Biruksew Medical Clinic

Biruksew Medical Clinic Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Biruksew Medical Clinic, Medical and health, summit chrkos condominium, Addis Ababa.

25/08/2026

እንኳን ለመውሊድ በዓል በሰላም አደረሰዎ!

በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን!
Irra deebiin baga geessan - Iid Mubaarak!
መልካም የመውሊድ በዓል!

+251936659999

እርግዝና እና የደም ማነስበእርግዝና ጊዜ የደም ማነስ ያጋጥማል?በእርግዝና ጊዜ ከብረት ማዕድን (አይረን) እጥረት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የደም ማነስ ማጋጠሙ የተለመደ ነው፤ ሆኖም በቀላሉ መከላ...
22/07/2026

እርግዝና እና የደም ማነስ
በእርግዝና ጊዜ የደም ማነስ ያጋጥማል?

በእርግዝና ጊዜ ከብረት ማዕድን (አይረን) እጥረት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የደም ማነስ ማጋጠሙ የተለመደ ነው፤ ሆኖም በቀላሉ መከላከል የሚቻልም ነው። ነፍሰ ጡር መሆንሽን ካወቅሽ በኋላ በምታደርጊው/ባደረግሽው የመጀመሪያ ምርመራ በሰውነትሽ ውስጥ ያለው የብረት ማዕድን መጠን ምርመራ ይካተታል፤ ሆኖም ያኔ መጠኑ የተስተካከለ የነበረ ቢሆን እንኳ በቀጣዮቹ ወራት የመቀነስ ዕድሉ ከፍተኛ ነው።

እርግዝናሽ አጋማሹ አካባቢ ሲደርስ (20 ሳምንት አካባቢ)፣ ሰውነትሽ ውስጥ የሚዘዋወረው ደም መጠን በጉልህ ይጨምራል። ሆኖም ቀይ የደም ሴሎችን ለማምረት የሚያፈልገው የብረት ማዕድን መጠን ደግሞ ይቀንሳል። ይህ ተደማምሮ የደም ማነስ ያስከትላል።

ደግነቱ ይህን መሰሉን የደም ማነስ በቀላሉ መከላከል ይቻላል። አንዱ መንገድ የብረት ማዕድን (አይረን) የያዙ እንክብሎችን መውሰድ ነው (ይህ እንደ አስፈላጊነቱ በሚከታተልሽ ሐኪም ሊታዘዝልሽ ይችላል)። ሌላው ደግሞ በብረት ማዕድን የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ ነው።

የሚከተሉት ምግቦች በብረት ማዕድን የበለጸጉ ናቸው:-

👉🏾 ጥቁር ወይም ሠርገኛ ጤፍ
👉🏾 ቀይ ሥጋ
👉🏾 ጉበት
👉🏾 ቱና
👉🏾 አረንጓዴ ቅጠላ ቅጠሎች (ጎመን፣ ቆስጣ የመሳሰሉት)
👉🏾 ባቄላ፣ አተር፣ ምስር
👉🏾 ቀይ ሥር
👉🏾 እንቁላል (በተለይ አስኳሉ)
👉🏾 አጃ

📌የስራ ሰዓት:- 24 በሰዓት 7 ቀናት እንገኛለን
🚨ለህክምና አገልግሎት ማማከር እገልግሎት ከፈለጉ በ 📞+251936659999 / +251911911895 ይደውሉ።
Telegram፦ https://t.me/biruksewclinic
Facebook፦https://www.facebook.com/share/1E9a6eHeGa/
e-mail ፦[email protected]
Tiktok፦ user7316172087151

ቅድመ እርግዝና ክትትል (Preconception Care)‎ቅድመ እርግዝና ስንል ምን ማለት ነው?‎ቅድመ እርግዝና ማለት በመውለጃ ዕድሜ ክልል ላይ ያሉ ጥንዶች በሚቀጥሉት 3 ወራት ውስጥ የመው...
13/07/2026

ቅድመ እርግዝና ክትትል (Preconception Care)

