Dr.Temesgen Dejene/ዶ/ር ተመስገን ደጀኔ

Dr.Temesgen Dejene/ዶ/ር ተመስገን ደጀኔ Join t.me/ dr_temesgen_dejene

📣እንክብል የእርግዝና መከላከያ መድሃኒት ጥቅሞች እና ጉዳቶች💬በዶ/ር ተመስገን ደጀኔ🟠ጥቅሞች                          ⬇️ 🔸ታማኝ እና እየተጠቀሙት እርግዝና  🔸የመፈጠር እድሉ...
05/02/2023

📣እንክብል የእርግዝና መከላከያ መድሃኒት ጥቅሞች እና ጉዳቶች💬
በዶ/ር ተመስገን ደጀኔ

🟠ጥቅሞች
⬇️
🔸ታማኝ እና እየተጠቀሙት እርግዝና 🔸የመፈጠር እድሉ ዝቅተኛ ነው
🔸የእንቁላል ማቀፊያ ካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል
🔸የማህጸን ግርግዳ ካንሰር ተጋላጭነት ይቀንሳል
🔸ከማህጸን ዉጪ የሚከሰትን እርግዝና ይቀንሳል
🔸የወር አበባ ዉህደት ወቅቱን ጠብቆ እንዱኖር ያደርጋል
🔸ከወር አበባ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ህመምን ይቀንሳል
🔸ብጉር ያስተካክላል
🔸የማህጸን ኢንፌክሽን የመያዝ እድልን ይቀንሳል

🔴ጉዳቶች
⬇️
🔺ቀን በቀን ተከታትለን መዉሰው ይጠበቅቦታል
🔺የአባላዘር በሽታን አይከልከልም
ማቅለሽለሽ
🔺ግፊትን ተያይዞ ሊያስከትል ይችላል
🔺የደም መርጋትን ይጨምራል

🔵ይህንን የእርግዝና መከላከያ መጠቀም የሌለባቸው ማናቸው?

🔷በፍጸም መጠቀም የሊለባቸው
⬇️

🔹ከዚህ በፊት ወይም አሁን ላይ

🔹የስትሮክ በሽታ ተጠቂ የሆነች
🔹የጉበት በሽታ ካለባት
🔹የልብ ድካም ህመም ያለባት
🔹እድሜዋ ከ35 በላይ ሆኖ ሲጋር ምታጨስ

◾️በሃኪም ትዛዝ ብቻ መጠቀም ያለባቸው
⬇️
▪️ወፍራም ሴት
▪️ሚግሬን ያለባት
▪️ግፊት ታካሚ
▪️የድብርት በሽታ ያለባት
▪️ምታጠባ እናት
▪️ምታጨስ ሴት
▪️እድሜዋ ከ 35 በላይ የሆነ

ማንኛዉንም የእርግዝና መከላከያ ከመጠቀሞት በፊት ስለ ጥቅሙ እና ጉዳቱ ባለ ሙያ ማማከሮን አይርሱ!!!
ይህ መረጃ ለወዳጅ ዘሞዶ እንዲደርስ ሼር ማድረግን አይርሱ

06/11/2022

➡በእርግዝ ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉና ልዩ ጥንቃቄ
ሊደረግባቸው የሚገባቸው ነገሮች

👉ከማህፀን የሚወጣ ደም ወይም ሌላ ፈሳሽ መኖር
👉የፊት የእጅ እና የእግር ማበጥ
👉ረጅም ግዜ የሚቆይ ራስ ምታት
👉 የአይን ብዥ ማለት
👉የማይታገስ የሆድ ህመም እና የጀርባ ህመም
👉የማያቋርጥ ማስመለስ
👉 ትኩሳትና ብርድ ብረድ ማለት
👉 የፅንስ እንቅስቃሴ ከወትሮው መቀነስ
👉-ሽንት ሲሸኑ ማቃጠል እና የሽንት መጠን መቀነስ

➡እነዚህ ምልክትች በእርሶ ላይ ካጋጠመዎ በአፋጣኝ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል፡፡

➡በእርግዝና ወቅት መደረግና መወሰድ የሌለባቸው ነገሮች
-አልኮልና ትንባሆ
-ያለሀኪም ትእዛዝ የሚሰጡ መድሃኒቶች
-የበዛ ቡናና ሻይ
-ሰው ሰራሽ ማጣፈጫዎችና ቅመሞች(ሶዳ)
-ያልበሰሉ ምግቦች

