ሚና ባህላዊ ህክምና -Mina Tradetional medicenሚና ኑሩ

ሚና ባህላዊ ህክምና -Mina Tradetional medicenሚና ኑሩ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ሚና ባህላዊ ህክምና -Mina Tradetional medicenሚና ኑሩ, Medical and health, Addis Ababa.

ከቀደምት አባቶቻችን የወረስነውን የህክምና ጥበብ ከዘመኑ ጋር አዋህደን ለሚገጥማችሁ ህመም ሁሉ ፍቱን የሆኑ መድሀኒቶችን አዘጋጅተናል ። በራሳችን ባስገነባነው ህንጻ ለህሙማን ምቹ በሆነ መልኩ ህክምና እየሰጠን እንገኛለን ።

አድራሻ:- አዲስአበባ ቤተል አደባባይ ወደ አየር ጤና በሚወስደው መንገድ አዲሱ መስጅድ ፊትለፊት

+251920525200
+251994777777

05/09/2026

ሚና የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል
ጠዋት በባዶ እግር ለ 30 ደቂቃ የመራመድ ጥቅሞች

ሚና የባህል ህክምና መስጫ ማዕከልበታካሚዎች የታመነ ፤በትውልድ ቅብብሎሽ የዳበረ ፤ለጤና እክል ሁሉ መፍትሄ የሚያስገኝ።
09/08/2026

ሚና የባህል ህክምና መስጫ ማዕከል

በታካሚዎች የታመነ ፤
በትውልድ ቅብብሎሽ የዳበረ ፤
ለጤና እክል ሁሉ መፍትሄ የሚያስገኝ።

ኑ ተፈጥሮዎን በተፈጥሮ ይታከሙ !
27/07/2026

ኑ ተፈጥሮዎን በተፈጥሮ ይታከሙ !


🌿  ​በተደጋጋሚ የመደካከም፣ የድካም እና የከፍተኛ እንቅልፍ ችግር አለብዎት? 🥱​ምስጢሩ ከጉበትዎ ጤና ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል!ጉበትን የሚያፀዳ እና አካልን የሚያነቃቃ ተፈጥሯዊ የሮዝመ...
22/07/2026

🌿 ​በተደጋጋሚ የመደካከም፣ የድካም እና የከፍተኛ እንቅልፍ ችግር አለብዎት? 🥱

​ምስጢሩ ከጉበትዎ ጤና ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል!

ጉበትን የሚያፀዳ እና አካልን የሚያነቃቃ ተፈጥሯዊ የሮዝመሪ (Rosemary) ውህድ! ✨

ፋርማሲ በቤተዎ #111
ፎሎ ፣ሸር፣ላይክ በማፍረግ ለሌሎች እንዲደርስ እናድርግ


​🍵 የውህዱ አዘጋጃጀት፦

​1️⃣ አንድ እጅ ሙሉ የሮዝመሪ (Rosemary) ቅጠል ይውሰዱ።
2️⃣ በአንድ ሊትር የፈላ ውሃ ውስጥ ለ30 ደቂቃ ዘፍዝፈው ያቆዩት።
3️⃣ በመጨረሻም በደንብ አጥልሎ ማስቀመጥ ።
​💡 የአጠቃቀም መጠን፦

​በቀን 3 ጊዜ (ጠዋት፣ ምሳ እና ከመተኛት በፊት) 1 መካከለኛ ብርጭቆ ይጠጡ።

​✨ የሮዝመሪ ዋነኛ ጥቅሞች፦
​💚 ለጉበት እና ለልብ ጤና፦
ድካምንና አላስፈላጊ እንቅልፍን በማስወገድ የሰውነትን ንቁነት ይጨምራል።
​🍃 ለምግብ መፈጨት፦ የሆድ ቁርጠትን ያረጋጋል፣ ጋዝ ያስወጣል፣ የምግብ ፍላጎትንም ይከፍታል።
​💧 ተፈጥሯዊ ማፅጃ፦ የሰውነትን መርዛማ ነገሮች (Toxins) በላብና በሽንት በኩል ያስወግዳል።
​🧠 ለአእምሮ፦ ትኩረትን እና የማስታወስ ብቃትን ያሳድጋል።

ሚና ባህላዊ ህክምና
አድራሻ :-አዲስአበባ ቤተል አደባባይ፣ ወደ አየር ጤና በሚወስደው መንገድ፣ በግ ተራ ፣አዲሱ መስጅድ ፊት ለፊት
0920525200
0994777777

https://youtube.com/-lp5ds?si=CoznQLwXiNWDfZkR

https://www.tiktok.com/?_t=8nRk5GNkGpi&_r=1

https://t.me/minatraditional

🌿 የቫይታሚን ዲ (Vitamin D) እጥረት እና የአጥንት ህመም ማስታገሻ 🌿ፋርማሲ በቤተዎ  #110ፎሎ፣ሸር፣ላይክ ያርጉ ለሌሎች እንዲፈርስ የበኩለዎትን ይወጡ !!?​የቫይታሚን ዲ እጥረት :...
21/07/2026

