WeCare ET

WeCare ET Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from WeCare ET, Medical and health, Nigist, Addis Ababa.
(2)

WeCare is Ethiopia’s digital healthcare platform where treatment seekers can discover practitioners to directly book appointments for online consultation or in clinic visits.

🚨ከወተት እና የወተት ተዋጽኦዎች ጋር መወሰድ የሌለባቸው 5 መድኃኒቶች !!🥛ምንም እንኳን የወተት ተዋጽኦዎች በንጥረ ነገሮች የበለፀጉ ቢሆኑም በውስጣቸው የሚገኘው ካልሲየም እና ፕሮቲን ሰውነ...
04/06/2026

🚨ከወተት እና የወተት ተዋጽኦዎች ጋር መወሰድ የሌለባቸው 5 መድኃኒቶች !!

🥛ምንም እንኳን የወተት ተዋጽኦዎች በንጥረ ነገሮች የበለፀጉ ቢሆኑም በውስጣቸው የሚገኘው ካልሲየም እና ፕሮቲን ሰውነትዎ አንዳንድ መድኃኒቶች የሚሰሩበትን መንገድ ሊያስተጓጉል ይችላል ።

💊የእንቅርት መድኃኒት

🔺የታይሮይድ ሆርሞን እጥረትን (hypothyroidism) ለማከም የሚያገለግለው ሌቮታይሮክሲን (Levothyroxine) ከወተት ተዋጽኦዎች ጋር አብሮ ሲወሰድ በሰውነት ጥቅም ላይ እንዳይውል ሊያደርጉት ይችላሉ።

🔺የወተት ተዋጽኦዎችን ለመመገብ ደግሞ ቢያንስ አራት ሰዓታት ይጠብቁ።

💊 የአጥንት መሳሳት (ኦስቲዮፖሮሲስ) መድኃኒት

🔺የአጥንት መሳሳትን ለማከም የሚረዱ እንደ አለንድሮኔት (alendronate)፣ ራይሴድሮኔት (risedronate) እና ኢባንድሮኔት (ibandronate) ያሉ መድኃኒቶች በካልሲየም የበለፀጉ ምግቦች ወይም መጠጦች ጋር አብረው ሲወሰዱ ውጤታማነታቸው ሊቀንስ ይችላል።

🔺መድኃኒቱን ከወሰዱ በኋላ የወተት ተዋጽኦዎችን ከመመገብዎ በፊት ጥቂት ሰዓታትን ይጠብቁ።

💊 የአይረን (የብረት) ሰፕልመንት

🔺ካልሲየም እና በወተት ውስጥ ያሉ ፕሮቲኖች ሰውነት የብረት ንጥረ ነገር የሚወስድበትን አቅም ይገድቡታል ። ይህም ከአይረን ሰፕልመንት የምናገኘውን ጥቅም ይቀንሰዋል።

🔺ስለዚህ የአይረን ሰፕልመንት የወተት ተዋጽኦዎችን ከመመገብዎ ቢያንስ ከሁለት ሰዓት በፊት ወይም ከሁለት ሰዓት በኋላ ይውሰዱ።

💊 ሊቲየም (Lithium)

🔺ሊቲየም ከፍተኛ የሆነ የስሜት መዋዠቅ (bipolar disorder) ያለባቸው ሰዎችን ለማከም የሚያገለግል ሲሆን ይህን መድኃኒት ለረጅም ጊዜ መጠቀም በሰውነት ውስጥ የካልሲየም መጠን እንዲጨምር ያደርጋል። ከወተት ወይም ከወተት ተዋጽኦዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ካልሲየም መውሰድ ይህን የጨመረውን የካልሲየም መጠን ይበልጥ እንዲጨምር እና ለተለያዩ የጤና እክሎች እንዲጋለጡ ያደርጋል።