‎ቅድመ እርግዝና ስንል ምን ማለት ነው?
‎ቅድመ እርግዝና ማለት በመውለጃ ዕድሜ ክልል ላይ ያሉ ጥንዶች በሚቀጥሉት 3 ወራት ውስጥ የመውለድ እቅድ ካላቸው ማግኘት ያለባቸው የቅድመ ዝግጅት እንክብካቤ ነው። ይህ አገልግሎት የጤና፣ የባህሪ እና የማህበራዊ ስጋቶችን በመለየት ጤናማ እርግዝና ለማረጋገጥ ይረዳል።

‎በቅድመ እርግዝና ክትትል ወቅት ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገቡ ነጥቦች

‎ለሴቶች (የእናቶች ጤና)
‎1. ሥር የሰደዱ በሽታዎች ምርመራ እና አያያዝ፦
‎▫️እንደ ስኳር፣ ደም ግፊት፣ የሚጥል በሽታ፣ የልብ ሕመም፣ የኩላሊት በሽታ እና የአእምሮ ጤና ችግሮች ያሉባቸውን ሴቶች ቀድመው መለየት።
‎▫️በሽታውን መቆጣጠር እና መድኃኒቶቻቸው ለፅንሱ ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ ወይም መቀየር።
‎▫️እንደ ልብና ኩላሊት ሕመም ያሉ ከባድ በሽታዎች ካሉ እርግዝናን ለማዘግየት ምክር መስጠት።
‎▫️የሚጥል በሽታ ካለ በእርግዝና ወቅት የሚፈቀድ መድሃኒት እንዲወስዱ እና ቢያንስ ለ6 ወር በሽታውን መቆጣጠር ይገባል።

‎2. ስነ-ምግብ እና የአመጋገብ ሁኔታ፦
‎▫️ፎሊክ አሲድ፦ ከመፀነሳቸው በፊት በየቀኑ 400μg (0.4mg) ፎሊክ አሲድ መውሰድ የፅንስ የነርቭ ቱቦ ጉድለቶችን ለመከላከል ይረዳል። ፎሊክ አሲድ ከአርንጓዴ ቅጠላቅጠሎች፣ ባቄላ፣ ኦቾሎኒ፣ ሱፍ፣ ፍራፍሬ፣ ጥራጥሬ፣ ጉበት እና ዓሣ ማግኘት ይቻላል።
‎▫️ተጨማሪ ንጥረ ነገሮች፦ በአዮዲን የበለጸገ ጨው መጠቀም እና የአንጀት ጥገኛ ትላልትሎችን ማከም ያስፈልጋል።
‎▫️አመጋገብ፦ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ እና ጤናማ የሰውነት ክብደት መጠበቅ አስፈላጊ ነው። ለደም ማነስ ምርመራ ማድረግ ይመከራል።

‎3. የተላላፊ በሽታዎች ምርመራ እና ክትባት፦
‎▫️እንደ ኤች.አይ.ቪ፣ የአባለዘር በሽታዎች እና ሄፓታይተስ ቢ ያሉ በሽታዎችን መመርመር እና ሕክምና መጀመር።
‎▫️እንደ መንጋጋ ቆልፍ (ቴታነስ)፣ ትክትክ (ኩፍኝ) እና ሄፓታይተስ ቢ ያሉ ክትባቶችን ማጠናቀቅ።

‎4. የማህጸን በር ካንሰር እና ሌሎች በሽታዎች፦ የማህጸን በር ካንሰር ምርመራ እና አስፈላጊውን ሕክምና ማግኘት።

‎5. የአእምሮ ጤና፦
‎▫️ሁሉም ሴቶች ለድብርት፣ ለጭንቀት፣ ራስን ስለማጥፋት ሃሳብ እና ከወሊድ በኋላ ስለሚታዩ የባህሪ ለውጦች መጠየቅ እና አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል ።

