Gandhi Memorial Hospital ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል

Gandhi Memorial Hospital                  ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል Gandhi Memorial Hospital is a pioneer Maternal and Neonatal Health Hospital located in Addis Ababa E

ወደርየለሽ  ደስታ! ሌሊት ነበር...... እኔም የወሊድ ምልክቶች መጀመራቸውን ስረዳ፣ በደስታና በፍርሃት መካከል ተወሰንኩ።“ልጄ ዛሬ ሊመጣ ነው!” የሚለው ሀሳብ ደስ ያሰኘኝ ነበር፤ ነገር ...
26/08/2026

ወደርየለሽ ደስታ!

ሌሊት ነበር......

እኔም የወሊድ ምልክቶች መጀመራቸውን ስረዳ፣ በደስታና በፍርሃት መካከል ተወሰንኩ።

“ልጄ ዛሬ ሊመጣ ነው!” የሚለው ሀሳብ ደስ ያሰኘኝ ነበር፤ ነገር ግን “ወሊዱ እንዴት ይሆን?” የሚለው ጥያቄ ልቤን ያሸብረዉ ነበር።

ወደ ጋንዲ ሆስፒታል ስደርስ ነርሷ በፈገግታ ተቀበለችኝ። “አትፍሪ፣ ከአንቺ ጋር ነን” አለችኝ። ያ አንድ አረፍተ ነገር በውስጤ ያለውን ጭንቀት ትንሽ አረጋጋው።

ምጡ እየጠነከረ ሲመጣ ህመሙ ከባድ ነበር። እኔ ግን አንድ ነገር ብቻ ነበር የማስበው፤ “ልጄን ማየት እፈልጋለሁ!”

ሐኪሙ፣ ነርሶቹና የወሊድ ቡድኑ በየደቂቃው ከእኔ ጋር ነበሩ። እያበረታቱኝ፣ እያረጋጉኝ እና የሚያስፈልገኝን እርዳታ እየሰጡኝ ነበር።

ከትንሽ ጊዜ በኋላ የህፃኑ ድምፅ ተሰማ.....

ያ ድምፅ...

እስከዛሬ ድረስ ከህይወቴ የማልረሳው ድምፅ ነው።

እንባዬ በደስታ ፈሰሰ። ህመሙ፣ ፍርሃቱና ጭንቀቱ ሁሉ በአንድ ቅፅበት የጠፉ መሰለኝ። ልጄን ወደ እጄ ሲያስጠጉልኝ የመጀመሪያ ጊዜ አየሁት።

“እናት ሆኛለሁ!”

ያንን ቃል በውስጤ ስደግመው እንባዬን ማቆም አልቻልኩም።

የወሊድ ገጠመኜ ህመም ብቻ አልነበረም፤ ትዕግስት፣ ተስፋ፣ ፍርሃት፣ ፍቅርና በመጨረሻም የእናትነት ደስታ የተቀላቀለበት የህይወቴ ትልቁ ቀን ነበር።

ዛሬ ልጄን በእጄ ይዤ ሳየው አንድ ነገር እረዳለሁ፤ አንዳንድ ህመሞች ከባድ ቢሆኑም ከኋላቸው የሚመጣው ደስታ ከሁሉም በላይ ነው።

ጋንዲ አይኔን በአይኔ ያዩሁበት ልዩ ስፍራ ነዉ!

(ታሪኩ የወ/ሮ አይንዓለም እሸቴ ነዉ ።ግዜዉም ጥቅምት 12,1989 መሆኑን ልብ ይሏል!)

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ፤ እንኳን ለ1 ሺህ 501ኛው  የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!በዓሉን  ስናከብር እንደከዚህ ቀደሙ የተቸገሩ ወገኖችን በመ...
24/08/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ፤ እንኳን ለ1 ሺህ 501ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በዓሉን ስናከብር እንደከዚህ ቀደሙ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት፤ ለሌላቸው በማካፈል፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የታመሙትን በመጠየቅ እንዲሆን እመኛለሁ።

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ - ኢድ ሙባረክ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

24/08/2026

ፊልም አይደለም!

21/08/2026

ጎበዝ ...እቺን ነገር ...!👀

ይመልከቱት!
18/08/2026

ይመልከቱት!