🔺ስለዚህ ወጥ የሆነ የአመጋገብ ልምድ እንዲኖርዎ በማድረግ እና ስለሚወስዱት የካልሲየም መጠን ሐኪምዎን በማማከር ይህን ይከላከሉ።

💊 አንዳንድ የፀረ ባክቴሪያ መድኃኒቶች

🔺እንደ ቴትራሳይክሊን እና ፍሎሮኪኖሎን (ለምሳሌ፦ ሲፕሮፍሎክሳሲን/ciprofloxacin እና ሌቮፍሎክሳሲን/levofloxacin) ያሉ አንዳንድ የፀረ ባክቴሪያ መድኃኒቶች በወተት ተዋጽኦዎች ውስጥ ካለው ካልሲየም ጋር ሊጣበቁ ይችላሉ፤ ይህም ውጤታማነታቸውን ይቀንሰዋል።

🔺የወተት ተዋጽኦዎችን እና እነዚህን የፀረ ባክቴሪያ መድኃኒቶች ጥቂት ሰዓታት አራርቀው ይውሰዱ።

👩‍⚕️👨‍⚕️ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን ለማማከር ☎️ 9394 ላይ ይደውሉ ።

#9394

🚨 የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሐኪም ማማከር ይፈልጋሉ ?👨🏽‍⚕️ዶ/ር ክፍሌ አላምረው የስፔሻሊቲ ሰርተፍኬታቸውን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያገኙ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሐኪም ናቸው።🗣የ WeCare E...
03/06/2026

🚨 የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሐኪም ማማከር ይፈልጋሉ ?

👨🏽‍⚕️ዶ/ር ክፍሌ አላምረው የስፔሻሊቲ ሰርተፍኬታቸውን ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያገኙ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሐኪም ናቸው።

🗣የ WeCare ET የስልክ መተግበሪያን በመጠቀም የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ሐኪም የሆኑትን ዶ/ር ክፍሌ አላምረውን ጨምሮ ሌሎች ስመጥር ስፔሻሊስት እና ሰብ ስፔሻሊስት ሐኪሞችን በቀላሉ በቤትዎ ሆነው ቢያሻዎት በቪዲዮ ፣ በስልክ ወይም በፅሁፍ መልዕክት ስለ እርሶ እና ስለ ወዳጆ ጤና ይመካከሩ !!

መተግበሪያውን ዛሬውኑ ያውርዱ እና ይሞክሩት።
👇👇👇👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient

💻በኮምፒውተር ታግዘው ለማማከር ካሾት የWeCareETን የታካሚዎች ድህረ-ገጽ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ።
👇 https://user.wecare.et

👩‍⚕️👨‍⚕️ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን ለማማከር ☎️ 9394 ላይ ይደውሉ ።

#9394

🚨ይሳተፉ ይመልሱ ይሸለሙ🎉🎉🎉🦴ጠንካራ አጥንት እና ጥርስ እንዲኖረን አስፈላጊ የሆነው ንጥረ ነገር ምን በመባል ይታወቃል?🩷ይህን ጥያቄ በትክክል ለሚመልሱ 3 ሰዎች  የ50 ብር የሞባይል ካርድ...
02/06/2026

🚨ይሳተፉ ይመልሱ ይሸለሙ🎉🎉🎉

🦴ጠንካራ አጥንት እና ጥርስ እንዲኖረን አስፈላጊ የሆነው ንጥረ ነገር ምን በመባል ይታወቃል?

🩷ይህን ጥያቄ በትክክል ለሚመልሱ 3 ሰዎች የ50 ብር የሞባይል ካርድ ሽልማት እንሰጣለን።

📱የ WeCareET የስልክ መተግበሪያን በመጠቀም ስመጥር ስፔሻሊስት እና ሰብ-ስፔሻሊስት ሐኪሞችን በቀላሉ በቤትዎ ሆነው ቢያሻዎት በቪዲዮ ፣ በስልክ ወይም በፅሁፍ መልዕክት ስለ እርሶ እና ስለ ወዳጆ ጤና ይመካከሩ !!!

