒቶችን በትክክል መውሰድ

• የታዘዙ መድኃኒቶችን በትክክል መውሰድ ይገባል። ያለ ሐኪም ምክር መድኃኒት ማቋረጥ ወይም መጠን መቀየር አይመከርም።

🤰 ለሴቶች አስፈላጊ መረጃ

• የሪዩማቲክ ልብ በሽታ ያለባት ሴት እርግዝናን ከማቀዷ በፊት ከሐኪም ጋር መማከር አለባት። ከባድ የቫልቭ ችግር ካለ እርግዝና ተጨማሪ አደጋ ሊያመጣ ስለሚችል ልዩ ቅድመ ክትትል ያስፈልጋል።

🚨 አስቸኳይ ሕክምና የሚያስፈልገው መቼ ነው?

• ከሚከተሉት አንዱ ከተከሰተ አስቸኳይ የጤና እርዳታ ያስፈልጋል፦

- ከባድ ወይም በፍጥነት የሚባባስ የትንፋሽ ማጠር
- የደረት ሕመም
- ራስ መሳት
- በጣም ፈጣን ወይም የተዛባ የልብ ምት
- በፍጥነት የሚጨምር እብጠት
- ድንገተኛ የፊት/የእጅ ድካም ወይም የንግግር ችግር

❤️ ዋና ዋና መልዕክቶች

• የሪዩማቲክ ትኩሳትን መከላከል ልብዎን ከተጨማሪ የቫልቭ ጉዳት መጠበቅ ነው። ስለሆነም፦
💉 የፔኒሲሊን መድሃኒትዎን በጊዜው ይውሰዱ ወይም ይወጉ።
🩺 የሐኪም ክትትልዎን አያቋርጡ።
💊 የታዘዙልዎትን መድኃኒቶች በትክክል ይውሰዱ።

❤️ ትክክለኛ የጤና መረጃ በማግኘት የልብዎን ጤና ይጠብቁ! ለሌሎችም ያጋሩ!

በዶ/ር ጋሻው ሶለላ (የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት፣ የማህበረሰብ ጤና ባለሙያና የልብ ህክምና ፌለው)

Telegram: https://t.me/EthioMedHeart⁠

Facebook: https://www.facebook.com/EthioMedHeart

📞 0928084444

በቴሌግራም ለማማከር:

#የሪዩማቲክልብበሽታ #የሪዩማቲክትኩሳት #የቶንሲልኢንፌክሽን #የጉሮሮኢንፌክሽን

16/08/2026

የምግብ አለመንሸራሸር (Dyspepsia)

