ጤና ይስጠን-Tena Yisten

ጤና ይስጠን-Tena Yisten ጤና ነክ መረጃዎች የሚተላለፉበት እና ትምህርታዊ ጽሁፎች የሚለጠፉበት መድረክ ነው።

ጤና ይስጠን: ጤና ይስጣችሁ።
Tena-Yisten Medical Information. add a member...

15/07/2026
Nice!
11/07/2026

Nice!

አለማወቅ ደፋር ያደርጋል!ይህ አባባል እንደ ዛሬው እውነት ሆኖ የሚያውቅበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም። በየፖድካስቱና በየቴሌቪዥን ጣቢያው ላይ የምናየው ነገር ይሄንኑ ነው።ስለ ጤና፣ ስለ ታሪክ፣...
04/07/2026

አለማወቅ ደፋር ያደርጋል!

ይህ አባባል እንደ ዛሬው እውነት ሆኖ የሚያውቅበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም። በየፖድካስቱና በየቴሌቪዥን ጣቢያው ላይ የምናየው ነገር ይሄንኑ ነው።

ስለ ጤና፣ ስለ ታሪክ፣ ስነ-ልቦና፣ ስለ ኢኮኖሚ... በቃ ስለ ሁሉም ነገር የሚያውቁ የሚመስሉ ግን ደግሞ ጥልቀት የሌላቸው ሰዎች ማይክ ይዘው በድፍረት ሲናገሩ እናያለን።

የሚገርመው ደፋር መሆናቸው ብቻ አይደለም። ዓመታትን ሙሉ በትምህርት እና ልምድ ያሳለፉትን ባለሙያዎችን በድፍረት ሲያጣጥሉ እና ስህተት እንደሆኑ ሊያስረዱን ሲሞክሩ ስናይ... ነገሩ ግርምትንም ቁጭትንም ይፈጥራል።

አንድ ሰው ስለ አንድ ርዕሰ ጉዳይ ያለው እውቀት ወይም ብቃት በጣም ዝቅተኛ በሆነ ቁጥር የራሱን ድክመት እና አለማወቅ የመገምገም አቅሙም አብሮ ይጠፋል።ግለሰቡ ስለ ጉዳዩ ጥልቀት ስለማያውቅ እራሱን "ከፍተኛ አዋቂ" አድርጎ ይገምታል። በዚያ ምክንያት ንግግሩ ውስጥ ምንም አይነት ጥርጣሬ ወይም ፍርሃት አይታይበትም።

በተቃራኒው ደግሞ አንድ ሰው ስለ ጉዳዩ እያጠና እና እያወቀ በሄደ ቁጥር ነገሩ ምን ያህል ሰፊ እና ውስብስብ እንደሆነ መረዳት ይጀምራል። ያን ጊዜ ገና ብዙ መማር አለብኝ፣የማላውቀው ነገር ብዙ ነው ብሎ እራሱን ዝቅ ያደርጋል፣ ንግግሩም ጥንቃቄ የተሞላበት ይሆናል።

አሁን የምናየዉ ድፍረት ማህበረሰባችን ውስጥ የሚያመጣው ትልቁ አደጋ ማህበረሰቡ ዓመታትን ሙሉ ለፍተው እውቀት ካካበቱ ባለሙያዎች ይልቅ፣ ማይክ ለያዙ ቦታ መስጠት ሲጀምር...የእውቀት እና የባህል መዋቅር መናጋት ይጀምራል።ይህ በሚሆንበት ጊዜ ወጣቱ ትውልድ ምን ይማራል? "ለመታወቅ፣ ለመከበር እና ሰው እንዲያዳምጠኝ መማርና መልፋት አያስፈልገኝም፤ ዝም ብዬ በድፍረት መናገር ብቻ ይበቃኛል" የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ ይይዛል።

ስለዚህ አንድ ሰው በከፍተኛ በራስ መተማመን ስላወራ ወይም ድምጹን ከፍ ስላደረገ ብቻ... ያ ሰው "አዋቂ" ነው ማለት እንዳልሆነ መረዳት አለብን።

የእውቀት ትልቁ ጠላት አለማወቅ ሳይሆን፣ አዋቂ መምሰል ነው ።

✍️ዶክተር ኃይለልዑል መኮንን | የአዕምሮ ሕክምና ስፔሻሊስት

04/07/2026

ወንድማችንን እናሳክመው

ይህ ወንድማችን አዳሙ ታከለ እጅጉ ይባላል። በሙያው ጤና መኮንን ሲሆን ከ 2014 ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ህብረተሰባችንን በማገልገል ላይ ይገኛል::

ሆኖም ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ባደረበት ህመም ሳቢያ በተደጋጋሚ በከባድ እራስ ምታት፣ የድካም ስሜት እና አልፎ አልፎ የአይን ብዠታ የነበረው ሲሆን አሁን ላይ ደግሞ የቀኝ አይኑ ሙሉ በሙሉ እይታውን አጥቱዋል።

ምክንያቱን ለማወቅ በተሰራው ምርመራ (Brain MRI) የጭንቅላት ውስጥ እጢ (Brain Tumor )እንዳለበት ተረጋግጡዋል:: ይህ ብቻ አይደለም በቶሎ የህክምና እርዳታ ካላገኘ እና እጢዉ እያደገ ከመጣ ለሌላኛዉ አአይኑም የእይታ ስጋት እንደሆነ ለመረዳት ተችልዋል።