የሰሊጥ የጤጥቅሞችአንድ የሾርባ ማንኪያ ሰሊጥ በዉስጡ 52 ካሎሪ ፤4 ግራም ስብ፤1 ግራም ካርቦሀይድሬት፤4 ሚሊ ግራም ኮፐር፤2 ሚሊ ግራም ማንጋኔስ፤ 87 ሚሊ ጋራማ  ካልሲየም፤31 ሚሊ ግራ...
22/07/2022

የሰሊጥ የጤጥቅሞች
አንድ የሾርባ ማንኪያ ሰሊጥ በዉስጡ
52 ካሎሪ ፤
4 ግራም ስብ፤
1 ግራም ካርቦሀይድሬት፤
4 ሚሊ ግራም ኮፐር፤
2 ሚሊ ግራም ማንጋኔስ፤
87 ሚሊ ጋራማ ካልሲየም፤
31 ሚሊ ግራም ማግኒዥየም፤
3 ሚሊ ግራም አይረን፤
57 ሚሊ ግራም ፎስፈረስ፤
7 ሚሊ ግራም ዚንክ እና
1 ሚሊ ግራም ቲያሚን ይዞዋል።

ስምንት የሰሊጥ የጤና ጥቅሞች
#ከፍተኛ የሆነ ኮሌስትሮልን መጠን የሚቀንስ ፋይቶስቴሮል በዉስጡ ይዟል

#የልብ ጤንነትን ለጠበቅ ይረዳል

#የደም ግፊትን መጠን ይቆጣጠራል

#የሆርሞንን መጠን መጠን ሚዛኑን እንዲጠብቅ ያግዛል ለምሳሌ ጾታዊ ሆርሞን

#ካንሰርን ለመዋጋት ይረዳል፦ለምሳሌ የጡት ካንሰር

#የሰውነት ስብን ለማቃጠል ይረዳል።

#የአልሚ ምግብን ምጠትን ያፋጥናል ለምሳሌ የቫይታሚን ኢ

#ለቫይታሚን እና ለተለያዩ ንጥረነገሮች ጥሩ ምንጭ ነው ።ለምሳሌ አይረን ማግኔዝየም እና የመሳሰሉት

በእርግዝና ወቅት አደጋ ምልክቶችበዶ/ር ተመስገን ደጀኔ አየለ 🔶ከማህፀን ደም መፍሰስ🔶የሽርት ውሃ መፍሰስ🔷የእይታ መደብዘዝ🔷ከባድ የራስ ምታት🔶የሆድ ቁርጠት🔶የሰውነት ማንቀጥቅጥ🔷የልጅ እንቅስ...
09/07/2022

በእርግዝና ወቅት አደጋ ምልክቶች
በዶ/ር ተመስገን ደጀኔ አየለ

🔶ከማህፀን ደም መፍሰስ

🔶የሽርት ውሃ መፍሰስ

🔷የእይታ መደብዘዝ

🔷ከባድ የራስ ምታት

🔶የሆድ ቁርጠት

🔶የሰውነት ማንቀጥቅጥ

🔷የልጅ እንቅስቃሴ ማቆም

🔷የፊትና እጅ ማበጥ

በዚህ ጊዜ በአፋጣኝ ወደ አቅራቢያ ጤና ተቋም መሄድ ይኖርብናል።


አናናስበዶ/ር ተመስገን ደጀኔ አየለ አናናስ በተፈጥሮ ሀሩር በሆኑ ስፍራዎች{tropical} የሚበቅል የፍራፍሬ አይነት ሲሆን🔸በቫይታሚን🔸ኢንዛይም እንዲሁም🔸በአንቲ ኦክሲዳንት የበለጸገ ጣፋጭ ...
09/07/2022

አናናስ
በዶ/ር ተመስገን ደጀኔ አየለ
አናናስ በተፈጥሮ ሀሩር በሆኑ ስፍራዎች{tropical} የሚበቅል የፍራፍሬ አይነት ሲሆን
🔸በቫይታሚን
🔸ኢንዛይም እንዲሁም
🔸በአንቲ ኦክሲዳንት የበለጸገ ጣፋጭ አትክልት ነው
አናናስ ምንም ያክል ጣፋጭ ቢሆን በዉስጡ የያዘው የካሎሪ መጠን 82 ብቻ ነው ከዚህ በተጨማሪ ከስብ እና ከኮሌስትሮል ነጻ ነው

