Et-Addis Telemedicine, Consultation and Home to home health care service -

Et-Addis Telemedicine, Consultation and Home to home health care service - Better care for a better life
ለተሻለ ሕይወት የተሻለ እንክብካቤ

27/03/2026

" የቲቢ መድኃኒት በነፃ ነው፤ ከፍሎ የሚወስድ የተሰረቀ መድኃኒት እየገዛ ነው " - ጤና ሚኒስቴር

በኢትዮጵያ በየአንድ ሰዓቱ የሁለት ሰዎች ሕይወት በቲቢ በሽታ ምክንያት እንደሚቀጠፍና ሀገራችን የበሽታው ከፍተኛ ጫና ካለባቸው 30 የዓለም ሀገራት ውስጥም አንዷ መሆኗ ተገለጸ።

ይህ የተገለጸው የዓለም የቲቢ ቀንን ምክንያት በማድረግ በጤናው ዘርፍና በሚዲያ ባለሙያዎች መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር ጤና ሚኒስቴር ባዘጋጀው የሚዲያ ፎረም ላይ ነው።

በጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ህይወት ሠለሞን እንደገለጹት ፤ መንግሥት ለአንድ የቲቢ ታካሚ በዓመት ከ6 እስከ 8 ሺህ ዶላር ወጪ እያደረገ ይገኛል።

" የቲቢ መድኃኒት ለታማሚዎች በነፃ ነው የሚሰጠው ፤ ከዚህ ውጭ መድኃኒቱን ከፍሎ የሚወስድ ሰው ካለ እየገዛ ያለው የተሰረቀ መድኃኒት ነው " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በአሁኑ ወቅት ከ2,000 በላይ የግል ጤና ተቋማት ምርመራና ሕክምና እየሰጡ ሲሆን ለ1,000 ተቋማት መመርመሪያ መሣሪያዎች መሰራጨታቸውን ገልጸዋል። በገጠሩ አካባቢ ለሚገኙ 690 ላቦራቶሪዎች የሶላር ፓነል ዝርጋታ መከናወኑን አመልክተዋል።

በሚኒስቴሩ የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ዴስክ ኃላፊ አቶ ታዬ ለታ በበኩላቸው ፥ ባለፉት 6 ወራት ብቻ የሶማሌ ክልልን ሳይጨምር ለ138,000 ሰዎች በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የታገዘ ምርመራ ተደርጎ 3,500 ያህል የቲቢ ተጠቂዎች መገኘታቸውን ተናግረዋል።

አክለውም ፥ በሀገራችን ከሚከሰቱ የቲቢ አይነቶች 70% ሳምባን የሚያጠቁ ሲሆኑ፣ 30% ደግሞ ሌሎች ሁሉንም የሰውነት ክፍሎችን እንደሚያጠቁ ተናግረዋል።

ምልክቶቹ ፦
• ለሁለት ሳምንትና ከዚያ በላይ የሚቆይ ሳል፣
• ትኩሳት፣
• ማታ ማታ ማላብ፣
• የሰውነት ክብደት መቀነስ፣
• አልፎ አልፎ ደም የቀላቀለ አክታ ናቸው።

አቶ ታዬ በዓለም ላይ በየዓመቱ 10.7 ሚሊዮን ሰዎች በቲቢ እንደሚያዙ ከ1.2 እስከ 1.3 ሚሊዮን የሚደርሱትም ሕይወታቸውን እንደሚያጡ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ በዓመት 19,000 ሰዎች ይሞታሉ።

" አንድ የታመመ ሰው ሲያስል ወይም ሲያስነጥስ እስከ 40,000 ሚደርሱ ጥቃቅን ጠብታዎችን ፤ ለ5 ደቂቃ ብቻ ሲያወራ ደግሞ 3,000 ጠብታዎችን ወደ አየር በመልቀቅ በሽታውን በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው ያሰራጫል " ብለዋል።

ሰዎች ሲያስነጥሱ ወይም ሲያስሉ አፍና አፍንጫቸውን በክንድ ወይም ባማስክ መሸፈን አለባቸው ሲሉ አስገንዝበዋል።

በየዓመቱ የብዙ ሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ቢሆንም ብዙ ሰው ግድ አይሰጠውም ብለዋል።

እስካሁን 150,000 ታካሚዎች ወደ ሕክምና ማስገባት ቢቻልም አሁንም 30,000 "የተደበቁ" ታማሚዎችን ለማግኘት የጤና ባለሙያዎች ቤት ለቤት ፍለጋ እያደረጉ እንደሚገኙ አመልክተዋል።

