Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) I feel I am still a student, a beginner journalist with a great zeal to learn more.

I am climbing up the ladder and register remarkable achievement in my profession. This page is dedicated to serve you with reliable news and voice for voiceless.

02/08/2026

ከባንኮክ እስከ ፉኬትና ፓታያ ( በወፍ በረር ... )

* ታይላንድ በዓይኔ ያየኋት፣ በእጄ የነካኋት፣ በልቤ የቀረች የባሕር ነፍስ…!

በገብረማርያም ይርጋ [ የጉዞ ማስታወሻ ]

| እውነተኛ ጉዞ የሚጀምረው ሰው ከራሱ ጋር ሲገናኝ ነው። እውነተኛ ጉዞ አውሮፕላኑ ሲያርፍ አያበቃም፤ ትዝታ በልብ ውስጥ ሲቀጥል እንጂ።

ዓለም አቀፍ የባህልና ጥበባት ልማት ሙያዊ ሽልማቴን ለመቀበል ወደ ደቡብ ምስራቅ እስያዋ እንቁ — ታይላንድ — ስጓዝ፣ አእምሮዬን የሞላው የጉዞው ዓላማ ብቻ ነበር።

ነገር ግን እግሬ የታይላንድን ምድር ሲረግጥ የተቀበለኝ የከተማዋ የሲሚንቶና የአስፋልት ግለት ወይም የዘመናዊነት ጫጫታ አልነበረም፤ ከሩቅ የባሕር ጥልቀት እየነፈሰ በፊቴ ላይ እንደ አሮጌ ወዳጅ ቀስ ብሎ የተራመደው ቀዝቃዛ የባሕር ነፋስ እንጂ።

ደቡባዊቷ እንቁ — ፉኬትና የፓታያ ሞገዶች

በውሃው ላይ የተበተኑት ባህላዊ የረጅም ጅራት (Long-tail) ጀልባዎች፣ የፀሐይ ወርቃማ ብርሃን በውሃው ላይ ሲያርፍ የሚፈጥረው ብልጭታ፣ የሰማዩና የባሕሩ አድማስ ላይ መገናኘት… እነዚህ ሁሉ ተደምረው እንደ ተአምራዊ ሕልም ይታዩ ነበር። በዚያ ቅጽበት እኔ ባሕሩን አልተመለከትኩትም፤ ባሕሩ እኔን በጥልቀቱ እየተመለከተኝ ነበር።

በጄትስኪ (Jet Ski) አየርና ውሃውን ሰንጥቄ ስነጥቅ፣ የነጭ አረፋ መስመር ከኋላዬ እንደ ግጥም ይሰመር ነበር። በወቅቱ የተረዳሁት ነገር ቢኖር—ፍጥነት ሰውን ከምድር አያርቀውም፤ ይልቁንም በውስጡ የተሸሸገውን እውነተኛ ደስታ ቅርብ ያደርገዋል!

የሰማይ ላይ በረራ (Parasailing)፦ገመዱ ተለቆ ሰማይ ሲከፈትልኝ፣ ከላይ ሆኜ ስመለከት ባሕሩ እንደ ታላቅ ሰማያዊ መስታወት ተንጣሎ ታየኝ።

በዚያ ከፍታ ላይ ዓለም ትንሽ ስትሆን፣ ሰውን የሚያስጨንቀው የዕለት ተዕለት ጭነቷም አብሮ ትንሽ ይሆናል። እንደ ልጅ ሆኜ የነፋሱን ሹክሹክታ ብቻ እሰማ ነበር… ወጣሁ፣ ተነጠቅሁ!

በፉኬት ነጭ አሸዋው በእግር ስር ሲለሰልስ፣ ግልጽና ሰማያዊው ውሃ እስከ ጉልበት ሲደርስ፣ ፀሐይ በቆዳ ላይ ወርቃማ ሙቀቷን ስትረጭ ዓለምና ጭንቋ ሙሉ በሙሉ የተረሱ ይመስላሉ።

የባንኮክ ድቅቅ ያለ ውበትና የሌሊት ከዋክብት
ባንኮክ በቀን በገዥና ሻጭ፣ በበዛ እንቅስቃሴና ህይወት ስትደምቅ፤ ሌሊት ደግሞ በምድር ላይ እንደወረዱ ከዋክብት የሚያበሩ መብራቶች ያሏት አስማተኛ ከተማ ትሆናለች። የከተማዋ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች መብራት በውሃው ላይ ሲሰበር፣ ወርቅና አልማዝ በውሃ ላይ የተበተነ ይመስላል።