🔺የአናናስ የጤና ጥቅም🔻

1🔷በሽታ የመከላከል አቅማችችንን ያጎለብታል
አናናስ በቀን መገብ ያለብንን የቫይታሚን ሲ በበቂ ሁኔታ የያዘ ሲሆን ይህም ቫይታሚን የሰዉነታችን ህዋሳት እንዳይጎዱ ይከላከላል ከዚህም የተነሳ ቫይታሚን ሲ የልብ ህመም በሽታን ለመከላከል እና የመገጣጠሚያ ቁርጥማትን ችግር ለማስወገድ ይረዳል

2🔷የአጥንት ጥንካሬን ይጨምራል
ይህም የሆነው አናናስ በዉስጡ ከፈተኛ የሆነ ማንጋኔዝ የተባለዉንጥረነገር ስላመቀ ነው

3🔶የአይን ጤንነት ለመጠበቅ
ማኩላር ደጄነሬሽን የሚባለውን ከእድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ የሚመጣዉን እክል ተጋላጭነት ይቀንሳል

4🔶የምግብ መፈጨትን ያፋጥናል
ይህም የሆነው በዉስጡ ከፍተኛ የሆነ ብሮሞሊን የተባለ ኢንዛይም ስላመቀ ነው

5🔷የሰዉነት መጉረብረብ ይከላከላል{Anti-Inflammatory }

6🔷ከፍተኛ የሆነ የደም መርጋትን ይከላከላል
ከፍተኛ የሆነው የብሮሞሊን መጠን ለዚህ አስተዋጾ እንዳለው ተረጋግጧል

7🔶ለጉንፋን በሽታ እንዲሁም ለሳይነሳይቲስ{በተለምዶ ሳይነስ የሚባለው} እክል አናናስ መመገብ ማሳሉን ለማስታገስ ጠቀሜታ እንዳለው University of Maryland Medical Center በሰፊው ገልጾታል

t.me/Dr_Temesgen_Dejene

 #የስኳር በሽታ ያለበት ሰው በተቻለው መጠን ጤናማ ሆኖ እንዴት መኖር ይችላል?በዶ/ር ተመስገን ደጀኔ አየለ              👇👇👇የስኳር በሽታ ታማሚ ጤንነቱን ጠብቆ ለመቆየት መከወን ያ...
08/07/2022

#የስኳር በሽታ ያለበት ሰው በተቻለው መጠን ጤናማ ሆኖ እንዴት መኖር ይችላል?
በዶ/ር ተመስገን ደጀኔ አየለ
👇👇👇
የስኳር በሽታ ታማሚ ጤንነቱን ጠብቆ ለመቆየት መከወን ያለበት ዋና ቁልፍ የሆኑ ነገሮችን እንደ ሚከተሉት አስቀምጬያቸዋለው{በጣም ብዙ የሚወሱ ቢኖሩም ዋናዎቹ እነዚህ ናቸው ለበለጠ ማብራርያ መልክት ላኩልን በተቻለ ፍጥነት ከጊዜ ጋር ተዛምጄ መልስ ለመስጠት ሞክራለው }

#🔸1 በደመችን ዉስጥ ያለውን የA1C የተባለዉን የደም ምርመራ በወቅቱ ማድረግ ላለፉት ጥቂት ወራቶች{3-4 ወር} በአማካይ በደማችን ዉስጥ የነበረዉን የስኳር መጠን ይነገረናል በተዘዋዋሪም መድሀኒት ሚጠቀሙ ከሆነ ምን ያህል መድሀኒቱ የስኳር መጠኑን በተፈለገው መንገድ እየተቆጣጠረ እንደነበርም መልስ ይሆናል ከዚህም በመነሳት ማስተካከል የነበሩ ነገሮ ካሉ ለምሳሌ
🔹አመጋገብ
🔹መድሀኒት አወሳሰድ
🔹የህይወት ዘይቤ ይበልጥ ማስተካከል ካለብን ለማስተካለ እንዲሁም መልካም ከሆነ አበጀ ብለን ለመቀጥል ይረደናል

#🔸2 የስኳራ በሽታ ታካሚ የስኳር መጠኑን በየጊዜ እንደሚቆጠጠረው ሁሉ የደም ግፊቱንም መቆጣጠር ይኖርበታል ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት
🔹ለልብ ህመም
🔹ስትሮክ እንዲሁም
🔹ለኩላሊት ህመም ያጋልጣል በእንቅርትላይ ጆሮ ደግፍ ይል የሀገሬ ሰው