‎6. ልዩ ሁኔታዎች እና በዘር የሚተላለፉ በሽታዎች፦
‎▫️ተደጋጋሚ ውርጃ፣ የሞተ ልጅ መውለድ፣ ያለጊዜው መውለድ፣ የተዛባ የፅንስ አፈጣጠር ወይም የእድገት ውስንነት ታሪክ ያላቸውን ሴቶች በልዩ ባለሙያ ማስተናገድ።
‎▫️በቤተሰብ ውስጥ በዘር የሚተላለፉ በሽታዎች ካሉ የዘረመል ምርመራ ማድረግ እና ከባለሞያዎች ጋር መምከር ያስፈልጋ፤ ይህ የእናትም የአባትም እኩል አስተዋጽኦ አለው።

‎7. የአኗኗር ዘይቤ ማስተካከያ፦
‎▫️ከመጠን ያለፈ ውፍረትን ማስተካከል፣ አልኮል እና ሲጋራ ማቆም፣ አደንዛዥ ዕፅ ከመጠቀም መራቅ።
‎▫️በየቀኑ ለ30 ደቂቃ ያህል የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ እና ክብደትን መቆጣጠር።
‎▫️ቡና እና ካፌይን ያላቸውን መጠጦች በቀን ከ3 ሲኒ በታች መጠጣት።

‎8. ለአደጋ ተጋላጭነት መከላከል የመሳሰሉት ተጠቃሽ ሲሆኑ በቂ መረጃ እንዲኖር ወጣቶች እና ጥንዶች ስለቤተሰብ ምጣኔ እና ስለ እርግዝና ዝግጅት በቂ መረጃ ማግኘት አለባቸው። የወሊድ መከላከያ አማራጮችን በማየት በመረጃ ላይ ተመስርተው እርግዝናን ማቀድ ይገባል።

‎ቅድመ እርግዝና ምርመራ እና ክትትል በማድረግ እና ማማከር እገልግሎት ከፈለጉ በ +251936659999 / +251911911895 ይደውሉ።
Telegram፦ https://t.me/biruksewclinic
Facebook፦https://www.facebook.com/profile.php?id=100063808903287
e-mail፦[email protected]
Tiktok፦ user7316172087151
Dylan Page - News Daddy Commercial Bank of Ethiopia Kana TV European Union in Ethiopia

እርግዝና እና የእግር ማበጥበእርግዝና ጊዜ የእግር ማበጥ (በተለይ መጫሚያ እና ቁርጭምጭሚት) ብዙ ሴቶችን ያጋጥማቸዋል። እብጠቱ ምቾት ሊነሣ፣ አንዳንዴም ሊያሳስብ ይችላል።የእግር ማበጥ የሚከ...
09/07/2026

እርግዝና እና የእግር ማበጥ

በእርግዝና ጊዜ የእግር ማበጥ (በተለይ መጫሚያ እና ቁርጭምጭሚት) ብዙ ሴቶችን ያጋጥማቸዋል። እብጠቱ ምቾት ሊነሣ፣ አንዳንዴም ሊያሳስብ ይችላል።
የእግር ማበጥ የሚከሰተው ለምንድን ነው?
በእርግዝና ጊዜ የእግር ማበጥን የሚያስከትሉ 3 ዋና ምክንያቶች አሉ።
1, በእርግዝና ጊዜ በሰውነትሽ ውስጥ የሚገኘው የደም መጠን ይጨምራል
2, ልጅሽ እያደገና ሆድሽ እየገፋ ሲመጣ፣ ማሕጸንሽ ከእግሮችሽ ወደ ልብ ደም የሚመልሱትን የደም ቧንቧዎች በመጠኑ ይጫናቸዋል
3, የሆርሞን ለውጥ ወደ ልብ ደም የሚመልሱትን የደም ቧንቧዎች ግድግዳ ውፍረት እንዲጨምር ያደርጋል፤ ይህም በቀላሉ ደም እንዳይመልሱ ያደርጋል
ከእነዚህ ምክንያቶች የተነሣ እግሮችሽ ደም ያግታሉ፤ ተያይዞም እብጠት ይፈጠራል።

የእግር እብጠት የሚፈጠረው የቱ'ጋ እና መቼ ነው?