በቻኦ ፕራያ (Chao Phraya) ወንዝ ላይ ያለ ምሽት
ከጉዞዬ ሁሉ በላይ በልቤ የተቀረፀው በመርከብ ላይ ያሳለፍኩት ምሽት ነው።

የምስራቃዊው የሙዚቃ ዜማ፣ የሰዎች ወዳጃዊ ሳቅ፣ ጣፋጭ እራት…

በወንዙ ላይ እያለፈች ባለው መርከብ ላይ ሆነን በከተማዋ መብራቶች መካከል ስንሳፈፍ፣ በአንድ ቅጽበት ውስጥ ዓለም በሙሉ የተሰበሰበች ያህል ተሰማኝ።

በዚያ ምሽት አንድ ታላቅ እውነት ተረዳሁ—ደስታ ታላቅና ውስብስብ ነገር አይፈልግም፤ በሙሉ ልብ የሚኖር አንድ ቅጽበት ብቻ ይበቃዋል።

በሻንጣ ያልተያዘ፣ በልብ የተያዘ ሀብት
ታይላንድ ከዚህ በኋላ ከእኔ አትጠፋም፤ በውስጤ ዘላለማዊ ቦታዋን ይዛለች። የፓታያ ነፋስ አሁንም በፊቴ ላይ ይነፍሳል፣ የፉኬት ሞገድ በልቤ ይመታል፣ የባንኮክ የሌሊት መብራት በዓይኔ ላይ ይበራል።

ከዚህ ጉዞ ስመለስ በሻንጣዬ ውስጥ ያሸግኩት ያበደሩኝን ልብስ ብቻ አይደለም፤

የሞገዱን ዘላለማዊ ድምፅ፣ ...

የፀሐይዋን አፍቃሪ ሙቀት፣ ...

የአሸዋውን ልስላሴ፣ ...

የሌሊት መብራቶቿን ብሩህነት፣ ...

እና ...

የልቤን ሙሉ ደስታ ነው።

እውነተኛ ጉዞ አውሮፕላኑ ሲያርፍ አይጨርስም፤ ትዝታው በልባችን ውስጥ መኖር ሲቀጥል እንጂ!

ታይላንድ በዓይኔ ያየኋት፣ በእጄ የነካኋት፣ በልቤ የቀረች የባሕር ነፍስ…!

የኤሎን ማስክን የሳለችው ደጋፊ በራሱ ታገደች?  ከ11 ሚሊዮን በላይ እይታ አግኝታለች  | በElon Musk ዙሪያ የተነሳ አዲስ የማኅበራዊ ሚዲያ ጉዳይ በዓለም አቀፍ የዲጂታል ማኅበረሰብ ው...
02/08/2026

የኤሎን ማስክን የሳለችው ደጋፊ በራሱ ታገደች? ከ11 ሚሊዮን በላይ እይታ አግኝታለች

| በElon Musk ዙሪያ የተነሳ አዲስ የማኅበራዊ ሚዲያ ጉዳይ በዓለም አቀፍ የዲጂታል ማኅበረሰብ ውስጥ ሰፊ ውይይት አስነስቷል።

አንዲት የማስክ ደጋፊ በእርሳስ የሳለችውን የማስክ ምስል በማኅበራዊ ሚዲያ በማጋራት "ለእርስዎ ብቻ የተሰራ ስጦታ ነው" ስትል ገልጻለች።

በ24 ሰዓታት ውስጥ ምስሉ 11 ሚሊዮን ያህል እይታ እንዳገኘ ተነግሯል። አንዳንዶች ሥዕሉ ማስክን በትክክል እንደሚመስል ሲገልጹ፣ ሌሎች ግን ተመሳሳይነቱን ተቃውመዋል።