#🔸3 የኮሌስትሮል መጠንን መቆጣር ሌላው ቁልፍ ጤናማ ሆኖ ለመኖር ከሚረዱ ያንበሳዉን ቦታ ይይዛል ቢባል ማጋነን አደለም

me/Dr_Temesgen_Dejene

 {ፕሪኢክላምፕሲያ}ይህ በእርግዝና ወቅት ከሚፈጠሩ የደም ግፊት አይነቶች መካከል አንዱ ሲሆን አንድ እናት እርጉዝ በምትሆንበት ወቅት የሚከሰት ከባዱ የደም ግፊት ነው። አንዳንድ እናቶች ላይ ...
07/07/2022

{ፕሪኢክላምፕሲያ}

ይህ በእርግዝና ወቅት ከሚፈጠሩ የደም ግፊት አይነቶች መካከል አንዱ ሲሆን አንድ እናት እርጉዝ በምትሆንበት ወቅት የሚከሰት ከባዱ የደም ግፊት ነው። አንዳንድ እናቶች ላይ ከባድ እና ለህይወት አስጊ ሊሆን ይችላል ይህ እክል በአብዛኛው ከ 20 ሳምንት በላይ በሆነ የእርግዝና ጊዜ ላይ የሚከሰት ነው ነገር ግን በወሊድ ወቅት ወይም ልጁ ከተወለደ በኋላ ሊከሰት ይችላል።
የዚህ እክል ተጠቂ የሆነች እናት የደም ግፊት መጠንዋ ከፍተኛ ይሆናል በተጨማሪም የሽንት ምርመራ በሚደረግበት ወቅት በሽንቷ ዉስጥ ከፍተኛ የሆነ የፕሮቲን መጠን ይኖራል ከዚህ በተጨማሪም ተጓዳኝ የሆነ የጉበት እና የኳላሊት በሽታም ተያያዥ ሆኖ ሊመጣ እንዲሁም የጽንሱም እድገት ሊገታ ፡ ከሽርት ዉሃ መጠን መቀነስ ጋር ተያይዘው የተለያዩ የሚወለደው ልጅ የአካል ጉድለት ሊከሰት ይችላል ለምሳሌ የመተነፈሻ አካል በተደገቢው አለማደግ፡እግር ወይም እጅ አለማደግ

🔷ምልክት
አብዛኛው ሲቶች ከባድ የሚባለው የግፊት አይነት ካልገጠማቸው ምልክት ላይኖራቸው ይችላል ነገርግን ከባድ ለሆነ የደም ግፊት ምልክቶቹ ሚከተሉት ናቸው

#🔺ከፍተኛ የሆነ እራስ ምታት

#🔺የእይታ ችግር ለምሳሌ ብዥ ማለት

#🔺ከተለመደው የችንት መጠን መቀነስ

#🔺የማቅለሽለሽ ስሜት ወይም ማስታወክ

#🔺የሆድ ህመም

#🔺የፊት እንዲሁም የእጅ ማበጥ

#🔺ክብደት መጨመር

እንዴት መመርመር ወይም ማወቅ እችላለው?
በእርግዝና ጊዜ ክትትል ማድረግ እንዲሁም የደም ግፊት መጠን መለካት ቀላሉ መንገድ ነው


t.me\Dr_Temesgen_Dejene

 /ትኩሳት ምክንያቶች______________________________አንድ እናት ምጥ ከተገላገለች ጊዜ አንስቶ ረዘም ላለ ወቅት ትኩሳት ሊኖርባት ወይም ሊያስሸግራት ይችላል ለዛሬ ከነዚህ መን...
06/07/2022

/ትኩሳት ምክንያቶች

______________________________
አንድ እናት ምጥ ከተገላገለች ጊዜ አንስቶ ረዘም ላለ ወቅት ትኩሳት ሊኖርባት ወይም ሊያስሸግራት ይችላል ለዛሬ ከነዚህ መንስኤዎች ዉስጥ ዋና ዋና ያላናቸዉን ምክንያቶች እንደ ምሳሌ ጽፈናል ይከታተሉን።

1🔸በወለዱ በመጀመርያው 24 ሰአት ዉስጥ ትኩሳት ከተከሰተ
-ለማደንዘዣ የሚሰጡ መድሃኒቶች የጎንዮሽ እክል

2🔸በወለዱ በ1 – 2 ቀን መሀል ከተከሰተ
-የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን

3🔷በወለዱ በ2 -3ኛ ቀን መሀል ከተከሰተ
-የማህጸን ግድግዳ ኢንፌክሽን

4🔷በወለዱ በ4-5ኛ ቀን መሀል ከተከሰተ
-በተለያኡ ምክንያት የመጡ ቁስሎች ኢንፌክትድ ሲሆኑ

5🔶በወለዱ በ5-6ኛ ቀን መሀል ከተከሰተ
-ሴፕቲክ ትሮምቦፍሌባይቲስ

6🔶በወለዱ 7-21 ቀን መሀል ከተከሰተ
-የጡት ኢንፌክሽን
ዋነኛ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ!!

t.me\Dr_Temesgen_Dejene

 #አንድ ሴት የዉራጃ መድሀኒት ወስዳ ምን እክሎችን ስታይ የሀክምና እርዳታ መሻት የሚኖርባት???1🔺ከማህጸን የሚወጣ ደም           👇👇👇በተለምዶ አንድ እንስት የዉርጃ መድሀኒቱን በወሰ...
05/07/2022

#አንድ ሴት የዉራጃ መድሀኒት ወስዳ ምን እክሎችን ስታይ የሀክምና እርዳታ መሻት የሚኖርባት???

1🔺ከማህጸን የሚወጣ ደም
👇👇👇
በተለምዶ አንድ እንስት የዉርጃ መድሀኒቱን በወሰደች በመጀመርያው 24 ሰአት ዉስጥ ከብልት የሚወጣ ደም ይኖራል ይህም ከ7-10 ቀን ሊቆይ ይችላል።ነገር ግን እታች ከተዘረዘሩት መካከል የትኛዉም ቢከሰት የሀክምና እርዳታ መሻት/ወዳያት ሀኪም ማምራት ይኖርባታል ማለት ነው።
🔸መድሀኒት ከወሰደች 48 ሰዓት አልፎ ምንም አይነት ከብልት የሚወጣ ደም ነክ ነገር ከሌለ ወይም ከተለመደዉ የወር አበባ መጥን ያልተለየ/ያነሰ ከሆነ

🔸በአንድ ሰዓት ዉስጥ 2 ወይም ከ2 በላይ በጣም ደም የራሰ ሞዴስ በተከታታይ ሁለት ሰአት ወስጥ ከቀየረች

🔸የዉርጃ መደሃኒት ከወሰደች አንስቶ ለተከታታይ ከ2 ሳምንት በላይ ከብልት ደም መፍሰስ ካለ

🔸ከ2 ሳምንት ህክምና በኋላ ከባድ የሆነ ከብልት ደም መፍሰስ ከተከሰተ

🔸ተቀምጠው ሲነሱ ማዞር፡ጭው ማለት ካለ

2🔺የሆድ ቁርጠት
👇
ይህ የሆድ ቁርጠት ከተለመደው የወር አበባ ላይ ከሚከሰተው ቁርጠት ትንሽ ከበድ/ላቅ ሊል ይችላል።በዚህ ወቅት በሃኪም ትእዛዝ የተለያዩ የህመም ማስታገሻ መድሃኒት መጠቀም ይመከራል።ነገር ግን አንድ እህት በወር አበባ ወቅት ከሚከሰተው ቁርጠት ለየት ያለና በጣም ከባድ ከሆነ ወይም ጽንሱ በመድሃኒት ከወጣ በኋላ ወይም የመጨረሻዉን መድሀኒት ከወሰድሽ 24 ሰአት አልፎ ከተከሰተ የህክምና አርዳታ መሻት ይኖርብሻል ማለት ነው።

3🔺ትኩሳት እና ማንቀጥቀጥ፡
👇👇
ይህ የተለመደ እና በአብዛኛው የሚከሰት ቢሆንም ነገር ግን ዘላቂ/ለበዙ ቀን የሚቆይ አይደለም።አንድ ዉርጃ የፈጸመች ሴት ከ38c በላይ የሆነ እና ከ24 ሰዓት በላይ የቆየ ትኩሳት ከሆነ ወደ ሀኪም ቤት መሄድ ይኖርባታል።

4🔺ተቅማጥ፡ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ
👇👇
ከመድሀኒቱ የጎንዮሽ ጉዳት ጋር ተያይዘው ሊመጡ ይችላሉ ነገር ግን በጣም ካስቸገረ ማስታገሻ መድሀኒት አብሮ ሊሰጥ ይችላል ሆኖም በመድሀኒት አልታገስ ካለ ሀኪም ማየት አስፈላጊ ነው

t.me\Dr_Temesgen_Dejene

የወር አበባሽ ተዛብቶብሽ ይሆን?=====================የወር አበባ ዑደት ተዛባ የምንለው አንዲት ሴት ወትሮ ከምታየው የተለየ ጠባይ ሲገጥማት ነው፡፡1) የወር አበባ መዛባት ዓይነቶ...
03/07/2022

