Yekatit 12 Hospital Medical College

Yekatit 12 Hospital Medical College Yekatit 12 Hospital was founded in 1923 and one of the 1st modern hospitals in the country.

Yekatit 12 Hospital started providing medical education in 2011 and changed its name to Yekatit 12 Hospital Medical College.

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለህክምና ተማሪዎቹ የጋወን ማልበስ (White Coat Ceremony) መርሃ-ግብር አካሄደ​የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የህክምና ዶክተርነት ትምህር...
06/08/2026

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለህክምና ተማሪዎቹ የጋወን ማልበስ (White Coat Ceremony) መርሃ-ግብር አካሄደ

​የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የህክምና ዶክተርነት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ እና የንድፈ-ሀሳብ (ቲዎሪ) ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ አንደኛ ዓመት የተግባር ህክምና ትምህርት (C1) ለሚሸጋገሩ ተማሪዎቹ የጋወን ማልበስ ስነ-ስርዓት በደመቀ ሁኔታ አካሂዷል።

​በዚህ በታላቅ ድምቀት በተካሄደው መርሃ-ግብር የሜዲካል ኮሌጁ ዲንና የጡት እና ኢንዶክራይን ሰብ-ስፔሻሊስት ዶክተር ወንደወሰን አምታታው እንዲሁም የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ም/ፕሮቮስት ዶክተር መአዛ ሮሪሳን ጨምሮ የኮሌጁ መምህራንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

​በመርሃ-ግብሩ ላይ የሜዲካል ኮሌጁ ዲን ዶክተር ወንደወሰን አምታታው እንደገለጹት፤ በህክምና ትምህርት ጉዞ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ጋወን መልበስ፣ በመቀጠልም የኢንተርንሺፕ ልምምድ እና በስተመጨረሻም የቃለ-መሐላ ስነ-ስርዓት መፈጸም ለሕክምና ተማሪዎች ልዩና የማይረሱ ታላላቅ ምዕራፎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

​በእለቱ የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ም/ፕሮቮስት ዶክተር መአዛ ሮሪሳ እና የኮሌጁ አመራሮች ለተማሪዎቹ ጋወን ያበሱ ሲሆን፣ ተማሪዎቹም እስከ አሁን በነበራቸው የንድፈ-ሀሳብ ትምህርት ወቅት ላስተማሩዋቸውና ላነፁዋቸው መምህራኖቻቸው የላቀ ምስጋና በማቅረብ የእውቅና ስጦታዎችን አበርክተዋል።

​📍 የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን

📅 ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም
📍
📌 Follow Us on Social Media
👉 Facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063650457050

👉 Telegram: Join Our Channel https://t.me/Y12HMCC

👉 Follow us on tiktok
https://vm.tiktok.com/ZMHWJyPGKQmQp-dftjE

🔖 💛✨

🌟🏆 YEKATIT 12 HOSPITAL MEDICAL COLLEGE LABORATORY ACHIEVES A FIVE-STAR RATING!A Major Milestone in Quality, Excellence &...
04/08/2026

🌟🏆 YEKATIT 12 HOSPITAL MEDICAL COLLEGE LABORATORY ACHIEVES A FIVE-STAR RATING!

A Major Milestone in Quality, Excellence & Patient-Centered Laboratory Services

The Laboratory of Yekatit 12 Hospital Medical College has achieved an outstanding milestone by earning a prestigious Five-Star Rating in the latest SLIPTA laboratory quality assessment, conducted using the SLIPTA Checklist Version 3:2023, aligned with the internationally recognized ISO 15189:2022 standard.

This achievement is particularly significant as it represents the laboratory’s first assessment following the transition from ISO 15189:2012 to the updated ISO 15189:2022 standard, marking an important step forward in strengthening laboratory quality and international best practices.