በዚህ መካከል ብዙ ተጠቃሚዎች ማስክ ሥዕሉን እንዲያይ በተደጋጋሚ መለያውን (tag) ማድረግ ጀመሩ።

ይሁን እንጂ ማስክ በይፋ ምንም አስተያየት አልሰጠም ተብሏል። ከዚህ ይልቅ ሥዕሉን ያጋራችውን ተጠቃሚ ከመለያው ላይ አግዶታል የሚል ምስል (screenshot) በመስመር ላይ ተሰራጭቷል። ይህ የእገዳ ምስል ከመጀመሪያው ሥዕል የበለጠ ትኩረት መሳቡ ተነግሯል።

ሆኖም ይህን ክስተት በተመለከተ ጥርጣሬዎችም ተነስተዋል። አንዳንድ ተጠቃሚዎች የተሰራጨው ሥዕል ከቀድሞ የተወሰደ ሊሆን እንደሚችል እና የእገዳው ማስረጃም የተረጋገጠ እንዳልሆነ ጠቁመዋል። እስካሁን ድረስ ከማስክ ወይም ከX ድርጅት ይፋዊ ማረጋገጫ አልተሰጠም።

በአጠቃላይ ይህ ጉዳይ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የታዋቂ ሰዎች ከደጋፊዎቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት፣ የመለያ እገዳ (blocking) አጠቃቀም እና የቫይራል ይዘቶች እንዴት በፍጥነት እንደሚሰራጩ ዳግም ወደ ውይይት አምጥቶታል።

በአሁኑ ጊዜ ማስክ ለምን ይህን እርምጃ እንደወሰደ የሚያረጋግጥ ይፋዊ ምክንያት የለም።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

መልካም ጉዞ...ተፃፈ በመሐሪ ነጋሽ (የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኮሚኒኬሽን )   | ዛሬ ማምሻውን የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ልዑክ ቡድናችንን በከፍተኛ ኩራትና በመልካም ...
02/08/2026

መልካም ጉዞ...

ተፃፈ በመሐሪ ነጋሽ
(የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኮሚኒኬሽን )

| ዛሬ ማምሻውን የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ልዑክ ቡድናችንን በከፍተኛ ኩራትና በመልካም ምኞት ወደ አሜሪካ ኦሪገን ሸኝተናል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌቶቻችን በተሟላ ዝግጅት ወደ ሻምፒዮናው እንዲያቀኑ ሱሉልታ በሚገኘው የጀግናው ኦሊምፒያን አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ሆቴል በማሳረፍ አስፈላጊውን ድጋፍ፣ ክትትልና ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል።

የቀነኒሳ በቀለ ሆቴልም አትሌቶቻችንን እንደቤተሰቦቹ በመቀበል፣ በፍቅር፣ በአክብሮትና በልዩ እንክብካቤ እስከ ሽኝታቸው ድረስ አግዟቸዋል።

ለዚህ ውድ አስተዋፅኦ ከልብ የመነጨ ምስጋና ተቀበሉ

ዓለም የሚጠብቀው ሻምፒዮና 21ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች (World Athletics U20 Championships) ሻምፒዮና ....

በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት ዩጂን ከተማ በሚገኘው ታሪካዊው ሄይዋርድ ፊልድ ከሐምሌ 29 እስከ ነሐሴ 3 ይካሄዳል።

ከ1,700 በላይ ወጣት አትሌቶች ከ190 የሚጠጉ አገራት በ44 የውድድር ዓይነቶች ላይ ይፎካከራሉ።

ዩጂን ከተማ በግምት 180,000 የሚጠጋ ህዝብ ያላት ብትሆንም፣ በዓለም ላይ "Track Town USA" በሚል ስም የምትታወቅ የአትሌቲክስ ዋና መዲና ናት።

የሻምፒዮናው ትኬቶች በፍጥነት እየተሸጡ እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጸዋል፣ ውድድሩም በብዙ የዓለም አቀፍ የቴሌቪዥን ኔትወርኮች፣ ዲጂታል መድረኮች እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የስፖርት ጋዜጠኞች ይሸፈናል። የዚህ ውድድር ቀደምት እትሞች በ140 በላይ አገራት በቴሌቪዥን ተሰራጭተው 16 ሚሊዮን በላይ የተጠራቀመ የቲቪ ተመልካች ደርሰው ነበር።

በ2024 በፔሩ ሊማ በተካሄደው 20ኛው ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 6 የወርቅ፣ 1 የብር እና 2 የነሐስ ሜዳሊያዎችን በማሸነፍ በአጠቃላይ 9 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ በዓለም 2ኛ ደረጃን ማስመዝገቧ ይታወሳል።

