Addis Hiwot General Hospital

Addis Hiwot General Hospital WHERE EVERY LIFE IS VALUED.

Office of the Hospital Administrator
Main Telephone:
Email: [email protected]
Metron Office
Main Telephone: 7560/+251116623916
Email: [email protected]
Reception
+7560
+251923280828
+251116180449
+251116623915
Matron Office

+251116623916
Opthalmology Office

+251985458500
Radiology Department

+251913080585
Medical Director Office

+251116354090

ለዚህም ክብር በመብቃትዎ መላው የሥራ ባልደረቦችዎ የተሰማንን ኩራት እየገለጽን፣ ለቀጣይ የሥራ ዘመንዎ ስኬትንና ጤናን እንመኛለን!የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ባከናወነው 41ኛው የሕክምና ተማሪዎች ም...
19/05/2026

ለዚህም ክብር በመብቃትዎ መላው የሥራ ባልደረቦችዎ የተሰማንን ኩራት እየገለጽን፣ ለቀጣይ የሥራ ዘመንዎ ስኬትንና ጤናን እንመኛለን!

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ባከናወነው 41ኛው የሕክምና ተማሪዎች ምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ፣ ለታዋቂው የቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ዘኪ አብዱራህማን የሙካሽ ካባ እና የጋሻ ሽልማት በማበርከት ታላቅ እውቅና ሰጥቷቸዋል።

ዶ/ር ዘኪ የጉበት፣ የቆሽትና የሀሞት ቀዶ ሕክምና (Hepatobiliary Surgery) ሰብ-ስፔሻሊስት ሲሆኑ፣ በሙያዊ ብቃታቸው ብቻ ሳይሆን ለታካሚዎቻቸው ባላቸው ጥልቅ ተቆርቋሪነት፣ ለተማሪዎቻቸውም ባላቸው አርአያነት በጎንደር ሕዝብና በዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ዘንድ ልዩ ቦታ አላቸው።

በጎንደር ተምረው ለታላቅ ስመ-ጥርነት የበቁት ዶ/ር ዘኪ፣ ዩኒቨርሲቲው "የእኔ እኮ ነው" ከሚላቸው ድንቅ የሕክምና ዕንቁዎች አንዱ ናቸው። ለዚህም ክብር በመብቃትዎ መላው የሥራ ባልደረቦችዎ የተሰማንን ኩራት እየገለጽን፣ ለቀጣይ የሥራ ዘመንዎ ስኬትንና ጤናን እንመኛለን!

እንኳን ደስ አሎት! 💐🎊

አዲስ ህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል
Addis Hiwot General Hospital

Source Hakim

የአጥንትና መገጣጠሚያ (ኦርቶፔዲክስ) ሕክምና ክፍል                                    👨‍⚕️ ዶ/ር ጌታሁን ገብረእግዚአብሔር  🗓 የሥራ ቀናት ሰኞ፣ ረቡዕና፣ ሐሙስና ቅ...
18/05/2026

የአጥንትና መገጣጠሚያ (ኦርቶፔዲክስ) ሕክምና ክፍል

👨‍⚕️ ዶ/ር ጌታሁን ገብረእግዚአብሔር

🗓 የሥራ ቀናት
ሰኞ፣ ረቡዕና፣ ሐሙስና ቅዳሜ

👨‍⚕️ዶ/ር ባሕሩ በዛብህ

🗓 የሥራ ቀናት
ሰኞ፣ ረቡዕና ቅዳሜ

👨‍⚕️ ዶ/ር አስፋው አየለ

🗓 የሥራ ቀናት
ማክሰኞ፣ ሐሙስና ዓርብ

አዲስ ህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል
Addis Hiwot General Hospital

ለበለጠ መረጃና ቀጠሮ ለማስያዝ
📞 7560 ላይ ይደውሉልን!