የወር አበባሽ ተዛብቶብሽ ይሆን?
=====================
የወር አበባ ዑደት ተዛባ የምንለው አንዲት ሴት ወትሮ ከምታየው የተለየ ጠባይ ሲገጥማት ነው፡፡

1) የወር አበባ መዛባት ዓይነቶች

🔺የፍሰት መጠን መብዛት (Heavy Menstrual Bleeding)

🔻የፍሰት መጠን ማነስ (Light menstrual bleeding)

🔺መቅረት (Amenorrhea)

🔻የቀኑ መዛባት (Irregular Bleeding)

🔺ቶሎ ቶሎ መምጣት (Frequent Bleeding)

2) የወር አበባ መዛባት መገለጫዎች

🔺የፍሰት መጠን መብዛት: ከዚህ በፊት ይፈስሽ ከነበረው መጠን በላይ ሲበዛ፣ ከ7 ቀናት ባላይ ሲፈስሽ፣ ብዙ የንጽሕና መጠበቂያ ለመጠቀም ስትገደጂ፣ ሲፈስሽ የሚረጋ ከሆነ፣ የድካ ስሜት ካለሽ፣ የማዞር ስሜት ካለሽ እና ራስን እስከ መሳት ስትደርሺ ፍሰቱ ተዛብቷል ማለት ነው፡፡

#መንስኤዎች፡ ማህፀን እጢዎች፣ የሆርሞን መዛባት፣ ጭንቀት፣ መድሀኒቶች፣ የደም መርጋት ችግር ሊሆን ይችላል።

🔻የፍሰት መጠን ማነስ፡ ከ35 ቀናት በላይ እየቆየ የሚመጣ ከሆነ፣ ከሁለት ቀናት ባነሰ ጊዜ ብቻ በመጠኑ የሚፈስሽ ከሆነ ይሄ የማነስ ምልክት ነው።
#መንስኤዎች፡- የእንቁላል አመራረት ሂደት መዛባት(PCOD)

▪️መቅረት፡ ለ3 ተከታታይ ዑደት ወይም ለ6 ወራት የወር አበባ መቅረት፤ መንስኤዎቸሁም
= እርግዝና፣ የማኅጸን ጠባሳ፣ የማኅጸን ኢንፌክሽን፣ የሆርሞን መዛባት
= ጭንቀት፣ ከባድ የሆነ የስፖርት እንቅስቃሴ ወይም ማረጥ ሊሆኑ ይችላሉ።

🔸ቀኑን ማዛባት፡ ወቅቱን ጠብቆ የማይፈስ የወር አበባ ዑደት
#መንስኤዎች፡ የማኅጸን ዕጢዎች፣ የማህጸን ጫፍ ካንሰር

🔹ቶሎ ቶሎ መጣ የምንለው፡ ከ21 ቀናት በታች ተደጋሞ የሚመጣ ከሆነ ነው።
#መንስኤዎች፡ የማህፀን እጢዎች፣ የሆርሞን መዛባት፣ ጭንቀት፣ መድሀኒቶች፣ የማረጥ እድሜ ላይ መድረስ ሊሆኑ ይችላሉ።
* መፍትሔዎች እንደ መንስኤዎች ዓይነት ይለያያል።

👉 ለበለጠ መረጃ - ማዕከላችንን ይጎብኙን፡
@ - ፀደይ የማህፀንና ጽንስ ሕክምና ማዕከል
t.Me/Dr_Temesgen_Dejene

02/07/2022

የወር አበባሽ ተዛብቶብሽ ይሆን?
=====================
የወር አበባ ዑደት ተዛባ የምንለው አንዲት ሴት ወትሮ ከምታየው የተለየ ጠባይ ሲገጥማት ነው፡፡

1) የወር አበባ መዛባት ዓይነቶች

🔺የፍሰት መጠን መብዛት (Heavy Menstrual Bleeding)

🔻የፍሰት መጠን ማነስ (Light menstrual bleeding)

🔺መቅረት (Amenorrhea)

🔻የቀኑ መዛባት (Irregular Bleeding)

🔺ቶሎ ቶሎ መምጣት (Frequent Bleeding)