Under the previous assessment framework, the laboratory was evaluated against 275 assessment points. With the introduction of the revised and more comprehensive assessment system, the laboratory was assessed against 367 points—a broader and more demanding quality framework.

According to Lecturer Tamrat Belema, Director of the Laboratory and Microbiology Academic and Service Directorate, this remarkable accomplishment was made possible through the strong commitment, coordinated efforts, and teamwork of the entire laboratory team.

He expressed his sincere appreciation to the Hospital Management, Laboratory Quality Team Microbiology staff Laboratory staff, and for their dedication, professionalism, accountability, and tireless efforts in strengthening laboratory quality standards.

This achievement demonstrates that sustainable quality improvement is not achieved by a single individual—it is built through shared responsibility, effective leadership, teamwork, accountability, and a culture of continuous improvement.

The Five-Star Rating is more than a recognition—it is a reflection of Yekatit 12 Hospital Medical College’s continued commitment to healthcare quality, patient safety, professional excellence, and internationally aligned laboratory services.

It reinforces our commitment to ensuring that every patient receives safe, accurate, reliable, timely, and high-quality laboratory services.

Your dedication, professionalism, and teamwork have transformed quality improvement into measurable excellence.

📌 Follow Us on Social Media
👉 Facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063650457050

👉 Telegram: Join Our Channel https://t.me/Y12HMCC

👉 Follow us on tiktok
https://vm.tiktok.com/ZMHWJyPGKQmQp-dftjE/

🔖

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ  ለአረንጓዴ ኢትዮጵያ የራሱን አሻራ አኑሯልየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አዲስ አበባ ሃምሌ 27/2018 ዓ.ምኢትዮጵያን በአረንጓዴ ልማት ለመልበስ ...
03/08/2026

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ለአረንጓዴ ኢትዮጵያ የራሱን አሻራ አኑሯል

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አዲስ አበባ ሃምሌ 27/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያን በአረንጓዴ ልማት ለመልበስ የተፈጥሮ ሀብቷን ለመጠበቅና ለመጪው ትውልድ ጤናማና ዘላቂ አካባቢን ለማስረከብ በተያዘው ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ጉዞ 800 ሚልዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር የመትከል ታላቅ እንቅስቃሴን ተቀላቅሏል።

በዚህ ሀገራዊ ተልዕኮ የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ከሀገራዊው ንቅናቄ ጎን በመቆም በተግባር ተሳትፎውን አሳይቶ የራሱን አረንጓዴ አሻራ አኑሯል።

ይህ ተግባር ችግኝ የመትከል ብቻ ተግባር አይደለም፤ ለነገ ተስፋ መዝራት ለተፈጥሮ ዕድሳት መሠረት መጣል እና ለመጪው ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን ማዘጋጀት ነው።

እንደ ጤና ተቋም የህብረተሰብ ጤናን ከአካባቢ ጥበቃ ጋር በማስተሳሰር የዛሬ ተግባራችን የነገ ጤናማ ትውልድ መሠረት እንዲሆን ሜዲካል ኮሌጁ ቁርጠኝነቱን በተግባር አሳይቷል።

📌 Follow Us on Social Media
👉 Facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063650457050

👉 Telegram: Join Our Channel https://t.me/Y12HMCC

👉 Follow us on tiktok
https://vm.tiktok.com/ZMHWJyPGKQmQp-dftjE/

🔖

የዘመናዊ የአጥንትና መገጣጠሚያ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አዲስ አበባ ሃምሌ 27/2018 ዓ.ም በየካቲት 12 ሆስፒታል ...
03/08/2026

የዘመናዊ የአጥንትና መገጣጠሚያ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አዲስ አበባ ሃምሌ 27/2018 ዓ.ም

በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የአጥንትና መገጣጠሚያ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት በልዩ ባለሙያዎችና በዘመናዊ የሕክምና አሰራር በጥራት እየተሰጠ ይገኛል።