እብጠት የሚኖረው መጫሚያ እግርሽ እና ቁርጭምጭሚትሽ ላይ ብቻ መሆን አለበት። የእግር እብጠት ስንልም ይህንን ማለታችን እንጂ ሌላውን የእግር ክፍል አይደለም። የእጅሽ ጣቶችም ከወትሮው ሞላ ሊሉ ይችላሉ፤ ቀለበትሽም ሊጠብሽ ይችላል — ሆኖም ሲታይ ልዩነቱ በሚያስታውቅ ደረጃ ሊያብጡ አይገባም።
የእግር እብጠት በአብዛኛው የሚሰማሽ ቀኑ እየገፋ ሲመጣ ነው። የዚህ ዋነኛው እና ግልጹ ምክንያት እግር ተዘቅዝቆ ስለሚቆይና ሰውነትሽ ውስጥ ያለው ፈሳሽ ወደ ታች ወርዶ ለመጠራቀም እድል ስለሚያገኝ ነው። ውሎሽ ብዙ መቆም የሚጠይቅ ከሆነ ደግሞ እብጠቱ የከፋ ይሆናል።
የእግር እብጠት የሚከሰተው በአብዛኛው ከ5ኛ ወር ጀምሮ ነው፤ ብሶ የሚሰማሽ ደግሞ ከ6 ወር በኋላ (በእርግዝና የመጨረሻው 3-ወር ጊዜ) ነው። ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄዱ ለአንቺም ሆነ ለልጅሽ የሚያመጣው ጉዳት ባይኖርም ምቾትሽን ግን ሊቀንስ ይችላል።

በእርግዝና ጊዜ የእግር ማበጥ አሳሳቢ የሚሆነው ምን ሲሆን ነው?

የእግር እብጠት የሚያጋጥም እና የተለመደ ቢሆንም፣ የሚከተሉት መለያዎች ካሉት በአፋጣኝ ወደ ሐኪም መሄድ ይኖርብሻል፡-
እብጠቱ ጠዋት ከመኝታ ስትነሺ ጀምሮ ካለ፣ ወይም ስታርፊ የማይጎድል ከሆነ
▶ፊትሽ ወይም እጆችሽ ካበጡ

▶እብጠቱ ወትሮ ከሚያጋጥምሽ በድንገት በሚያስታውቅ መጠን ከጨመረ

▶ከእብጠቱ ጋር ከባድ ራስ ምታት ካለሽ፣ ብዥ ካለብሽ፣ ካቅለሸለሸሽ፣ ትንፋሽ ካጠረሽ ወይም ሕመም ከተሰማሽ
እነዚህ ምልክቶች ከታዩብሽ “ፕሪኤክሌምፕሲያ” የተሰኘ በእርግዝና ጊዜ የሚያጋጥም የደም ግፊት መጨመር ምልክቶች ሊሆኑ አሊያም ሌላ ሕመምን የሚጠቁሙ ሊሆኑ ስለሚችሉ ወደ ሕክምና ማዕከል መሄድ ይኖርብሻል።

በእርግዝና ጊዜ የእግር ማበጥን እንዴት መቀነስ ይቻላል?

አንዳንድ ቀላል እርምጃዎችን መውሰድ በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የእግር ማበጥን ለመቀነስ ይቻላል።
የእግር እብጠትን ለመቀነስ የሚከተሉትን ነገሮች ማድረግ ይመከራል፡-
👉ሳትንቀሳቀሺ ለረጅም ሰዓት አንድ ቦታ አትቁሚ፤ የግድ ብዙ ሰዓት መቆም ቢኖርብሽ እንኳ ለመንቀሳቀስ ሞክሪ