የምግብ አለመንሸራሸር ወይም በሕክምናው መጠሪያው ዲስፔፕሲያ (Dyspepsia) የሚባለው የጤና እክል፣ በዕለት ተዕለት የምግብ መፍጨት ሂደት ላይ የሚፈጠር መስተጓጎል ነው። ይህ የምግብ መፍጫ ችግር አብዛኛውን ጊዜ ከምግብ በኋላ በሆድ የላይኛው ክፍል ላይ የሚሰማ የቃጠሎ፣ የክብደት፣ የቁርጠት ወይም ያለጊዜው የመጥገብ ስሜትን ያጠቃልላል።
ከእነዚህም በተጨማሪ የሆድ መነፋት፣ የጋዝ መብዛት እና የማቅለሽለሽ ስሜት የዲስፔፕሲያ ዋነኛ መገለጫዎች ናቸው። ዲስፔፕሲያ ራሱን የቻለ በሽታ ሳይሆን፣ በምግብ አመጋገብ ዘይቤያችን ወይም በምግብ መፍጫ ሥርዓታችን ውስጥ ያለ የጤና እክል የሚያሳይ ምልክት ሊሆን ይችላል።
የምግብ አለመንሸራሸር መንስኤዎች
ለዚህ ችግር መከሰት በርካታ መንስኤዎች የሚጠቀሱ ሲሆን፣ ዋነኞቹ ከዕለት ተዕለት የአኗኗር ዘይቤያችን ጋር የተያያዙ ናቸው። ምግቦችን በጣም በፍጥነትና ሳያኝኩ መዋጥ፣ ቅባትና ቅመም የበዛባቸውን ምግቦች በብዛት መመገብ፣ እንዲሁም ካፌይንና የአልኮል መጠጦችን ማዘውተር ለችግሩ መባባስ ትልቅ አስተዋፅዖ አላቸው።
ከዚህም ባለፈ የአእምሮ ጭንቀት፣ በቂ እረፍት ማጣት እና ሲጋራ ማጨስ የጨጓራን መደበኛ ሥራ ያውካሉ። በአንዳንድ ሁኔታዎች ግን የምግብ አለመንሸራሸር ስሜት እንደ የጨጓራ ቁስለት (Ulcer)፣ የሐሞት ከረጢት እብጠት ወይም የአሲድ መመለስ (Acid Reflux/GERD) ያሉ የሕክምና እክሎች ምልክት ሊሆን ይችላል።
የምግብ አለመንሸራሸርን እንዴት መከላከል ይቻላል?
ይህን የጤና እክል ለመከላከልና ለመቀነስ በመጀመሪያ ደረጃ የአመጋገብ ሥርዓትን ማስተካከል ተገቢ ነው። ምግቦችን ቀስ እያሉ በደንብ አኝኮ መመገብ፣ በፋይበርና በቪታሚን የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር እና በየቀኑ በቂ ውሃ መጠጣት የምግብ መፍጫ ሥርዓታችንን ያግዛሉ።
እንዲሁም ምግብ እንደተመገቡ ወዲያውኑ ከመተኛት መቆጠብና ቅመም የበዛባቸውን ምግቦች መቀነስ ተገቢ ነው።
ሆኖም ግን፣ የምግብ አለመንሸራሸር ስሜቱ ከአንድ ሳምንት በላይ ከቆየ፣ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የክብደት መቀነስ ካጋጠመ፣ ወይም የማያቋርጥ ትውከት ካለብዎት፣ ችግሩን በቤት ውስጥ ለማከም ከመሞከር ይልቅ የሕክምና ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል።
በመቅረዝ ጠቅላላ ሆስፒታል በዘርፉ የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸውን የጨጓራና አንጀት ስፔሻሊስት (Gastroenterologist) ሐኪሞች እና ዘመናዊ የምርመራ መሣሪያዎችን በማዘጋጀት የተሟላና አስተማማኝ የጨጓራና አንጀት ሕክምና ለመስጠት ዝግጁ ነው።
ስለሆነም የማያቋርጥ የሆድ መነፋት፣ የምግብ አለመንሸራሸር ወይም ሌሎች የጨጓራ ችግሮች እየረበሹዎት ከሆነ፣ ዛሬውኑ ወደ ሆስፒታላችን በመምጣት ተገቢውን የሕክምና ምክርና ምርመራ ያግኙ።

6 Ways to Prevent Type 2 Diabetes Diabetes happens when your blood sugar stays too high over time. There are several typ...
05/08/2026

6 Ways to Prevent Type 2 Diabetes

Diabetes happens when your blood sugar stays too high over time. There are several types, but the main forms are Type 1 and Type 2.

Type 1 diabetes is an autoimmune disease and generally isn’t preventable. Type 2 diabetes happens when your body can’t use insulin properly. This is called insulin resistance. You can help limit this resistance with lifestyle changes.

While fiber is well known as being extremely good for your gut and digestive health, it does far more than that for your...
30/07/2026

While fiber is well known as being extremely good for your gut and digestive health, it does far more than that for your body. Eating enough fiber can also:

🟢Lower your risk of diseases, including several types of cancer
🟢Boost heart health
🟢Help maintain healthy cholesterol levels
🟢Keep you feeling fuller longer to control appetite
🟢Support energy levels during the day
🟢Balance blood sugar levels

Source: Cleveland Clinic

23/07/2026

ሪዩማቲክ የልብ ሕመም (RHD)፡ ከቀላል የጉሮሮ ሕመም የሚጀምር ከባድ የልብ በሽታ

ብዙዎቻችን የልብ ሕመም የሚከሰተው በዕድሜ መግፋት ወይም በአኗኗር ዘይቤ ብቻ እንደሆነ እናስባለን። ነገር ግን በኢትዮጵያና በብዙ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ አገሮች፣ በሕፃናትና በወጣቶች ላይ ለሚከሰቱ ከባድ የልብ ጉዳቶች ዋነኛ ምክንያቶች መካከል አንዱ ሪዩማቲክ የልብ ሕመም (Rheumatic Heart Disease - RHD) ነው።

