Dr K Health Media

Dr K Health Media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dr K Health Media, Medical and health, Addis Ababa.

“Dr. K Health Media is Ethiopia’s authoritative Health Education and Systems reform platform delivering evidence-based, policy-aligned, and ethically grounded health Information.”

04/07/2026
✨Did you know that July 2nd, is National Doctors’ Day in Ethiopia? Often called National Hakims Day, this date marks a m...
01/07/2026

✨Did you know that July 2nd, is National Doctors’ Day in Ethiopia? Often called National Hakims Day, this date marks a monumental milestone in the country’s history.
Here is why today is so special:

🗓 On July 2nd, Ethiopia celebrates the graduation anniversary of its very first batch of home trained modern medical doctors.

This pioneering class graduated from the Gondar College of Medical Sciences (originally the Public Health College founded in 1954) and the Tikur Anbessa Specialized Hospital under Addis Ababa University, which officially opened its medical school gates in the mid-1960s. These institutions laid the blueprint for modern healthcare training across the nation.

Long before these schools, trailblazers like Hakim Workneh Eshete (Dr. Charles Martin)—the first Ethiopian western-educated physician—paved the way for generations of brilliant Ethiopian medical professionals to serve their community.

To all the Hakims keeping the nation healthy, thank you for your selfless service!
Ethiopian Medical Association

Via;  Ministry of Health,Ethiopia ለ175 የልብ ህሙማን ህጻናት ነጻ የልብ ቀዶ ህክምና ለመስጠት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ __________የመግባቢያ ሰነዱ በጤ...
16/04/2026

Via; Ministry of Health,Ethiopia

ለ175 የልብ ህሙማን ህጻናት ነጻ የልብ ቀዶ ህክምና ለመስጠት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ
__________

የመግባቢያ ሰነዱ በጤና ሚኒስቴር እና የልብ ቀዶ ህክምና አጋር በሆኑ የግል እና የመንግስት ሆስፒታሎች የተፈረመ ሲሆን፤ ነጻ የልብ ቀዶ ህክምና ዘመቻው ከሚያዝያ 12 ጀምሮ ለ45 ቀናት በግል እና በመንግስት ሆስፒታሎች የሚሰጥ ይሆናል።

የመግባቢያ ሰነዱን ከጤና ሚኒስቴር ጋር የተፈራረሙት የኸርት ቱ ኸርት ችልድረን ኤይድ፣ የኢትዮጵያ የልብ ማህበር፣ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እና ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ፣ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ የቅዱስ ዼጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ የኢትዮ-ኢስታንቡል ሆስፒታል፣ የኤልውዘር የልብ ህክምና ማዕከል እና የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን መርጃ ናቸው።

የልብ ቀዶ ህክምና ዘመቻው በዘርፉ ያለውን ጫና ለማቃለል የጎላ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው የተናገሩት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፤ የመንግስት እና የግል ተቋማት በትብብር ሲሰሩ ዘለቄታዊ ለውጥ እንደሚያመጣ ገልፀው፣ የመግባቢያ ሰነዱን የፈረሙ አካላትን አመስግነዋል፡፡

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እና ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ዋና ፕሮቮስት ዶ/ር ሙሉቀን ተስፋዬ እና የኸርት ቱ ኸርት ችልድረን ኤይድ ድርጅት መስራች አቶ ብርሀን ተድላ የመንግስት እና የግል ዘርፍ በትብብር መስራት እውቀትን፣ ልምድን እና ሀብትን በመካፈል ሀገራዊ የልብ ህክምና አቅምን ለመገንባት ይጠቅማል ብለዋል።

በተጨማሪም በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ለ20 የልብ ህሙማን ህጻናት ህክምናው የሚሰጥ ሲሆን፤ ይህም በአጠቃላይ አገልግሎቱን የሚያገኙ ህጻናት ቁጥርን ወደ 195 ከፍ ያደርጋል፡፡

ለነፃ የልብ ህክምና ዘመቻ የሚውለው ግብዓት በኸርት ቱ ኸርት ችልድረን ኤይድ ድርጅት የሚቀርብ ይሆናል።

Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

28/03/2026

በጤናው ዘርፍ የሪፎርም ስራዎችን ለማፅናት የብቃትና የሰዉ ሃብት አስተዳደር ዘርፍ የተያዙ ግቦችን ማሳካት ያስፈልጋል
___________

በጤና ሚኒስቴር የብቃትና የሠው ሀብት አስተዳደር የ2018 ዓ ም የመጀመሪያው ግማሽ አመት የአፈፃፀም እንዲሁም የጤናው ዘርፍ የሪፎርም ትግበራ አፈፃፀም ላይ በድሬደዋ የተካሄደዉ መድረክ ተጠናቋል።

የጤናው ዘርፍ የብቃትና የሰው ሀብት አስተዳደር የአፈፃፀም የጋራ መድረክ የጤና ሚኒስቴር፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮዎች፣ የጤና ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት እና የፌደራል ሆስፒታሎች የብቃትና የሠው ሀብት አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች እና ተወካዮች በተገኙበት ተካሄዷል።

ውይይቱን በይፋ የከፈቱት ዶ/ር ፅጌረዳ ክፍሌ የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ እንደተናገሩት እንደሀገር ተግባራዊ ለሚደረገው ሪፎርም የጤናው ዘርፍ የመንግስት አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ ውስጥ እንዲካተት መመረጡን ገልጸው ይህም ትልቅ ስኬት መሆኑን አንስተዋል።

ይህንን በጤናው ዘርፍ የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎችን ክልሎችም ወጥ የሆነ ሪፎርም አተገባበርን በመከተል ወደ ትግበራ ለማድረስ በቅንጅት መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የጤና ሚኒስቴር የብቃትና የሰው ሀብት አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ደምሴ እንደገለጹት መድረኩ ባለፉት ስድስት ወራት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠልና ውስንነቶችን በመለየት በቀጣዩ ግማሽ ዓመት በተሻለ አፈፃፀም አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ ያለመ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን አያይዘውም በመድረኩ የሚገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በመቀመርና ልምድ በመለዋወጥ ለተሻለ አፈፃፀም ዝግጅት እንደሚደረግ ገልፀዋል።

በመድረኩ የክልልና የከተማ መስተዳድሮች የ6 ወራት የሰው ሀብት ሥራ አፈፃፀም ሪፖርቶች በተጨማሪም የጤናው ዘርፍ አስተዳደርና ኣገልግሎት ሪፎርም ያለበት ደረጃ ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
Ministry of Health,Ethiopia

Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

Address

Addis Ababa
1000

Telephone

+251912433818

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr K Health Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Dr K Health Media:

Shortcuts

Share