ዘንድሮም አትሌቶቻችን በ5000 ሜትር፣ 3000 ሜትር፣ 1500 ሜትር፣ 800 ሜትር፣ 3000 ሜትር መሰናክል፣ 400 ሜትር እና በርምጃ ውድድሮች ላይ የኢትዮጵያን ስም በክብር ለማስጠራት ዝግጁ ናቸው።

ለጀግኖቻችን...
ውድ አትሌቶቻችን!
ከእናንተ ጋር የሚጓዘው የኢትዮጵያ 60 ዓመታትን ያስቆጠረ የድል ታሪክ ነው፤ የአበበ ቢቂላ ጨምሮ
የብዙ ጀግኖች የድል አሻራ ነው።

ኢትዮጵያውያን ልብ ከእናንተ ጋር ነው። በእግራችሁ የምትሮጡት ለራሳችሁ ብቻ ሳይሆን ለሀገራችሁ፣ ለሕዝባችሁ እና ለመጪው ትውልድ ነው።

መልካም ጉዞ!
መልካም ውድድር!

መልካም ዕድል! 🇪🇹❤️

በዚህ ዓመት ቼልሲን ነው ማየት  | ​አርጀንቲናዊው አማካይ ቫለንቲን ‘ኮሎ’ ባርኮ ከፈረንሳዩ አርሲ ስትራስቡርግ በቋሚ ዝውውር ወደ ቼልሲ ለማቀናት የሚያስችለውን ስምምነት በይፋ ማጠናቀቁ ተ...
02/08/2026

በዚህ ዓመት ቼልሲን ነው ማየት

| ​አርጀንቲናዊው አማካይ ቫለንቲን ‘ኮሎ’ ባርኮ ከፈረንሳዩ አርሲ ስትራስቡርግ በቋሚ ዝውውር ወደ ቼልሲ ለማቀናት የሚያስችለውን ስምምነት በይፋ ማጠናቀቁ ተረጋገጠ።

በዚህ ወር አዲሱን ክለቡን የሚቀላቀለው ይህ ወጣት ተጫዋች ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለመመለስ ሙሉ ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ሲሆን ሁሉም አስፈላጊ የውል ስምምነቶችም በይፋ ተፈራርመዋል።

የአሰልጣኝ ሻቢ አሎንሶን ሙሉ ይሁኝታ ያገኘው የባርኮ ዝውውር የቼልሲን የአማካይ ክፍል በከፍተኛ ሁኔታ ያጠናክራል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

አሜሪካ የዓመቱ ምርጥ መምህር ካለች በኋላ በቁጥጥር ስር ያዋለቻቸው ኢትዮጵያዊው መምህር  | ​በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት ኢትዮጵያዊው ዶክተር በርሃኑ ገረሱ...
02/08/2026

አሜሪካ የዓመቱ ምርጥ መምህር ካለች በኋላ በቁጥጥር ስር ያዋለቻቸው ኢትዮጵያዊው መምህር

| ​በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት ኢትዮጵያዊው ዶክተር በርሃኑ ገረሱ ክብረት ከአሜሪካ የፋርማሲ ኮሌጆች ማህበር የ"ዓመቱ ምርጥ መምህር" ሽልማት ተቀብለው በመመለስ ላይ እያሉ በዳላስ-ፎርት ዎርዝ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የሀገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት እንደገለጸው ዶክተር በርሃኑ እ.ኤ.አ በሰኔ 2021 በሕጋዊ መንገድ ወደ አሜሪካ የገቡ ቢሆንም የተቀመጠላቸው የቪዛ ጊዜ እ.ኤ.አ ግንቦት 31 ቀን 2024 ካበቃ በኋላ በሀገሪቱ ውስጥ መቆየታቸውን ተከትሎ በኢሚግሬሽንና ጉምሩክ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ አስታውቋል።

​የሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ በሰጠው መግለጫ ድርጊቱ እጅግ እንዳሳሰበውና ዶክተር በርሃኑ ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ ያላቸው በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ዘንድ እጅግ የሚወደዱና ውጤታማ መምህር መሆናቸውን ገልጿል።