በአጥንት ቀዶ ህክምና ዘርፍ የሙሉ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ (Total Hip Replacement) እና የሙሉ ጉልበት መገጣጠሚያ ቅየራ (Total Knee Replacement) በተለያዩ የመገጣጠሚያ ችግሮች ምክንያት የሚያጋጥም ከባድ ሕመምን ለማከም፣ የመንቀሳቀስ አቅምን ለማሻሻልና የታካሚዎችን የኑሮ ጥራት ለማሳደግ ወሳኝ የሆኑ የቀዶ ሕክምና አማራጮች ናቸው። እነዚህን አገልግሎቶች በማስፋፋቱ ረገድ ግንባር ቀደም የሆነው ተቋማችን አሁንም በከፍተኛ ጥራት አገልግሎት ፈላጊዎችን ፣ በሠብ ስፔሻሊቲ ደረጃ እያስተናገደ ይገኛል።

ይህ ከፍተኛ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት በተቋማችን መሰጠቱ ታካሚዎች ለሕክምና ወደ ሌሎች ቦታዎች መሄድ ሳያስፈልጋቸው፣ በአገራቸው ውስጥ ተደራሽና ጥራት ያለው ልዩ የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል አቅምን ያሳያል።

📌 Follow Us on Social Media
👉 Facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063650457050

👉 Telegram: Join Our Channel https://t.me/Y12HMCC

👉 Follow us on tiktok
https://vm.tiktok.com/ZMHWJyPGKQmQp-dftjE/

🔖

01/08/2026
🧠✨ EMPOWERING YOUTH. BUILDING CONFIDENT LEADERS.Yekatit 12 Hospital Medical College – Youth-Friendly Health Services Aug...
01/08/2026

🧠✨ EMPOWERING YOUTH. BUILDING CONFIDENT LEADERS.

Yekatit 12 Hospital Medical College – Youth-Friendly Health Services

August 1, 2026
15 OTZ Club Members | Ages 18–20

Yekatit 12 Hospital Medical College, in partnership with the Operation Triple Zero (OTZ) Club, delivered an engaging one-day training on Emotional Intelligence & Advanced Communication Skills, equipping young people with practical tools to manage emotions, overcome peer pressure, handle difficult situations, communicate assertively, and build healthy relationships.

As part of the program, participants visited the Youth-Friendly Health Service, learning how to access confidential, respectful, and non-judgmental healthcare for young people aged 10–24, including mental health, sexual and reproductive health, HIV counseling and testing, personal development, career counseling, relationship counseling, addiction recovery, and GBV care.

Special appreciation to the Yekatit 12 HMC ART Clinic Team, CDC Facilitators, Media Team, and OTZ Club Members for their commitment, expertise, and active participation.

🌱 We are not just developing skills—we are empowering a generation to think, communicate, connect, and lead with confidence and emotional intelligence.

💚 Empower the Youth. Strengthen Their Voice. Shape the Future.

📌 Follow Us on Social Media
👉 Facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063650457050

👉 Telegram: Join Our Channel https://t.me/Y12HMCC

👉 Follow us on tiktok
https://vm.tiktok.com/ZMHWJyPGKQmQp-dftjE/

🔖

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የ2019 ዓ.ም የሥራ ዕቅድ ዝግጅት አደረገ።የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አዲስ አበባ ሃምሌ 24/2018 ዓ.ም ዕቅዱ የመንግስትን የሪፎርም ትግበራ...
01/08/2026

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የ2019 ዓ.ም የሥራ ዕቅድ ዝግጅት አደረገ።

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አዲስ አበባ ሃምሌ 24/2018 ዓ.ም

ዕቅዱ የመንግስትን የሪፎርም ትግበራ እቅድ የተቋሙን 10 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ እና ተቋማዊ የስራ አቅጣጫዎችን መሠረት አድርጎ የተዘጋጀ ነው