ለቲቢ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑት ፦
- ከታካሚ ጋር የሚኖሩ፣
- ስኳርና ኤችአይቪ ያለባቸው
- የአየር ዝውውር በሌለው ቤት የሚኖሩ ናቸው።

በሌላ መረጃ ፥ ባለፉት 6 ወራት 1,460 አዳዲስ የሥጋ ደዌ ታማሚዎች ተለይተዋል። በአሁኑ ወቅት 1,800 ሰዎች በሕክምና ላይ ናቸው። ይህ ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በዚህ በሽታ በዓመት እስከ 3000 ሰዎች ይሞታሉ።

25/03/2026

የእለት ተዕለት ኑሮ የበለጠ ፈታኝ በሆነበት ወቅት ኢት-አዲስ የቤት ለቤትና ቅድመ ሆስፒታል ህክምና በሙያው በተካኑ ባለሙያዎች እርስዎ ቤት ድረስ በመምጣት
🩺 በሀኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን መስጠት እና አወሳሰዳቸውን መከታተል።
🩺 ከድህረ ቀዶ ጥገና በኋላ ቁስልን በኬሚካል አጥቦ የማሸግና የመቀየር አገልግሎት።
🩺 የሽንት ቱቦ ማስገባትና መቀየር።
🩺 መመገብ ለማይችሉ ህመምተኞች የመመገቢያ ቱቦ ማስገባት።
🩺 ማጠብ፣ ማልበስና መነከባከብ።
🩺 ለደም ግፊት ፣ ስኳር እና ካንሰር ህመምተኞች ክትትልና የማስታመም አገልግሎት መስጠት።
🩺 ለአእምሮ ህሙማንና የአረጋውያን ክትትል፣ድጋፋና የማማከር አገልግሎት
🩺የቤት ለቤት የህክምና እቃዎችና በሃኪም የታዘዙ መድሃኒቶችን፣ የህክምና ዊልቸር፣ ኦክስጅን እና ሌሎችም) የአቅርቦትና ስለአጠቃቀማቸዉ ማስተማር።
🩺በህክምና ምክንያት ወደ ሌላ ቦታ ለሚሄዱ ታካሚዎች የማማከርና የዕጀባ አገልግሎት።
🩺 የቤት ለቤት የፊዝዮቴራፒ አገልግሎት።
🩺 ሆስፒታል ውስጥ ለተኙ ህሙማን አስተማሚን ተክቶ የማስተማም አገልግሎት።
🩺 የሚያስፈልጎትን ፊዝዮቴራፒ፣ ላብራቶሪ እና የሀኪም ምክር አገልግሎት አንዲያገኙ ከጤና ተቋማት ጋር በጋራ እንሰራለን
🩺 በየትኛዉም የጤና እክል ዙሪያ የማማከረ አገልግሎት

አድራሻ፡- አአ አያት
0713603646/+251 98 332 6745/+251 96 275 8523

Better care for a better life
ለተሻለ ሕይወት የተሻለ እንክብካቤ

For more join our telegram group
📱https://t.me/Etadiss
Better care for a better life
ለተሻለ ሕይወት የተሻለ እንክብካቤ

23/12/2022

👉 መጥፎ የላብ ጠረን

👉 ምን አይነት ዶዶራንት ነው የምትጠቀሙት ወይም የትኛው አንቲፐሪስፖይራት ነው ለናንተ የሚስማማው?

👉ዶዶራንት እና አንቲፐሪስፖይራንት ሁለት የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸው፣ ምርቶች ናቸው።

👉 አንድ ሰው ብብት ላይ ፣ከልክ ያለፈ ላብ ስላለ ብቻ መጥፎ የላብ ጠረን ይፈጠራል ማለት አይደለም።

👉 አንድ ሰው ቆዳ ላይ ሁለት አይነት የላብ አምራች እጢዎች ይገኛሉ፣ እነዚህ የላብ አምራች እጢዎች አቀማመጣቸው እና የሚያመርቱት የላብ ይዘት የተለያየ ነው።

👉 ታዲያ፣ ማናቸውም አይነት የላብ እጢዎች የሚያመነጩት የላብ አይነት፣ በአንዳንድ የጤና ችግሮች ምክኒያት ካልሆነ በስተቀር፣ አብዛኛውን ግዜ የተፈጥሮ ሽታ ወይም ጠረንን የያዘ አይደለም።

