Hakim Mereja ሀኪም መረጃ

Hakim Mereja ሀኪም መረጃ Sometimes take a LOSS for a bigger WIN.

Message of condolencesWe are saddened to learn of the passing of Dr. Tamirat Sahlemariam. Our sincere condolences to his...
30/08/2026

Message of condolences

We are saddened to learn of the passing of Dr. Tamirat Sahlemariam. Our sincere condolences to his family, friends, patients and colleagues.

May his soul rest in peace.

ልዩ ዜና ከጎፋ፡ አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 4 ህፃናትን በሰላም ተገላገለች::በጎፋ ዞን በአንድ ወሊድ የአራት ህፃናት እናት የሆኑት ወ/ሮ አንድነት አማረ የድጋፍ ጥሪ አቀረቡሣውላ፣ ኢትዮጵያ...
30/08/2026

ልዩ ዜና ከጎፋ፡ አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 4 ህፃናትን በሰላም ተገላገለች::

በጎፋ ዞን በአንድ ወሊድ የአራት ህፃናት እናት የሆኑት ወ/ሮ አንድነት አማረ የድጋፍ ጥሪ አቀረቡ

ሣውላ፣ ኢትዮጵያ — በጎፋ ዞን ሣውላ አጠቃላይ ሆስፒታል በአይነቱ ልዩ የሆነ አስደሳች የወሊድ ኩነት ተመዝግቧል።

ወ/ሮ አንድነት አማረ የተባሉ እናት በአንድ ጊዜ አራት ሴት ህፃናትን በሰላም ተገላግለዋል። በሆስፒታሉ የህክምና ቡድን በተደረገላቸው ቅርብ ክትትል በአሁኑ ወቅት እናቲቱም ሆኑ አራቱም አራስ ህፃናት ሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተረጋግጧል።

የህፃናቱ አባት አቶ ናፍቆት ቡሼ ከዚህ ቀደም የአምስት ሴት ልጆች አባት የነበሩ ሲሆን፣ ከአዲሶቹ አራት ጨቅላዎች መወለድ ጋር ተያይዞ በአጠቃላይ የ ዘጠኝ ሴት ልጆች አባት ለመሆን በቅተዋል።

አባት አቶ ናፍቆት ለተደረገላቸው የህክምና እርዳታ ምስጋናቸውን አቅርበው፤ ነገር ግን በአንድ ጊዜ የተጨመሩትን አራት ህፃናት ጨምሮ አጠቃላይ ዘጠኙን ልጆቻቸውን በበቂ ሁኔታ ለማሳደግ የኢኮኖሚ አቅማቸው እጅግ አነስተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም ህፃናቱ አስፈላጊውን እንክብካቤ እና አስተዳደግ እንዲያገኙ፡

• መንግስታዊ አካላት
• የበጎ አድራጎት ድርጅቶች
• መላው የህብረተሰብ ክፍል

የሚቻላቸውን ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

©️የጎፋ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን

A single picture speaks thousands of words.
28/08/2026

A single picture speaks thousands of words.

የጤና ባለሙያ VS የኑሮ ውድነት😀
28/08/2026

የጤና ባለሙያ VS የኑሮ ውድነት😀

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ያለፈ የትርፍ ሰዓት ውዝፍ ክፍያ አልፈፅምም አለ።በቅርቡ ከተቋማት ኃላፊዎች ጋር በነበረ አንድ ስብስባ ላይ የቢሮው ከፍተኛ አመራር እስከ ሀምሌ 1/2018 ዓ.ም ድረስ...
27/08/2026

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ያለፈ የትርፍ ሰዓት ውዝፍ ክፍያ አልፈፅምም አለ።

በቅርቡ ከተቋማት ኃላፊዎች ጋር በነበረ አንድ ስብስባ ላይ የቢሮው ከፍተኛ አመራር እስከ ሀምሌ 1/2018 ዓ.ም ድረስ የሰሩበትን የትርፍ ሰዓት (ዱቲ) ውዝፍ ክፍያ ወደ ኋላ ተመልሶ ክፍያ እንደማይፈጽም መናገራቸው ተሰምቷል።

አመራሩ አሁን ላይ ወጥቷል ባሉት አዲስ የትርፍ ሰዓት ክፍያ መመሪያ መሰረት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ከሀምሌ 1/2018 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