2) የወር አበባ መዛባት መገለጫዎች

🔺የፍሰት መጠን መብዛት: ከዚህ በፊት ይፈስሽ ከነበረው መጠን በላይ ሲበዛ፣ ከ7 ቀናት ባላይ ሲፈስሽ፣ ብዙ የንጽሕና መጠበቂያ ለመጠቀም ስትገደጂ፣ ሲፈስሽ የሚረጋ ከሆነ፣ የድካ ስሜት ካለሽ፣ የማዞር ስሜት ካለሽ እና ራስን እስከ መሳት ስትደርሺ ፍሰቱ ተዛብቷል ማለት ነው፡፡

#መንስኤዎች፡ ማህፀን እጢዎች፣ የሆርሞን መዛባት፣ ጭንቀት፣ መድሀኒቶች፣ የደም መርጋት ችግር ሊሆን ይችላል።

🔻የፍሰት መጠን ማነስ፡ ከ35 ቀናት በላይ እየቆየ የሚመጣ ከሆነ፣ ከሁለት ቀናት ባነሰ ጊዜ ብቻ በመጠኑ የሚፈስሽ ከሆነ ይሄ የማነስ ምልክት ነው።
#መንስኤዎች፡- የእንቁላል አመራረት ሂደት መዛባት(PCOD)

▪️መቅረት፡ ለ3 ተከታታይ ዑደት ወይም ለ6 ወራት የወር አበባ መቅረት፤ መንስኤዎቸሁም
= እርግዝና፣ የማኅጸን ጠባሳ፣ የማኅጸን ኢንፌክሽን፣ የሆርሞን መዛባት
= ጭንቀት፣ ከባድ የሆነ የስፖርት እንቅስቃሴ ወይም ማረጥ ሊሆኑ ይችላሉ።

🔸ቀኑን ማዛባት፡ ወቅቱን ጠብቆ የማይፈስ የወር አበባ ዑደት
#መንስኤዎች፡ የማኅጸን ዕጢዎች፣ የማህጸን ጫፍ ካንሰር

🔹ቶሎ ቶሎ መጣ የምንለው፡ ከ21 ቀናት በታች ተደጋሞ የሚመጣ ከሆነ ነው።
#መንስኤዎች፡ የማህፀን እጢዎች፣ የሆርሞን መዛባት፣ ጭንቀት፣ መድሀኒቶች፣ የማረጥ እድሜ ላይ መድረስ ሊሆኑ ይችላሉ።
* መፍትሔዎች እንደ መንስኤዎች ዓይነት ይለያያል።

👉 ለበለጠ መረጃ - ማዕከላችንን ይጎብኙን፡
@ - ፀደይ የማህፀንና ጽንስ ሕክምና ማዕከል
T.Me/Dr_Temesgen_dejene

 (Hepatitis B)ሄፓታይትስ ቢ ቫይረስ ጉበትን ከሚያጠቁ አምስቱ የሄታይትስ ቫይረሶች አንዱ ሲሆን እንደ የአለም ጤና ድርጅት መረጃ በአለማችን እስከ 2 ቢሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በሄፓታይትስ...
20/06/2022

(Hepatitis B)

ሄፓታይትስ ቢ ቫይረስ ጉበትን ከሚያጠቁ አምስቱ የሄታይትስ ቫይረሶች አንዱ ሲሆን እንደ የአለም ጤና ድርጅት መረጃ በአለማችን እስከ 2 ቢሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በሄፓታይትስ ቢ ቫይረስ የተጠቁ ናቸዉ፡፡ በየዓመቱም 600,000 ሰዎች በሄፓታይትስ ቢ ምክንያት ለህልፈተ ሞት ይዳረጋሉ፡፡ሄፓታይትስ ቢ በጉበት ላይ ጉዳት የሚያመጣ ሲሆን በዚህ ቫይረስ የተያዙ የተወሰኑ ሰዎች ቫይረሱን ሙሉ በሙሉ ከሰዉነታቸዉ ዉስጥ ማጥፋት ስለማይችሉ ቫይረሱ ለረጅም ጊዜ በጉበታቸዉ ዉስጥ በመቆየት (chronic hepatitis B) በጉበት ላይ ጉዳት እነዲደርስ ያደርጋል፡፡
ሄፓታይትስ ቢ ቫይረስ እና ኤችአይቪ ቫይረስ የመተላለፊያ መነገዶቻቸዉ ተመሳሳይ ቢሆንም ሄፓታይትስ ቢ ቫይረስ ከኤችአይቪ አንፃር ሲታይ ከ50 እስከ 100 ጊዜ እጅግ ተላላፊ ነዉ፡፡