መተግበሪያውን ዛሬውኑ ያውርዱ እና ይሞክሩት ።
👇👇👇👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient

💻በኮምፒውተር ታግዘው ለማማከር ካሾት የWeCareETን የታካሚዎች ድህረ-ገጽ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ።
👇 https://user.wecare.et

👨🏽‍⚕️👩‍⚕️ ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን ለማማከር 📞 9394 ላይ ይደውሉ ።

#9394 See less

🚨 የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ሐኪም ማማከር ይፈልጋሉ !! 👨🏽‍⚕️ዶ/ር አለም መከተ ጠቅላላ የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ሐኪም ሲሆኑ የስፔሻሊቲ ዲግሪያቸውንም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ...
31/05/2026

🚨 የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ሐኪም ማማከር ይፈልጋሉ !!

👨🏽‍⚕️ዶ/ር አለም መከተ ጠቅላላ የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ሐኪም ሲሆኑ የስፔሻሊቲ ዲግሪያቸውንም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አግኝተዋል ። አሁን ላይ በአዲስ አበባ ሲልክሮድ አጠቃላይ ሆስፒታል በመስራት ላይ ናቸው።

🗣የ WeCare ET የስልክ መተግበሪያን በመጠቀም የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ሐኪም የሆኑትን ዶ/ር አለም መከተን ጨምሮ ሌሎች ስመጥር ስፔሻሊስት እና ሰብ ስፔሻሊስት ሐኪሞችን በቀላሉ በቤትዎ ሆነው ቢያሻዎት በቪዲዮ ፣ በስልክ ወይም በፅሁፍ መልዕክት ስለ እርሶ እና ስለ ወዳጆ ጤና ይመካከሩ !!

መተግበሪያውን ዛሬውኑ ያውርዱ እና ይሞክሩት።
👇👇👇👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient

💻በኮምፒውተር ታግዘው ለማማከር ካሾት የWeCareETን የታካሚዎች ድህረ-ገጽ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ።
👇 https://user.wecare.et

👩‍⚕️👨‍⚕️ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን ለማማከር ☎️ 9394 ላይ ይደውሉ ።

#9394

🚨 ግንቦት የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ወር !!🗓 በግንቦት ወር የሚታሰበውን የአእምሮ ጤና ግንዛቤን በማስመልከት የአእምሮ ጤናዎን የሚያዳብሩበትን አንዳንድ ዘዴዎች እንንገሮት 👩🏽‍⚕️የአእምሮ ጤና...
30/05/2026

🚨 ግንቦት የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ወር !!

🗓 በግንቦት ወር የሚታሰበውን የአእምሮ ጤና ግንዛቤን በማስመልከት የአእምሮ ጤናዎን የሚያዳብሩበትን አንዳንድ ዘዴዎች እንንገሮት

👩🏽‍⚕️የአእምሮ ጤና የአንድ ግለሰብን ስሜታዊ እና ስነልቦናዊ ደህንነት የሚያመለክት ቃል ነው። ጤናማ የአእምሮ ጤና መኖር በአንፃሩ ደስተኛ እና ጤናማ ህይወት ለመምራት ያግዛል።

👉👉የሚከተሉትን ስልቶች በመጠቀም ጤናማ የአእምሮ ጤናን ማዳበር እንችላለን

📌ነገሮች ላይ አዎንታዊ አመለካከት እንዲኖረን መሞከር

📌የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተር

📌ሰዎችን መርዳት

📌በቂ እንቅልፍ ማግኘት

📌ከምንወደው ሰው ጋር አብረን ጊዜ ማሳለፍ

📌ችግሮችን ለመቋቋም የሚያስችሉ ክህሎቶችን ማዳበር

📌ባስፈለገ ጊዜም በአእምሮ ጤናችን ላይ ባለሙያዎችን ማማከር የአእምሮ ጤናችን እንዲዳብር ያግዛል።

🗣የስነ-አእምሮ ስፔሻሊስት ሐኪም ለማማከር የ WecareET የስልክ መተግበሪያንን በመጠቀም ማማከር ይችላሉ ።

👩‍⚕️👨‍⚕️ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን ለማማከር ☎️ 9394 ላይ ይደውሉ ።