📍አድራሻ: ሀያ ሁለት፣ ከጌታሁን በሻ ህንፃ ጀርባ

ዓለም አቀፍ የነርሶች ቀን ዛሬ ዓለም አቀፍ የነርሶች ቀን ሲከበር፣ በታካሚዎቻችን ፊት ላይ ፈገግታ እንዲመለስ ሌት ተቀን በቁርጠኝነት ለምትደክሙ ነርሶቻችን ልዩ አክብሮትን እናቀርባለን። ነር...
12/05/2026

ዓለም አቀፍ የነርሶች ቀን

ዛሬ ዓለም አቀፍ የነርሶች ቀን ሲከበር፣ በታካሚዎቻችን ፊት ላይ ፈገግታ እንዲመለስ ሌት ተቀን በቁርጠኝነት ለምትደክሙ ነርሶቻችን ልዩ አክብሮትን እናቀርባለን።

ነርሶች የጤና አገልግሎታችን ምሰሶዎች ብቻ ሳይሆኑ፣ ለታካሚዎቻችን የተስፋ እና የፈውስ ድልድዮችም ናቸው።

መልካም የነርሶች ቀን!

አዲስ ህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል
Addis Hiwot General Hospital

ለበለጠ መረጃና ቀጠሮ ለማስያዝ
📞 7560 ላይ ይደውሉልን!

📍አድራሻ: ሀያ ሁለት፣ ከጌታሁን በሻ ህንፃ ጀርባ

የአለም አቀፍ የእናቶች ቀን እናቶች የማኅበረሰባችን የጥንካሬ ምንጭ፣ የቤተሰብ ምሰሶ እና የጤናማ ትውልድ መሠረት ናቸው።አዲስ ሕይወት አጠቃላይ ሆስፒታል፣ እናቶች ለሰው ልጅ ደህንነት እና ለ...
10/05/2026

የአለም አቀፍ የእናቶች ቀን

እናቶች የማኅበረሰባችን የጥንካሬ ምንጭ፣ የቤተሰብ ምሰሶ እና የጤናማ ትውልድ መሠረት ናቸው።

አዲስ ሕይወት አጠቃላይ ሆስፒታል፣ እናቶች ለሰው ልጅ ደህንነት እና ለትውልድ ግንባታ የሚያበረክቱትን የማይተካ ሚና እና የሚከፍሉትን የላቀ መስዋዕትነት በታላቅ አክብሮት ያስባል። ሆስፒታላችን በተለይም በእናቶች ጤና (Maternal Health) ዙሪያ ያለውን ዘመናዊ የሕክምና አገልግሎት ይበልጥ በማጠናከር፣ የእናቶችን ደህንነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል።

በዛሬው ዕለት የሚከበረውን የአለም አቀፍ የእናቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ፣ ለእናቶቻችን በሙሉ ያለንን ጥልቅ ፍቅር እየገለጽን፤ ለእናንተ ለብርቱዎቹ እናቶቻችን መልካም ጤንነትን፣ ረጅም ዕድሜን እና ደስታን እንመኛለን።

አዲስ ህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል
Addis Hiwot General Hospital

📍አድራሻ: ሀያ ሁለት፣ ከጌታሁን በሻ ህንፃ ጀርባ

የአእምሮ ጤና ለሁሉም! 🧠💚ግንቦት የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ወር ነው። ብዙ ጊዜ ለአካላዊ ጤንነታችን የምንጨነቀውን ያህል ለአእምሮአችን ጤንነት ትኩረት ላንሰጥ ይችላል። ነገር ግን "ጤና" ማለት...
08/05/2026

የአእምሮ ጤና ለሁሉም! 🧠💚

ግንቦት የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ወር ነው። ብዙ ጊዜ ለአካላዊ ጤንነታችን የምንጨነቀውን ያህል ለአእምሮአችን ጤንነት ትኩረት ላንሰጥ ይችላል። ነገር ግን "ጤና" ማለት የአካልና የአእምሮ ሰላም ድምር ውጤት ነው።
የአእምሮ ጤና ችግር በማንም ላይ ሊከሰት የሚችል እና በህክምና ሊድን የሚችል መሆኑን ማወቅ ትልቅ ለውጥ ያመጣል።

✅ ከመጠን በላይ መጨነቅ
✅ የድብርት ስሜት
✅ የእንቅልፍ መዛባት ወይም
✅ ተከታታይነት ያለው የባህሪ ለውጥ ካጋጠመዎት

አዲስ ህይወት ጠቅላላ ሆስፒታል ሙያዊ ድጋፍ እና የምክር አገልግሎት ለመስጠት ሁልጊዜም ከጎንዎ ነው።

ለበለጠ መረጃና ቀጠሮ ለማስያዝ
📞 7560 ላይ ይደውሉልን!