👉 ነገር ግን በቆዳ ላይ የሚገኙ ጥቃቅን ህዋሳት፣ ከላብ የሚወጣውን የስብ እና የፕሮቲን ይዘት፣ እንደ ምግብ በመጠቀም ያብላሉት እና፣ መጥፎ ጠረን ወዳለው ንጥረ ነገር ይቀይሩታል።

👉 በሌላ መልኩ ደሞ አንድ ሰው፣ መጥፎ የላብ ጠረን እንዲኖረው አስተዋፆ የሚያደርጉ የተለያዩ ምክኒያቶች አሉ፣

👉 በቆዳላይ ፣በተለይ በሰውነት እጥፋቶች መሀል የሚወጣ የቆዳ ኢንፌክሽን ካለ፣
👉 አብሽ ቀይ ሽንኩርት እና ነጭሽንኩርት የበዛበት ምግብ በብዛት የሚመገቡ ሰዎች፣
👉ከፍተኛ የኩላሊት ድክመት ያለባቸው ታካሚዎች፣
👉 የአልኮል መጠጥ እና የ ፔኒሲሊን ይዘት ያላቸው መዳኒቶች ለረጅም ግዜ የሚወሰዱ ከሆነ ፣ የሰውነት ጠረንን የመቀየር አቅም አላቸው።

👉ከዚህ በተለየ መልኩ ደሞ አንዳንድ ሰዎች ላይ የሚታይ የስነ አእምሮ ችግር አለ፣ በህክምናው Delusional bromosis ወይም Olfactory reference syndrome በባል ይታወቃል። የዚህ ችግር ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ምንም አይነት የሰውነት ጠረን ሳይኖራቸው ፣ነገር ግን ሰውነታቸው መጥፎ ጠረን ያለው እንደሆነ ያህል ይሰማቸዋል።

👉 አንድ ሰው ላይ ፣መጥፎ የሆነ የብብት ወይም የሰውነት ላብ ጠረን ሲያጋጥም፣ ምን መደረግ አለበት?

👉በብብት ቆዳ ላይ የሚታይ የቆዳ ገፅታ መቀየር ካለ
👉መጥፎ ጠረን በተፈጠረበት ቦታ ላይ ፣ የቆዳ ማሳከክ ፣መቅላት እና ማንኛውም አይነት የህመም ስሜት የሚታይ ከሆነ፣

👉 ችግሩ ከተጓዳኝ የቆዳ በሽታ እንዲሁም በሌላ የጤና ችግር ምክኒያት የመጣ ሊሆን ስለሚችል ሀኪምጋ መቅረብ ያስፈልጋል።

👉 አንድ ሰው ላይ፣ ተጓዳኝ የቆዳም ሆነ የውስጥ ደዌ እና የስነአእምሮ ችግር ሳይኖር ፣መጥፎ የላብ ጠረን የሚያጋጥም ከሆነ፣ በመጀመሪያ ደረጃ መደረግ ያለበት ተግባር ወትሮአዊ በሆነ መልኩ ንፅህናን መጠበቅ ነው።

👉 ለዚህም ተመራጭ የሚሆኑት በውስጣቸው እንደ Clindamycin እና Benzoyle Peroxide የመሳሰሉ የፀረ ተህዋስያን መዳኒት የተጨመረባቸው ሳሙናዎች ናቸው። እነዚህን ሳሙናዎች በመጠቀም መጥፎ የላብ ጠረን ባለበት ቦታ በቀን 2 ግዜ መታጠብ ያስፈልጋል።

👉 በብብት እና በብልት አካባቢ የሚበቅል ፀጉር ፣ላብን እና መጥፎ ጠረንን የሚፈጥሩ ጥቃቅን ህዋሳት አጣብቆ ስለሚይዝ ፣በቦታው ላይ ያለ ፀጉርን ማሳጠር።

👉ብብት ላይ ጥብቅ የሚል ልብስን አለመልበስ ፣
መጥፎ የሰውነት ጠረን እንዲባባስ የሚያደርጉ ፣እንደ አብሽ፣ የአልኮል ይዘት ያላቸው መጠጦች፣ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት እና ቅመማ ቅመሞች የበዙበት ምግብን አለማዘውተር ያስፈልጋል።

👉 አብዛኛውን ግዜ ደሞ፣ የላብ መጠንን የሚቀንሱ እና መጥፎ ጠረንን የሚሸፍኑ፣ አንቲቶሪስፖይራንቶች እና ዶዶራንቶች፣ ለዚህ ችግር ተጨማሪ መፍትሄዎች ናቸው።