መልካሙ ዜና ግን ይህ በሽታ በአብዛኛው በጊዜው በሚደረግ ምርመራ፣ ትክክለኛ ሕክምና እና ተገቢ መከላከያ ሙሉ በሙሉ ሊከላከሉት የሚቻል መሆኑ ነው።

በሽታው እንዴት ይከሰታል?
1. የጉሮሮ ኢንፌክሽን (Strep Throat)
ሕፃናትና ወጣቶች በGroup A Streptococcus ባክቴሪያ ምክንያት የጉሮሮ ወይም የቶንሲል ኢንፌክሽን ሊይዛቸው ይችላል።
2. ሪዩማቲክ ትኩሳት (Rheumatic Fever)
ይህ ኢንፌክሽን በጊዜው እና በትክክል በፀረ-ባክቴሪያ መድሀኒት ካልታከመ፣ የሰውነት የበሽታ መከላከል ስርዓት ተሳስቶ የራሱን መገጣጠሚያዎች፣ ልብ እና ሌሎች አካላት ማጥቃት ሊጀምር ይችላል።
3. ሪዩማቲክ የልብ ሕመም (RHD)
ሪዩማቲክ ትኩሳት በልብ ቫልቮች ላይ ቋሚ ጉዳትና ጠባሳ ያስከትላል። ይህም ደም በትክክል እንዳይፈስ በማድረግ ለልብ ድካም፣ ለልብ ምት መዛባት እና ለሌሎች ከባድ የልብ ችግሮች ሊያጋልጥ ይችላል።
ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
በሪዩማቲክ ትኩሳት ወቅት
• ከፍተኛ ትኩሳት
• ከአንድ መገጣጠሚያ ወደ ሌላ የሚዘዋወር እብጠትና ህመም
• ድካም
• አንዳንድ ጊዜ የቆዳ ሽፍታ ወይም ያልተፈለገ የሰውነት እንቅስቃሴ
የልብ ቫልቭ ሲጎዳ (RHD)
• በቀላሉ መድከም
• በእንቅስቃሴ ወቅት ወይም ሲተኙ የትንፋሽ ማጠር
• የልብ ምት መፍጠን ወይም መዛባት
• የደረት ህመም
• የእግር፣ የቁርጭምጭሚት ወይም የሆድ እብጠት
እንዴት መከላከል ይቻላል?
✔️ የጉሮሮ ሕመምን እንደ ቀላል ችግር አለመቁጠር።
✔️ የጉሮሮ ኢንፌክሽን ሲኖር በቶሎ ወደ ጤና ተቋም መሄድ።
✔️ ሐኪም የሚያዝዘውን ፀረ-ባክቴሪያ መድሀኒት በተወሰነው ጊዜና መጠን ሙሉ በሙሉ መውሰድ።
✔️ ሪዩማቲክ ትኩሳት ካጋጠመ በኋላ ሐኪም የሚመክረውን የረጅም ጊዜ መከላከያ ሕክምና በትክክል መከተል።
ያስታውሱ!
ሪዩማቲክ የልብ ሕመም ብዙ ጊዜ ከቀላል የጉሮሮ ኢንፌክሽን ይጀምራል። የጉሮሮ ኢንፌክሽንን በጊዜው መመርመርና በትክክል መታከም የልጆቻችንንና የወጣቶቻችንን ልብ ከዘላቂ ጉዳት ሊጠብቅ ይችላል።
የጉሮሮ ሕመምን በጊዜው ማከም የወደፊቱን የልብ ጤና መጠበቅ ነው።

📞 ለበለጠ መረጃ ወይም ቀጠሮ ለማስያዝ፦
በ 6757 ፣ በ 0921636465 ወይም በ 0952272727 ላይ ይደውሉ።
መቅረዝ ጠቅላላ ሆስፒታል
የጥራት ፈርጥ!!