ከዚህ ቀደም በዊልያም ፓተርሰን ዩኒቨርሲቲ በሱሰኝነት መንስኤዎችና ሕክምና ዙሪያ በምርምር የሰሩት ዶክተር በርሃኑ ያለባቸው የቪዛ ስጋት በፍጥነት ተፈትቶ ወደ ተቋሙ ተመልሰው አጠቃላይ የማስተማርና የምርምር ሥራቸውን እንደሚቀጥሉ ዩኒቨርሲቲው ተስፋ ማድረጉን አስታውቋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

የሼክ ሙሐመድ አል አሙዲ ሀብታቸው እየጨመረ ነው  | ​በኢትዮጵያ ቀዳሚው ባለሀብት ሼክ ሙሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ጠቅላላ የሀብት መጠናቸው 10.1 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ተከተሎ በዓለም አቀ...
02/08/2026

የሼክ ሙሐመድ አል አሙዲ ሀብታቸው እየጨመረ ነው

| ​በኢትዮጵያ ቀዳሚው ባለሀብት ሼክ ሙሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ጠቅላላ የሀብት መጠናቸው 10.1 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ተከተሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ በ10 ቢሊዮን ዶላር የሀብት ማማ ላይ ከተቀመጡ የዓለማችን ቢሊየነሮች ክበብ ውስጥ ዳግም ተቀላቀሉ።

እንደ ብሉምበርግ ቢሊየነርስ ኢንዴክስ አዲስ መረጃ የሳዑዲ-ኢትዮጵያዊው ቢሊየነር ሀብት ከፈረንሳይኞቹ ዓመት መ ካት ጀምሮ በ1.67 ቢሊዮን ዶላር ወይም በ19.7 በመቶ እድገት በማሳየቱ በዓለም አቀፍ የሀብታሞች ዝርዝር ውስጥ በ375ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

በኢንዱስትሪ፣ በኢነርጂ እና በበርካታ ዘርፎች ላይ ባሏቸው መዋዕለ ንዋዮች ላይ የታየው ከፍተኛ የገበያ ዋጋ ጭማሪ ለዚህ የሀብት እድገት ዋና ምክንያት የሆነ ሲሆን ይህም የሀገራችን ቁጥር አንድ ባለሀብትነታቸውን ይበልጥ ያጠናከረ አጋጣሚ ሆኗል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

ባህርዳር ዩኒቨርስቲ በEVACONET የአርክቴክቸር ዲዛይን ውድድር አንደኛ ሆነ   | አዲስ አበባ – በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው የEVACONET ዲጂታል የኮንስትራክሽን ገበያ ፕላት...
02/08/2026

ባህርዳር ዩኒቨርስቲ በEVACONET የአርክቴክቸር ዲዛይን ውድድር አንደኛ ሆነ

| አዲስ አበባ – በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው የEVACONET ዲጂታል የኮንስትራክሽን ገበያ ፕላትፎርም የምረቃ ሥነ ሥርዓት አካል በሆነው የአርክቴክቸር ዲዛይን ውድድር ባህርዳር ዩኒቨርስቲ አንደኛ ደረጃን በማስመዝገብ አሸናፊ ሆኗል።

ውድድሩ በዩኒቨርስቲዎች የአርክቴክቸር ዲፓርትመንት 5ኛ ዓመት ተማሪዎች መካከል የተካሄደ ሲሆን፣ ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ሁለተኛ፣ አዲስ ኮሌጅ ደግሞ ሶስተኛ ደረጃን አግኝተዋል። አዘጋጆቹ ውድድሩ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን ያስተዋወቀ እንደነበር ገልጸው፣ ከዚህ በኋላም በየዓመቱ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።

EVACONET በኢንጂነር አቤሴሎም መለሰ የተቋቋመ ዲጂታል የኮንስትራክሽን ገበያ ፕላትፎርም ሲሆን፣ የኮንስትራክሽን ማቴሪያል ወቅታዊ ዋጋዎችን በማነጻጸር ሻጮችና ገዢዎችን በአንድ መድረክ የሚያገናኝ የዲጂታል ገበያ ሥርዓት ነው።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር የትምጌታ አስራት፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ባለድርሻ አካላትና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል። ተናጋሪዎቹም ፕላትፎርሙ የ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ራዕይን ለማሳካት እንደሚያግዝ፣ በኮንስትራክሽን ገበያ ውስጥ ግልጽነትና ተወዳዳሪነትን እንደሚያሳድግ ገልጸዋል።