📍አድራሻ: ሀያ ሁለት፣ ከጌታሁን በሻ ህንፃ ጀርባ

አስም የመተንፈሻ ትቦዎች በሚቆጡበት፣ በሚያብጡበትና በሚጠቡበት ጊዜ አየር ወደ ሳንባ በቀላሉ እንዳይገባና እንዳይወጣ የሚያደርግ የመተንፈሻ አካላት የጤና እክል ነው። የአስም ትክክለኛ መንስኤ...
05/05/2026

አስም የመተንፈሻ ትቦዎች በሚቆጡበት፣ በሚያብጡበትና በሚጠቡበት ጊዜ አየር ወደ ሳንባ በቀላሉ እንዳይገባና እንዳይወጣ የሚያደርግ የመተንፈሻ አካላት የጤና እክል ነው።

የአስም ትክክለኛ መንስኤ በውል ባይታወቅም፣ የዘር ውርስ/Genetics እና አካባቢያዊ ሁኔታዎች (Environmental Triggers) ለዚህ ሁኔታ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው::

የሚከተሉት ምልክቶች በተደጋጋሚ ይታዩብዎታል?
🔹 የትንፋሽ ማጠር
🔹 በደረት ላይ የሚሰማ የመጨምደድ ወይም የማፈን ስሜት
🔹 ሳል (በተለይ ሌሊት እና ማለዳ ላይ)
🔹 በሚተነፍሱበት ወቅት የሚሰማ የፉጨት ድምፅ

አስም የእለት ተእለት እንቅስቃሴዎን እንዲያስተጓጉል አይፍቀዱ። በትክክለኛ ክትትልና ጥንቃቄ ሙሉ በሙሉ ሊቆጣጠሩት የሚችሉት የጤና ሁኔታ ነው።

ወደ አዲስ ህይወት ጠቅላላ ሆስፒታል በመምጣት በዘመናዊ የምርመራ መሳሪያዎች በእስፔሻሊስት ሐኪም የታገዘ የምክር እና የህክምና ክትትል ያግኙ።

ለበለጠ መረጃ
📞 7560 ላይ ይደውሉልን!

📍አድራሻ: ሀያ ሁለት፣ ከጌታሁን በሻ ህንፃ ጀርባ

የማህፀንና ፅንስ ህክምና ክፍል 👨‍⚕️ ዶ/ር ተስፋዬ ኃይለስላሴ የማህፀንና ፅንስ ህክምና እስፔሻሊስት ሐኪም 🗓 የስራ ቀናትከሰኞ እስከ ቅዳሜ 3:00 - 11:00👨‍⚕️ ዶ/ር ትእዛዙ አለሙ ...
04/05/2026

የማህፀንና ፅንስ ህክምና ክፍል

👨‍⚕️ ዶ/ር ተስፋዬ ኃይለስላሴ
የማህፀንና ፅንስ ህክምና እስፔሻሊስት ሐኪም

🗓 የስራ ቀናት
ከሰኞ እስከ ቅዳሜ 3:00 - 11:00

👨‍⚕️ ዶ/ር ትእዛዙ አለሙ
የማህፀንና ፅንስ ህክምና እስፔሻሊስት ሐኪም

🗓 የስራ ቀናት
ከሰኞ እስከ ቅዳሜ 3:00 - 11:00

👨‍⚕️ ዶ/ር ስመኘው ጥላሁን
የማህፀንና ፅንስ ህክምና እስፔሻሊስት ሐኪም

🗓 የስራ ቀናት
ከሰኞ እስከ ቅዳሜ 3:00 - 11:00

👨‍⚕️ ዶ/ር እያሱ መስፍን
የማህፀንና ፅንስ ህክምና እስፔሻሊስት፣ የመካንነት ህክምና ሰብ-እስፔሻሊስት ሐኪም

🗓 የስራ ቀናት: ረቡዕ

👨‍⚕️ ዶ/ር እስክንድር ከበደ
የማህፀንና ፅንስ ህክምና እስፔሻሊስት፣ የመካንነት ህክምና ሰብ-እስፔሻሊስት ሐኪም

🗓 የስራ ቀናት: ረቡዕ

ለበለጠ መረጃና ቀጠሮ ለማስያዝ
📞 7560 ላይ ይደውሉልን!

