Kibatu berore

Kibatu berore Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kibatu berore, AIDS Resource Center, Addis Ababa.

26/11/2024
02/10/2024

22/09/2024
18/09/2024
18/09/2024

ኢትዮጵያዊ እሴቶችን ማጎልበት ለጋራ ተጠቃሚነት!

አብሮ መብላት፣ ተያይዞ ማደግ፣ ተጋምዶ መኖር፣ ሀዘንንም ደስታንም መካፈል የኢትዮጵያውያን ልዩ እሴቶቻችን ናቸው። የመተሳሰብ እሴታችን ድንበር ሳይገድበን ለአፍሪካውያን እህት ወንድሞቻችን እንድናስብና በምንችለው ሁሉ ከጎናቸው እንድንቆም አስችሎናል፡፡

አፍሪካውያን በቅኝ ግዛት በሚማቀቁበት ዘመን ኢትዮጵያውያን ሉዓላዊነታቸውን በመስዋዕትነታቸው አስጠብቀው የነፃነት ብርሀን ከመፈንጠቃቸው ባሻገር አለኝታነታቸውን በተለያየ አግባብ በመግለፅ የነፃነት ትግላቸውን እንዲያጠናክሩ የሞራል ስንቅም ሆነዋቸዋል፡፡

ታላቁን የዓባይ ወንዝ ጨምሮ የተፈጥሮ ሀብቶቿንም ቢሆን ብቻየን ልጠጣ፣ ብቻየን ልመገብ ሳትል ሁሉም የተፋሰሱ ሀገራት የተሻለ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት ብርቱ እንቅስቃሴ አድርጋለች፤ ማንንም በማይጎዳ አግባብ ተገንብቶ ወደ መጠናቀቁ የተቃረበውን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እንደ ማሳያ መጥቀስ ይቻላል፡፡

የጋራ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለቀጠናዊ እና አህጉራዊ ትስስር የሚኖረውን ጉልህ ሚና በመረዳት የሚደረጉ ዲፕሎማሲያዊ እርምጃዎችም የትብብርና የፉክክር ሚዛንን የጠበቁ ናቸው፡፡
እኛ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት በወንድማማችነት እና በእህትማማችነት ያስተሳሰሩን የማንነት መገለጫዎች፣ ዓለምን ያስደመሙ ድንቅ እሴቶች፣ ባህልና ወጎች ያሉን ህዝቦች ነን፡፡ ይህ ዓለም የሚመሰክረው ዘመናትን የተሻገረ የእኛ እውነት ነው፡፡

እነዚህን እሴቶች ይዘን ከሌሎች ሀገራት ጋር ሀገራዊ ክብርን ያስቀደመ፣ ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ፣ ለጎረቤት ሀገራት ቅድሚያን በመስጠት ቀጠናዊ ትብብርና የኢኮኖሚ ውህደት ላይ መሠረት ያደረገ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲን በመከተል ባለፉት የለውጡ አመታት የዛሬዋንና የነገዋን ኢትዮጵያ በፅኑ መሠረት ላይ ሊገነባ የሚችል የውጭ ግንኘነት ስራ እየተሰራን እንገኛለን፡፡

ብልፅግና ፓርቲ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በፉክክር እና በትብብር መካከል ሚዛን በመጠበቅ፣ ተቃርኖዎችን በማስታረቅ የሚጓዝ መሆን እንዳለበት የሚያምን በመሆኑ ከዚሁ አንፃር ጠንካራ የውጭ ግንኙነትና የዲፕሎማሲ ስራዎች ተሰርተዋል፤ ፍሬም አፍርቷል፡፡ ለአብነትም የህዳሴ ግድባችን አሁን ያለበት ደረጃ ሊደርስ የቻለው የሁሉም ኢትዮጵያዊ የእውቀት የጉልበት እና የገንዘብ አሻራ እንደተጠበቀ ሆኖ በዲፕሎማሲ መስክ በፓርቲያችን እሳቤ ላይ በመሆን በተከናወነው ብርቱ ስራ ነው።

በፓርቲያችን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዐብይ አህመድ እና በሌሎችም የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች እልህ አስጨራሽ ትግል እና የተግባቦት ብቃት የተገኘው፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ቅቡልነቷን በማጎልበት የግዙፉ የብሪክስ ስብስብ አባል መሆኗም ተጠቃሽ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ በፈጣን የለውጥ ጉዞ ላይ ናት ፤ በቅርቡ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያም ይህንን የተገኘውን ስኬት የሚያፀና፣ ሀገራችን የጀመረችውን ሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዞ ፍጥነት የሚጨምር እና እውን የሚያረግ ሲሆን ፤ ከሀገራት ጋር የኢኮኖሚ ትስስርን በማሳደግ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀማመሩ ተግባራትም ከራዕያችን ስኬታማነት ጋር የማይነጣጠሉ ናቸው።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት

11/09/2024

በአዲስ ተስፋ ብርሃን በአበባየሆሽ ታጅበን፣ ለአዲሱ ትውልድ ተስፋን ሰንቀን እነሆ 2016ን በድል አጠናቀን 2017ን አሃዱ ብለን ጀምረናል።

እንኳን ለ2017 አዲሱ አመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን!