🌿 የቫይታሚን ዲ (Vitamin D) እጥረት እና የአጥንት ህመም ማስታገሻ 🌿

ፋርማሲ በቤተዎ #110
ፎሎ፣ሸር፣ላይክ ያርጉ
ለሌሎች እንዲፈርስ የበኩለዎትን ይወጡ !!?

​የቫይታሚን ዲ እጥረት :-ለአጥንትና መገጣጠሚያ ህመም፣ ለከፍተኛ ድካም፣ ለማዞር እንዲሁም ለጭንቀት (ድብርት) እንደሚዳርግ ያውቃሉ?

​ይህንን ችግር ለመቅረፍ እና አጥንትን ለመጠገን የሚረዳ አንድ ድንቅ የባህል ህክምና ውህድ እነሆ

​🥣 የሚያስፈልገው ነገር፡

​ዳጉሳ። (Millet) 🌾

​አንድ ብርጭቆ ወተት ወይም እርጎ 🥛

​💡 አዘገጃጀት እና አጠቃቀም፡
​የዳጉሳ ፍሬ በሚገባ መቁላት።
​የተቆላውን ፍሬ ፈጭቶ ማድቀቅ።

​አንድ የሻይ ማንኪያ የዳጉሳ ዱቄት በአንድ ብርጭቆ ወተት ወይም እርጎ ውስጥ በጥብጦ ማዘጋጀት።

​ይህንን ውህድ ለአንድ ወር ያህል በየቀኑ አዘውትሮ መጠጣት።

​🔬 ከተመራማሪ እና ፋርማሲስት እይታ (ሳይንሳዊ ማብራሪያ)፦
​ዳጉሳ በአጥንት ጥንካሬ ውስጥ ትልቅ ሚና ያላቸውን ካልሲየም፣ ማግኒዚየም እና ፎስፈረስ በከፍተኛ መጠን የያዘ ድንቅ ተፈጥሯዊ እህል ነው። ሆኖም ግን ቫይታሚን ዲን በከፍተኛ ሁኔታ ለማግኘት ከዚህ ውህድ በተጨማሪ የጠዋት ፀሐይ መሙቅ እና እንደ ዓሳ ያሉ ምግቦችን ማዘውተር ተመራጭ ነው። ውህዱ ግን አጥንትን እና መገጣጠሚያን ለማጠናከር እጅግ ፍጹም ነው!



​ሚና ባህላዊ ህክምና
አድራሻ :-አዲስአበባ ቤተል አደባባይ፣ ወደ አየር ጤና በሚወስደው መንገድ፣ በግ ተራ ፣አዲሱ መስጅድ ፊት ለፊት
0920525200
0994777777

https://youtube.com/-lp5ds?si=CoznQLwXiNWDfZkR

https://www.tiktok.com/?_t=8nRk5GNkGpi&_r=1

https://t.me/minatraditional

21/07/2026

ዛሬ ስለ ዳጉሳ (ደጉ እሳ )እፅፍለሁ
ስለ ዳጉሳ የምታውቁትን ኮመንት ላይ ፃፍ

🚨 «ሀብ አል-ሙሉክ» (የነገሥታት ፍሬ)፦ ጥቅምዋ ከጉዳትዋ የሚያንስ አደገኛ ፍሬ! 🚨​🌿 ለጤናዎ ቅድሚያ ይስጡ! 🌿​✍️ ዝግጅትፎሎ ፣ሸር ፣ላይክ ያድርጉየጥንቃቄ መልዕክት !!!!!​የባህል ...
20/07/2026

🚨 «ሀብ አል-ሙሉክ» (የነገሥታት ፍሬ)፦

ጥቅምዋ ከጉዳትዋ የሚያንስ አደገኛ ፍሬ! 🚨
​🌿 ለጤናዎ ቅድሚያ ይስጡ! 🌿
​✍️ ዝግጅት
ፎሎ ፣ሸር ፣ላይክ ያድርጉ

የጥንቃቄ መልዕክት !!!!!