📍አድራሻ: ሀያ ሁለት፣ ከጌታሁን በሻ ህንፃ ጀርባ

ጤናዎን በቅርበት ለመከታተል እና ትክክለኛውን የህክምና ውሳኔ ለመስጠት እንዲቻል፤ ሆስፒታላችን ዘመናዊ እና ጥራት ያላቸውን አዳዲስ የላቦራቶሪ ምርመራዎች በከፍተኛ ጥራት መጀመሩን በደስታ እን...
01/05/2026

ጤናዎን በቅርበት ለመከታተል እና ትክክለኛውን የህክምና ውሳኔ ለመስጠት እንዲቻል፤ ሆስፒታላችን ዘመናዊ እና ጥራት ያላቸውን አዳዲስ የላቦራቶሪ ምርመራዎች በከፍተኛ ጥራት መጀመሩን በደስታ እንገልፃለን::

🧪 የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ መጠን (HBV Viral load)
🧪 የሄፓታይተስ ሲ ቫይረስ መጠን (HCV Viral load)
🧪 የኤች አይ ቪ (HIV) ቫይረስ መጠን (HIV Viral load)
🧬 GeneXpert ምርመራ: ለፈጣን የሳንባ ነቀርሳ (TB) እና መድኃኒት የለመደ የቲቢ በሽታን ለመለየት የሚረዳ ዘመናዊ ምርመራ

ለበለጠ መረጃና ቀጠሮ ለማስያዝ
📞 7560 ላይ ይደውሉልን!

📍አድራሻ: ሀያ ሁለት፣ ከጌታሁን በሻ ህንፃ ጀርባ

የሽንት ቧንቧ ፣ ፊኛ እና ኩላሊት (Urology ) ህክምና ክፍል👨‍⚕️ ፕሮፌሰር አንዱአለም ደነቀ የሽንት ቧንቧ ፣ ፊኛ እና ኩላሊት ቀዶ-ህክምና ሰብ-እስፔሻሊስት ሐኪም 👨‍⚕️ ዶ/ር ተክለ...
27/04/2026

የሽንት ቧንቧ ፣ ፊኛ እና ኩላሊት (Urology ) ህክምና ክፍል

👨‍⚕️ ፕሮፌሰር አንዱአለም ደነቀ
የሽንት ቧንቧ ፣ ፊኛ እና ኩላሊት ቀዶ-ህክምና ሰብ-እስፔሻሊስት ሐኪም

👨‍⚕️ ዶ/ር ተክለብርሃን በርሄ
የሽንት ቧንቧ ፣ ፊኛ እና ኩላሊት ቀዶ-ህክምና እስፔሻሊስት እንዲሁም የኩላሊት ንቅለ-ተከላ እስፔሻሊስት ሐኪም

🗓 የስራ ቀናት: ማክሰኞ ፣ ረቡዕ ፣ አርብና ቅዳሜ

👨‍⚕️ ዶ/ር ሀብታሙ አደራው
የሽንት ቧንቧ ፣ ፊኛ እና ኩላሊት ቀዶ-ህክምና እስፔሻሊስት ሐኪም

🗓 የስራ ቀናት:
ማክሰኞ፣ ረቡዕ፣ አርብ እና ቅዳሜ

👨‍⚕️ዶ/ር አድማሱ መላኩ
የሽንት ቧንቧ ፣ ፊኛ እና ኩላሊት ቀዶ-ህክምና እስፔሻሊስት ሐኪም

🗓 የስራ ቀናት: ሰኞና ሀሙስ

👨‍⚕️ ዶ/ር ማስረሻ
የሽንት ቧንቧ ፣ ፊኛ እና ኩላሊት ቀዶ-ህክምና እስፔሻሊስት ሐኪም

🗓 የስራ ቀናት: ሰኞ

አዲስ ህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል
Addis Hiwot General Hospital

ለበለጠ መረጃና ቀጠሮ ለማስያዝ
📞 7560 ላይ ይደውሉልን!