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የ2019 ዓ.ም የሥራ ዕቅድ ዝግጅት በተቋሙ የህክምና አገልግሎት የአካዳሚክ እና የአስተዳደር ዘርፎች የዲፓርትመንት ሃላፊዎችና ዳይሬክተሮች በተገኙበት ነው የታቀደው።

የ2019 ዓ.ም የሥራ ዕቅዱ ከመንግስት የወረደውን የሪፎርም ትግበራ እቅድ እንደ ዋና መነሻና መሠረት በማድረግ እንዲሁም ከተቋሙ የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድና ከተቋሙ ራዕይ ተልዕኮና ተቋማዊ ግቦች ጋር በማስተሳሰር እየተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም መሠረት የመንግስት የሪፎርም አቅጣጫዎች በተቋሙ የሥራ ዘርፎች ውስጥ በተጨባጭ የሚተገበሩበት መንገድ በዕቅዱ ውስጥ እንዲካተት ትኩረት ተሰጥቷል። ይህም የሪፎርሙ ዓላማዎች በዕቅድ ደረጃ ብቻ ተወስነው እንዳይቀሩ፣ ወደ ተግባር በመቀየር የሚጨበጥ ውጤት እንዲመጣ ለማስቻል ነው።

የዕቅድ ዝግጅቱን ያስጀመሩት የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሮቮስት አቶ አለሙ ክብረት ለተሳታፊዎች ስለ2019 ዓ.ም ዕቅድ አዘገጃጀት ሂደት ሰፊ ማብራሪያና ኦረንቴሽን ሰጥተዋል።

በሰጡት ማብራሪያም የ2019 ዓ.ም ዕቅድ በመንግስት የተቀመጡ የሪፎርም አቅጣጫዎችን ከተቋሙ ስትራቴጂክ ግቦች ጋር በማጣጣም እንዲዘጋጅ አስገንዝበዋል። በተለይም ዕቅዱ ተጨባጭ ሊለካ የሚችል፣ ተፈጻሚና ውጤት ተኮር እንዲሆን እና የሪፎርም ትግበራው በየደረጃው በግልጽ የሥራ ኃላፊነት እንዲወርድ አፅንዖት ሰጥተዋል።

በዕቅድ ዝግጅቱ የተቋሙ አጠቃላይ ዕቅድ ወደ የሥራ ክፍሎች በተዋረድ እንዲወርድ የሚያስችል አሠራር ተቀምጧል።

በመጀመሪያ ዳይሬክቶሬቶች የመንግስትን የሪፎርም ትግበራ አቅጣጫና የተቋሙን ዕቅድ ወደ ኬዝ ቲሞች ያወርዳሉ። ኬዝ ቲሞችም የተሰጣቸውን የሥራ ድርሻ በመተንተን ወደ ግለሰብ ዕቅድ ያወርዳሉ።

ይህ ሂደት ከመንግስት የሪፎርም አቅጣጫ ወደ ተቋማዊ ዕቅድ ወደ ዳይሬክቶሬት ወደ ኬዝ ቲም ወደ ግለሰብ ዕቅድ የሚወርድ በመሆኑ እያንዳንዱ ሠራተኛ በሪፎርሙ ትግበራና በተቋሙ ስትራቴጂካዊ ግቦች ላይ የራሱን ድርሻ በግልጽ እንዲያውቅና እንዲወጣ የሚያደርግ ነው።

በአጠቃላይ የ2019 ዓ.ም የሥራ ዕቅድ ዝግጅቱ የመንግስትን የሪፎርም ትግበራ አቅጣጫ መሠረት ያደረገ ከተቋሙ የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ጋር የተጣጣመ ከተቋም ወደ ዳይሬክቶሬት ከዳይሬክቶሬት ወደ ኬዝ ቲም እና ከኬዝ ቲም ወደ ግለሰብ የሚወርድ ውጤት ተኮር የዕቅድ ሥርዓት ለመዘርጋት ያለመ ነው።

