Eldan

Eldan Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Eldan, AIDS Resource Center, Addis Ababa.

26/11/2024
06/11/2024
31/10/2024

ሀገራዊ ሪፎርምን በተመለከተ

በተለያዩ ዘርፎች ሲከናወኑ የነበሩ ሪፎርሞችን አጠናቀን ሀገራዊ ማንሰራራት የምንጀምርበት ዘመን የመጀመሪያ ምእራፍ ላይ ተገኝተናል፡፡ በመሆኑም በ2017 በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ለውጥ የምናስመዘግብ ይሆናል፡፡ ከዚህ አኳያ ከትናንት እሳቤ ወጥተን በጋራ ወደ ነገ መሻገር አለብን፡፡

28/10/2024

አሳታፊና አካታች ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለህዝባችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት!

በነበሩብን የኢኮኖሚ ስብራቶች ምክንያት ሀገራችንም ህዝባችንም ለመልማት እና ለመለወጥ ያላቸው ፍላጎት ተገቢውን ምላሽ ሳያገኝ ቆይቷል፡፡ ህዝባችን በድህነት አረንቋ እንዲማቅቁ ሀገራችንም በምግብ እራሷን ባለመቻል ጭምር ያደጉ ሀገራት ላይ ጥገኛ እንድትሆን ተፅዕኖአቸውም ቀላል አልነበረም፡፡

የቀደምት ስልጣኔ ባለቤት የሆነችውን፣ ነጻነቷን እና ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ የቆየችው ሀገራችን ስሟን የረሀብ እና የድህነት ምልክት ተደርጎ በመዝገበ ቃላት ጭምር መዘባበቻ መሆኑ አይዘነጋም፡፡

የሀገራችንን ስብራቶች በጥልቀት የተረዳው ፓርቲያችን ኢኮኖሚያዊ ስብራቷን ለመጠገንም ባለ ዘርፈ ብዙ የኢኮኖሚ አቅጣጫ መርህ በመከተል አስተማማኝ ኢኮኖሚ ለመገንባት እየተረባረበ ይገኛል፡፡ ኢኮኖሚያዊ ዕድገቱ ጠቅላላ ሀገራዊ ምርትን ከማሳደግ ባሻገር የህዝባችንን ሰብአዊ ልማት እንዲያረጋግጥም ይደረጋል፡፡

ኢኮኖሚያችን ለሁሉም የኢኮኖሚ ተዋንያን ፍትሐዊ እና በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ተመጣጣኝ የዕድገት ዕድልን የሚፈጥር፣ የዕድገት ምጣኔው እየሰፋና ግለቱን ጠብቆ የሚዘልቅ፣ ጥራቱን የጠበቀና በቀጣይ ትውልድ ኪሳራ ላይ የማይገነባ መሠረተ ፅኑ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ ፖሊሲዎችን በማሻሻል ተጨባጭ እንቅስቃሴ ውስጥ ተገብቷል።

ፓርቲያችን መንግስት መር ሆኖ የቆየውን ዕድገት ዘላቂነቱን ለማረጋገጥ የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ የሚኖረውን ሚና አሁን ከሚገኝበት አነስተኛ ተሳትፎ ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ እንዲል ተገቢውን ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።

የኢኮኖሚያዊ ዕድገታችን ጥራት ያለው፣ የአካታችነት እና የዘላቂነት ችግሮችን የሚቀርፍ ፣ ምርታማነትን የሚያረጋግጥ እንዲሁም ከከፍተኛ የዕዳ ጫና የተላቀቀ እና ጤናማ የፋይናንስ ስርዓትን የተከተለ ነው። አርሶና አርብቶ አደሮችን ፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማ ነዋሪዎችን፣ ሴቶችና ወጣቶችን ከኢኮኖሚ ዕድገቱ በተጨባጭ ፍትሐዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ፖሊሲዎችም እየተተገበሩ ይገኛሉ።

ልማትን የሚያሳልጥና ለህዝባችን ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ተደራሽ የሚሆን የኢኮኖሚና የማኅበራዊ መሠረተ ልማት መኖር ለሀገራችን በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ፓርቲያችን በጥብቅ ያምናል። በመንግሥት፣ በመንግሥትና በግል ባለሀብት ትብብር ብሎም በግል ባለሀብት መዋዕለ ነዋይ፣ ጥራት ያላቸው መሰረተ ልማቶች በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ህዝባችንን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ የተጀማመሩ አበረታች ጥረቶችም ለዚህ ማሳያ ናቸው።

በቀጣይም በኢኮኖሚው ያሳየነውን ሀገራዊ እድገት በማጠናከር ጥራት ያለው የኢኮኖሚ ልማት እና ምርታማነትን መሠረት ያደረገ ማኅበራዊ ፍትህን ማረጋገጣችንንም እናጎለብታለን፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

02/10/2024

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Eldan posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share