👉🏾 ምቹ ጫማ አድርጊ (የጠበቀ ማሠሪያ ያላቸው ጫማዎችን እንዲሁም እግርሽ ላይ ከበድ ያለ ጫና ሊያሳርፍ የሚችሉ ታኮዎችን አታድርጊ)
👉🏾 በምታርፊበት ጊዜ እግርሽን ወደ ላይ ደግፊ (እግርሽን አትዘቅዝቂ)
👉🏾 የምትመገቢው ምግብ ውስጥ የምትጠቀሚውን ጨው ብዛት ቀንሺ
👉🏾 በግራ ጎንሽ ተኚ (በግራ ጎን መተኛት ከሌሎች ጥቅሞች በተጨማሪ፣ ደም በቀላሉ ወደ ልብ እንዲመለስ ያግዛል)
👉🏾 በእግር ከመንሸራሸር አንሥቶ የአካል እንቅስቃሴ አድርጊ

የስራ ሰዓት:- 24 በሰዓት 7 ቀናት እንገኛለን
ለህክምና አገልግሎት ማማከር እገልግሎት ከፈለጉ በ +251936659999 / +251911911895 ይደውሉ።
Telegram፦ https://t.me/biruksewclinic
Facebook፦https://www.facebook.com/profile.php?id=100063808903287
G-mail፦[email protected]
Tiktok፦ user7316172087151

28/05/2026

እርግዝና እና የሆድ ድርቀት/ Constipation in Pregnancy

በእርግዝና ጊዜ የሆድ ድርቀትና ተያይዞየሚመጣ የሆድ መነፋት ስሜትበአንድ ወቅትወይም በሌላ ሊያጋጥም ይችላል።
ለዚህ 3 ዋናዋና መነሻምክንያቶችይጠቀሳሉ፡-
👉ሰውነትሽ ለወሊድ እንዲዘጋጅ የሚያደርገው “ፕሮጄስትሮን”ሆርሞን የአንጀትጡንቻ እንዲላላ ስለሚያደርግ ምግብቶሎ አይንሸራሸርም። ይህምግብውስጥያሉ ንጥረነገሮች በደንብ እንዲመጠጡእናለልጅሽ እንዲደርሱቢያስችልም፣ድርቀትሊያመጣ ይችላል።
👉የማሕጸን መጠን መጨመር አንጀት ላይ የሚፈጥረው ጫና እንደ ወትሮው ሥራውን እንዳያከናውን እንቅፋት ይሆናል።
👉 በእርግዝና ጊዜ የሚወሰዱ ቫይታሚኖች ውስጥ የሚገኘውየብረት ማዕድን (አይረን) መብዛት (አስፈላጊነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ)፣ የምግብ መፈጨትንበመቀነስ ድርቀት እንዲባባስ ሊያደርግ ይችላል።
ድርቀትን ለማስወገድ ላድርግ?
• “ፋይበር” ያላቸውንምግቦች በብዛት መመገብ በቀን ቢያንስ ከ25 እስከ 30 ግራም ፋይበር መመገብ ይመከራል። ፋይበር (ጭረት) በተክሎች ውስጥ የሚገኝና ጨጓራ ስለማይፈጨው ሆድ የሚያለሰልስ ነው፤ ፍራፍሬዎች፣ አትክልት (በጥሬው ወይም ሙክክ ብሎ ሳይበስል፣ ከተቻለ ሳይላጥ) የመሳሰሉት በፋይበር የበለጸጉ ናቸው።
• ውሃ በብዛት መጠጣት በቀን ከሚመከረው መደበኛ 6 ብርጭቆ ውሃ በላይ 8 ብርጭቆ (ከአንድ ተኩል እስከ 2 ሊትር) ውሃመጠጣት ድርቀትን ለመቀነስ ይረዳል።
• ተስማሚ የአካልብቃት እንቅስቃሴማድረግ አንዱ የድርቀት መነሻ ሰበብ ጽንሱ አንጀት ላይ የሚያሳድረው ጫና እንደመሆኑ፣ በእግር ከመንሸራሸር አንሥቶ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ ምግብእንዲንሸራሸርናድርቀት እንዲቀንስያግዛል።
📌የስራ ሰዓት:- 24 በሰዓት 7 ቀናት እንገኛለን
🚨ለህክምና አገልግሎት ማማከር እገልግሎት ከፈለጉ በ
📞+251936659999 / +251911194824 ይደውሉ።
Telegram፦t.me/biruksewclinic
Facebook፦facebook.com/profile.php id=100063808903287
e-mail ፦[email protected]
Tiktok፦ user731617208715
Dylan Page - News Daddy Kana TV ゚viralシ

