Dr. Seife ዶ/ር ሰይፈ

Dr. Seife ዶ/ር ሰይፈ 🔴 ለህክምና ቀጠሮ 09 74 16 34 24
(1)

13/04/2026

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ

*Profession - Nurse BSC or diploma
* Required - 2
*Experiance - 6 month and above
*Place of work - Osler dermatovenerology Speciality Clinic,
* Address - CMC, Meri
* Salary - Negotiable
Interested applicants can send their CV with contact information telegram using the following number 0974163424

07/01/2025
18/04/2024
14/04/2024

የዘንድሮ ቫይታሚን ዲ

26/02/2024

I've received 75,000 reactions to my posts in the past 30 days. Thanks for your support. 🙏🤗🎉

17/02/2024

የወገብ ህመም

15/02/2024
➕➕ የነርቭ ህመም ➕➕ 🖲የነርቭ ህመም፣  በአንድ የህመም ምልክት ብቻ የሚገለፅ ህመም አይደለም፣ እንደ ቦታው እና እነደ ነርቭ ጉዳቱ ደረጃ፣ በተለያየ አይነት የህመም ምልክቶች ይገለፃል። 🖲...
10/01/2024

➕➕ የነርቭ ህመም ➕➕

🖲የነርቭ ህመም፣ በአንድ የህመም ምልክት ብቻ የሚገለፅ ህመም አይደለም፣ እንደ ቦታው እና እነደ ነርቭ ጉዳቱ ደረጃ፣ በተለያየ አይነት የህመም ምልክቶች ይገለፃል።

🖲መቆጥቆጥ፣ ማቃጠል፣ መለብለብ ፣መደንዘዝ ፣መዛል ፣ እና ከአቅም ማጣት ጀምሮ እስከ ራስ መሳት ድረስ ሁሉ ያሉ የህመም ምልክቶች ፣በነርቭ ህመም ተጠቂዎች ሊገለፁ ይችላሉ።

🖲ነርቭ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰ፣ አንዳንዴ፣ በህክምና እንኳን መመለስ ስለማይቻል ፣ ብዙ ሰዎችን ዘላቂ ለሆነ የአካል ጉዳት ይዳርጋል።

🖲ጉዳቱ አነስተኛ ከሆነ ደሞ፣ እንደ ተጎዳው ነርቭ እና፣ ጉዳቱን እንዳስከተለው በሽታ፣ በህክምና ፣ ወደነበረበት መመለስም ይቻላል።

🖲አንድ ሰው ላይ፣ ባጋጣሚ ከሚደርስ አደጋ አንስቶ በቂ ክትትል በሌላቸው ስር ሰደድ በሽታዎችም ጭምር የነርቭ ህመም ሊጀምር ይችላል።

🖲አንድ ጤናማ ሰው ላይ ያለ የነርቭ አካል አፈጣጠር በአቀማመጡ በሁለት ይከፈላል፣ ማእከላዊ የነርቭ አካል እና ውጫዊ የነርቭ አካል።

🖲ማእከላዊ የነርቭ አካል ማለት፣ አይምሮ እና ሀብለ ሰረሰር ናቸው። ውጫዊ የነርቭ አካሎች ደሞ፣ ከአይምሮ እና ከ ሀብለ ሰረሰር የሚነሱ የነርቭ መስመሮች ናቸው።

🖲አይምሮ ውስጥ ያሉ የነርቭ ህዋሶች በከፍተኛ ደረጃ ሲጎዱ ራሳቸውን መልሶ የማደስ ብቃታቸው አነስተኛ ስለሆነ አይምሮ ላይ የሚደርስ ጠንከር ያለ የነርቭ ጉዳት ሲኖር ዘላቂ ለሆነ ወይም በህክምና ለማይመለስ የአካል ጉዳት ሊዳርግ ይችላል።

🖲ከአይምሮ እና ከሀብለሰረሰር ውጪ ያሉ የነርቭ መስመሮች ደሞ፣ እንደ ጉዳት ደረጃቸው ራሳቸውን የማደስ የተወሰነ አቅም አላቸው።

🖲አብዛኛውን ግዜ፣ ቀለል ያለ እና መካከለኛ የጉዳት ደረጃ የደረሰባቸው ከሆነ በግዜ ሂደት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የሚያገግሙ ይሆናሉ።