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

ሰኞ የተኮላ ወርቅ መስሎ አለፈ!.....የሆስፒታላችን ዋና ስራ አስኪያጅ ሳይጠበቁ...ሳይገመቱ "ጥቁር እንግዳ " ሆነዉ በአዳራሹ ከተፍ አሉ!                    (በተለየ  አለባበ...
18/08/2026

ሰኞ የተኮላ ወርቅ መስሎ አለፈ!.....የሆስፒታላችን ዋና ስራ አስኪያጅ ሳይጠበቁ...ሳይገመቱ "ጥቁር እንግዳ " ሆነዉ በአዳራሹ ከተፍ አሉ!
(በተለየ አለባበስ! )
ዶ/ር ታሪኩ የልጅነት ፣የተማሪነት እንዲሁም በስራዉ አለም ያሳለፋትን በማዉሳት ....ጀመሩ!

ለመርሃ-ግብሩ በሚመጥን ሁናቴ ያሰናዱትን ቁልፍ ጉዳዬች የሚነካካዉን ፅሁፍ መነሻ አድርገዉ ተቋማዊ ነባራዊ ጉዳዬችን ዳሰስ አድርገዋል።

"ስራን በባለቤትነት ስሜት ማከናወን" ወሳኝ መሆኑን አፅንዖት ሠጥተዉ ተናግረዋል"
..በስራ ቦታ አሉ! ዶ/ር ታሪኩ....
" የሆስፒታል ስራ የቡድን ቅንጅት!...መተባበር...! የሚጠይቅ በመሆኑ ስራን ማዕከል ባደረገ መልኩ ህብረት አስፈላጊ ነዉ" ሲሉ መከረዋል።

(ስራ አስኪያጁ ቀጥለዋል....)

በሌላኛዉ ገፅ ዶ/ር ታሪኩ ያነሱት የ "መሪነት ሚና" የተሠኘዉን አንኳር ጉዳይ ነበር አጥልለዉ ያሳዩት።

" መሪ የሠራተኛን እምቅ አቅም አዉጥቶ ለመጠቀም፤ ሆደ ሰፊ መሆን አለበት" ሲሉ ከእራሳቸዉ የአመራር ስልት ጋር አዛምደዉ !በምሳሌ አብራርተዋል።

መሪነት በግል እና በቡድን ስራዎች የሚታይ.....በየደረጃዉ ዉሳኔ ሰጪነት የሚያሻዉ......ለዚህ ስኬት ቁልፋ ደግሞ የተሳካ ስነ-ተግባቦት መሆኑን ተንትነዋል።

የማትጊያ እና ማነቃቂያ ጉዳይ የሰራተኛን ስሜት ከፍ ለማድረግ አይነተኛ ሚና እንዳላቸዉ ተቋማዊ ተሞክሮን አጣቅሰዉ አብራርተዋል......
(ቀጥለዋል)

ጎበዝ ! ስሙኝ እማ!.... He is only 36! ..ዶ/ር ረጅም ዕድሜ ከጤና ጋር ተመኘን!

ይጠብቁን!
17/08/2026

ይጠብቁን!

የሀገራችን ወዳጅ !የሆስፒታላችን ቤተሰብ ! የሆነችዉ ህንድ በዛሬዉ ዕለት 80ኛ የነፃነት በዓሏን እያከበረች ትገኛለች!በአዲስ አበባ በሚገኘዉ የሀገሪቱ ኤምባሲም 300 የሚደርሱ በኢትዮጵያ የ...
15/08/2026

የሀገራችን ወዳጅ !የሆስፒታላችን ቤተሰብ ! የሆነችዉ ህንድ በዛሬዉ ዕለት 80ኛ የነፃነት በዓሏን እያከበረች ትገኛለች!

በአዲስ አበባ በሚገኘዉ የሀገሪቱ ኤምባሲም 300 የሚደርሱ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የህንድ ማህበረሰብ አባላት በዓሉን በድምቀት አክብረዋል።

ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታልም ከመጠሪያዉ እስከ ምስረታዉ የኢትዮ-ህንድ ትስስር ጉልህ ነፀብራቅ ነዉና "እንኳን ለ80ኛዉ የነፃነት በዓል አደረሳችሁ!" በማለት ደስታዉን ይገልፃል!

A friend of our country and a member of our hospital family, India is celebrating its 80th Independence Day today!

At the Indian Embassy in Addis Ababa, nearly 300 members of the Indian community living in Ethiopia gathered to celebrate the occasion with great enthusiasm and color.

Gandhi Memorial Hospital, from its very name to its establishment, stands as a significant reflection of the strong and historic bond between Ethiopia and India. With great joy, we extend our warmest wishes to the people of India on the occasion of their Independence Day.
Happy 80th Independence Day!

14/08/2026

ዕዉነት ብላችኋል!👍👍👍

Address

Addis Ababa
782

Telephone

+251115514981

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gandhi Memorial Hospital ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Gandhi Memorial Hospital ጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል:

Shortcuts

Share

Category