27/05/2026

Kabajamoo Maamila Keenya,
Ayyaana Iid Al-Adhaa (Arafaa) bara 1447ffaan Baga Nagaan isin ga'e .
Iid Mubaarak!

እንኳን ለ1447ኛ የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሰዎ!
ዒድ ሙባረክ!

📧 tiktok.com/
📧 [email protected]
📧 https://t.me/+4tJHL-3fdpM1ZDRk

Ministry of Health,Ethiopia Gojjam Health professional page-የጎዣም ጤና ባለሙያዎች ገጽ ゚viralシ

With BBC News Africa – I just got recognized as one of their top fans! 🎉
21/05/2026

With BBC News Africa – I just got recognized as one of their top fans! 🎉

With Kana TV – I'm on a streak! I've been a top fan for 2 months in a row. 🎉
21/05/2026

With Kana TV – I'm on a streak! I've been a top fan for 2 months in a row. 🎉

እርግዝና እና የጽንስ እንቅስቃሴየጽንስ እንቅስቃሴ አብዛኛውን ጊዜ ለነፍሰ ጡር እናቶች መጀመሪያ የሚሰማቸው ከ18 እስከ 20 ሳምንት ባለው የእርግዝና ጊዜ ነው። ሆኖም የመጀመሪያ እርግዝና ላ...
21/05/2026