🖲ነገር ግን፣ አንዳንዴ እነዚህ የነርቭ መስመሮች ላይ የሚደርሰው አደጋ ከፍተኛ ከሆነ፣ ጉዳቱ የነርቭ መስመሮቹ ራሳቸውን ከሚያድሱበት አቅም በላይ ስለሚሆን ዘላቂ ለሆነ የአካል ጉዳት ሊዳርጉ ይችላሉ።

🖲የነርቭ ህመም በተለያዩ አደጋዎች እና የውስጥ ደዌ በሽታዎች ምክኒያት ሊከሰት ይችላል፣ የነርቭ ህመሙ በአደጋ ምክኒያት ሲጎዳ፣ ነርቩ ሊጨፈለቅ፣ በከፍፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ሊቆረጥ ይችላል።

🖲ስርሰደድ በሽታዎችን ተከትለው የሚመጡ የነርቭ ህመሞች፣ ለምሳሌ፣ የስኳር በሽታን ተከትሎ የሚመጣ የነርቭ ህመም፣ ከእይታ ድክመት ጀምሮ እንደ ደረጃው በብዙ መንገድ ሊገለፅ ይችላል፣

🖲ነገር ግን አብዛኛውን ግዜ ፣ ከጉልበት በታች በሁለቱም እግር ላይ የሚሰማ የመለብለብ እና የማቃጠል ስሜት በተለይ ከመሀል እግር ጀምሮ ወደላይ ከፍ እያለ የሚሄድ የህመም አይነት ይሰማቸዋል።

🖲ከዚህ ውጪ ፣ ለምሳሌ፣ በአልኮል ጥገኝነት፣ በቫይታሚን ቢ እጥረት፣ በመመረዝ፣ በታይሮይድ ህመም እና በተለያዩ ኢንፌክሽኖችም ጭምር የሚመጡ ሌሎች አሳሳቢ የሆኑ የነርቭ ህመም አይነቶችም አሉ።

⭕️የነርቭ ህመምን በተመለከተ፣ ሰፋ ያለ መረጃ በ YouTube ቻናሌ ላይ አስቀምጫለሁ፣ የሚቀጥለውን ማስፈንጠሪያ ተጭናችሁ መመልከት ትችላላችሁ። መልካም ግዜ!!
👇👇👇👇👇👇👇

እኔን በስልክ ለማማከር የምትፈልጉ ዘወትር ቅዳሜ ከ 9 እስከ 11 ሰዐት ብቻ መደወል ትችላላችሁ። 0974163424 ወይም ደሞ በአካል ቀርቦ ለመታየት በዚሁ ቁጥር ቴሌግራም ላይ ቀጠሮ ማስያዝ ይቻላል።...

➕➕ቋቁቻ ➕➕🖲 ቋቁቻ እና ጭርት ሊመሳሰሉ ይችላሉ ፣ ነገር ግን፣ ሁለቱም  የተለያየ ዝርያ ባለው ተህዋስ የሚፈጠሩ የቆዳ በሽታዎች ናቸው፣ 🖲 ቋቁቻ ከሰው ወደሰው አይተላለፍም፣ ጭርት ከሆነ ...
24/12/2023

➕➕ቋቁቻ ➕➕

🖲 ቋቁቻ እና ጭርት ሊመሳሰሉ ይችላሉ ፣ ነገር ግን፣ ሁለቱም የተለያየ ዝርያ ባለው ተህዋስ የሚፈጠሩ የቆዳ በሽታዎች ናቸው፣

🖲 ቋቁቻ ከሰው ወደሰው አይተላለፍም፣ ጭርት ከሆነ ግን ከሰው ወደሰው ብቻ ሳይሆን ከእንስሳት ወደሰውም ጭምር በንክኪ መተላለፍ ይችላል።