በሄፓታይትስ ቢ እንፌክሽን ምክንያት የሚታዩ ምልክቶች የሚታዩት ኢንፌክሽኑ ከተከሰተ ከ3 ወራት በኃላ ሲሆን ምልክቶቹ ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ከነዚህ ምልክቶች ዉስጥ ጥቂቶቹ፡-
• የሆድ ህመም
• ጠቆር ያለ የዉሃ ሽንት
• የሰዉነት ትኩሳት
• የመገጣጣሚያ ላይ ህመም
• የምግብ ፍላጎት መቀነስ
• ማቅለሽለሽና ማስታወክ
• የድካም ስሜት
• የቆዳና የአይን ነጩ ክፍል ቢጫ መሆን ናቸዉ፡፡
ነገር ግን በሄፓታይትስ ቢ የተያዙ ህፃናትና የተወሰኑ አዋቂዎች ምንም አይነት የህመም ምልክቶች አያሳዩም፡፡


• የሆነ የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ
• ያለ ጥንቃቄ ሄፓታይትስ ቢ ቫይረስ ከተያዘ/ች ሰዉ ጋር የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ
• እንደ ጨብጥና ከርክር ባሉ የአባለዘር በሽታዎች ተይዘሁ ከሆነ
• መርፌ፣የጥርስ ብሩሾችንና ሌሎች ነገሮችን በጋራ የሚጠቀሙ ከሆነ
• ለሄፓታትስ ቢ ሊያጋልጦት የሚችል ስራዎች፡-የጤና ባለሙያዎች፣የእሳት አደጋ ሰራተኞች
• ዲያሊስስ(የኩላሊት ዕጥበት) የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡


• ልቅ በሆነ የግብረስጋ ግንኙነት
• ከእናት ወደ ልጅ
• በደምና ደም ንኪኪ(ጤንነቱን ያልጠበቀ የሌላ ሰዉ ደም በመዉሰድ፣ጤንነቱን ያልጠበቀ መርፌ መወጋት፣አደንዛዥ ዕፅ ለሚጠቀሙ መርፌ በጋራ መጠቀም)
• ሄፓታይትስ ቢ ከተያዘ ሰዉ ጋር በጣም የቀረበ ግንኙነት መኖር (intimate contact)



• የሄፓታይትስ ቢ ክትባት መዉሰድ
• ጥንቃቄ ያለዉ የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ
• ማንኛዉንም ደም የነካቸዉን ነገሮች በጋራ ያለመጠቀም(መርፌ፣ምላጭ፣የጥርስ መቦረሻ፣የፂም መላጫ)
• እናቶች በእርግዝና ወቅት ለሄፓታይትስ ቢ ምርመራ ማድረግ
• ደም ለሌላ ሰዉ ከመሰጠቱ በፊት ለሄፓታይትስ ቢ መመርመር

(HBV vaccine)

ሄፓታይትስ ቢ ቫየረስን ለመከላከል ከሚረዱ ነገሮች ዉስጥ አንዱ የሄፓታይትስ ቢ ቫይረስ ክትባትን መከተብ ሲሆን ማንኛዉም ሰዉ ከላይ በተገለፀዉ መሰረት ተጋላጭነት ካለዉ ተመርምሮ በሄፓታይትስ ቢ ያልተያዘ መሆኑ ከተረጋገጠ የሄፓታትስ ቢ ቫይረስን ለመከላከል ክትባት መዉሰድ የሚችል ሲሆን ክትባቱ ሙሉ ለሙሉ እንዲሰራ ሶስት ጊዜ መከተብ ያስፈልጋል፡፡ሄፓታይትስ ቢ ቫይረስ ቫክሲንን ሙሉ ለሙሉ የተከተቡ ከ95% በላይ የሚሆኑ ህፃናትና አዋቂዎች በሽታዉን የሚከላከሉ አንቲቦዲዎችን(Antibodies) የሚያዘጋጁ ሲሆን ክትባቱ ቢያነስ ለ 20 ዓመታትና ምናልበትም እስከ እድሜ ልክ በሽታዉን ሊከላከል ይችላል፡፡
የሄታይትስ ቢ እንፌክሽን ያላቸዉ ሰዎች የህክምና ክትትል ማድረግና ሊደረጉ የሚገባቸዉን ጥንቃቄዎች መዉሰድ ያስፈልጋቸዋል፡፡

t.me/Dr_Temesgen_Dejene

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr.Temesgen Dejene/ዶ/ር ተመስገን ደጀኔ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Dr.Temesgen Dejene/ዶ/ር ተመስገን ደጀኔ:

Shortcuts

Share

Category