አመራሩ ሆስፒታሎች ባለሙያዎችን ብዙ ሳታጉላሉ ክፈሉ ፤እኛ በጀት ይዘናል ሲሉ ተደምጠዋል።

የክልሉ የጤና መምሪያዎች የቅድመ-ወጪ ስሌታቸውን እንዲያቀርቡም የተጠየቁ ሲሆን፣ ሆስፒታሎችም የቀደመውን የትርፍ ሰዓት ክፍያ ሳይነኩ የዱቲ ክፍያን በተሰጠው ግልጽ የሒሳብ ስሌት መመሪያ መሠረት ብቻ እንዲፈጽሙ ኃላፊው አሳስበዋል።

አሁን በጸደቀው መመሪያ ከዚህ በኋላ ያለውን ነው እንድከፈል የሚያዘው ያሉት አመራሩ ወደኋላ ያለ የዱቲ ክፍያ የለንም፤ ውዝፍ ክፍያ (backlog) የሚባል ነገር የለም። በነበረው ደሞዝ፣ በተበጀተው በጀት ነው ክፈሉ ያልናችሁ። የድጎማ በጀት እናገኛለን ብለን ከክልል እስከ ፌዴራል ሄደናል፤ የበጀት እጥረት ስላለ ድጎማ የለም ብለዋል።

የትርፍ ሰዓት ክፍያ የሰጣችሁትን ሰው አንነካም። የተከሰሰ ሰው ካለ እኔ በተመደበልኝ በጀት ይህንን ከፍያለሁ፤ የበጀት ስርጭቱ ላይ አልተካተተም ' ብላችሁ መልሱ ከዚያ የሚሆነውን አብረን እናየዋለን፣ ምክንያቱም የክልሉ በጀት ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

በአንፃሩ 3.7 ቢሊዮን ብር ለሆስፒታል፣ 5.3 ቢሊዮን ለጤና ጣቢያ ከሀምሌ 1/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለትርፍ ሰዓት ክፍያ የሚውል በጀት አስፈቅደናል ሲሉ ተናግረዋል።

አመራሩ ለዱቲ ክፍያ የሚሆን 8.9 ቢሊዮን ብር ከራሳቸው ከተቋማቱ የውስጥ ገቢ የሚሸፈን ሆኖ፣ በCGS በኩል የቅድመ-ወጪ ግምት ተሰርቶለት በጀት ሆኖ ተይዟል፤ በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ ተመስርተን መደራደር ያስፈልጋል ብለዋል።

እኛ ስለተፈቀደልን ይሄንን እናስቀጥላለን፤ እናንተ መረጃ (ዳታ) ላይ ተመስርታችሁ ውሳኔ እየሰጣችሁ ሂዱ፤ በተቻለ መጠን ሥራዎቹን በዚያ መሠረት ለማስቀጠል እንሄዳለን እንጂ በትርፍ ሰዓት ክፍያ ሰበብ አድርጎ ሌሎች ሥራዎችን ማስተጓጎል አይቻልም ሲሉ የጤና ተቋማት ኃላፊዎችን አስጠንቅቀዋል።

የክፍያ ስሌት ከባለሙያ ብዛት ይልቅ ትክክለኛውን የሕክምና አገልግሎት በመቁጠር የሚከናወን ነው። የትኛው ባለሙያ ምን ዓይነት አገልግሎት እንደሰጠ ግልጽ ያደርጋል ሲሉ ገልፀዋል።

27/08/2026

Good news
በኢትዮጵያ ሙያ ፊቃድ(License) አፍሪካ ሀገራትን ዞሮ መስራት እንደሚቻል ለጤና ባለሙያዎች ስምምነት ላይ መደረሱ ተሰማ🥰

የወደፊቱ ጠቅላይ ሚኒስትር 😀
27/08/2026

የወደፊቱ ጠቅላይ ሚኒስትር 😀

በዚህ ዓመት 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 87% ( 87 ከመቶ ) የሚሆኑት የማለፊያ ነጥብ እንዳልመጣላቸው የትምህርት ሚንስቴሩ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ አስታውቀዋል።ከነዚህ ...
22/08/2026

በዚህ ዓመት 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 87% ( 87 ከመቶ ) የሚሆኑት የማለፊያ ነጥብ እንዳልመጣላቸው የትምህርት ሚንስቴሩ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ አስታውቀዋል።
ከነዚህ ደግሞ ምን ያህሉ ወደ ህክምና ትምህርት መግባት ይችላሉ የሚለውን መገመት ቀላል ነው ።