​የባህል መድኃኒት ስለሆነ ብቻ ሁሉንም እፅዋት በቤት ውስጥ ዝም ብለን ልንወስድ አይገባም። ዛሬ በጥንቱ ዘመን ይታወቅ ስለነበረው ነገር ግን እጅግ አደገኛ ስለሆነው «ሀብ አል-ሙሉክ» (ሳይንሳዊ ስሙ፦ Croton tiglium) ጥቂት እንበላችሁ።
​🔍 «ሀብ አል-ሙሉክ» ምንድን ነው?
​ይህ ፍሬ በሕክምና ታሪክ ውስጥ እጅግ በጣም መርዛማ ከሆኑ እፅዋት መካከል አንዱ ነው። በጥንታዊ የባህል ሕክምና ሥርዓቶች ውስጥ በጣም በጥንቃቄና በደቂቅ መጠን (Micro-dosage) ጥቅም ላይ ይውል የነበረ ቢሆንም፣ ዛሬ ግን በሳይንሱ ዓለም ወደ ውስጥ (በአፍ) መወሰዱ ፈጽሞ የተከለከለ ነው።
​🧪 በውስጡ ምን ይዟል?
​ይህ ፍሬ ለጤና አደገኛ የሆኑ በርካታ ኬሚካሎችን የያዘ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ፦
​⚠️ የክሮቶን ዘይት (Croton Oil)፦ እጅግ ኃይለኛና የሰውነት ክፍልን የሚበላሽ ዘይት።
​⚠️ ፎርቦል ኤስተርስ (Phorbol esters)፦ ለከፍተኛ መርዝነት እና ለካንሰር ተጋላጭነት ምክንያት የሚሆኑ ውህዶች።
​📜 በጥንት ዘመን ለምን ይጠቀሙበት ነበር?
​በጥንታዊ የባህል ሕክምና ውስጥ እጅግ በጣም ሥር የሰደደ እና አስቸጋሪ የሆድ ድርቀትን (Chronic constipation) ለማስለቀቅ እንደ ኃይለኛ ሆድ ማለስለሻነት ያገለግል ነበር።
​❌ ዛሬ ለምን ተከለከለ? (ከባድ አደጋዎቹ)
​ይህንን ፍሬ በቤት ውስጥ መጠቀም የሚከተሉትን ከባድ የጤና እክሎች ያስከትላል፦
​🛑 ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ኃይለኛ ተቅማጥ እና ትውከት
​🛑 ከባድ የሆድ ቁርጠት እና የአንጀት መቁሰል
​🛑 ከፍተኛ የሰውነት ፈሳሽ ማጣት (Dehydration) እና የደም ግፊት ማሽቆልቆል
​🛑 ዘይቱ ቆዳን ከነካ ከባድ መተርተርና መቁሰል ያመጣል
​💀 ማስጠንቀቂያ፦ ፍሬውን በከፍተኛ መጠን መውሰድ ለሞት ሊዳርግ ይችላል!
​💡 የማጠቃለያ መልዕክት
​«ሀብ አል-ሙሉክ» ምንም እንኳን የቆየ የባህል ሕክምና ታሪክ ቢኖረውም፣ ጉዳቱ ከጥቅሙ በእጅጉ ያደላል።


መጠቀም የሌለባቸው ሰዎች:-

ህፃናት፣ነፍሰጡር፣የሚያጠቡ እናቶች፣የማይቃረጥ መድኃኒት የሚወስዱ ሰዎች፣ልብ ድካም ያለባቸው ሰውች፣አዛውንቶች በፍፁም መጠቀም የለባቸውም።

ለመውሰድ ከፈለጉ :
አንድ ፍሬ ከግማሽ ቅርፊቱን ልጠው ውስጡን ገምሰው ውስጥ ላይ ያለችውን ሽፋን አስወግደው በባዶ ሆድ በአንድ ብርጭቆ ውሐ ይውሰዱ ።ኃይለኛ ተቅማጥ አለው
እስከ ስድስት ሰዓት ምግብ አይብሉ።ተቅማጡን ማቆም ሲፈልጉ ቡና ወይም ሻይ ወይም ወተት ይጠጡ።ሻወር ይውሰዱ
ሙሉ ቀን በርበሬ የሌለው ወጥ ይብሉ

​🌿 ለጤናዎ ቅድሚያ ይስጡ! 🌿
​✍️ ዝግጅት፦
​ተመራማሪ ኡስታዝ ኑሩ ጀማል

ሚና ባህላዊ ህክምና
አድራሻ :-አዲስአበባ ቤተል አደባባይ፣ ወደ አየር ጤና በሚወስደው መንገድ፣ በግ ተራ ፣አዲሱ መስጅድ ፊት ለፊት
0920525200
0994777777

https://youtube.com/-lp5ds?si=CoznQLwXiNWDfZkR

https://www.tiktok.com/?_t=8nRk5GNkGpi&_r=1

https://t.me/minatraditional

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሚና ባህላዊ ህክምና -Mina Tradetional medicenሚና ኑሩ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share