https://youtu.be/2a0p0TQRBts?si=-yfh4Z5umYRXy_Sv
30/05/2026

https://youtu.be/2a0p0TQRBts?si=-yfh4Z5umYRXy_Sv

በዚህ ቪዲዮ ስለ ዲቶክስ (Detox) ወይም ዲቶክሲፊኬሽን (Detoxification) በዝርዝር እናያለን ። 👩‍⚕️👨‍⚕️ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናላችን ሰብስክራይብ ያድርጉ ፣ ለየትኛውም የህክምና...

🚨የደም ግፊትዎን ለመቀነስ የቀይ ስር ጭማቂ አሪፍ እንደሆነ ያውቃሉ?👉በቤትዎ  የቀይ ስር ጭማቂ ለማዘጋጀት ይህን መመሪያ ይከተሉ !🔺1 ወይም 2 መካከለኛ መጠን ያላቸውን ቀይ ስሮች በደንብ ...
29/05/2026

🚨የደም ግፊትዎን ለመቀነስ የቀይ ስር ጭማቂ አሪፍ እንደሆነ ያውቃሉ?

👉በቤትዎ የቀይ ስር ጭማቂ ለማዘጋጀት ይህን መመሪያ ይከተሉ !

🔺1 ወይም 2 መካከለኛ መጠን ያላቸውን ቀይ ስሮች በደንብ አጥበው ይላጡ

🔺ከዚያም ቀይ ስሮቹን በትናንሹ ይከተፉ

🔺የከተፈውን ቀይ ስር 1 ብርጭቆ ውሃ እና እንደ ምርጫዎ ካሮት ወይም አፕል በመጨመር መፍጫ ውስጥ ይክተቱ

🔺ከዚያም በደንብ እስኪልም ድረስ ይፍጩት

🔺ጭማቂው ይበልጥ ለስላሳ እንዲሆን የሚፈልጉ ከሆነ የፈጩትን ጭማቂ በማጥለያ ማጥለል ይችላሉ

🔺ለተጨማሪ ጣዕም 1 የሻይ ማንኪያ የሎሚ ጭማቂ ይጨምሩበት

🔺ከዚያም ጭማቂውን ሳያቆዩ ወዲያውኑ ይጠጡት ምክንያቱም ጭማቂው ለረጅም ጊዜ ከተቀመጠ በውስጡ ያለው የናይትሬት ንጥረ ነገር ኃይሉን ያጣል

🔷እዚህ ላይ ልብ ሊሉት የሚገባው ነገር ዝቅተኛ የደም ግፊት ካለብዎ የቀይ ስር ጭማቂን አዘውትሮ መጠጣት የደም ግፊትዎን ይበልጥ ሊቀንሰው ስለሚችል የደም ግፊትዎን በመለካት መከታተል ይኖርቦታል።

🔷ከዚህም በተጨማሪ ቀይ ስር ከፍተኛ የኦክሳሌት (oxalates) እና የፖታሲየም (potassium) መጠን ስላለው የኩላሊት ችግር ካለብዎ ወይም የደም ግፊት መድኃኒት የሚወስዱ ከሆነ ጭማቂውን በመደበኛነት የአመጋገብዎ አካል ከማድረግዎ በፊት ሐኪምዎን ማማከር አለብዎ።

👩‍⚕️👨‍⚕️ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን ለማማከር ☎️ 9394 ላይ ይደውሉ ።

#9394

🚨በዓለም አቀፍ የወር አበባ ንጽህና አጠባበቅ ቀን ፡ ስለ የወር አበባ ያለውን ዝምታ እንስበር !!🇪🇹 ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ተመጣጣኝ ዋጋ ያላችውን የወር አበባ የንፅህና ምርቶች ማግኘት...
28/05/2026

🚨በዓለም አቀፍ የወር አበባ ንጽህና አጠባበቅ ቀን ፡ ስለ የወር አበባ ያለውን ዝምታ እንስበር !!