የዕቅድ ዝግጅቱ በቀጣይ ቀናትም በየዘርፉ በጥልቀት የሚቀጥል ሲሆን የተቋሙን የ2019 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም በሪፎርም ትግበራ በህክምና አገልግሎት በአካዳሚክ በአስተዳደርና በሌሎች ተቋማዊ ዘርፎች የተሻለ ውጤት ላይ ለማድረስ መሠረት ይጥላል።

📌 Follow Us on Social Media
👉 Facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063650457050

👉 Telegram: Join Our Channel https://t.me/Y12HMCC

👉 Follow us on tiktok
https://vm.tiktok.com/ZMHWJyPGKQmQp-dftjE/

🔖

የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የሠራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር የ2018 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ አደረገ!የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አዲስ አበባ ሐምሌ 23...
31/07/2026

የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የሠራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር የ2018 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ አደረገ!

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አዲስ አበባ ሐምሌ 23/ 2018 ዓ.ም

የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የሠራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር የ2018 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ አካሂዶ የ2017 ዓ.ም ኦዲት ሪፖርትና የ2018 ዓ.ም የስራ አፈፃፀምን በመገምገም የቀጣይ ዘመን የስራ አቅጣጫዎችን ለይቷል።

በግምገማው ወቅት የማህበሩን የብድር አገልግሎት የበለጠ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ለአባላት ምቹ ለማድረግ የተያዙ የማሻሻያ ስራዎች በጠቅላላ ጉባኤው ውሳኔ አግኝተዋል። በዚህ መሠረተረ ከተሻሻሉት ውስጥ የብድር ጣሪያ ፣ ብድር ተከፍሎ የሚጠናቀቅበት ጊዜ ፣ የዋስትና ስርዓቱ እና የብድር የአገልግሎት ክፍያ ናቸው። በተጨማሪም የ2017 ዓ.ም ትርፍ ክፍፍል ውሳኔ ተሰጥቶበታል።

የማህበሩን የሂሳብ አያያዝ digitalize ለማድረግ Peachtree Accounting የሂሳብ አስተዳደር ስርዓትን በመተግበር የሂሳብ አያያዙ ዘመናዊ ሆኗል። እህም በማህበሩ ታሪክ የመጀመሪያው ሲሆን በቀጣይም ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን በመተግበር አባላት ገንዘባቸውን በቀላሉ መከታተል የሚችሉ ይሆናል። ይህም የማህበሩን የገንዘብ አያያዝ ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ትክክለኛነት ለማጠናከር የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።

በማህበሩ ታሪክ በ2018 ዓ.ም የማህበሩ አባላት በከፍተኛ ደረጃ የገንዘብ ብድር የወሰዱበት ዓመት ነው። በተለይም መንግስት ለሠራተኞች ባመቻቸው የመኖሪያ ቤት ዕድል አባላት የሚያስፈልጋቸውን የገንዘብ ለማሟላት የማህበሩ የብድር አገልግሎት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል። በዚህ አመት ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር ለአባላት ተሰኣጭቷል። ይህ አፈጻጸም ማህበሩ ለአባላቱ የገንዘብ አቅም ማሳደጊያና የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት የሚያበረክተውን ሚና የሚያሳይ መሆኑ ተመላክቷል።

የማህበሩ አባላት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱም በግምገማው ተጠቁሟል። የአባላት ቁጥር መጨመር የማህበሩ አገልግሎት ተደራሽነት እየሰፋ መምጣቱን የሚያመላክት ሲሆን፣ ከዚህ ጋር ተያይዞ የማህበሩን አገልግሎት አቅም ማሳደግና የአባላትን ፍላጎት በተሻለ ሁኔታ ማሟላት ቀጣይ ትኩረት እንደሚሻ ተገልጿል።