🖲 ቋቁቻን የሚያስከትለው ተህዋስ፣ አንድ ጤናማ ሰው ቆዳ ላይ፣ ምንም አይነት ቋቁቻን ሳያስከትል ፣ ልከኛ በሆነ መንገድ በተፈጥሮ የሚኖር ተህዋስ ነው፣በህክምናው malassezia ተብሎ ይጠራል።

🖲በተለያዩ ምክኒያቶች ፣ይህ ተህዋስ ከልክ ባለፈ መልኩ ቆዳ ላይ ማደግ ሲጀምር እና የላይኛውን ቆዳ ሲያጠቃ፣ በቦታው ላይ ቋቁቻን ይፈጠራል።

🖲 ይህ ቋቁቻን የሚያስከትል ተህዋስ፣ የተለያዩ ዝርያዎች ያሉት ቢሆንም፣ ነገር ግን፣ አንድ ሰው ላይ ቋቁቻን ሊፈጥሩ የሚችሉት በዋነኝነት 3 አይነት ዝርያዎች ናቸው።

እነዚህ ዝርያዎች፣ አንድ ሰው ቆዳ ላይ ፣ ቋቁቻን የሚያስከትሉበት የተለያየ ምክኒያት አላቸው፣

👉 ወዛም የሆኑ ሰዎች፣ ሞቃታማ ቦታ የሚኖሩ ከሆነ እና ፣ የንፅህና ጉድለት ካላቸው
👉ዘይታማ ቅባቶችን ቆዳ ላይ አዘውትሮ በመቀባት
👉የአንድ ሰው የበሽታ መከላከል አቅም ሲቀንስ
👉እንደ ደርሞቬት ፣ቤትኖቬት፣ ቤታሴት የመሳሰሉትን መዳኒቶች ፣ ከሀኪም ትእዛዝ ዉጪ ለረጅም ግዜ አዘውትሮ በመቀባት
👉ጥራታቸውን ያልጠበቁ እና ፊትን የሚያቀሉ ክሬሞችን ማዘውተር የመሳሰሉት፣ አንድ ሰው ላይ በተደጋጋሚ ግዜ ቋቁቻ እንዲወጣ የሚያደርጉ ምክኒያቶች ናቸው።

🖲 ቋቁቻ በቆዳ ላይ ሲወጣ፣ ነጣ ያለ ወይም ደሞ ጠቆር ያለ ገፅያን ሊይዝ ይችላል፣ አብዛኛውን ግዜ ደሞ፣ ከሌላው የሰውነት ክፍል ይልቅ፣ ወዝ በበዛበት የቆዳ ክፍል ላይ የመውጣት ባህሪ አለው።

🖲 ፊት ላይ የሚወጣ ቋቁቻ ፣ አብዛኛውን ግዜ በአዋቂዎች ላይ የተለመደ አይደለም፣ ነገር ግን፣ ካዋቂዎች ይልቅ አንዳንዴ የልጆች ፊት ላይ ሊያጋጥም ይችላል።

🖲 ቋቁቻ መሆኑን ለመለየት ፣ አንድ ሰው ከታጠበ በኋላ ምንም አይነት ቅባት ሳይቀባ፣ ቋቁቻው በወጣበት ዙሪያ ያለውን ቆዳ በመለጠጥ ፣ወይም ደሞ ፣ቋቁቻው ሲታከክ፣ አመድ የመምሰል ገፅታን ይሰጣል።

🖲 እየከሰመ ያለ ቋቁቻ ሲሆን ደሞ፣ አብዛኛውን ግዜ አመድ የመምሰል ባህሪ ላይኖረው ይችላል።

⭕️ታዲያ ቋቁቻን ለማጥፋት የሚያስፈልገው መዳኒት ምንድነው? በቤት ውስጥ ቀምሞ መጠቀም የሚቻል ውህድስ አለ?

🔴የቋቁቻ ህክምናን በተመለከተ ሰፋ ያለ መረጃ በ YouTube ላይ አስቀምጫለው። ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን መመልከት ትችላላችሁ። መልካም ግዜ።
👇👇👇👇👇👇👇

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr. Seife ዶ/ር ሰይፈ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category