🇪🇹 ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ተመጣጣኝ ዋጋ ያላችውን የወር አበባ የንፅህና ምርቶች ማግኘት በኢትዮጵያ አሁንም ትልቅ ፈተና ሆኖ ቀጥሏል።

🌸ወደ 75 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች እና ልጃገረዶች በወር አበባ ጊዜ ንፅህናቸውን የሚጠብቁበት ምርት አያገኙም፤ 25 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የንጽህና መጠበቂያዎችን መግዛት የሚያስችል አቅም የላቸውም።

🌸በዚህም ምክንያት ብዙዎች እንደ ጨርቅ፣ ጋዜጣ ወይም ደረቅ ሣር ያሉ ደህንነታቸው ያልተጠበቁ አማራጮችን እንዲጠቀሙ ይገደዳሉ፤ ይህም ለኢንፌክሽን እና ለሌሎች የጤና እክሎች የመጋለጥ እድላቸውም እጅጉን ይጨምራል።

🌸የንጽህና መጠበቂያ ምርቶች ታሪፍ ቅናሽ እንዲደረግባቸው የተለያዩ ጥረቶች ቢደረግም ዋጋቸው ግን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ብቻ በ75 በመቶ ጨምሯል።

🌸በርካታ ሴቶች የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ምርቶችን በበቂ ሁኔታ ማግኘት አለመቻላቸው በጤናቸውና በሥነ-ልቦናቸው ላይ ከሚያሳድረው ተጽዕኖ ባለፈ በትምህርት ተሳትፎአቸው እና በራስ መተማመናቸው ላይ ከፍተኛ ችግር ያደርሳል።

🌸በሀገራችን ውስጥ ወደ 17 በመቶ የሚሆኑ ልጃገረዶች በወር አበባ ንጽህና አጠባበቅ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው ይቀራሉ። ይህ ቁጥር በአንዳንድ የገጠር አካባቢዎች ወደ 50 በመቶ እንደሚጠጋም ይመገመታል።

🌺የወር አበባ ንጽህና ቅንጦት ሳይሆን ከክብር፣ ከጤና እና ከእኩልነት ጋር የተያያዘ መሠረታዊ ሰብአዊ መብት እንደሆነ በመገንዘብ እያንዳንዱ ሴት እና ልጃገረድ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ተመጣጣኝ እና ክብርን የሚጠብቅ የወር አበባ እንክብካቤ የምታገኝበትን መጪ ጊዜ ለመፍጠር በጋራ መሥራት ይኖርብናል።

👩‍⚕️👨‍⚕️ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን ለማማከር ☎️ 9394 ላይ ይደውሉ ።

#9394

☪️እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ☪️🕋 በዓሉ የደስታ የፍቅር የመተሳሰብ እና የአንድነት እንዲሆንልዎት እንመኛለን። 🎁🎉👩🏽‍⚕️ ጤና ነክ መረጃዎችን ...
27/05/2026

☪️እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ☪️

🕋 በዓሉ የደስታ የፍቅር የመተሳሰብ እና የአንድነት እንዲሆንልዎት እንመኛለን። 🎁🎉

👩🏽‍⚕️ ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን ለማማከር 📞 9394 ላይ ይደውሉ ።

☪️🌙 ኢድ ሙባረክ🌙☪️

#9394

Address

Nigist
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when WeCare ET posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to WeCare ET:

Share