በተጨማሪም በማህበሩ የአባልነት መስፋፋት ሂደት ውስጥ የኮንትራት ሰራተኞችን በብድርና ቁጠባ ማህበሩ ውስጥ እንዲካተቱ የሚያስችል ማሻሻያ ተደርጓል። ይህም ሰራተኞች በቁጠባ ባህል እንዲሳተፉና አስፈላጊ በሆኑ ጊዜያት ከማህበሩ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዕድል የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል።

በግምገማው ከተነሱ ጉዳዮች መካከል የማህበሩ አገልግሎት ለሁሉም አባላት ተደራሽና ፍትሃዊ እንዲሆን የተለያዩ አማራጮችን ማስፋት አንዱ ነው። በዚህም የሙስሊም ሰራተኞች ከሃይማኖታዊ እሴቶቻቸው ጋር የሚስማማ በሸሪዓ መርሆች መሰረት የሚቀርብ የቁጠባና የብድር አማራጭ እንዲያገኙ ማድረግ በቀጣይ የሚታይ ጉዳይ መሆኑ ተገልጿል።

ዶ/ር አብዮት አለሙ የሆስፒቲል ሜዲካል ኮሌጁ የኘሮቮስት አማካሪና የብድርና ቁጠባ ማህበሩ ዋና ሰብሳቢ እንዳሉት የ2018 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም ግምገማው ማህበሩ ባለፈው ዓመት ያስመዘገባቸውን ውጤቶች በመገምገም፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመለየትና የአባላትን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የማሻሻያ አቅጣጫዎችን በመለየት በቀጣይ ዘመን የማህበሩን አገልግሎት የበለጠ ዘመናዊ፣ ተደራሽና ቀልጣፋ ለማድረግ ጠንካራ መሰረት የጣለ መሆኑ ገልጿል።

የማህበሩ ዋና ዓላማም የአባላትን ቁጠባ በማበረታታት፣ ተገቢ የብድር አገልግሎት በመስጠትና የአባላትን የኢኮኖሚ አቅም በማጠናከር የአባላቱን ተጠቃሚነት ማሳደግ ነው።

በጨረሻም የሆስፒታሉ ማኔጅመንት ለማህበሩ ቢሮ እና ሌሎች አገልግሎቶች በነፃ በመፍቀዳቸው ለሰራተኛው ጥቅም የቆሙ በመሆናቸው በከፍተኛ ደረጃ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል። የማህበሩ ሰራተኞች ላበረከቱት አስተዋፅኦ ምስጋና ተችሮአቸዋል። የማህበሩ ኮሚቴዎች እንዲሁም ወረዳ 6 ማህበራት ማደራጃ ላደረጉት አስተዋፅኦ በአባላት ስም ምስጋና ቀርቦላቸዋል።
በመጨረሻም አባላት ለስብሰባ ሲጠሩ ሰዐት አክብረው በመገኘት በገንዘባቸው ላይ ለሚወሰነው ውሳኔ የበኩላቸውን እንዲያደርጉ ተጠይቋል።

📌 Follow Us on Social Media
👉 Facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063650457050

👉 Telegram: Join Our Channel https://t.me/Y12HMCC

👉 Follow us on tiktok
https://vm.tiktok.com/ZMHWJyPGKQmQp-dftjE/

🔖

በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በተካሄደው የክረምት በጎ ፈቃድ የደም ልገሳ መርሃ ግብር 34 ዩኒት ደም በስኬት ተሰበሰበየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ | አዲስ አበባ | ሃምሌ 2...
29/07/2026

በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በተካሄደው የክረምት በጎ ፈቃድ የደም ልገሳ መርሃ ግብር 34 ዩኒት ደም በስኬት ተሰበሰበ

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ | አዲስ አበባ | ሃምሌ 22/2018 ዓ.ም.