በዚህ ከቀጠልን አገራችን የዛሬ 20 እና 30 አመታት ከፍተኛ የሆነ የተማረ የሰው ኃይል እጥረት ስለሚያጋጥማት ልክ እንደ ስንዴ ዶክተሮችን፣ ኢንጅነሮችን፣ ፓይለቶችን...ወዘተ ከሌሎች ያደጉ አገሮች በልመና እያስመጣች ማሰራት ትጀምራች።

Someone said, "ብርሀኑ ነጋ የጣለውን ብርሀኑ ጁላ ያነሳዋል" ነው ነገሩ😀

ለወንዶ ገነት መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቦርድ ሰብሳቢ፣ክቡር የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ኃላፊ አቶ ፃድቁ በጥሶ፣ለወንዶ ገነት ከተማ አስተዳደር ኃላፊ ክቡር ኢንጂነር ተመስገን ተረፌ፣እና ለወንዶ ገነ...
19/08/2026

ለወንዶ ገነት መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቦርድ ሰብሳቢ፣
ክቡር የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ኃላፊ አቶ ፃድቁ በጥሶ፣
ለወንዶ ገነት ከተማ አስተዳደር ኃላፊ ክቡር ኢንጂነር ተመስገን ተረፌ፣
እና ለወንዶ ገነት ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ሁሴን ከድር።
ጉዳዩ፦ በወንዶ ገነት መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እየተከሰቱ ስላሉ አስተዳደራዊ እና የፋይናንስ ክፍተቶች ምርመራ እንዲደረግ ስለመጠየቅ
ክቡራን ኃላፊዎች፣
በወንዶ ገነት መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በአሁኑ ወቅት እየተከሰቱ ያሉ አንዳንድ አስተዳደራዊ፣ የሥራ አመራር እና የፋይናንስ ክፍተቶች በግልጽ ደረጃ እየታዩ ስለሆነ፣ ጉዳዩ በአግባቡ እንዲመረመርና ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ በትህትና እናሳውቃለን።
1. የሥራ አመራር እና የዱቲ ክፍያ ጉዳይ
አቶ ታደለ ተሰማ፣ የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ፣ የሆስፒታሉን ማኔጅመንት በመወሰን በአንድ ሰዓት 330 እና ከዚያ በላይ የዱቲ ሰዓት እንዲያገኙ ያለ ግልጽ መመሪያና ፈቃድ 31,862.88 ብር ወደ አካውንታቸው እንዲገባ መደረጉን የሚያሳይ ማስረጃ እንዳለ ተገንዝበናል። ስለሆነም ጉዳዩ በሰነድ እንዲጣራ እንጠይቃለን።
2. የአቶ ገዜሀኝ ወቃዮ የዱቲ ክፍያ
አቶ ገዜሀኝ ወቃዮ 120 ሰዓት እና ከዚያ በላይ የዱቲ ሰዓት ወደ ገንዘብ ሲቀየር 8,919.00 ብር መከፈሉን የሚያሳይ መረጃ እንዳለ ተገንዝበናል። ይህም ክፍያ በሚመለከተው መመሪያ መሠረት መፈጸሙን እንዲጣራ እንጠይቃለን።
3. የኦዲት እና የግምገማ ሥራን በተመለከተ
አቶ ቡዙነህ ቡርቃ በሆስፒታሉ ውስጥ ኦዲት በሚያካሂዱበት ወቅት የሚያገኟቸውን findings በተመለከተ ሪፖርት እንዳያቀርቡ ገንዘብ እንዲሰጣቸው ይጠይቃሉ የሚል መረጃ ደርሶናል። ይህ ክስ እውነት ከሆነ በኦዲት ሂደት ነፃነትና ገለልተኛነት ላይ ከፍተኛ ጥያቄ የሚያስነሳ በመሆኑ በአግባቡ እንዲመረመር እንጠይቃለን።
በተጨማሪም ሆስፒታሉ በ12 ወራት ውስጥ 18,000,000 ብር ማሰባሰብ የሚጠበቅበት ሆኖ፣ በ9 ወር ግምገማ ወቅት 9,000,000 ብር መሰብሰቡን የሚያሳይ ሪፖርት መኖሩን ተመልክተናል። ይህም በሰነድ እንዲጣራ እንጠይቃለን።