👉 አንድ ምርት ላይ ዲኦዶራንት (Deodorant )የሚለው ፅሁፍ ብቻ ካለው፣ የሚያመላክተው መጥፎ ጠረንን በጥሩ መአዛ የሚተካ መሆኑን ብቻ እንጂ የላብ መጠንን የሚቀንስ አይደለም።

👉አንድ ዶዶራንት ላይ አንቲፐሪስፖይራንት (Antiperispirant) የሚል ፅሁፍ ካለው፣ በውስጡ የላብ መውጫ ቀዳዳዎችን በመድፈን ፣የላብ መጠንን መቀነስ የሚችል ይዘት እንዳለው ያመላክታል።

👉ገበያ ላይ ፣የብብት ላብ እና ጠረንን ለመቀነስ የተዘጋጁ ዶዶራንቶች እና አንቲፐሪስፖይራንቶች ፣በተለያየ ይዘት የተዘጋጁ ናቸው፣

👉 ከነዚህ ውስጥ አብዛኛውን ግዜ፣ ቁጡ ለሆነ ቆዳ ተስማሚ የሚሆኑት ምርቶች ፣በሚዳሰስ መልክ የተዘጋጁት የዶቭ ምርቶች ናቸው። እነዚህ በውስጣቸው ሽታን እና የላብ መጠንን የሚቀንስ የአልሙኒየም ይዘት ያላቸው ምርቶች ናቸው።

👉ከዛ በተጨማሪ ደሞ፣ የአልኮል ይዘት እና ሽታ የሌላቸው ምርቶች፣ አብዛኛውን ግዜ ተስማሚ እና የቆዳ ቁጣን የማይፈጥሩ ምርቶች ናቸው።

👉 ሽታ የሌላቸውን የላብ መቀነሻ ምርቶች የምትጠቀሙ ከሆነ፣ እነዚህ ምርቶች ላብን የመቀነስ አቅማቸው የሚጨምረው፣ ላብ በሚያልብ ግዜ በመጠቀም ሳይሆን፣ ታጥቦ በደረቀ ብብት ላይ ፣ማታማታ ብትቀቧቸው እና ጠዋት ላይ ፣የፀረተህዋስያን ይዘት ባላቸው ሳሙናዎች ብትታጠቡ ፣የሰውነት መጥፎ ጠረንን ለማጥፋት የበለጠ አቅም ይኖራቸዋል።

አድራሻ፡- ጅጋ ቀበሌ-2 ከፀደይ ባንክ (የበፊቱ አብቁተ) ፊት ለፊት ባለዉ ኮብል ስቶን መንገድ 100 ሜትር ገባ ብሎ ዶ.ር ጌታነህ መካከለኛ ክሊኒክ አጠገብ እንዲሁም በፍኖተሰላም ከተማ ያገኙናል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0587790873 / 09-18-53-63-00 / 09-42-05-21-45 ላይ ይደውሉልን!
Facebook https://www.facebook.com/Gihoncare/
Telegram https://t.me/Gihonhealthcareservice
Email [email protected]

ግዮን ኬር የቤት ለቤትና የቅድመ ሆስፒታል ህክምና አገልግሎት
Gihon care home to home & pre-hospital medical service