📍አድራሻ: ሀያ ሁለት፣ ከጌታሁን በሻ ህንፃ ጀርባ

🌍 የዓለም የክትባት ሳምንት 2026! 💉✨ 📢 "በክትባት ጤናማ ትውልድን እንገንባ!"ክትባት በሽታን ለመከላከልና ሕይወትን ለማዳን ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። ራሳችንን እና የምንወዳቸውን ሰዎች ...
24/04/2026

🌍 የዓለም የክትባት ሳምንት 2026! 💉✨
📢 "በክትባት ጤናማ ትውልድን እንገንባ!"

ክትባት በሽታን ለመከላከልና ሕይወትን ለማዳን ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። ራሳችንን እና የምንወዳቸውን ሰዎች ከተላላፊ በሽታዎች ለመጠበቅና ጤናማ ማህበረሰብን ለመፍጠር ይረዳል።

በዚህ የክትባት ሳምንት፣ የእርስዎንና የልጆችዎን የክትባት ካርድ በመፈተሽ አስፈላጊ የሆኑ ክትባቶች በወቅቱ መሰጠታቸውን ያረጋግጡ።
ስለ ክትባቶች አስፈላጊነት ግንዛቤዎን በማሳደግ ለሚወዷቸው ሰዎች ደህንነት የበኩሎን ይወጡ።

አዲስ ህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል
Addis Hiwot General Hospital

ለበለጠ መረጃና ቀጠሮ ለማስያዝ
📞 7560 ላይ ይደውሉልን!

📍አድራሻ: ሀያ ሁለት፣ ከጌታሁን በሻ ህንፃ ጀርባ

እነዚህን 5 ነገሮች በማስተካከል የስትሮክ ስጋትን ይቀንሱ (Modifiable Risk Factors)ስትሮክ በድንገት የሚመጣ ቢመስልም፣ በአብዛኛው ቀድመን መከላከል የምንችላቸው ጤናማ ያልሆነ ...
22/04/2026

እነዚህን 5 ነገሮች በማስተካከል የስትሮክ ስጋትን ይቀንሱ (Modifiable Risk Factors)

ስትሮክ በድንገት የሚመጣ ቢመስልም፣ በአብዛኛው ቀድመን መከላከል የምንችላቸው ጤናማ ያልሆነ የአኗኗር ዘይቤ ውጤት ነው።

ዛሬ የምናደርገው ጥንቃቄ እኛንና የምንወዳቸውን ሰዎች ከድንገተኛ ህመምና ሞት ሊታደግ ይችላል።

1. ጤናማ አመጋገብ፦ የጨው፣ የቅባት እና የጣፋጭ ምግቦችን መቀነስ በአትክልትና ፍራፍሬ የበለፀጉ ምግቦችን ያዘውትሩ።

2. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፦ በቀን ቢያንስ ለ30 ደቂቃ በእግር መጓዝ ወይም ቀለል ያሉ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ የደም ዝውውርን ያሻሽላል።

3. ከሲጋራ፣አልኮልና ከጫት መራቅ

4. የደም ግፊት፣ ስኳር ህመም፣ ልብ ህመም ቆሚ የህክምና ክትትል ማድረግና መቆጣጠር

5. ጤናማ የሰውነት ክብደት፦ ከመጠን ያለፈ ውፍረትን መቀነስ ለልብና ለአንጎል ጤንነት ወሳኝ ነው።

⚠️ ጥንቃቄ! እነዚህ ምልክቶች ከታዩ በአስቸኳይ ወደ ህክምና ተቋም ያምሩ!

✅ የፊት መጣመም
✅ የእጅ ወይም የእግር መስነፍ
✅ ለመናገር መቸገር
✅ ድንገተኛ የሆነ ከፍተኛ የራስ ምታት እና የዕይታ መጋረድ

ምልክቶቹን ካዩ "ይለቀኛል" ብለው ሳይዘናጉ በአስቸኳይ ወደ ህክምና ተቋም ያምሩ!

አዲስ ህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል
Addis Hiwot General Hospital

ለበለጠ መረጃና ቀጠሮ ለማስያዝ
📞 7560 ላይ ይደውሉልን!

📍አድራሻ: ሀያ ሁለት፣ ከጌታሁን በሻ ህንፃ ጀርባ

Address

Haile Gebre Silase Street
Addis Ababa
170023

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Hiwot General Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Addis Hiwot General Hospital:

Share

Category