ይህ ወንድማችን ለዚህ ህክምና የተጠየቀውን ወጪ እጅ ከፍተኛ ፣ ብቻውን ለሸፈን ከአቅሙ በላይ ስለሆነበት እና ጊዜ የሚሰጥ ነገር ስላልሆነ ሁላችሁም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ያላችሁ ኢትዮጲያዊያን የእርዳታ እጃችሁን እንድትዘረጉለት በፈጣሪ ስም ተጠይቃችኋል።

ለመርዳት ፈቃደኛ ለሆናችሁ ከታች በተዘረዘሩት የባንክ የሂሳብ ቁጥሮች ከጐኑ መቆም ትችላላችሁ።

የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ (CBE)
ስም፦ Adamu Takele Ejigu
የ ሂሳብ ቁጥር፦ 1000195495444

የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ
የሂሳብ ቁጥር፦ 01320893584300

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ
የሂሳብ ቁጥር፦ 1000030535484

[Share]

04/07/2026
27/05/2026

ከአገው ግምጃ ቤት መጀ/ደ/ሆስፒታል አሳዛኝ ነገር ተፈፅሟል! የ 5 ወር ዲዩቲ ክፍያ መቅረቱን ተከትሎ ባለሙያዎቹ የዲዩቲ ስራ ማቆም አክሽን ፕላን ስላወጡና ማስጠንቀቂያ ስለሰጡ የሆስፒታሉ አስተዳደር ኬዝ ቲም በቁርጥ ውሳኔያቸው ስጋት ስላደረበት ባለሙያን ማሳደድ ጀምሯል! ከዚህ በፊት ታስሮ የነበረውን ዶክተር አፈወርቅ ደመላሽን ለማሰር የእስር ትዕዛዝ ሲያወጡበት ጀግናው ዶክተር ጥሎ ሸሽቷል ። ሀኪም የማይከበርባትና የሚሸማቀቅባት ሀገር ሆናለች ሀገሪቱ ።
ፎቶዉ ከዚህ በፊት በእስር በነበረበት ወቅት የተነሳ ነዉ።

በብዙ እንቅልፍ አልባ ሌሊቶች የተገኘ የወርቅ ሜዳልያ📌የዶክተር ሜሮን ለገሰ ድል  | አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት በተለያዩ የሕክምና ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 263 አዳዲስ ባለሙያዎችን...
21/03/2026

በብዙ እንቅልፍ አልባ ሌሊቶች የተገኘ የወርቅ ሜዳልያ

📌የዶክተር ሜሮን ለገሰ ድል

| አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት በተለያዩ የሕክምና ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 263 አዳዲስ ባለሙያዎችን ሲያስመርቅ፣ የአንድ ወጣት ጥረትና ጽናት በክብር አዳራሹ ውስጥ በልዩ ድምቀት ተስተጋብቷል።

ለዓመታት የዘለቁ አድካሚ የጥናት ሌሊቶች፣ እረፍት የሌላቸው ቀናትና ፈታኝ ፈተናዎች ዛሬ በደስታ እንባና በድል አክሊል ተተክተዋል። በዚህ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከመላው ተመራቂዎች የላቀ 3.95 ውጤት በማስመዝገብ የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ ለመሆን የበቃችው ዶክተር ሜሮን ለገሰ የዕለቱ ደማቅ ኮከብ ሆናለች።

የስኬቱ ምስጢር፡ ትጋትና ድጋፍ

ዶክተር ሜሮን ስኬቷን አስመልክቶ ለጋዜጣ ፕላስ በሰጠችው ቃል፣ መንገዱ አልጋ በአልጋ እንዳልነበረ ገልጻለች። "ፈተናው ቢነገር አያልቅም" የምትለዋ ሜሮን፣ ለዚህ ክብር እንድትበቃ የሚከተሉት ወሳኝ ነበሩ ብላለች፦

* የፈጣሪ እገዛ፡ በሁሉም እርምጃዎቿ አጋዥ እንደነበራት።

* የቤተሰብና የመምህራን ድጋፍ፡ ከጎኗ ያልተለዩዋት የቤተሰቧ አባላትና ዕውቀት ያጋሯት መምህራኖቿ።

* የጊዜ አጠቃቀም፡ ሰፊ ንባብና ከፍተኛ ትኩረት የሚጠይቀውን የሕክምና ትምህርት በብቃት ለመወጣት ጊዜዋን በአግባቡ የመጠቀም ጥበቧ።

"ትምህርቱ ሰፊ የማንበብ ጊዜና ትኩረት የሚጠይቅ ነበር፤ ነገር ግን ያን ጊዜ በአግባቡ መጠቀሜ ዛሬ ለዚህ ስኬት አብቅቶኛል" — ዶክተር ሜሮን ለገሰ

ዶክተር ሜሮን በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሴት ተማሪዎች ውጤታማነት እየጨመረ መምጣቱ ለሌሎች ተነሳሽነት እንደሚፈጥር ጠቅሳለች። ትምህርቷን አጠናቃ ስትመረቅ ግን የያዘችው ትልቁ ራዕይ ሜዳልያውን ማጥለቅ ብቻ አይደለም፤ ሕዝቧንና ሀገሯን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል ነው።
ጤና ይስጠን-Tena Yisten

17/03/2026

Meet Dr. Meron Legesse, the gold medalist from Addis Ababa University's medicine class of 2026, with a CGPA of 3.95.

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጤና ይስጠን-Tena Yisten posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share