እርግዝና እና የጽንስ እንቅስቃሴ
የጽንስ እንቅስቃሴ አብዛኛውን ጊዜ ለነፍሰ ጡር እናቶች መጀመሪያ የሚሰማቸው ከ18 እስከ 20 ሳምንት ባለው የእርግዝና ጊዜ ነው። ሆኖም የመጀመሪያ እርግዝና ላይ እስከ 20 ሳምንት ድረስ ምንም እንቅስቃሴ ላይሰማሽ/ላይታወቅሽ ይችላል። እርግዝናሽ የመጀመሪያሽ ካልሆነ አንዳንዴ 16 ሳምንት ሲሆንሽ ጀምሮ እንቅስቃሴው ሊሰማሽ ይችላል።
በእርግዝና ጊዜ እናቶች ልጃቸው እጁን እና እግሩን ሲያወናጭፍ ወይም ሲገለባበጥ ይሰማቸዋል።
ልጅሽ እያደገ ሲመጣ፣ የሚሰማሽ እንቅስቃሴ ብዛትም ዓይነትም እየተቀያየረ ይሄዳል። አብዛኛውን ጊዜ እንቅስቃሴው የሚጨምረው ከሰዓት በኋላ እና ምሽት ላይ ነው። ቀንም ሆነ ሌሊት ልጅሽ በአብዛኛው ከ20 እስከ 40 ደቂቃ ለሚሆን ጊዜ ያህል (ረዘመ ቢባል በአብዛኛው ከ90 ደቂቃ ያልረዘመ ጊዜ) ይተኛል። ልጅሽ በሚተኛባቸው በእነዚህ ሰዓታት እንቅስቃሴው ላይሰማሽ ይችላል።
ከ32 ሳምንት በኋላ የልጅሽ እንቅስቃሴ ብዛት የመቀነስ አዝማሚያ ያሳያል፤ ከዚያ መልሶ በመጠኑ ይጨምራል። ያም ሆኖ የሚሰማሽ የእንቅስቃሴ ዓይነት መውለጃሽ እየተቃረበ ሲመጣ እየተቀየረ መሄዱ አይቀርም።
አብዛኛውን ጊዜ በተለይ በሥራ ተወጥረሽ ከሆነ ሁሉም እንቅስቃሴ ላይሰማሽ ይችላል።
አስፈላጊው ነጥብ ምጥ እስኪጀምርሽ ወይም ልትወልጂ እስከደረስሽበት ሰዓት ድረስ የልጅሽ እንቅስቃሴ ሊሰማሽ ይገባል። (ልጅሽ በምጥ ሰዓትም እንቅስቃሴ አያቆምም።)
🚨ምን ሲሆን ሊያሳስበኝ ይገባል?
የጽንስ እንቅስቃሴ ከ18 - 20 ሳምንት እርግዝና ጊዜ አንሥቶ ለእናት የሚሰማና እስከ ወሊድ ጊዜ የማያቆም ነው።
የጽንስ እንቅስቃሴ መቀነስ ሲያጋጥም፣ አሳሳቢነቱና የሚያስፈልገው ክትትል እንደ እርግዝናሽ ደረጃ ይወሰናል።
✒ከ24 ሳምንት በፊት ለሆነው እርግዝና፦
በአብዛኛው የጽንስ እንቅስቃሴ ከ18 - 20 ሳምንት ጊዜ ውስጥ ስለሚሰማ፣ 24 ሳምንት ሆኖሽ ጽንሱ ሲንቀሳቀስ ተሰምቶች
የማያውቅ ከሆነ፣ ወደ ሕክምና መሄድ ይኖርብሻል። ሐኪም የልጅሽን የልብ ምት ከማዳመጥ ጀምሮ፣ እንደ አስፈላጊነቱ የአልትራሳውንድ ምርመራ ሊያዝ ይችላል።
✒ከ24 እስከ 28 ሳምንት ለሆነው እርግዝና፦
በዚህ ጊዜ ውስጥም የጽንሱ እንቅስቃሴ ካልተሰማሽ ወይም በጣም ከቀነሰ፣ ወደ ሕክምና መሄድ ይኖርብሻል። በዚህ ጊዜም ሐኪም የልጅሽን የልብ ምት ያዳምጣል፣ እንደ አስፈላጊነቱ የአልትራሳውንድ ምርመራ ያዛል፤ የደም ግፊትሽ ይለካል፣ ሽንትሽ ውስጥ ፕሮቲን ይገኝ እንደሁ ምርመራ ይደረጋል።
✒28 ሳምንት ላለፈው እርግዝና፦
ከ28 ሳምንት በኋላ የጽንስ እንቅስቃሴ መቀነስ ወይ መቆም ካጋጠመ ሳይውል ሳያድር ወደ ሕክምና መሄድ ያስፈልጋል። በዚህ ጊዜም ከላይ የተገለጹት ምርመራዎች ይበልጥ ጊዜ ተወስዶ ይደረጋሉ።
የጽንስ እንቅስቃሴ አንዴ ሊጨምር አንዴ ሊቀንስ ስለሚችል በአብዛኛውን ምርመራው ሁሉ ነገር ሰላም እና ጤና እንደሆነ ለማረጋገጥ የሚደረግ ቢሆንም፣ “ሰላም ነው” ብሎ ቸል ከማለት ምረምራውን አድርጎ ማረፉ በእጅጉ የተሻለ ነው።

📌የስራ ሰዓት:- 24 በሰዓት 7 ቀናት እንገኛለን
🚨ለህክምና አገልግሎት ማማከር እገልግሎት ከፈለጉ በ 📞+251936659999 / +251911194824 ይደውሉ።

Telegram፦ https://t.me/biruksewclinic
Facebook፦https://www.facebook.com/profile.php?id=100063808903287
e-mail ፦[email protected]
Tiktok፦ user7316172087151
Kana TV BBC News Afaan Oromoo BBC News Africa Ethiopian Nurses Association Ethiopian health today ゚viralシ

Address

Summit Chrkos Condominium
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Biruksew Medical Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share