በተጨማሪም እነዚህን ክፍተቶች ለሚያሳዩ ግለሰቦች ተገቢው የሥራ ኃላፊነት እንዲሰጥ እና የዱቲ ሰዓት እና ክፍያ በመመሪያ መሠረት ብቻ እንዲወሰን እንጠይቃለን።
4. የአቶ ገታሁን ሳሙኤል ጉዳይ
አቶ ገታሁን ሳሙኤል ከበላም ይብላ በሚል አመለካከት ሳይሆን፣ በሥራቸው የሚታመኑ፣ ትጉህና በሥራ ላይ ብቃት የሚያሳዩ ሠራተኛ መሆናቸውን ለመግለጽ እንወዳለን።
5. የዱቲ ሰዓት አጠቃቀምና የ“ሳደን ሱፐርቪዥን” ጉዳይ
እነዚህ ሰዎች ከፍተኛ የዱቲ ሰዓት የሚያገኙበት ምክንያት ሲጠየቁ “ሳደን ሱፐርቪዥን እንገባለን” የሚል መልስ እንደሚሰጡ ይነገራል።
ነገር ግን በመንግሥት የሥራ ሰዓት ውስጥ በሥራ ቦታቸው በመገኘት የሚጠበቅባቸውን ሥራ ሳይሠሩ ተጨማሪ የዱቲ ሰዓት እንዲከፈላቸው መደረጉ ካለ ይህ በግልጽ ሁኔታ እንዲመረመር ያስፈልጋል።
6. የግዥ እና የአቅርቦት ሂደት
በሆስፒታሉ ውስጥ ብዙ የሥራ እቃዎች የሚገዙበት ሂደት በግልጽ ጨረታ እና በተገቢው የግዥ ሥርዓት መፈጸሙን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
በተለይ የሕትመት እቃዎችን በተመለከተ “ባባ” ተብላ የምትጠራ አቅራቢ ለ6 ዓመታት ያለ ግልጽ የጨረታ ሂደት የግብር ሕትመት እቃዎችን ብቻዋን እያቀረበች እንደሆነና በየወሩ ከ400,000 እስከ 500,000 ብር የሚደርስ ወጪ እንደሚደረግ መረጃ አለ።
ስለሆነም የግዥው ሂደት፣ የጨረታ ሰነዶች፣ የውል ስምምነቶች፣ የክፍያ ማስረጃዎች እና የአቅርቦት ሂደቱ በአግባቡ እንዲመረመር እንጠይቃለን።
7. የምርመራ እና የሠራተኞች ፎረም ጥያቄ
ስለ አቶ ታደለ ተሰማ እና ስለ ሆስፒታሉ አስተዳደር ተጨማሪ መረጃና ማስረጃ በእጃችን ያለ ሲሆን፣ ጉዳዩ በተገቢው አካል እንዲመረመር እንጠይቃለን።
በተጨማሪም ሠራተኞች በነፃነት ሀሳባቸውን የሚያቀርቡበት የStaff Forum በቅርቡ እንዲዘጋጅ፣ እነዚህ ጉዳዮችም በግልጽ እንዲወያዩባቸው እንጠይቃለን።
የመጨረሻ ጥያቄ
ከላይ የተጠቀሱት ጉዳዮች እውነተኛነታቸው በሰነድና በማስረጃ እንዲረጋገጥ፣ ከተረጋገጠም በሕግና በመመሪያ መሠረት ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ፣ የሆስፒታሉም አስተዳደር በግልጽነት፣ በተጠያቂነትና በፍትሐዊነት እንዲመራ በትህትና እንጠይቃለን።

“ለባን በአንድነት እንከላከል!”

Via Inbox

እኛ የደሞዝ ግብር ጨመረ ይቀነስ እንላለን ጭራሽ ከDuty ላይ ግብርለጤና ባለሙያዎችም ሆነ ለአስተዳደር ሠራተኞች የሚከፈለው የትርፍ ሰዓት (Overtime) አበል ከወርሃዊ ደሞዛቸው ጋር ተደ...
19/08/2026

እኛ የደሞዝ ግብር ጨመረ ይቀነስ እንላለን ጭራሽ ከDuty ላይ ግብር
ለጤና ባለሙያዎችም ሆነ ለአስተዳደር ሠራተኞች የሚከፈለው የትርፍ ሰዓት (Overtime) አበል ከወርሃዊ ደሞዛቸው ጋር ተደምሮ የሥራ ግብር (Income Tax) ሊታሰብበትና ሊቆረጥ እንደሚገባ ያረጋግጣል።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251934647389

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hakim Mereja ሀኪም መረጃ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Hakim Mereja ሀኪም መረጃ:

Shortcuts

Share