Better care for a better life
ለተሻለ ሕይወት የተሻለ እንክብካቤ

22/12/2022

የእለት ተዕለት ኑሮ የበለጠ ፈታኝ በሆነበት ወቅት ግዮን ኬር የቤት ለቤትና ቅድመ ሆስፒታል ህክምና በሙያው በተካኑ ባለሙያዎች እርስዎ ቤት ድረስ በመምጣት
👉 በሀኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን መስጠት እና አወሳሰዳቸውን መከታተል።
👉 ከድህረ ቀዶ ጥገና በኋላ ቁስልን በኬሚካል አጥቦ የማሸግና የመቀየር አገልግሎት።
👉 የሽንት ቱቦ ማስገባትና መቀየር።
👉 መመገብ ለማይችሉ ህመምተኞች የመመገቢያ ቱቦ ማስገባት።
👉 ማጠብ፣ ማልበስና መነከባከብ።
👉 ለደም ግፊት ፣ ስኳር እና ካንሰር ህመምተኞች ክትትልና የማስታመም አገልግሎት መስጠት።
👉 ለአእምሮ ህሙማንና የአረጋውያን ክትትል፣ድጋፋና የማማከር አገልግሎት
👉 የቤት ለቤት የህክምና እቃዎችና በሃኪም የታዘዙ መድሃኒቶችን፣ የህክምና ዊልቸር፣ ኦክስጅን እና ሌሎችም) የአቅርቦትና ስለአጠቃቀማቸዉ ማስተማር።
👉 በህክምና ምክንያት ወደ ሌላ ቦታ ለሚሄዱ ታካሚዎች የማማከርና የዕጀባ አገልግሎት።
👉 የቤት ለቤት የፊዝዮቴራፒ አገልግሎት።
👉 ሆስፒታል ውስጥ ለተኙ ህሙማን አስተማሚን ተክቶ የማስተማም አገልግሎት።
👉 የሚያስፈልጎትን ፊዝዮቴራፒ፣ ላብራቶሪ እና የሀኪም ምክር አገልግሎት አንዲያገኙ ከጤና ተቋማት ጋር በጋራ እንሰራለን
👉 በየትኛዉም የጤና እክል ዙሪያ የማማከረ አገልግሎት የምንሰጥ ሲሆን ለተለየ ጉዳይ አዲስ አበባን ጨምሮ ወደ ሌሎች ከተሞች መሄድ ካስፈለገ አብረዉን ከሚሰሩ አጋሮቻችን ጋር በመሆን በቀጠሮ ብዛት ሳይንገላቱ በቶሎ ታክመዉ የሚመለሱበትን መንገድ እናመቻቻለን።

አድራሻ፡- ጅጋ ቀበሌ-2 ከፀደይ ባንክ (የበፊቱ አብቁተ) ፊት ለፊት ባለዉ ኮብል ስቶን መንገድ 100 ሜትር ገባ ብሎ ዶ.ር ጌታነህ መካከለኛ ክሊኒክ አጠገብ እንዲሁም በፍኖተሰላም ከተማ ያገኙናል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0587790873 / 0918-53-63-00 / 09-42-05-21-45 ላይ ይደውሉልን!
Facebook https://www.facebook.com/Gihoncare/
Telegram https://t.me/Gihonhealthcareservice
Email [email protected]

ግዮን ኬር የቤት ለቤትና የቅድመ ሆስፒታል ህክምና አገልግሎት
Gihon care home to home & pre-hospital medical service

Better care for a better life ለተሻለ ሕይወት የተሻለ እንክብካቤ

እኔን ብሎ ገላጋይ!«ዘውድአለም ታደሠ»ኮንዶሚኒየም ውስጥ መኖር ችግሩ ብዙ ነው። ዋነኛ ችግሩ የባለትዳሮች ፀብ ነው።ህዝቤኮ ኬክ እየተጎራረሰ ሲጋባ ሚጣላ አይመስልም። በኮንዶሚኒየም ኑሮዬ እን...
08/08/2022

እኔን ብሎ ገላጋይ!

«ዘውድአለም ታደሠ»