ሰውን ከሞት ለማዳን ከሚደረጉ በጎ ተግባራት መካከል የደም ልገሳ ከፍተኛ ስፍራ ይይዛል። በዚህ እሳቤ መሠረት የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የክረምት በጎ ፈቃድ የደም ልገሳ መርሃ ግብርን በማዘጋጀት ለእናቶች፣ ለህፃናት፣ ለአደጋ ተጎጂዎች እና በአስቸኳይ ደም ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች የህይወት ተስፋ የሚሆን 34 ዩኒት ደም በስኬት ማሰባሰብ ችሏል።

መርሃ ግብሩ የተካሄደው በሆስፒታሉ ውስጥ የበጎ ፈቃድ የደም ልገሳ ባህልን ለማጠናከር፣ የደም እጥረትን ለመቀነስ እና ለታካሚዎች ቀጣይነት ያለውን የደም አቅርቦት ለማረጋገጥ በታለመ መልኩ ነበር።

በመርሃ ግብሩ የሆስፒታሉ አመራሮች፣ ሐኪሞች፣ ነርሶች፣ ሌሎች የጤና ባለሙያዎች፣ የአካዳሚ አባላት፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እና ተማሪዎች በሰፊው በመሳተፍ ለሰው ሕይወት ያላቸውን ቁርጠኝነት በተግባር አሳይተዋል። ይህም ተቋሙ ከሕክምና አገልግሎት ባሻገር ማህበራዊ ኃላፊነቱን በከፍተኛ ደረጃ እየተወጣ መሆኑን አረጋግጧል።

የመርሃ ግብሩ አስተባባሪ ሸዋዬ ንጉሴ እንደገለፁት፣ የተሰበሰበው 34 ዩኒት ደም በተለይም በወሊድ ጊዜ ከፍተኛ ደም ለሚያጡ እናቶች፣ ለሕፃናት፣ ለቀዶ ህክምና ታካሚዎች፣ ለአደጋ ተጎጂዎች እና በአስቸኳይ ደም ለሚፈልጉ ታካሚዎች ሕይወት ለማዳን ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ገልፀዋል።

የሆስፒታሉ የአካዳሚ አባልና የላብራቶሪና የማይክሮባዮሎጂ ትምህርትና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር ሌክቸረር ታምራት ቤሌማ በበኩላቸው፣ አንድ ዩኒት የተለገሰ ደም ከአንድ በላይ ሰው ሕይወትን ማትረፍ እንደሚችል በመግለጽ፣ የበጎ ፈቃድ የደም ልገሳ ባህል በማህበረሰቡ ዘንድ የዘወትር ልምድ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

እንደ ገለፃቸው፣ የዚህ መርሃ ግብር ስኬት የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ማህበረሰብ ለሕይወት ማዳን ስራ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየ ሲሆን፣ ወደፊትም ተመሳሳይ የደም ልገሳ መርሃ ግብሮች በመደበኛነት እንደሚካሄዱ እና የደም እጥረትን ለመቀነስ ተቋሙ በትጋት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በመጨረሻም ለዚህ ሰብዓዊ ተግባር በፈቃደኝነት ደም የለገሱ ሁሉንም አመስግነው፣ የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ጥራት ያለውን ሕክምና ከመስጠት ባሻገር ሕይወትን የሚያድኑ ማህበራዊ ፕሮግራሞችን በቀጣይነት በማጠናከር ለማህበረሰቡ የላቀ አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጧል።

"ደም መለገስ ሕይወትን ማዳን ነው፤ የእናንተ አንድ ልገሳ ለሌላ ሰው አዲስ የሕይወት ተስፋ ይሆናል።"

📌 Follow Us on Social Media
👉 Facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063650457050

👉 Telegram: Join Our Channel https://t.me/Y12HMCC

👉 Follow us on tiktok
https://vm.tiktok.com/ZMHWJyPGKQmQp-dftjE/

🔖

29/07/2026

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yekatit 12 Hospital Medical College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Yekatit 12 Hospital Medical College:

Shortcuts

Share