የአስራ ሶስት ወራት ጸጋ ባለቤት የሆነችው ሀገራችን ኢትዮጵያ አሮጌውን አመት ሸኝታ እነሆ አዲሱን አመት በክብር ተቀበለች።

በነበረው አመት የነበረንን የመልካም እሳቤ ወረት፣ የአዲሱ ትውልድን ብልጽግናን በመሻት እና በመታተር ወደ ድል የሚያመጡ ጉዳዮችን አሳልፈናል።

እኛ ኢትዮጵያዊያን የጋራ ጠላት የሆነውን ድህነትን ለማሸነፍ በየደረጃው የበርካታ ውጣ ውረዶች ገፈት ቀማሾች ሆነን አያሌ ጊዜያትን አሳልፈናል።

የሚያግባቡን በርካታ ጉዳዮችን አጎልብተን ከዘመን ዘመን የተሸጋገርን በራሳችን ሀገር የራሳችንን ሚና በመወጣት ሀገር ሳናስደፍር ለትውልድ ለማስረከብ ደፋ ቀና የምንል የመደመር ትውልድ ፍሬዎችም ጭምር ነን!

አዲሱን አመት ስንቀበል በአሮጌው አመት የነበሩትን ተግዳሮቶች የበለጠ ተምረንባቸው በአዲሱ አመት አዳዲስ የድል ብስራቶችን ጨምረን ወደ ተሻለ ብልጽግና መጓዝ ይጠበቅብናል።

በዓሉን ስናሳልፍ በመተባበር፣በመተሳሰብና በአብሮነት በማድረግ አብሮ የመኖር እሴቶቻችንን በማጎልበት ያለው ለሌለው ካለው ላይ በማካፈል መሆን ይገባዋል።በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣የመተሳሰብ፣ የአብሮነትና የአንድነት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

:- አቶ ሙሉጌታ ጉሉማ
በብልጽግና ፓርቲ የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ


https://linktr.ee/addis_ababa_prosperity_party

11/09/2024

ውድ ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ2017 አዲስ አመት አደረሰን!!

በአዲሱ አመት ብዝሃነታችን የሚያፀኑ ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን በማጎልበት ፤ አንዳችን ለሌሎቻችን አቅም በመሆን ለዘላቂ ብልጽግና መረጋገጥ እንደ አንድ ልብ አሳቢ ፤ አንድ ቃል ተናጋሪ በመሆን ጠንክረን መስራት ይኖርብናል።

በ2016 ዓ/ም የሠራናቸው በርካታ የልማት ስራዎችን በ2017 ከመቼውም ጊዜ በላይ አጠናክረን በመፈፀም የህብረተሰባችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተግተን መስራት ይጠበቅብናል።

የ2017 አዲስ አመት ስናከብር ኢትዬጵያዊ እሴቶቻችን የሆኑ መቻቻልን ፣ መከባበርን ፣ እንዲሁም መደጋገፍን ማዕከል አድርገን በማክበር ፤ የሌላቸውን በማሰብና በመደገፍ በዓብሮነት ስሜት ልናከብር ይገባል።

መጪው አዲስ አመት አንድነታችንን የምናጠናክርበት የሀገራችንን ተጠናክሮ የቀጠለ የለውጥ ጎዞ ከግብ የምናደርስበት የውጤት ዘመን እንዲሆን እመኛለሁ።

በመጨረሻም በዓሉ የሠላም ፣ የፍቅር ፣ የብልጽግና እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ።

፦አቶ ተወዳጅ ኃ/ማርያም
በብልፅግና ፓርቲ የአራዳ ክ/ከተማ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ


https://linktr.ee/addis_ababa_prosperity_party

11/09/2024

ለመላው ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የከተማችን ወጣቶች መልካም አዲስ አመት!
አዲሱ አመት የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት ይሁንልን!!

እኛ ወጣቶች አዲሱን አመት ስንቀበል ያለፈውን አመት በምስጋና ሸኝተን መጪውን ጊዜ በተስፋ እና በብርሃን በተሻለ አስተሳሰብ ከፍታ ፤በህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት እሳቤ ለመቀበል ዝግጁነታችን የምናረጋግጥበት ሊሆን ይገባል ።

አዲሱ ዓመት ለሀገራዊ ራዕያችን፤ እሴቶቻችን እና ምኞቶቻችን ስኬት በአዲስ መንፈስና ብርታት የምንቆምበትና ቃላችንን የምናድስበት እንዲሆን ምኞቴ ነው ።

ወጣቶች መጪው ዘመን በጽናት እና በቁርጠኝነት ለሀገራችን ብልጽግና እውን መሆን በተሰማራንበት የሙያ መስክ የምንተምበት ፤ የተሻለ ስኬቶች የምናስመዘግብበት እንዲሆን እየተመኘው በድጋሚ እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰን አደረሳቹ።

፦ ወጣት መለሰ አባተ
በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ወጣቶች ሊግ ኃላፊ


https://linktr.ee/addis_ababa_prosperity_party

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kibatu berore posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share