ኮንዶሚኒየም ውስጥ መኖር ችግሩ ብዙ ነው። ዋነኛ ችግሩ የባለትዳሮች ፀብ ነው።
ህዝቤኮ ኬክ እየተጎራረሰ ሲጋባ ሚጣላ አይመስልም። በኮንዶሚኒየም ኑሮዬ እንደተረዳሁት
ግን ትዳር ማለት ተፈራርመው የሚደባደቡበት የቦክስ ሜዳ መሆኑን ነው።
ትናንት እንቅልፍ ሸለብ ሊያደርገኝ ሲል ደጋግሞ “ድው! ድው!” የሚል ድምፅ ይሰማኝ
ጀመር። ማነው ደሞ በዚህ ለሊት ኳስ ሚደልቀው ብዬ ወጣ ስል አንዱ አባወራ ነው ለካ
የሚስትየውን ጀርባ ሚደልቀው። ፀጉሯን ጨምድዶ አስጎንብሶ በቦክስ ደጋግሞ ጀርባዋን
ይነርተዋል። “ድው! ድው! ድው!”
መቼም የኢትዮጵያ ሴቶች ጀርባ ማይችለው ጉድ የለም። ልጅ እያለች የውሃ ጀሪካን ወይም
ማሰሮ ትሸከማለች፣ ስትወልድ ልጇን ተሸክማ ታሳድጋለች፣ ልጇን ስታወርድ የባሏን ቡጢ ...
ሰውየው ቁና ቁና እየተነፈሰ «የታባሽ ነው ያመሸሽው?» እያለ ይደልቃታል።
«ምናባህ አገባህ?» ትላለች ዱላውን ተቋቁማ! ድው!!
«ከጎረምሳሽ ጋር ነው ያመሸሽው?» ድው!
«ምናባክ አገባህ ከፈለግሁት ጋር ባመሽ?» ድው!!
ለአፍታ ቆሜ የጀርባዋን ጥንካሬ አደነቅሁ! ጀርባዋ የኢትዮጵያ ህዝብ መሰለኝ (ማይችለው
ቡጢ የለም)
ፀጉሯን በሃይል ሲጎትተው ፀጉሯ ተነጫጭቶ እጁ ላይ ቀረ። የሷ ፀጉር ለተነቀለው እኔን
ዝግንን አለኝ። ቀና ብላ «አንተ ውሻ ሂውማን ሄሬን አበላሸኸው!» ብላ አነቀችው።
እንደማይላቀቁ ሲገባኝ ተንደርድሬ ሄጄ መሃል ገባሁና ሰውዬውን ያዝኩት። ሰውዬው በዚያ
ቁመቱ ቁልቁል በጥርጣሬ እያየኝ «አሃ ጎረምሳሽን በር ላይ አቁመሽልኛላ!» አለ እያፈጠጠ.. «አረ ጎረቤት ነኝ» ብዬ ላስተባብል ስል ልጅቱ ጀርባዬ ላይ ለምን አትጠመጠምም?
ሰውዬው «ጭራሽ ፊቴ ትተቃቀፉልኝ ጀመር? እቺን ይወዳል ደምመላሽ!» ብሎ እጁን
ሲጨብጥ እቺን መስቲሽ የሆነች ልጅ ከላዬ ላይ ለማላቀቅ እየሞከርኩ «አረኔ ጎረቤት ነኝ
ወዳጄ» ብየ ተማፀንኩ።
«ጭራሽ ከጎረቤት ጋር ነው ምትማግጪልኝ?» አለና መዳፉን ወደፊቴ ሲያስወነጭፈው...... መልአኩ ሚካአል ጣልቃ ገባ መሰለኝ ለጥቂት ሳተኝ! ድጋሜ ሊሰነዝር ሲመጣ
እንደምንም ሸሽቼ በሩቅ አያቸው ጀመር።
«ና ወዲህ አንት ቦቅቧቃ» አለኝ ደረቱን አሳብጦ። አያቶቻችንም ጣሊያንን አባርረው እንዲህ
አልጎረሩም! ሰውዬው ጠቡን ረስቶ እኔን በሚስቱ ፊት አባርሮ ጀግንነቱን በማሳየቱ የረካ
ይመስላል።
ዝም ብዬ ቆሜ ሳየው የሚስቱን እጅ እየጎተተ ወደቤቱ ይዟት ገባ! ፖሊስ ልጥራላት ወይስ
ዝም ብዬ ቤት ልግባ? እያልኩ ትንሽ ቆይቼ ወደበራቸው ተጠጋሁ። ልጅቷ አሳዘነችኝ። ፈራ
ተባ እያልኩ ከውስጥ የሚመጣውን ድምፅ መስማት ጀመርኩ ...
ከውስጥ ግን ያልጠበቅሁት የልጅቷ ሳቅ ነበር የተሰማው! ግራ ገብቶኝ በደምብ ማዳመጥ
ጀመርኩ .... ረጋ ብለው ያወራሉ ...
«እናትህ ቤት ነበርኩ እያልኩህ ...» አለችው
«እና መጀሪያ አትነግሪኝም የኔ ውድ?» አላት
«መቼ ጠየቅከኝ የኔ ማር?» አለችው
«ይቅርታ ፍቅሬ» አላት ረጋ ብሎ
«ሂውማን ሄሬን ደግሞ ትገዛታለህ!»
«ነገውኑ እገዛለሁ የኔ አበባ!»
«በል አሁን ጀርባዬን ማሳጅ አርገኝ ..»
ወይ ሐገሬ .. የሰባበሩን እጆች ማሳጅ አረንዲያደርጉን ጀርባችንን እያቀበልን እንዴት
መከራችን ያብቃ? ለማንኛውም እኔ ሁለተኛ በባልና ሚስት መሃል ላልገባ እየማልኩ
ወደቤቴ ገብቻለሁ! እኔን ብሎ ሰላም አስከባሪ!

Address

AA
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Et-Addis Telemedicine, Consultation and Home to home health care service - posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Et-Addis Telemedicine, Consultation and Home to home health care service -:

Shortcuts

Share

Category