04/06/2026
የትክሻ ህመም መንስኤዎች ምንድን ናቸው?
የትክሻ ህመም በዕድሜ፣ በጉዳት ወይም በተለያዩ የመገጣጠሚያና የጡንቻ ችግሮች ሊከሰት ይችላል። ከተለመዱት መንስኤዎች መካከል፦
✅ የጡንቻ ወይም የጅማት ጉዳት
✅ የትክሻ መገጣጠሚያ ብግነት (Arthritis)
✅ የ Rotator Cuff ጉዳት
✅ Frozen Shoulder (የትክሻ መደንዘዝ)
✅ የትክሻ አውልቃ ወይም ስብራት
✅ ከአንገት አከራካሪ ነርቮች የሚመነጭ ህመም (Cervical Radiculopathy)
👉ህመሙ ከቀጠለ፣ እጅዎን ማንቀሳቀስ ካስቸገረዎ ወይም በዕለታዊ እንቅስቃሴዎ ላይ ተጽዕኖ ካሳደረ፣ የአጥንትና መገጣጠሚያ ሐኪምን ያማክሩ።
👉 ቀደም ብሎ የሚደረግ ምርመራ ችግሩን በትክክል ለመለየት እና ተገቢውን ህክምና በጊዜው ለማግኘት ይረዳል።
🩺 ጤናዎን ይጠብቁ — ህመምን ችላ አይበሉ!
Birlew Teshome