በእለቱ "ሕይወትን በኮንስትራክሽን እንገንባ" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የኮንስትራክሽን ፋሽን ሾውና የሞዴሎች ትዕይንትም ቀርቦ የተሳታፊዎችን ቀልብ ስቧል።

ዝግጅቱ ለተሳካ አፈጻጸም አስተዋጽኦ ላደረጉ ተቋማትና ግለሰቦች የእውቅና እና የልዩ ሽልማት ስጦታዎች በመበርከት ተጠናቋል።

መድኃኔአለም በሐጢዓት ፈተና ተጠልፎ ከመውደቅ ይጠብቀን🙏የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ቄርሎስ “ለቤተ ክርስቲያን ስትል በአደባባይ በጥፊ የተመታህ አቤቱ ይህን ማድረግህ እርስዋን በከበረ ደ...
02/08/2026

መድኃኔአለም በሐጢዓት ፈተና ተጠልፎ ከመውደቅ ይጠብቀን🙏

የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ቄርሎስ “ለቤተ ክርስቲያን ስትል በአደባባይ በጥፊ የተመታህ አቤቱ ይህን ማድረግህ እርስዋን በከበረ ደምህ ትቀድሳት ዘንድ ነው፡፡

ለእርስዋ ሲል ታሥሮ መጎተት የቻለ የበደለውም በደል ሳይኖር፣ ርኩስ ምራቅን ሲተፋበት የታገሠ መድኃኔ ዓለም በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ” በማለት ገለጸው፡፡ በመለኮቱ ሕያው ሲሆን በስጋው ግን ሞትን ቀመሰ፡፡ የአዳምን ሞት በሞቱ ሊሽር መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን በገዛ ፈቃዱ አሳልፎ ሰጠ፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ሰው ሆኖ እንደሚያድነን በመጀመሪያ ለአዳም ቃል ገባለት፡፡ ከዚያም በነቢያት ትንቢት አስነገረ፡፡ በስጋ በተገለጠ ጊዜም የሰቀሉትና የገደሉት አይሁድ ሳይቀሩ እንዲናገሩ አፋቸውን አስከፈታቸው፡፡

ቅዱስ ጳውሎስም “ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን… አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን” ይላል፡፡ “ስለ ሕዝቡም ሁሉ አይደለም፣ ነገር ግን የተበተኑትን የእግዚአብሔርን ልጆች በአንድነት እንዲሰበስባቸው መጥቷል እንጂ።” ተብሎ ተጽፏልና፡፡ በድንቅ ተዋህዶ አምላክ ሰው፣ ሰውም አምላክ ሆኗልና ከኛ በነሳው ስጋም ወደ ሰማይ አረገ፡፡ ስለፍጹም የሰው ልጆች ፍቅር መድኃኔ ዓለም ተላልፎ ተሰጠ፡፡

በፊልጵ 2÷8 “በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፣ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ” ተብሎ እንደተጻፈው፡፡ በማዳኑ ስራ ውስጥ የቅድስት ድንግል ማርያም ድርሻ ታላቅ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም በገላ 4÷4 “የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ፡፡” ሲል ጽፏል፡፡

ዕለት ዕለት ፍቅሩን የከፈለልንን ዋጋ፣ ይህን መከራውንና ማዳኑን ዕለት ዕለት የሚያስቡ ገዳማውያን ሌሊትና ቀን በስግደትና በጸሎት ይተጋሉ፡፡ ገዳማቱን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጸና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

ስንጀምር የደረሰብን ተቃውሞና ትችት ፈታኝ ነበር፦ሙላቱ አስታጥቄአለም ለስራዎቻችን የሚገባቸውን ክብር አልሰጠም፦ ሙላቱ አስታጥቄ  | የኢትዮ ጃዝ አባት ሙላቱ አስታጥቄ ለአፍሪካ ባህላዊና ሀገ...
02/08/2026