☕ #ካፌይን   ላይ ያለው ተፅእኖ: የ2026 የአሜሪካ የልብ ማህበር (AHA) ሳይንሳዊ መግለጫ☕ መጠነኛ የካፌይን አጠቃቀም (በቀን እስከ 400 ሚ.ግ፣ በግምት ከ3 እስከ 5 ኩባያ ቡና) ለ...
20/07/2026

☕ #ካፌይን ላይ ያለው ተፅእኖ: የ2026 የአሜሪካ የልብ ማህበር (AHA) ሳይንሳዊ መግለጫ

☕ መጠነኛ የካፌይን አጠቃቀም (በቀን እስከ 400 ሚ.ግ፣ በግምት ከ3 እስከ 5 ኩባያ ቡና) ለአብዛኞቹ ጤናማ አዋቂዎች ችግር አያመጣም፤ ለልብና ደም ስር ጤና እንደ ጥሩ የአኗኗር ዘይቤም ሊቆጠር ይችላል።

✅ ቡናን በመጠኑና እና በመደበኛ ሁኔታ መጠጣት ለሚከተሉት በሽታዎች ያለንን ተጋላጭነት ይቀንሳል፦

❤️ የልብ ቧንቧ በሽታ (Coronary artery disease) እና የልብ ድንገተኛ ጥቃት (Heart Attack)
❤️ የልብ ድካም (Heart failure)
🧠 ስትሮክ (Stroke)
💓 የልብ ምት መዛባት፣ በተለይ አትሪያል ፊብሪሌሽን (Atrial fibrillation)
🩸 ዓይነት 2 የስኳር በሽታ (Type 2 Diabetes)
🩺 ከፍተኛ የደም ግፊት [Hypertension]
⏳ አጠቃላይ የሞት አደጋ (All-cause mortality)

⚠️ አስፈላጊ ነጥቦች፦

• ካፌይን በአንዳንድ ሰዎች፣ በተለይ ከፍተኛ የደም ግፊት ባላቸው ወይም ለካፌይን ተጋላጭ በሆኑ ሰዎች፣ ለጊዜው የደም ግፊትን ሊጨምር ይችላል።

• የተጣራ (Filtered) ቡና የተመረጠ ነው። ያልተጣራ ቡና (ለምሳሌ የፈረንሳይ ፕሬስ፣ የቱርክ፣ የግሪክ ወይም የተቀቀለ ቡና) የ LDL cholesterol (“መጥፎ” ኮሌስትሮል) መጠንን ሊጨምር ይችላል።

• ቡናን በመጠኑ መጠጣት የላይኛው (የደም ተቀባይ) የልብ ምት መዛባትን (atrial fibrillation) አይጨምርም፤ ነገር ግን በአንዳንድ ሰዎች የታችኛው የልብ ምት መዛባትን (premature ventricular contractions) ሊጨምር ይችላል።

• ከፍተኛ መጠን ያለው ካፌይን፣ በተለይ ከኢነርጂ መጠጦች፣ ካፌይን ዱቄት ወይም ማሟያዎች (supplements) የሚመጣ፣ የደም ግፊትን ሊጨምር እና አደገኛ የልብ ምት መዛባትን ሊያስነሳ ይችላል።

• ብዙ ስኳር፣ ጣዕም ያላቸው ሽሮፖች እና ከፍተኛ ስብ ያላቸው ክሬሞችን ቡና ውስጥ መጨመር የቡና የጤና ጥቅሞችን ሊቀንስ ይችላል።

• ሰዎች ለካፌይን የሚሰጡት ምላሽ ይለያያል፤ ይህም በካፌይን መፈጨት ልዩነት ምክንያት ነው።

💡 ዋና ዋና መልዕክቶች፦

• ለአብዛኞቹ አዋቂዎች የተጣራ ቡና በመጠኑ መጠጣት የጤና ችግር አያመጣም፤ ይልቁንም ለተሻለ የልብና የደም ስር ጤና ይረዳል።

• ከመጠን በላይ ካፌይን እና ከፍተኛ ካፌይን ያላቸው ኢነርጂ መጠጦችን ያስወግዱ።

• ካፌይን በተደጋጋሚ የልብ መምታት፣ የደም ግፊት መጨመር ወይም ሌሎች ምልክቶችን ካስከተለ የጤና ባለሙያን ያማክሩ።

Source: Caffeine and Cardiovascular Disease: A Scientific Statement From the American Heart Association. Circulation. 2026.
https://doi.org/10.1161/CIR.0000000000001454

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Medical & Heart Health posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Ethio Medical & Heart Health:

Shortcuts

Share