ስንጀምር የደረሰብን ተቃውሞና ትችት ፈታኝ ነበር፦ሙላቱ አስታጥቄ

አለም ለስራዎቻችን የሚገባቸውን ክብር አልሰጠም፦ ሙላቱ አስታጥቄ

| የኢትዮ ጃዝ አባት ሙላቱ አስታጥቄ ለአፍሪካ ባህላዊና ሀገር በቀል የጥበብ ስራዎች በአለም መድረክ ላይ ተገቢው ክብርና እውቅና አልተሰጣቸውም ሲል ተናግሯል።

የኢትዮ ጃዝ ሙዚቃ ስልት መሥራችና ባለቤት የሆነው አንጋፋው ባለብዙ መሣሪያ ተጫዋቹ ሙላቱ አስታጥቄ የአፍሪካ ሀገር በቀል የጥበብ ስራዎች እና ባህላዊ ሙዚቃዎች የሚገባቸው ዓለም አቀፋዊ እውቅና እና ክብር እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮ ጃዝ የሙዚቃ አባት ሙላቱ አስታጥቄ ከ ዘጋርዲያን ጋር ባደረገው ቆይታ ስለ ኢትዮጵያና አፍሪካ ባህላዊና ሀገር በቀል የሙዚቃ ስራዎች ሰፊ ማብራርያ ሰጥቷል።

የኢትዮ ጃዝን አዲስ የሙዚቃ ስልት በ1960ዎቹ ለመጀመሪያ ጊዜ ለህዝብ ሲያስተዋውቅ ከፍተኛ ተቃውሞና ፈታኝ ሁኔታዎች ገጥመውት እንደነበር አስታውሷል።

ሙላቱ አስታጥቄ ባለፉት ሁለት አሥርት አመታት ይህ ድንቅ ስልት በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅግ የተወደደና የብዙዎችን ቀልብ መሳብ መቻሉን ገልጿል።

በመሆኑም የአፍሪካን የሙዚቃ ሀብትና ባህላዊ እሴቶች ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ የቀደሙትም ሆነ የዛሬዎቹ ሀገር በቀል የጥበብ ስራዎች የሚጫወቱት ሚና ትልቅ በመሆኑ ተገቢውን ክብር ማግኘት እንዳለባቸው አሳስቧል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል



ታይዋን ለሞሮኮ ዜጎች የምትሰጠውን የቪዛ አገልግሎት አገደች  | ታይዋን ለሞሮኮ ዜጎች የምትሰጠውን የቪዛ አገልግሎት ማገዷን ይፋ አድርጋለች።ሞሮኮ "አንድ ቻይና" ("One-China") ፖሊሲ...
02/08/2026

ታይዋን ለሞሮኮ ዜጎች የምትሰጠውን የቪዛ አገልግሎት አገደች

| ታይዋን ለሞሮኮ ዜጎች የምትሰጠውን የቪዛ አገልግሎት ማገዷን ይፋ አድርጋለች።

ሞሮኮ "አንድ ቻይና" ("One-China") ፖሊሲ ጋር የተያያዘውን የቤጂንግ አቋም የምትደግፍ በመሆኗ ከታይዋን ጋር ያለው የንግድና የጉዞ ግንኙነት እንቅፋት ገጥሞታል።

ውሳኔው የተሰማው ሞሮኮ በንጉሥ ሞሃመድ 6ኛ አመራር ስር ያስመዘገበችውን የ27 ዓመታት የኢኮኖሚና የማህበራዊ እድገት በታላቅ ድምቀት በማከበር ላይ በምትገኝበት ወቅት ነው።

የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እገዳውን የጣለው ሞሮኮ ቀደም ሲል ለታይዋን ዜጎች ትሰጥ የነበረውን የመግቢያ ፈቃድ በማቋረጧ ምክንያት እንደሆነ አስታውቋል።

የሞሮኮ ንጉሥ ሞሃመድ 6ኛ ስልጣን ከተረከቡበት ጊዜ ጀምሮ ሞሮኮ በሰሜን አፍሪካ የኢንዱስትሪና የንግድ ማዕከል ለመሆን ያደረገችው ጉዞ ስኬት አምጥቶላታል።

የሁለቱ ሀገራት የቪዛ ውሳኔ በዜጎች እንቅስቃሴ እና በንግድ ልውውጥ ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ የማይቀር ነው ተብሏል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል



Address

Gabon Avenue (Washington DC Square/Sterling Buildg)
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን):

Shortcuts

Share